Quantcast
Channel: ጤና – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Health: ‹‹የልጄን እናት ድንግል ሆና ባገባትም ከኤች.አይ.ቪ አልፀዳችም!! እኔ ግን አሁንም ኔጌቲቭ ነኝ››

$
0
0

እኔ የ26 ዓመት ወጣት ስሆን፣ ከዩኒቨርሲቲ አብራኝ የተማረች ጓደኛዬን ከተመረቅን በኋላ ተጋብተን ስንኖር ልጅ ፀነሰች፡፡ ሆኖም የእርግዝና ክትትል ታደርግ የነበረ በመሆኑ፤ ከእነዚህም ምርመራዎች ውስጥ አንዱ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ነበር፡፡ በዚህ መካከል ፖዘቲቭ መሆኗ ተረጋገጠና ቫይረሱ ወደ ልጁ እንዳይተላለፍ አስፈላጊው ጥንቃቄና ህክምና እንደሚያስፈልግ ተነገረን፡፡ እኔም መመርመር አለብህ ተባልኩ፡፡ ስፈራ ስቸር ተመረመርኩ፡፡ ሆኖም ውጤቱ ኔጌቲቭ ነበር፡፡ በጣም ተደሰትኩ፡፡ በአንድ በኩልም በጣም ተሰማኝ፡፡ በጣምም የገረመኝ ጉዳይ ግን ምን መሰላችሁ? ባለቤቴን ሳገባት ድንግል ሆና ሳለ እንዴት ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭ ልትሆን እንደቻለች ነበር? ምክንያቱም ከእኔ እንዳልተያዘች እኔ ምስክር ነኝና፡፡ በዚህ የተነሳም በመካከላችን ችግር ተፈጥሯል፡፡ እባካችሁ ዘሐበሻዎች መፍትሄ አታጡምና ምክር ለግሱኝ፡፡

መዝገቡ ነኝ

ask your doctor zehabesha

መልስ፡- ውድ ጠያቂያችን መዝገቡ ለጥያቄህ በቅድሚያ ልባዊ ምስጋናን ልናቀርብልህ እንወዳለን፡፡ በተፈጠረው ጉዳይም ስሜትህን ተጋርተናል፡፡ ሆኖም ጥያቄዎችህ በሁለት ግራ በሚያገቡ ጉዳዮ የተመላ ይመስላል፡፡ የመጀመሪያ ጉዳይ እንዴት ድንግል ሆና ኤች.አይ.ቪ ፖዝቲ ሆነች? የሚል ሲሆን ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ እንዴት እሷ ፖዘቲቭ ሆና እኔ ኔጌቲቭ ልሆን ቻልኩ? የሚልም ነው፡፡ በእውነቱ ሁለቱም ከበድ ባለ መልኩ ግራ የሚያጋቡ ይመስላሉ፡፡ ወደ ጥያቄህ ስንመለስ እንዳልከው ልጃገረድ ሆኖመገኘት ለወንዱ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ይመስላል፡፡ ባህሉም መሰረት የሚያደርገው ይህንኑ ስለሆነ፡፡

በእርግጥ ሳይንስም ልጃገረድ ሆኖ መቆየትን ጥሩና ገንቢ ባህሪ አድርጎም ያየዋል፡፡ በተለይ በዚህ ረገድ ከጋብቻ በፊት የሚደረግን ወሲብ አጥብቆ ይቃወማል፡፡ (አስገዳጅ ካልሆነ በቀር)፡፡ በተቻለ መጠንም ተጋቢዎች ከጋብቻ በፊት የኤች.አይ.ቪ ምርመራ አድርገው እንዲጋቡም ይመክራል፡፡ ልጃገረድነት ከኤች.አይ.ቪ ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ካልተፈለገ እርግዝና (ይህንንም ተከትሎ ከሚመጣው ውርጃ) እና ከሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ራሳቸውን ለመጠበቅ ‹‹ንፁህ›› ሆኖ መቆየት ይጠቅማቸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በሀገራችን የልጃገረዶች ማህበር ተቋቁሟል፡፡ አስተማሪነቱ ደግሞ የአስፈሪ ሁኔታ ስርጭቱን እያፋጠነ ለመጣው ኤች.አይ.ቪ እንደ አንድ የባህሪ ለውጥ የሚታይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ልጃገረድነት የሴቷ እንጂ የወንዱ መስፈርት ሊሆን ባለመቻሉ እምብዛም አመርቂ ለውጥ ማምጣት ግን አልቻለም፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ሴቶችና ወንዶ እኩል ናቸው በሚባልበት ዘመን የሴቶችን ልጃገረድነት ብቻ እንደታማኝነት መለኪያ መቁጠርና በጋብቻም ወቅት ይህን መስፈርት መጠቀም አይመከርም፡፡ ወንዱስ ታማኝነቱ በምን ይረጋገጥ? የሚል ያስነሳልና፡፡

የሴት ልጅ ክብረ ንፅህና በግንኙነት ብቻ ሳይሆን በራሱ ጊዜም ሊጠፋ የሚችልበት አጋጣሚ አለ፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አስገድዶ መድፈር በዓለም ደረጃ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ተገዳ በመደፈሯም ድንግልናዋን ልታጣ ትችላለች፡፡ በተለይም መደፈር በህጻንነት ወቅት የተደረገ ከሆነ ሴቷ ስለክብረንፅህናዋ መኖርና አለመኖር ሳታወቅ ልታድግ ትችላለች፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎች ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ ልጃገረድነትን ከታማኝነት ማረጋገጫ ጋር ማያያዙ ተገቢ አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ልጃገረድ ስለሆነች በኤች.አይ.ቪ አትያዝም ብሎ መደምደም አይቻልም፡፡ ቫይረሱ ከግንኙነት ውጭ በሌሎች መንገዶች ሊተላለፍ ይችላልና፡፡ ድንግልና ስለሌላትም በቫይረሱ ተይዛለች ማለት አይቻልም፡፡ እስካልተመረመረች ድረስ፡፡

በዚያ ላይ የሴቷን ማንነት በዚህ መልኩ የሚፈትሸው ወንዱ ራሱ ማን ሆነና ነው፡፡ የእሱስ ታማኝነት በምን ይረጋገጥ? ይህ የድንግልና ፍተሻ ሂደት እንደዛምቢያ፣ ማላዊ፣ ስዊዘርላንድ፣ ዚምባብዌ እና መሰል የአፍሪካ ሃገርም የሚከናወን ባህል ነው፡፡ በተለይም በእነዚህ ሀገራት አንዲት ሴት ከጋብቻዋ በፊት ወደ ልጃገረድ ፈታሾች ትላካለች፡፡ እነዚህ ፈታሾች ሴቶች ሲሆኑ ፍተሻውንም የሚያካሂዱት በጣታቸው ነው፡፡ አንድን ጣት ወደ ብልታቸው ቀዳዳ በመክተት የጥበቱን ሁኔታ ይገመግማሉ፡፡ እናም በእነዚህ ሀገራት ወንዶ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ቢቀብጡ ባህሉ የሚፈቅድላቸው ሲሆን ሴቶቹ ግን በጋብቻ ወቅት ሲፈተሹ ድንግል ሆነው ካልተገኙ ወንድ የሰርግ ጥሎሽ ሳይጥል ሊያገባት ወይም ሊያባርራት ይችላል፡፡

ወላጆቿም በእሷ የተነሳ የሚታፈርባቸው ይሆናል፡፡ በእዚህም የተነሳ በእነዚህ ሀገራት ሴቷ ከጋብቻው በፊት ወሲብ መፈፀም ከፈለገች በፊንጢጣ በኩል የሚደረግን ግንኙነት እንድትፈፅም ትገደዳለች፡፡ ይህ ደግሞ ከተለመደው አይነት ወሲብ በበለጠ ኤች.አይ.ቪን ከወንዱ ወደ ሴቷ የሚያስተላልፍ ነው፡፡

በተለይ በብዙዎች የአፍሪካ ሀገራት እየታመነ የመጣው ጉዳይ ከልጃገረዶች ጋር ወሲብ መፈፀም ከኤች.አይ.ቪ ይፈወሳል የሚል ኢ-ሳይንሳዊ አመለካከት ሲሆን በዚህም የተነሳ ልጃገረድነታቸው ተፈትሾ የተረጋገጠላቸው ሴቶች ለእነዚህ ወንዶች የሚዳሩበት አጋጣሚም እንዳለ ይታያል፡፡

በአጠቃላይ የድንግልና መኖርም ሆነ አለመኖር የአንድን ሴት ልጅ በኤች.አይ.ቪ መያዝና ያለመያዝ የሚያረጋግጥ አይደለም፡፡ ለባሏም የሚኖራት ታማኝነት እንዲሁ በልጃገረድነት መኖርና አለመኖር የሚወሰን አይደለም፡፡ በእርግጥ በድንግልና መቆየት በኤች.አይ.ቪ ላለመያዝ አንዱና ጥሩው አማራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግን እውን ሊሆን የሚችለው ይህቺ ልጅ ቫይረሱ ከሌለባት ወንድ ጋር ከተጋባች ብቻ ይሆናል፡፡

ይህ ደግሞ የሚረጋገጠው በምርመራ ብቻ ነውና ፍቅረኞች በድንግልና ሳይተማመኑ ተመርምረው ቢጋቡ ነው የሚመከረው፡፡ ታማኝነትም ቢሆን እንዲህ ነው፡፡ መተማመን ለራስም ሆነ ለጋራ ፍቅር ሲባል ታምኖበት የሚደረግ እንጂ በድንግልና ስለፀኑ ብቻ የሚመጣ ባህሪ አይደለም፡፡ እንደዛማ ከሆነ ሁሉም ወንድ ክብረ ንፅህና ስለሌለው ታማኝ አይደለም ሊባል ነው፡፡

በዚያ ላይ አንዲት ሴት ድንግልና የላትም ማለት በወሲብ የተነሳ አጥታዋለች ማለት አይደለም፡፡ በራሱ ጊዜም ሆነ በልጅነቷ በመደፈሯ ሳታውቅ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ በተረፈ አንተም ሆንክ ሌሎች የድንግልና አፍቃሪያን ከዚህ አመለካከታችሁ እንድትፀዱ እምነቴ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚም ከጋብቻ በፊት ፀንቶ በመቆየትና በጋብቻም ወቅት ተመርምሮ መጋባት የሴቶችም የወንዶችም ባህል ይሁን እላለሁ፡፡ ይህም በመሆኑ እንግዲህ በአንድም በሌላ መልኩ ባለቤትህ በቫይረሱ ተያዘች፡፡ አንተ ደግሞ በአንጻሩ ኔጌቲቭ ሆንክ፡፡ ይህ መሰሉ ከባልና ሚስት ውስጥ አንዳቸው ኔጌቲቭ ሌላኛቸው ደግሞ ፖዘቲቭ የሚሆኑበት ክስተት ‹‹Discordance›› በመባል የሚጠራ ሲሆን አልፎ አልፎ የሚከሰት የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ለእሷ መያዝ ምናልባት ከግንኙነት ውጭ ያሉ ምክንያቶች እንደ አንድ ምክንያትም ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ ምናልባትም ድንግልና ሳይገረሰስ በተደረገም ግንኙነት ሊሆን ይችላል፡፡

ይህ መሰል በጥንዶች ላይ የሚስተዋልና አንዱ ኔጌቲቭ ሌላው ፖዘቲቭ የሚሆንበት ምክንያት በውል የሚታወቅ ምክንያት የሌለው ቢሆንም ወደ ፊት የኤች.አይ.ቪ መከላከያና ክትባት ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ግን ይታመናል፡፡

ይህም ማለት ምናልባት ኤች.አይ.ቪ የተለያዩ ዝርያዎች ያሉት በመሆኑ የተያዝከው በአንዱ አይነት ሊሆን ይችላል እንጂ በሌላው አይነት ዝርያ አትያዝም ማለት ስላልሆነ ጥንቃቄ ማድረግን እንዳትዘነጋ እንላለን፡፡ ከዚህ በተረፈ የትዳር አጋርህ ለራስህና ለልጅህ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረጋችሁ ስላለፈው ሳይሆን ስለወደፊቱ ትኩረት በማድረግ በፍቅር ትኖሩ ዘንድ እመኛለሁ፡፡ መልካም ፍቅር!

The post Health: ‹‹የልጄን እናት ድንግል ሆና ባገባትም ከኤች.አይ.ቪ አልፀዳችም!! እኔ ግን አሁንም ኔጌቲቭ ነኝ›› appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>