Quantcast
Channel: ጤና – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Health: በእንቅልፍ እጦት ይሰቃያሉ? –እንግዲህ ማር ይላሱ ያላሉ ዶክተሮች |የማር የጤና በረከቶችን ያንብቡ

$
0
0

Honey for health

ለማንኛውም በቤት ውስጥ በሚያገኟቸው አትክልትና ፍራፍሬ እንዴት ጤናዎን በቤትዎ በቀላሉ መንከባከብና ከበሽታ መከላከል እንደሚችሉ ለማወቅ የሚከተለውን ያንብቡ::

አልጋዎ ላይ ጋደም ብለው እንቅልፍ እምቢ ብሎዎት ሲገላበጡ እና አሁንም አሁንም በመንቃት ያለ እንቅልፍ ሌሊቱን አሳልፈውት ይሆናል።

ታዲያ ፈልገው ያጡትን እንቅልፍ ለማግኘት ምን አይነት ዘዴ ይጠቀማሉ?

ለምግብነት የሚጠቀሟቸው ምግቦች ለዚህ ፈውስ እንደሚሆኑ አስበው ሞክረውታል?

ለምግብነት ከሚጠቀሙት አንዱ የሆነው ማር ለሰውነት ከሚያስገኛቸው በርካታ ጠቀሜታዎች ባሻገር የእንቅልፍ እጦትን ለማስወገድም ይረዳል።

ጣፋጭ ነገሮችን በመኝታ ሰአት መጠቀም ጉዳት እንዳለው የህክምና ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፤ ይሁን እንጅ ማር ከዚህ የተለየ እና ተፈጥሯዊ ጣዕም ባለቤት በመሆኑ በዚህ በኩል የሚመከር እንጅ የሚነቀፍ አይደለም።

በዚህ በኩል የማርን ሁለንተናዊ ጠቀሜታዎች አስመልክቶ መጻህፍትን የጻፉት ዶክተር ሮን ፌሰንደን፤ ማርን በገበታ ላይ በተለይም ደግሞ በእንቅልፍ ሰአት አካባቢ መጠቀም ከእንቅልፍ ጋር ለመታረቅ ሁነኛ መፍትሄ ነው።

ማር ለሰውነት ጠቃሚና ተፈጥሯዊ ይዘቱ አስፈላጊ በመሆኑም ሁሌም ቢሆን በየቀኑ መመገብ አዋጭ እንደሆነም ነው የሚናገሩት።

ከሁሉም በላይ ግን በመኝታ ሰአት አቅራቢያ

ማርን መጠቀም ጤናማ እና የተስተካከለ የእንቅልፍ ሰአት ለማግኘት ይረዳል ይላሉ፤ ከጣፋጭነቱ አንጻር ባይመስልም በመኝታ ሰአት ሰውነት በሚያደርጋቸው ሽግግሮች ወቅት የመታደስ ሂደቱን እንዲያገኝ ይረዳዋል።

ታዲያ ይህን የማር ጠቀሜታ ለማግኘት ካሰቡ ተፈጥሯዊውንና በአብዛኛው ከአርሶ አደሮች የሚገኘው ጥሬ እና ንጹህ ማር መጠቀሙ መልካም ነው፤ ከዚህ በታች ማር ያለውን የተወሰኑ ጠቀሜታዎች ይመልከቱ።

እንደ ዶክተር ፌሰንደን ገለጻ ከንጹህ ማር ግሉኮስ እና ከእፅዋት የሚገኘው ጣፋጭ ውህድ ( ፍሩክቶስ) በተስተካከለ መጠን ማግኘት ይቻላል። ይህ ደግሞ በእንቅልፍ ሰአት የጉበትን ስራ

የተስተካከለና ውጤታማ ያደርገዋል።

ንፁህ ማር በመኝታ ሰአት መጠቀምዎ ሌሊቱን ሙሉ ስራ የማይፈታው ጉበትዎ ለሰውነት ሃይልን የሚያከማቸውን ግላይኮጅንን በተሻለ መጠን እንዲያገኘው በማድረግ ሙሉ ሃይሉን ስራ ላይ እንዲያውል ይረዳዋል።

ታዲያ የወሰዱትን ማር በተመጠነ ውሃ ሲታጀብ ደግሞ በመኝታ ሰአት ከሚከሰቱ የጤና መዘዞች እና ድንገተኛ አደጋዎች ተጠበቁ ማለት ነው።

ማር በመኝታዎ ሰአት መጠቀምዎ በተለያዩ መንገዶች ተጠቃሚ ያደርግዎታል፤ ጉበትዎ 100 ግራም ግላይኮጅን ብቻ ይይዛል፤ ሰውነትዎ ደግሞ በቀን ውሎው በየሰአቱ 10 ግራም ያክል

ግላይኮጅን ይፈልጋል።

ታዲያ በመኝታ ሰአት ጉበትዎ ያከማቸው ግላይኮጅን ጥቅም ላይ ውሎ ያልቅና ተጨማሪ ይጠይቅበታል።

በመኝታ ሰአት የሚወሰድ ማር ትልቁ ጠቀሜታም ይኼው ነው፤ ለጉበት ግላይኮጅን ምንጭነት በበቂ ሁኔታ በማገልገሉ ምክንያት፤ ምሽት ላይ እስከ 2 የሻይ ማንኪያ ማርን መውሰድ ጉበት የሚፈልገውን የግላይኮጅን መጠን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኝ ያስችለዋል።

ይህ ደግሞ በንጥረ ነገሩ እጥረት ሳቢያ በመኝታ ሰአት አዕምሮን ለከፍተኛ ጭንቀት እና ውጥረት ከመዳረግም ይታደገዋል።

ጤናማ ጉበት እንዲኖር በማድረጉና የእንቅልፍ እጦት የሚያስከትለውን የሜላቶኒንን ምርት በማስወገድ ሰላማዊ ሌሊትን እንዲያያሳልፉም ያግዛል።

ሌሊት ላይ የሚከሰቱ አላስፈላጊ የህመም ስሜቶችን በዚህ ወቅት በማስወገድ ሰውነት በእንቅልፍ ሰአት የሚያደርገውን ሽግግር ጤናማ እና የተስተካከለ ያደርገዋል።

ለየት ካለው የጤናማ እንቅልፍ ጠቀሜታው ባሻገርም ንፁህ ማር ባክቴሪያና ፈንገሶችን በመዋጋት እና በመከላከል ረገድ የተዋጣለት እንደሆነም ይነገርለታል። በዚህም የሰውነት መቆጣትን በእጅጉ ይከላከላል።

ከላይ ያሉትን ጨምሮ ያልተዘረዘሩትን በርካታ የጤና ጠቀሜታዎቹን ለማግኘት ንጹህ እና ያልተበረዘ ማር ይጠቀሙ።

The post Health: በእንቅልፍ እጦት ይሰቃያሉ? – እንግዲህ ማር ይላሱ ያላሉ ዶክተሮች | የማር የጤና በረከቶችን ያንብቡ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>