(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
*ለጉበት ጤናማነት
ቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት የማነቃቃት አቅም አለው።
*ከሳንባ ጋር ተያያዥ ችግሮችን ይከላከላል
ቀይስር ቫይታሚን ሲ በውስጡ ስለያዘ የአስም ምልክቶች እንዳይነሱ ይረዳል፣ በሽታ የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርም ያግዛል። ቤታ ካሮቲን የሚባለው ንጥረ ነገር በሳንባ ካንሰር የመጠቃት እድልን ይቀንሳል።
*ካታራክትን ይከላከላል
ቤታ ካሮቲን የሚባል ንጥረ ነገርን የያዘው ቀይስር ከእድሜ ጋር ሊመጣ የሚችልን የአይን ሞራ እንዳይከሰት ይከላከላል።
*የሃይል መጠንን ይጨምራል
ቀይስር በካርቦሀይድሬት የበለፀገ ስለሆነ ሀይል ሰጭ ከሚባሉት ምግቦች እንዲመደብ ያደርገዋል።
*ካንሰርን ይከላከላል
አንዳንድ ጥናቶች ቀይስር ከቆዳ፣ ከሳንባ እና ከአንጅት ካንሰር የመከላከል አቅም እንዳለው ያሳያሉ።