Quantcast
Channel: ጤና – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 384 articles
Browse latest View live

Health: የሙዝ ልጣጭ ለጤና ያለው 7 በረከቶች

$
0
0

banana and health
1. የሙዝ ልጣጭ በቆዳ ላይ የሚወጡ የተለያዩ እብጠቶችን ለማከም ይረዳል።
እብጠቱን ወይም ቁስሉን ለተከታታይ ቀናት በሙዝ ልጣጭ ላይ በመሸፈን እና በጨርቅ ወይም በባንዴጅ በመጠቅለል ቁስሉን በቀላሉ ማከም እንደሚያስችል ነው የሚነገረው።

2. የፊት ቆዳን በሙዝ ልጣጭ ለ30 ደቂቃ ያህል ማሸት እና በውሃ መታጠብ ያለ እድሜ የሚከሰት የፊት ቆዳ መጨማደድን ለመከላከል ይረዳል።
ይህ ዘዴ በፊት ቆዳ ላይ ብቻ ሳይሆን በተለያየ የሰውነታችን ክፍል የሚወጡ ሽፍታዎችን ለማጥፋት እና በብጉር የተሸፈነ ፊትን ንጹህ ለማድረግም ያግዛል።

3. የቤት እቃዎችን፣ ከነሃስ የተሰሩ ቁሳቁሶችን እና ለስላሳ ጫማዎችን በሙዝ ልጣጭ ማጽዳት ውበታቸው እንዲጎላ ያደርጋል።

4. በየቀኑ በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ክፍል ጥርስን ማጽዳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጤናማ እና ማራኪ ጥርስ ያላብሳል።

5. በተባይ የተጠቃነውን ቦታ በሙዝ ልጣጭ በመሸፈን ለተወሰነ ደቂቃ መያዝ ከህመም ስሜቱ በፍጥነት ለመውጣት ይጠቅማል።

6. የሙዝ ልጣጭን ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ቆዳ ላይ በማስቀመጥ የቆዳ መቆጣትን መከላከል ይቻላል

7. በተጨማሪም ሙዝ የድብርት ስሜትን ያስወግዳል እንዲሁም የሆድ ደርቀትን ይከላከላል፡፡


ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

$
0
0

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
*ለጉበት ጤናማነት
ቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት የማነቃቃት አቅም አለው።
*ከሳንባ ጋር ተያያዥ ችግሮችን ይከላከላል
ቀይስር ቫይታሚን ሲ በውስጡ ስለያዘ የአስም ምልክቶች እንዳይነሱ ይረዳል፣ በሽታ የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርም ያግዛል። ቤታ ካሮቲን የሚባለው ንጥረ ነገር በሳንባ ካንሰር የመጠቃት እድልን ይቀንሳል።

beets1-640x330
*ካታራክትን ይከላከላል
ቤታ ካሮቲን የሚባል ንጥረ ነገርን የያዘው ቀይስር ከእድሜ ጋር ሊመጣ የሚችልን የአይን ሞራ እንዳይከሰት ይከላከላል።
*የሃይል መጠንን ይጨምራል
ቀይስር በካርቦሀይድሬት የበለፀገ ስለሆነ ሀይል ሰጭ ከሚባሉት ምግቦች እንዲመደብ ያደርገዋል።
*ካንሰርን ይከላከላል
አንዳንድ ጥናቶች ቀይስር ከቆዳ፣ ከሳንባ እና ከአንጅት ካንሰር የመከላከል አቅም እንዳለው ያሳያሉ።

የቀዝቃዛ ሻወር በረከቶች

$
0
0

የቀዝቃዛ ሻወር በረከቶች

የብዙዎቻችን አንደኛ ምርጫ ሙቅ ሻወር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ቀዝቃዛ ሻወርን መርጠን የምንጠቀም እምብዛም ነን፡፡ ሙቅ ሻወር ከሌለ፣ አማራጭ ሲጠፋ ነው ወደ ቀዝቃዛው ሻወር የምንገባ እንጂ የምንግዜውም የብዙዎቻችን ምርጫ ሙቅ ሻወር ነው፡፡

iStock_000015417910Small-660x330

ግን ለመሆኑ ቀዝቃዛ ሻወር ታላላቅ ጥቅሞች እንዳሉት የምናውቅ ስንቶቻችን ነን…

1. በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ስብ እንዲቀልጥ ያደርጋል…፡፡ በቀዝቃዛ ውሃ ገላችንን በምንታጠብበት ጊዜ ሰውነታችን የሙቀት መጠኑን ለመጠበቅ የተከማቸውን ስብ ያቀልጣል፡፡ ይህም በፋንታው በተወሰነ መልኩ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

አንድ የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በቀዝቃዛ ውሃ ገላን መታጠብ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 9 ፓውንድ ያህል ክብደት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

2. በቀዝቃዛ ውሃ ገላን መታጠብ ስሜትና መንፈስን ነቃ ያደርጋል፡፡ ከእንቅልፍዎ ተነስተው ወደ ስራ ከመሄድዎት በፊት በቀዝቃዛ ውሃ ገላን መታጠብ የውሃው ቅዝቃዜ በገላዎት ላይ የሚፈጥረው ስሜት በጥልቀት ዓየር እንዲስቡ ያደርገዎታል፣ ይህም ሰውነትዎ ኦክስጅን በብዛት በመሳብ ሙቀት ለመፍጠር የሚያደርገው ነው፡፡

የልብ ምትዎም ይጨምራል – ይህም በፋንታው ደም በሰውነትዎ ውስጥ በፍጥነት እንዲዘዋወርና ቀኑን ነቃ ብለው በመልካም ሀይል እንዲጀምሩት ያደርጋል፡፡

3. በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ የሰውነትዎን ሜታቦሊክ ሂደት በማፋጠን የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓት ያነቃቃል፡፡

4. ከአድካሚ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በኋላም ገላን በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ በተለይም በበርካታ አትሌቶች ዘንድ የሚዘወተርና የሚመከር ተግባር ነው፡፡

5. በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ማራኪ ጸጉርና ቆዳ እንዲኖርዎት ያደርጋል፡፡ በተለይም ቆዳ ላይ የሚወጡትን ቀያይ ብጉር መሳይ እብጠቶች እንዳይከሰቱ ለማድረግ ቀዝቃዛ ውሃ ተመራጭ ነው፡፡

ከገበታ በኋላ እነዚህ ያስወግዱ..

$
0
0

የስርአተ ምግብ መፈጨት ላይ አደጋ የሚፈጥሩ ድርጊቶችን ማድረግ አይመከሩም፡፡

በዘልማድ ከምግብ በኋላ የሚደረጉ ድርጊቶች ብዙ ጊዜ ችግር ሲፈጥሩ ይስተዋላል፤ ከምግብ አለመፈጨት እስከ የጤና እክል።

እነዚህ ደግሞ ከምግብ በኋላ ባይደረጉ የሚመከሩ ናቸው፡፡
2654372_orig
ሲጋራ ማጨስ፦ ይህን ማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ የካንሰር ተጋላጭነትን የሚጨምር ሲሆን ከዚህ ባለፈም ሰውነት ላይ ከፍተኛ ድካምን ያስከትላል፡፡

መተኛት፦ ይህን ማድረግ ደግሞ ሆድ አካባቢ ምቾት የመንሳት እና ድካም እና ጫናን ያስከትላል።

ከዚህ ባለፈም አላስፈላጊ ውፍረትን ያስከትላል፤ ይህን ከማድረግ ከተመገቡ በኋላ ከቅርብ ጓደኛዎ ወይም ወዳጅዎ ጋር መጨዋወት መልካም ነው።

ገላን መታጠብ፦ በተመገቡበት ፍጥነት ገላን መታጠብ ምግብ ለመፍጨት የሚያስፈልገውን የሰውነት ሙቀት ሌላ ስራ እንዲሰራ ያደርገዋል፤ሰውነትን ለማሞቅ።

ይህ ደግሞ በሆድ አካባቢ ያለውን ደም ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች እንዲሰራጭ በማድረግ አንጀት ላይ ከፍተኛ ችግርን ያስከትላል።

ፍራፍሬ መመገብ፦ ለመፈጨት ቀላል ቢሆኑም ምግብ ከተመገቡ በኋላ በቅጽበት ይህን ማድረግ ግን አይመከርም።

ከቻሉ ከምግብ በፊት አንድ ሰአት ወይም ከተመገቡ ከሁለት ሰአት በኋላ፤ ያ ካልሆነ ግን መደራረብ እና መጨናነቅን በማስከተል የምግብ መፈጨትን ያዘገያሉ።

ሻይ መጠጣት፦ በተመገቡበት ቅፅበት ይህን ማድረግም አደጋ አለው፤ የምግብ መፈጨትን አስቸጋሪ በማድረግ የማስጨነቅ ስሜትን ስለሚፈጥር።

ምናልባት በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ተመግበው ከሆነ ደግሞ ከሻይ የሚወጣው አሲድ በከፍተኛ ሁኔታ የምግብ መፈጨቱን ስለሚያስተጓጉለው አደገኛ ይሆናል።

ከምግብ በኋላ ሻይ መጠጣት ከፍተኛ የሆነ የብረት መጠን ለሚያስፈልጋቸው ህጻናትና ሴቶች ደግሞ ጭራሽ አይመከርም።

የእግር ጉዞ ማድረግ፦ ይህን ሲያደርጉ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የአሲድ መጠንን በመርጨት እና የምግብ አለመፈጨትን በማስከተል ችግር ይፈጥራል።

ስለዚህም ከተመገቡ ከግማሽ ሰአት በኋላ የእግር ጉዞ ማድረግ እና በተመገቡበት ፍጥነት ይህን ማስወገድ ለጤናዎ መልካም ነው።

ምንጭ፦ mavcure.com

– See more at: http://www.fanabc.com/index.php/%E1%8C%A4%E1%8A%90%E1%8A%9B-%E1%8A%91%E1%88%AE/item/13893-%E1%8A%A8%E1%8C%88%E1%89%A0%E1%89%B3-%E1%89%A0%E1%8A%8B%E1%88%8B-%E1%8A%A5%E1%8A%90%E1%8B%9A%E1%88%85-%E1%8B%AB%E1%88%B5%E1%8B%88%E1%8C%8D%E1%8B%B1.html#sthash.asLbFMpK.dpuf

Health: “በሚስቴም ሆነ በወንዶች መሀልም በድንገት እንኳን ስጋለጥ እያፈርኩ ነው |ለብልት ማነስ መፍትሄው ምን ይሆን?”

$
0
0

ask your doctor zehabesha
ብልቴ በደህና ቀን ሆዴ ውስጥ ትገባና ትጠፋለች፡፡ በዚህ የተነሳ በሚስቴ አጠገብ መቆም እያፈርኩ ነው፡፡ ሌላ ችግር የለብኝም፡፡ ሳውና ባዝ ስጠቀም የአንዳንድ ወንዶችን ብልት ስመለከት ደግሞ መጠኑ ረዘም ያለ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ በሚስቴም ሆነ በወንዶች መሀልም በድንገት እንኳን ስጋለጥ እፈራለሁ፡፡ እባካችሁ ህክምና ካለው አንድ በሉኝ፡፡
ዘላለም

ውድ ዘላለም ጥያቄህ የብዙ አንባቢዎቻችን እንደሚሆን እንረዳለን፡፡ በመሆኑም ምላሽህን እንደሚከተለው አስተናግደንልሀል፡፡

ለመሆኑ የብልት መጠን ወንዶች እንደሚጨነቁበት፣ ሴቶችስ ተመሳሳይ የሆነ አመለካከት ይኖራቸው ይሆን? ወይስ ሴቶች ከወንዶች የፍትወት አካል ይልቅ የሚያስጨንቃቸው ፍቅር ብቻ ይሆን? አነስተኛ የወንዶች የብልት መጠንስ፣ በሩካቤ አፈፃፀምና በመውለድ ብቃት ላይ የሚያስከትለው ተፅዕኖስ ይኖር ይሆን፣ ጥናቱ በእነዚህ ዙሪያ ምን ይላል?

አጭር ቁመት ያለውም ብልቱ አጭር ነው ካለ መናገርም አይቻልም፡፡ እንዳውም የአጭሩ ሰው ብልት ከቀውላላው ሰውዬ ሊበልጥ ይችላል፡፡ ታዋቂው የስነ ወሲብ ሐኪም ዶ/ር ሩት በዚህ ጉዳይ ላይ የምትለው አላት፡፡ ብዙዎች ወንዶች ከሌላው ያነሰ የብልት መጠን አለን ብለው ስለሚጨነቁና በራሳቸው ስለማይተማመኑ ወደ ድክመተ ወሲብ ያመራሉ፡፡ ምክንያቱም ጭንቀቱ ራሱ ስኬታማ ግንኙነት እንዳያደርጉ ስለሚያደርጋቸው ነው፡፡ በመሆኑም ትላለች ዶ/ር ሩት የወንዶች ብልት የሚያንሰው ጭንቅላታቸው ውስጥ ነው፡፡

በተለያዩ ሰዎች ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፣ ሴቶች ለወንዶች የብልት መጠን ትኩረት እንደሚሰጡ ይታወቃል፡፡ ለወንዶች ልጆች  የሴቶች መልክና ቅርጽ ስሜት ቀስቃሽ የመሆኑን ያህል ለሴቶች ደግሞ የወንዱ የብልት መጠን ትኩረት እንደሚሰጡ ይታወቃል፡፡ ለወንዶች ልጆች የሴቶች መልክና ቅርፅ ስሜት ቀስቃሽ የመሆኑን ያህል ለሴቶች ደግሞ የወንዱ የብልት መጠን ተነፃፃሪ እንደሆነ ነው የሚታወቀው፡፡ በእርግጥ የብልት መጠን በተለይ በውፍረት ደረጃ ገዘፍ ማለቱ፣ ብዙዎቹን የሴቷ ፍትወት አካል ውስጥ የሚገኙ የነርቭ ጫፎችን የመዳሰስ አቅም ስለሚኖው ለሴቷም ስሜት ለጭነቱ አያጠያይቅም፡፡ በተለያዩ ወሲባዊ ችግሮች ወደ ህክምና ከሚሄዱ ሴቶች ውስጥ 67 በመቶ የሚሆኑት፣ በወንዶቻቸው የብልት መጠን አይረኩም፡፡ በእርግጥ ለወንዱ ስሜት አንቃቂነት የሴቷ የብልት ቀዳዳ መጠን መጥበቡ ነው ተፈላጊ የሚያደርገው፡፡ ይሄም በወንዱ ብልት ላይ ያሉትን የነርቭ ጫፎች በመፋተግ ስሜትን ስለሚያነቃቃ ነው፡፡

ለመሆኑ የወንዶች የብልት መጠን በአማካይ ምን ያህል ይሆናል? በአብዛኛው 90 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች ብልታቸው በተነሳሳ ጊዜ፣ በጋራ የሚጋሩት የብልት መጠን እርዝማኔ ከ5-7 ኢንች ወይም በአማካይ 6.16 ኢንች የሚርስ ሲሆን ይሄም ከ12.7-17.8 ሴ.ሜ ወይም በአማካይ 13.65 ሴንቲ ሜትር ይደርሳል፡፡
የብልት መጠን ማሳያ ቻርት/ሙሉ በሙሉ ከተወጠረ በኋላ/
መጠን      ቁመት
ትንሽ        <6 ኢንች አማካይ            6-7 ኢንች ትልቅ       7-8 ኢንች ግዙፍ       > 8 ኢንች

የብልት ርዝማኔን እንዴት ማወቅ ይቻላል?

በቅድሚያ መለካቱ የሚመጣው በራስ ካለመተማመን ግፊት ነው፡፡ በጥናት እንደሚታወቀውም 98 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች፣ ትክክለኛ ወይም በጤናማ የመጠን ልኬት ውስጥ እንደሚያርፉ ነው፡፡ እንግዲህ የግድ ይህንን ማወቅ አለብኝ የሚል ወንድ ካለ፣ እንደሚከተለው አድርጎ መለካት ማንም የማይነፍገው መብቱ ነው፡፡
1. ማስመሪያ በመያዝ ብልት በስሜት ተነቃቅቶ ሙሉ በሙሉ እስኪወጠር ጠብቅ፡፡

2. ማስመሪያውን ከብልት መነሻ እስከ ጫፍ ድረስ በትክክል አጋድመው፡፡ ይህን ስታደርግ ግን ማስመሪያውን የኢንች ክፍል ወደ ሰውነትህ ሳትጫነው መሆን አለበት፡፡

የተለያዩ የብልት ማነስ ችግር ያለባቸው ወንዶች፣ ብልታቸውን ለማስረዘም ታዲያ ፍላጎት ማሳደራቸው አልቀረም፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ያሰቡት ያልተሳካላቸው ግለሰቦች ለከፍተኛ የስነ ልቦናዊ ችግር ተጋልጠዋል፡፡ ከእነዚህ ዘዴዎች መካከል ውስይ እምደው፣ የተወሰኑት ዘዴዎች ከ2-3 ኢንች ድረስ የብልት መጠን ቁመትን የመጨመር ኃይል ሁሉ ያላቸው ናቸው፡፡ ከመቶ በላይ ያሉ ልዩ ልዩ ዘዴዎች ይገኛሉ፡፡ ያም ሆኖ ውጤታማ የተባሉት ዘዴዎ ጥቂት ብቻ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ዘዴዎች አሰራሩን የሚያዘወትሩም፣ ኮርፖራ ካቫርኖዛ በተባለው የብልት ጡንቻ ላይ ነው፡፡ ኮርፖራ ካቫርኖዛ የብልት ውስጥ ጡንቻ ሲሆን፣ በውስጡም ጥቃቅን የደም ስሮችን የያዘ በወሲብ ወቅትም በደም በመሞላት የሚለጠጥ ክፍል ነው፡፡

ስለ ወንዶች ብልት ሴቶች ምን ይላሉ?

ወንዶች የሚያስጨንቃቸውን ያህል ሴቶች ለወንዶች የብልት መጠን ትኩረት ይሰጣሉ ወይ በሚለው ላይ ያጠነጥናል፡፡ እንደሚታወቀው ወንዶችን በብልት መጠናቸው የሚጨነቁት፣ በአመዛኙ ሴቶች ለመጠን ግዝፈት የተለየ ምርጫ ይኖራቸዋል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ስለሚጨነቁም ምንም እንኳን ተገቢ መጠን ቢኖራቸውም በቂ አይደለም ብለው ይረብሻሉ፡፡ ብዙዎቹ በዚሁ ዙሪያ የሚቸገሩ ወንዶች ችግሩ ራሳቸው በፈጠሩት ጭንቀት ሳቢያ የሚመጣ ነው፡፡ ሌላው የችግሩ መነሻ ደግሞ ወንዶች ብልታቸውን እርስ በርስ በማወዳደር ልማዳቸው ነው፡፡ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም፡፡ የእያንዳንዱ ወንድ ቁመትና ክብደት ተመሳሳይ እንደማይሆን ሁሉ የብልት መጠናቸውም እኩል ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ዋናው ጭብጥም መሆን ያለበት የብልት ልኬታቸው መጠን በተገቢው መስፈርት ውስጥ ይገኛል ወይ? ብሎ ማወቁ ላይ ነው፡፡

እንደሚታወቀው የወንዱ የብልት መጠን ከፍተኛ መሆን፣ በግንኙነት የበላይነትን እንደሚያስጨብጥ በአፈ ታሪክ ደረጃ ቢነገርም፣ እውነታው ግን በሴቶች ዘንድ ብዙ የሚታመንበት አለመሆኑ አስተሳሰቡን አስቂኝ ያደርገዋል፡፡ ‹‹ለምን?›› የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስም፣ የሚከተሉትን መረጃዎች ማየቱ በቂ ነው፡፡
1. እንደሚታወቀው የሴት ልጅ ፍትወት አካል፣ በአፈጣጠሩ ከተለጣጭ ጡንቻዎች የተሰራ እንደመሆኑ መጠን በውስጡ የህፃን ልጅን ያክል ግዙፍ አካል ማሳለፍ የሚችል ነው፡፡ እንዲሁም ሞዴስን ያህል የደም መምጠጫ በውስጥ አፍኖ የመያዝም አቅም ያለው ነው፡፡ በአጠቃላይም ማንኛውንም በውስጡ የሚገባ አካል የመቀበልና የማፈን ባህሪ አለው፡፡ ከዚህ አንፃር ታዲያ የወንዶች ብልት ወፍራምም ይሁን ቀጭን የሚያመጣው ለውጥ እምብዛም ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱንም አይት መጠኖች ለማስተናገድ ከተለጣጭነት ባህሪው የተነሳ በተመሳሳይ ደረጃ የማፈን ብቃት ስላለው ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ብዙውን ጊዜ ሁለቱም ፆታዎች የበለጠ ክብደት የሚሰጡት ለስሜት ነው፡፡ ማለትም የሴቷን ስሜት ከመኮርኮርና ከማርካት አንፃር፣ ረዘም ያለው የወንዱ የፍትወት አካል የተሻለ እንደሚሆን ያምናሉ፡፡ ይህም ምክንያት የሴቷ ውስጠናው የፍትወት አካል የበለጠ ተነቃቂ እንደሆነ በማሰባቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ 70 በመቶ ከፍተኛ የተነቃቂነት ባህሪ ያለው የሴቷ የፍትወት አካል ከውጫዊ አካል ቀረብ ያለው የብልት ውስጣዊ ክፍል ነው፡፡ ማለትም 10 ሣንቲ ሜትር ያህል ገባ ብሎ የሚገኘው ነው፡፡ ይህን አካባቢ ደግሞ አማካይ ርዝማኔ ያለው አብዛኛው የወንዶች ፍትወት አካል በቀላሉ ሊደርስበት የሚችል እንደመሆኑ መጠን መርዘሙ የግድ አይደለም፡፡

በሶስተኛ ደረጃ ከአራት ሴቶች ውስጥ ሶስቱ፣ በተራክቦ ወቅት አብሮ የክሊቶሪስ /ቂንጥር/ መነቃቃት እንዲኖር ካልተደረገ በቀላሉ መርካት የሚችሉ አለመሆናቸው በጥናት የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ዋናው ቁም ነገር በዚህ መልኩ የሚደረግ የግንኙነት አፈፃፀም ችሎታ እንጂ የወንዱ ብልት ስለወፈረና ስለረዘመ አይደለም፡፡

በእርግጥ ርዝማኔው ከ20 ሣ.ሜ በላይ አካባቢ የሚሆን መጠን ያለው ወንድ፣ የሴቷን የማህፀን ጫፍ ጋር የመፈጋፈግ ዕድሉ ላቅ ስለሚል፣ በሴቷ ላይ ህመምና ስቃይን ሊፈጥርባት ይችላል፡፡በአጠቃላይ ምንም እንኳን አብላጫ የርዝማኔና የውፍረት መጠን ያለው የወንድ ፍትወት አካል፣ ከአናሳዎቹ ጋር ሲነፃፀር በተወሰነ መልኩ የተሻለ ቢሆንም በግርድፉ ሲታይ ግን እውነታው በአፈፃፀም ብቃት መለያየት ላይ የሚመሰረት ይሆናል፡፡ እርግጥ ነው ሴትን ልጅ ለማስረገዝ ወንዱ የዘር ፈሳሹን የማህፀን በር/ጫፍ አካባቢ ማድረስ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ አንፃር የበለጠ ውጤታማው አብላጫ እርዝማኔ ያለው ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ረዘም ያለው የማስረገዝ ዕድልን ያሰፋል ለማለት እንጂ አነስተኛ መጠን ያላቸው አያስረግዙም ለማለት አይደለም፡፡

በብልት መጠን ዙሪያ ወንዶች ያላቸው ስነ ልቦና እንደተጠናው ከሆነ 50 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች የፍትወት አካላቸው መጠን ቢምርላቸው የሚመኙ ናቸው፡፡ ይሄው ተመሳሳይ ጥናት በሴቶች ላይ ያሳየው አስገራሚ ውጤት፣ 85 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች በወንድ ፍቅረኞቻቸው የብልት መጠን በጣም የረኩና የተለየ አሉታዊ መልክ እንደሌላቸው ነበር የተደረሰበት፡፡ 9 በመቶ የሚሆኑት በቂ ነው ብለው የተቀበሉ ሲሆን፣ 6 በመቶ የሚሆኑት ብቻ በፍቅረኞቻቸው የብልት መጠን ቅራኔ እንዳለባቸው የገለፁት በመሆኑም ይህ በ50 ሺ ሴቶችና ወንዶች ላይ የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ፣ የወንዶች የብልት መጠን የሚያስጨንቃቸው ወንዶችን እንጂ ብዙዎች ሴቶች ላይ የሌለ አስተሳሰብ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

ለብልት ማነስ መፍትሄው ምን ይሆን?

እንደሚታወቀው ህክምና የሚያስፈልገው፣ በውል የታወቀና ባይስተካከል ችግር ለሚያስከትል እንከን ነው፡፡ በመሆኑም የዘርፉ ባለሙያዎች አነስተኛ የብልት መጠን ላላቸው ወንዶች የተለያዩ የመፍትሄ አማራጮችን መጠቀም እንደሚቻል ይመክራሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
1. የሆርሞን ህክምና፡- ይህ ቴስቴስትሮን የተባለውንና የወንዳወንድነት ባህሪ የሚያላብሰውን ሆርሞን በመርፌ መልክ በመስጠት የሚደረግ ህክምና ሲሀን፣ ብዙውን ጊዜ በህፃንነት ሲሰጥ ውጤታማነቱ የጎላ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በጎልማሳነት ዕድሜ ላይ መውሰዱ አናሳ ውጤታማነት ያለው ነው፡፡

2. መድሃኒቶች፡- እነዚህ በሚዋጥና በቅባት መልክ ተዘጋጅተው የመውሰዱ የህክክና ዘዴዎች ሲሆኑ የሚዘጋጁትም ከአንዳንድ ዕፅዋት ነው፡፡ በእነዚህ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንዳስረገጡት ከሆነ፣ መድሃኒቶቹ ውስጥ አንዳንድ ጎጂ አካል ነገሮች ተገኝቶባቸዋል፡፡ ለምሳሌም ሻጋ /ፈንገስን/፣ ኢ ኮላይ የተሰኘ ባክቴሪያ፣ እንዲሁም ፀረ አረም ኬሚካሎችነ ሊድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ባለሙያዎቹ እንዳመለከቱትም ምናልባት መድሃኒቶቹ ከተሰሩባቸው ዕፅዋቶች አካባቢ የሚጋለጡ እንስሳት አይነ ምድር ብክለት የተነሳ ሳይሆን እንደማይቀር ይጠረጥራሉ፡፡ በመድሃኒቶቹ ውጤታማነት ላይም ቀጥተኛ የሆነ ብቃት አልያም ምናልባትም ውጤት ቢያመጡ፣ ተጠቃሚዎቹ ችግሬን ይቀርፉልኛል ብለው በማመናቸው የመጣ ስነ ልቦናዊ የህይወት ለውጥ እንደሚሆን ነው፡፡ ይህም በራስ የመተማመንን ባህሪ ያዳብርላቸዋል ብለዋል፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች በክኒን ወይም በቅባት መልክ የሚዘጋጁ ሲሆን በኢንተርኔት በኩል ለሽያጭ የሚቀርቡ ናቸው፡፡

3. ፓምፕ፡- ይህ በብልት ላይ የሚገጠም አነስተኛ መሳሪያ ሲሆን ትንሽ በእጅ የሚሰራ መዝውር ያለው ነው፡፡ ዋናው አላማውም በብልት ውስጥ በዛ ያለ ደም እንዲገባ በማድረግ የብለትን ውጥረት በመጨመር መጠኑን መጨመር ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው በብልት ላይ የሚገጠመው መሳሪያ ‹‹ኔጌቲቭ ፕሬዠር›› በመፍጠር የመሳብ ኃይል የሚኖረው ሲሆን፣ በዚህ የመሳብ ኃይሉም ደምን ከደም ስሮች ወደ ብልት ውስጥ በደንብ እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ልክ ነዳጅን በቱቦ በኩል በእ ስቦ እንደማስተላለፍ ይቆጠራል፡፡ የመዘውሩም ጥቅም ኔጌቲቭ ፕሬዠሩን ለመፍጠር ነው፡፡

ይሁን እንጂ የመሳብ ኃይሉ ከበዛ ወደ ብልት የሚገባው የደም መጠን በጣም ስለሚጨምር፣ የብልት ውስጣዊ ለስላሳ አካላት ላይ ጉዳት ሊያስከትልበት ስለሚችል የግፊት አጨማመሩ በፋብሪካው ትዕዛዝ መሰረት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ፓምፕ አንዳንዶች ራስን በራስ ለማርካት ዘዴም ይጠቀሙበታ፡፡ በዚህ በኩል ለየት ያለ ዕውቅና ያተረፈው ዶናሊድ ቶምሰን የተባለው ዳኛ ሲሆን፣ በፍርድ ሂደት ወቅት ማሽኑን በመጠቀም ማስተርቤሽን ሲፈፅም ስለተደረሰበት የአራት ዓመት እስር እንደተፈረደበት በታሪክ ይዘከራል፡፡ በተለይ በስሜት የመነቃቃት እና የመወጠር ችግር ላለበት ብልት የተዋጣለት ዘዴነው፡፡ እንዲሁም ቶሎ የመርካት ችግር ላለባቸው ወንዶችም በሰፊው ጠቀሜታን የሚሰጥነው፡፡ መሳሪያው ለረጅም ጊዜ ብልት እንደተወጠረ እንዲቆይ የማድረግ ብቃትም ያለው ነው፡፡ መሳሪያው በልዩ ስሙ ‹‹ቫኪውም ፓምፕ›› በመባል የሚታወቅ ነው፡፡

4. ተወጣሪ ተቀባሪዎች፡-እነዚህን የሕክምና አማራጮች ‹‹Inflatable Implants›› በመባል የሚጠሩ ሲሆን፣ በብልት ውስጥ የሚቀበሩና ከፍተኛ የተለጣጭነት ባህሪያቸው ቀጫጭን ቱቦዎች ናቸው፡፡ አላማውም ብልት በስሜት በሚነሳሳበት ወቅት ደም እንደ ልብ ወደ እነዚህ ቱቦዎች በቀላሉ በመግባትና እነሱን በመለጠጥ፣ የብልትን የውጥረት መጠን መጨመር ነው፡፡ እንዳስፈላጊነቱ የቱቦዎቹ መጠን መጨመር ነው፡፡ እንዳስፈላጊነቱ የቱቦዎች መጠን ተለቅ ተለቅ ማድረግ የሚቻል ሲሀን፣ ለረጅም ጊዜም ብልትን እንደተወጠረ የማቆየት ኃይል አላቸው፡፡ ቱቦዎቹ በብልት ውስጥ የሚቀበሩት በቀዶ ጥገና ሲሆን መጥፎው ነገር የተቀበሩትን ቱቦዎች መልሶ ማውጣት የማይቻል መሆኑ ሲሆን ባይወጡ ግን ጉዳት አያስከትሉም፡፡

5. የማሰብ ዘዴ፡- ይህ ዘዴ ዋና አላማው በብልት ውስጥ የሚገባውን የደም መጠን በመጨመር፣ የብልትን ውጥረት በሂደት የመጨመር ዘዴ ሲሆን የሚደረገውም በእጅ ጣቶች ነው፡፡ በከፊል የተነሳሳ ብልትን በአውራ ጣትና በሌባ ጣት ጠበቅ አድርጎ በመያዝ ወደ ላይ የመግፋት ሁኔታ ሲሆን አላማውም ደምን ወደ ብልት የማስገባት ሂደት ነው፡፡ ዘዴው የብልትን ውስጣዊ የደም አቀባበል አቅም በመጨመር በቋሚነት መጠኑን መጨመር ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ በሞቀ ውሃ የተነከረን ጨርቅ ከጣቶቹ ስር (ከብልቱ ላይ) አብሮ በመጠቀም መከወን የበለጠ ውጤት እንዳላውም ይታወቃል፡፡

6. ክላምፒንግ፡- ይህ ደግሞ በአንድ የተወጠረ ብልት ስር ጠበቅ ባለ ቀለበት ወይም የጫማ ማሰሪያ ማሰርና ከዚያም ረዘም ያለ ማስተርቤሽን ማድረግን የሚያካትት ነው፡፡ ብልቱን የሚያስሩት ቀለበት ወይም ክር አላማው ወደ ብልት የገባው ደም ወደ ኋላ እንዳይመለስና ብልት በደንብ እንደተወጠረ እንዲቆይ የሚያደርግ ሲሆ፣ብልትን በሚገባ ማሸት ዘለቄታዊ የደም የመቀበል አቅምንና መጠኑን እንዲጨምር ለማድረግም ነው፡፡

7. በቅድሚያ አትጨነቅ፡- የብልት መጠን መርዘምን፣ ከታላቅ የፍቅር ስኬት ጋር አጣምረህ ለማየት የምትሞክር ከሆነ ሲበዛ የዋህ ነህና፣ ይህ ባህሪህ በተለይ ለፅድቅ ብቻ እጅግ ይጠቅምሃል፡፡ ረጅም ብልት ስላለህ ታላቅ አፍቃሪ ትሆናለህ ወይም ደግሞ የወንዶች የበላይ ነህ ማለት አይደለም፡፡ ተፈቃሪነት ብዙ ነገሮች በውስጡ የያዘ ቃል ነውና፡፡ በዚያ ላይ ሴቶች በግንኙነት ትልቅ ግምት ሊሰጡት ቢችሉ የሚሰጡት አፈፃፀምህን እንጂ ያለህን ብልት መጠን ማጠርና መርዘም አለመሆኑን ልብህ ልብ ይበል፡፡ ቁመትህም ቢሆን!

8. አወዳድር /አትወዳደርም/፡- በቅድሚያ ትንሽ ነው ወይም ትልቅ የሚለው ሐሳብ በጭንቅላትህ አይምጣ፡፡ ምክንያቱም ስለማያስፈልግ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በቁመትና በክብደት እንዲሁም በሌላው አካሉ ከሌላው እንደሚለይ ሁሉ፣ በብልት መጠንም እንዲሁ ልዩነት መኖሩን ተፈጥሯዊ መሆኑን፣ እንዲሁምበፊልምና ኢንተርኔት ፓርኖግራፊ ላይ የምታየውን የወንዶች ብልት ከአንተ ጋር አታነፃፅር፡፡ እነዚህ ወንዶች ከስንት አንድ የተገኙና በብልት ርዝማነሀያቸው ብቻ ፊልሙ እንዲሳተፉ የተደረጉ ናቸውና አብዛኛውን ወንድ አይወክሉም፡፡ በተጨማሪም በካሜራ አንግላዊ አተያይ ውስጥ ትንሹም ቢሆን ገዝፎ እንዲያድግ ማድረግ ስለሚቻል አትጭበርበር፡፡

9. አትገረም! የብልት መጠን እንደ አቋቋምህ፣ አቀማመጥህ፣ እንደ ብልትህ የስሜት መነቃቃት ደረጃ፣ እንደ አየሩ ሙቀትና ቅዝቃዜ በየጊዜው ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ሙቀትና ቀዝቃዛ ሻወር ስትወድ እንኳ በቅፅበት ውስጥልዩነቱን ስለምታየው ባነሰብህ ወቅት አትበርግግ፡፡
10. በመቀነስ ጨምር፡- የብልትህን መጠን በአንድ ኢንች ለማስረዘም ወደ ከፍተኛ ህክምና ውስጥ ከመግባትህ በፊት አንድ ቀላል ዘዴን ተግበር፡፡ የሰውነትህን ክብደት መቀነስ (ወፍራም ከሆንክ ማለት ነው) ይህ አካሄድ ብልት ያረፈበትን የቆዳ ስር ቅባትም ስለሚቀንስ ቁመቱን ማስረዘም ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ 16 ኪሎ ግራም ክብደት ከነበረህ ላይ ብትቀንስ በብልትህ ላይ የአንድ ኢንች ርዝማኔ (2.54 ሣ.ሜ) መጨመር ያስችልሃል፡፡
11. ክብደት ማንጠልጠል፡- ይህ አይነቱ ዘዴ ደግሞ የኮርፖራ ካቫርኖሳ ጡንቻን ከመለጠጥ አንፃር ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ብልት በቆመበት ወቅት መጠነኛ የሆነና ሊቋቋመው የሚችለውን ክብደት ወደ ታች እንዲያንጠለጥል ማድረግ ነው፡፡ ይህ በየቀኑ ለሁለት ወይም ለሶስት ጊዜ የሚከወን ዘዴ ሲሆን፣ ክብደቱ ብልቱን እንዳይጎዳው መጠንቀቅን ይጠይቃል፡፡

12. የቀዶ ጥገና ዘዴ፡- ብልትን በቀዶ ጥገና ከወትሮ መጠኑ እንዲጨምር ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህ ዘዴ የሚታወቀው ደግሞ በዋጋው ውድነት ሲሆን፣ አንድን ብልት በቀዶ ጥገና ቴክኒክ ለማስረዘም በትንሹ የ6000 ዶላር ወጪን ይጠይቃል፡፡ ከቀዶ ትገናው በኋላም ብልት ወደነበረበት እንዳይመለስ ወደ 15 ፓውንድ የሚመዝን ክብደት ወደ ታች እንዲታሰርበት ይሆናል፡፡ ይህም እንኳን ቢሆን አንዳንዶቹ እንደ ስንፈተ ወሲብ መሰል ተያያዥ ችግሮች መጋለጣቸው አይቀርም፡፡

Health: ለቤተሰቦቻቸው፣ለአገራቸውና ለዓለም መመኪያ የሚሆኑ ልጆችን ማፍራት የሚቻለው በአጋጣሚ ወይስ በዕድል?

$
0
0

ask your doctor zehabesha

ሁለት ልጆች አሉኝ፡፡ ሁል ጊዜ የልጆቼ ጉዳይ የሚያሳስበኝ ተምረው ለአገር የሚጠቅሙ እንዲሆኑ በበኩሌ ማድረግ ያለብኝን ሳላደርግ እንዳልቀር ነው፡፡ እናም በዚህ ረገድ ዘሃበሻ መልስ የሚሆን መልዕክት አታጣም ብዬ ይህችን አጭር ጥያቄ ላኩላችሁ፡፡ መልሳችሁን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡

የእናንተው አንባቢ የውብ ዳር

የእኛ ምላሽ!

‹‹ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች›› ብሎም ሀገር ተረካቢዎች እንደመሆናቸው መጠን፣ በአስተዳደጋቸው አስፈላጊው ሁሉ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ያስፈልጋል፡፡

ሲግመንድ ፍሮይድ የተባለው የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ተመራማሪ፣ (ኢፌክትስ ኦፍ ፓረንቲንግ ኦን ቻይልድ ዴቨሎፕመንት) በሚለው ጥናቱ አንድ ህፃን ተወልዶ 7 ዓመት እስኪሞላው ድረስ፣ የሚደረግለት አካላዊና ሞራላዊ ድጋፍ የልጁን የወደፊት ማንነት እንደሚወስን ይናገራል፡፡

በዚሁ ጥናት ሌሎች ተመራማሪዎች፣ በልጆች ሁለንተናዊ ሰብዕና ላይ ያነሷቸው የክርክር ነጥቦችም ተካተዋል፡፡ የተከራካሪው አንደኛ ወገን ‹‹ልጆች ሲወለዱ እንደ ባዶ ወረቀት ናቸው፣ ምንም አይነት ባህሪም ሆነ ዕውቀት ይዘው አይመጡም፣ ሰብዕናቸው የሚቀረፀው ወደዚህች ምድር ከመጡ ጀምሮና በምናሳያቸው እንክባቤና ምልክት ነው›› ሲል ሌላኛው የክርክር ቡድን ደግሞ ‹‹የለም! የአንድ ህፃን ባህሪ የሚወሰነው በዘር ነው፣ ሲለድ ጀምሮ የአባት የእናቱ ወይም ከዚያ ቀደም ያሉትን አያቶቹን ባህሪና ዕውቀት ይጋራል፡፡ ከተወለደ በኋላ የምናደርግለት እንክብካና ከማህበረሰቡ የሚያገኘው ምላሽ፣ በልጁ ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ ተፅዕኖ ያስከትላል›› ይላል፡፡ ለዚህ ጥናቱ እንደ ማጠናከሪያነት የሚጠቀመው ሐሳብ፣ የልጆች ባህሪ አለመመሳሰል፣ የአንድነትና የስኬት መለያየትን ነው፡፡

እነዚህ ሐሳቦች ለበርካታ ዓመታት ሲያከራክሩ ቆይተው፣ በስተመጨረሻ ተቀባይነት ያገኘው፣ የሰው ሰብዕና የሚወሰነው በእርግጥ ከቤተሰብ የምጋራቸው ነገሮች እንደተጠቀቡ ሆነው በአስተዳደግ ሂደት ውስጥ ከቤተሰብ፣ ከትምህርት ቤትና ማህበረሰብ በምንቀስማቸው ዕውቀቶችና ባህሪዎች ይሆናል፡፡

አንዳንድ ወላጆች ስለልጆች አስተዳደግ ያላቸው አመለካከት የተገደበ ነው፡፡ ልጆች መሰረታዊ ፍላጎታቸው ከተሟላላቸው ከቤተሰብ መጠበቅ እንደሌለባቸው ያምናሉ፡፡ ሌሎች ወላጆች ደግሞ ለልጆቻቸው ከመሰረታዊ ፍላጎታቸው በተጨማሪ፣ መጫዎቻዎችን መግዛትና የተለያዩ ስፍራዎች መውሰዳቸውን የእንክብካቤ መጨረሻ አድርገው ይወስዱታል፡፡ እርግጥ ነው ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱም ድርጊቶች፣ ቤተሰቦች ለልጆቻቸው አቅም በፈቀደ መልኩ ሊፅሙት የሚገባ መልካም ተግባር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ግን ልጆች ከምንም በላይ የስሜት ድጋፍ ማግኘትን ይፈልጋሉ፡፡

እንግዲህ የስሜት ድጋፍ በተለያየ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ልጆች ሲናገሩ ማድመጥ፣ አዳዲስ ሙከራዎችን ሲያደርጉ አድናቆት መለገስ፣ ራሳቸውን እንዲሆኑና በራሳቸው እንዲተማመኑ ማበረታታት፣ የበታችነት እንዳይሰማቸው ማገዝ የመሳሰሉት የስሜት ድጋፎች ለአንድ ህፃን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚኖረው ፋይዳ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

በባለትዳሮች መሀል ልጅ ሲፈጠር ትዳር ይባረካል፣ የወላጆችም ደስታ ወደር አይኖረውም፣ ይሄንንም ደስታ አስጠብቆ ለማቆየት ወላጆች አቅማቸውና ዕውቀታቸው በፈቀደ መጠን ልጆቻቸውን የተሻለ ዜጋ አድርገው በማሳደግ ጥረት ሲያደርጉ እናስተውላለን፡፡ በመሆኑም ወላጆች ቀዳሚ የልጅነት ጊዜ ላይ የሚያከናውኗቸው ድርጊቶች፣ በልጆቻቸው የወደፊት ህይወት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ ስለሚኖረው ልጆችን በማሳደግ ሂደት ላይ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

(Baum rind D) የተባለች የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ፣ በተለያዩ ወላጆችና ስለሚተገበሩ የልጆች የአስተዳደግ አይነቶችና ውጤቶቻቸው በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ወላጆች ላይ ጥናት አካሂዳለች፡፡ አምስት ዓመት በፈጀው በዚህ ጥናቷም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያለቻቸውን አራት የልጆች አስተዳደግ አይነቶችን አሳውቃለች፡፡ እነዚህም ‹ፈላጭ ቆራጭ›፣ ‹ሚዛናዊ›፣ ‹ነፃ› እና ‹ቸልተኛ› በመባል የሚታወቁ ናቸው፡፡ አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡፡

1. ፈላጭ ቆራጭ፡ ይሄ አይነት አስተዳደግ ወላጆች ህግና ደንብ በማውጣት፣ ልጆች ምንም አይነት ጥያቄ ሳያቀርቡ የወጣውን ህግና ደንብ እንዲያከብሩ ያስገድዳል፡፡ ልጆች እቤት ውስጥ ባለው የዕለት ተዕለት ሂደት ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ አይኖራቸውም፡፡ በዚህ ቤተሰብ ውስጥ የሚያድጉ ልጆች፣ በተጣለባቸው ሕግና ገደብ ‹ለምን?› ብለው ቢጠይቁም፣ የሚሰጣቸው ምላሽ ‹‹እኔ ስላልኩ ይህን ማድረግ ይኖርብሃል›› የሚል ይሆናል፡፡ ሕግና ደንቡን ሲጥሱም የተደነገገ ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡

በፈላጭ ቆራጭ ቤተሰብ ውስጥ የሚያድጉ ልጆች በአብዛኛው

– ህግና ደንብ በማክበር ይታወቃሉ፡፡

– እልኸኛ የመሆን ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

– ዝቅተኛ የሆነ በስራ መተማመን ይስተዋልባቸዋል፡፡

– ከሰው ጋር ያላቸው ተግባቦት በጣም ዝቅተኛ ይሆናል፡፡

– በትምህርት ቤት ቆይታቸው መልካም የሚባል ባህሪ ይስተዋልባቸዋል፡፡

2. ሚዛናዊ፡

ሚዛናዊ የሆነ የአስተዳደግ ዘዴ የሚከተሉ ቤተሰቦች፣ እንደ ፈላጭ ቆጮቹ ሁሉ የቤተሰብ ህግና ደንብ ያወጣሉ፡፡ ሆኖም የእነዚህን የሚለየው የሚያወጡትን ህግና ደንብ አላማውን ያስረዳሉ፡፡ አንዳንዶቹም የቤተሰቡን ሕግ ከልጆቻቸው ጋር በትብብር ያወጣሉ፡፡ ሕጉ ሲጣስም ምን መቀጣት እንዳለባቸው የመወሰን እድሉንም ይሰጧቸዋል፡፡ ልጆቹም የቤቱን ህግና ደንብ ሲጥሱ የሚጠብቃቸው ቅጣት ራሳቸውን ዝግጁ ስለሚያደርግ፣ በውስጣቸው ጥላቻን ሲያሳድሩ አይስተዋሉም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስነ ምግባራቸውን ለማበረታታት ወላጆች የተለያዩ ስጦታዎችን ያበረክቱላቸዋል፡፡ ሚዛናዊ አስተዳደግን በሚጠቀም ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ልጅ በአብዛኛው፡፡

– ደስተኛ እና ስኬታማ ይሆናሉ፡፡

– ከፍተኛ የሆነ የውሳኔ ብቃት ሲታይባቸው፣ በውሳኔ ጊዜም የተለያዩ አማራጮችን መመልከትና ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችንም ቀድመው ለመገመት ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡

– በህይወታቸው ላይ ኃላፊነትን የሚስዱ ግለሰቦች ይሆናሉ፡፡

– ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ይታይባቸዋል፡፡

– ራሳቸውን መግለፅ ይችላሉ፡፡

– የሰውን ሐሳብ የመቀበል ችግር አይኖባቸውም፡፡

– በአጠቃላይ ለህይወት በጎ የሆነ ዕይታ ያዳብራሉ፡፡

– በቀላሉ ራሳቸውን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር ማለማመድ ይችላሉ፡፡

3. ነፃ አስተዳደግ

ይህን የአስተዳደግ ዘዴ የሚጠቀሙ ቤተሰቦች፣ ምንም አይነት ህግ እና ደንብ ለቤታቸው አያወጡም፡፡ ለልጆቻቸው ያስፈልጋሉ ያሉትን ቁሳቁስ በራሳቸው ተነሳሽነትም ሆነ በልጆቹ ጠያቂነት ከማሟላት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ‹‹ልጆች ልጆች›› ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ ጥፋታቸውም ከልጅነታቸው ጋር የተያያዘ እንጂ በወደፊት ህይወታቸው ላይ ሊያመጣ የሚችለውን የባህሪ ብልሹነት አይቀበሉትም፣ ሁሉንም ነገር ሲያድጉ ይተዉታል ብለውም ያስባሉ፡፡ ከልጆቻቸው ጋር ሊወያዩ የሚችሉት ምናልባት እቤት ውስጥ ከባድ የሚባል ችግር ሲፈጠር ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ቢሆን የተፈጠረውን ችግር ወይም ልጁ የሚያንፀባርቀውን መልካም ያልሆነ ባህሪ ለማስተካከል ብዙም ጥረት አያደርጉም፡፡ ከልጆቸው ጋር የሚኖራቸውም ግንኙነት የወላጅ እና የልጅ ሳይሀን የጓደኛ አይነት ነው፡፡

ነፃ አስተዳደግን በሚጠቀም ቤተሰብ ውስጥ የሚያድግ ልጅ የሚያንፀባርቃቸው ባህሪዎች በአብዛኛው፡-

– ከልክ ያለፈ በራስ መተማመን ይስተዋልባቸዋል፡፡

– በሚፈልጉት ጊዜ ማንኛውንም ነገር እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡

– ሕግና ደንብን ያለማክበር ችግር ይታይባቸዋል፡፡

ወላጆቻቸው ሁሉንም ነገር እየሰጡ ስላሳደጓቸው፣ በትምህርት ህይወታቸውም ሆነ ስራ ላይ፣ ይሄነው የሚባል ጥረት ስለማያሳዩ እኔ ብቻ የተሻልኩ ነኝ ብለው ስለሚያስቡ ስኬት ሲርቃቸው ይስተዋላል፡፡ ዝቅተኛ የሆነ የድብርት መጠን ይስተዋልባቸዋል፡፡

4. ቸልተኛ

እነዚህ አይነት ቤተሰቦች በአብዛኛው፣ የልጆቻቸውን መሰረታዊ ፍላጎት እንኳን በአግባቡ የማያሟሉ ናቸው፡፡ የእነሱ እምነት ልጅ በዕድሉ ያድጋል የሚል ሲሆን በራሳቸው ተፍጨርጭረው ህይወታቸውን እንዲለውጡ ይጠብቃሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ልጆች በስራና በሌላው ህይወታቸው በጣም የተዋጡ ወይም ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የሱስ ተጠቂዎች፣ የአዕምሮ በሽተኞች ወይም ደግሞ በልጅነት ዘመናቸው ከቤተሰባቸው ወይም ከማህበረሰቡ መልካም እንክብካ ያልተደረገባቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥናቶቹ ያመለክታሉ፡፡ እንደ ጥናቱ ምናልባት ልጆቹ የተፈጠሩት ሁለቱም ወላጆች፣ ልጅ ወልደው ለማሳደግ ዝግጁ ሳይሆኑ ወይም በአንደኛው ወገን ግፊትና ፍላጎትም ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል፡፡

እንደዚህ አይነት ባህሪ በሚንፀባረቅበት ቤተሰብ ያደጉ ልጆች በአብዛኛው

– ለመኖር አስፈላጊ የሆነ የህይወት ልምድና ክህሎት ማጣት ይስተዋልባቸዋል፡፡

– በሱስ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

– የወላጆቻቸውን በቂ ፍቅርና አትኩሮ ሳያገኙ ያደጉ ስለሆነ፣ ካደጉ በኋላም የሰውን ‹አትኩሮት የመሳብ ይስተዋልባቸዋል፡፡

– ዕድሜያቸው ለተቃራኒ ፆታ ፍቅር ሲደርስም፣ ተፈላጊነታቸውን ለማረጋገጥ ከቀረቧቸው ሰዎች ጋር ሁሉ በቀላሉ በፍቅር የመውደቅ አባዜ ይስተዋልባቸዋል፡፡

– በአብዛኛው ወንጀል በመፈፀም የሚታወቁ ግለሰቦች ከዚህ አይነት ቤተሰብ እንደመጡ ይኸው ጥናት ያመለክታል፡፡

ምን ይደረግ?

ከላይ በመግቢያችን የጠቀስናት ተመራማሪ በጥናቷ ያሰፈረችው፣ ልጆችን በማሳደግ አስፈላጊ የሆነው ነጥብ (Responsiveness and demanding) ኃላፊነትን መወጣትና ከልጆች መጠበቅ የሚል ሲሆን፣ ከዚህ እሴት አኳያ እያንዳንዱን የአስተዳደግ ዘዴ እናያለን፡፡ ፈላጭ ቆጭ የልጅ አስተዳደግ ዘዴ (Demanding not responsive) ተብሎ የሚፈረጅ ሲሆን፣ እንዲከበርለት የሚፈልጋቸውን የቤተሰብ እሴቶች ከመዘርዘር ውጪ ልጁ ከቤተሰቡ የሚፈልጋቸውን ቅድመ ሁኔታ ስለማያሟላ፣ ተመራጭ ያልሆነ የልጅ አስተዳደግ መሆኑን ትገልፃለች፡፡

ነፃ የሆነ የቤተሰብ አስተዳደግን ስንመለከት ደግሞ (Responsive but not demanding) ይህም ማለት፣ ቤተሰቡ ለልጁ የማያቋርጥ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ፣ ሆኖም አንድ መልካም እሴት ወይም ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ በመሆኑ፣ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ትላለች፡፡

ቸልተኛ የሚባለው አይነት ባህሪ የሚንፀባረቅባቸው ወላጆች፣ ለህይወት አስፈላጊ የሆኑት (Neither Responsiveness Not demanding) ተብሎ የሚፈረጅ የአስተዳደግ አይነት ስለሆነ እጅግ አደገኛ የአስተዳደግ አይነት መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል፡፡

በመጨረሻም የጥናቱ ማጠቃለያ እንዳሰፈረው፣ Demanding (ሚዛናዊ) የሚባለው የአስተዳደግ አይነት ‹‹Bothe responsive and emanding›› በመሆኑ፣ እጅግ ተመራጭና ለልጁ ሁለንተናዊ ዕድገት አዎንታዊ የሆነ ተፅዕኖ የሚያሳድር፣ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ወላጆች ቢከተሉት መልካም ውጤት እንደሚያመጣ ይታመናል፡፡ እንግዲህ የዛሬው ህፃን፣ የነገው አባወራና ሐገር ተረካቢ ነውና በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፣ ልጆቻችንን በማሳደግ ሂደት ውስጥ ለምናከናውናቸው ተግባሮች ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ልጆች የምንፈልገውን ነገር እንዲያደርጉ ከመናገር ይልቅ፣ ምሳሌ ሆኖ መገኘቱ ከሁሉም በላይ ተመራጭ ስለሆነ፣ የመልካም ባህሪ ባለቤትነት ፈርቀዳጅ በመሆን የመልካም ቤተሰብ ባለቤት መሆን ይችላል እላለሁ፡፡

Health: ወንዶች በፍፁም ችላ ሊሏቸው የማይገቡ አደገኛ 5 የጤና ችግር ምልክቶች

$
0
0

health

ጤናና ገንዘብ አያያዝን ጨምሮ በብዙ ነገሮች ጥንቃቄ በማድረግ ከወንዶች በተሻለ ሴቶች ፈጣን ናቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሚበዙት ወንዶች ግን በተለይ የጤና ችግሩ የሆስፒታል አልጋ ላይ የሚጥል ካልሆነ በቀር በምልክቶች መነሻነት ወደ ሆስፒታል መሄድን ልምድ አላደረጉም፡፡ ነገር ግን ይህ የቸልተኝነት ልምድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወንዶችን ከክፉ የጤና ችግር እስከሞት በሚያደርስ አደጋ ላይ እየዋለ መሆኑን ጥናቶች እያመለከቱ ነው፡፡

ችላ የማይገባቸው የጤና ችግሮች

የ52 ዓመቱ ሰው አቶ ግርማ ደጋግሞ ያስቸግራቸው የነበረውን ተደጋጋሚ የትንፋሽ ማጠር በምንም ምክንያት ከክፉ የጤና ችግር ጋር የተያያዘ ነው ብለው አስበው አያውቁም፡፡ አንድ ቀን ግን ነገሮች ተጣደፉና ሐኪም ቤትን በድንገተኛ ታካሚነት መጎብኘት ግዴታቸው ሆነ፡፡ ምርመራ ያደረገላቸው ሐኪም ችግሩ ከልባቸው ጋር የተያያዘ መሆኑንና ሳምባቸውም ውሃ ሳይቋጥር እንዳልቀረ ሲነግራቸው ከፍተኛ ድንጋጤም ውስጥ ገቡ፡፡ የልብ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ ኦፕሬሽን ማድረግ ግዴታ ሆኖባቸው ነበር፡፡ በተደጋጋሚ ችላ ይሉት የነበረውን የትንፋሽ ማጠር ተጠራጥረው ቀድመው ወደ ሐኪም ቢሄዱ ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ህክምና ውስጥ ከመግባት ይድኑ እንደነበርም አቶ ግርማ ይገልጣሉ፡፡ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖ የቅርብ ሰዎችና ባለቤታቸው እቤት ባሉበት ወቅት ችግሩ መከሰቱ ፈጣን ህክምና ለማግኘት አስቻላቸው እንጂ የትንፋሽ ማጠሩ የትም ሊከሰት እና ህይወታቸውንም ሊያሳጣቸው ይችል እንደነበር ሐኪሙ እንደገለጠላቸው እና እድለኛ እንደነበሩም ያስታውሳሉ፡፡

ሁሉም ሰው ግን እን አቶ ግርማ ዕድለኛ ሊሆን አይችልም፡፡ የህመም ምልክቶችን ችላ በማለት ቆይተው በቂ ህክምናን አግኝተው ከከባድ በሽታዎች የሚያገግሙ ሰዎችም ብዙ አይደሉም፡፡ አንዳንዴ እጅግ ከዘገዩ የሚታወቁ ምልክቶችም በቀጥታ ለዘላቂ የአካል ጉዳት አለዚያም ሞት የሚያደርሱበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ ከሴቶች በበለጠ ወንዶች የበሽታ ምልክቶችን ችላ የማለት እና የህክምናን እርዳታ ለመጠየቅም እጅግ እንደሚዘገዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እንዲያውም በቅርቡ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው በብዙ አገራት ከ38 በመቶ በላይ ወንዶች ሆስፒታሎችን የሚጎበኙት ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥል ችግር ሲገጥማቸው ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ተደጋጋሚ ጥናትን ያካሄዱ ባለሙያዎች እባካችሁ ወንዶች የከፋ የጤና ችግርን ጠቋሚ ለሚሆኑት ምልክቶች ትኩረት አድርጉ ሲሉ የሚያሳስቡት፡፡

5. ሽንት መሽናት መቸገር፣ ደም የቀለመ ሽንት

ሽንት ሰውነት ቆሻሻን አጣርቶ የሚያስወጣበት ፈሳሽ እንደመሆኑ ጤነኛ መጠን፣ ቀለም እና ድግግሞሽ የሰውነትን የማጣራት አቅም እንዲሁም ኩላሊትና መላውን የማጣሪያ ስርዓት ጤንነት ደረጃ ይገልጣል፡፡ በወንዶች ዘንድ ከሚታዩ የችግር ምልክቶች አንዱ ሽንት ለመሽናት መቸገር ነው፡፡ በተለይ ሲሸኑ ህመም የሚሰማዎት ከሆነ እና መሽናት እየፈለጉ ከመፀዳጃ ቤት ሲደርሱ ግን የሚታገሉ ከሆነ ጉዳዩ የፕሮስቴት እጢ ችግርን ይጠቁማልና ቶሎ የሐኪም እርዳታን ይጠይቁ ሲሉ ይመክራሉ፡፡ የፕሮስቴት እጢ የወንድ ዘርን እንደልብ ለመቀስቀስ የሚያስችለውን ፈሳሽ የሚያመርት ከሽንት ከረጢት በታች የሚገኝ በጣም አነስተኛ ዕጢ ነው፡፡ የዚህ እጢ ችግር በጊዜ ካልተቀረፈ ከፕሮስቴት ካንሰር እስከ ልጅ የመውለድ ብቃትን ማሳጣት የሚያደርስ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል፡፡

ሽንት በተፈጥሮ ጤናማ ቀለሙ ቢጫ ነው፡፡ ከዚህ በመጠኑ የተለየ ሽንት ማየት ከተመገቡት ምግብ ጋር የሚያያዝ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ ባለፈ ሁኔታ ግን በተደጋጋሚ ደም ማየት ከበድ ያለ ችግርን ጠቋሚ ምልክት ነው፡፡ ይህ መሰሉ ችግር የፕሮስቴት እጢ ካንሰርን ከመጠቆም ባለፈ የሽንት ቧንቧ መስመር መቆጣት፣ ኢንፌክሽን፣ የኩላሊት ጠተር እንዲሁም ሌሎች የኩላሊት በሽታ አይነቶች እየተከሰቱ መሆናቸውን አመላካች በመሆኑ በፍፁም ችላ ሊሉት አይገባም ሲሉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

 

4. የደረት ላይ ህመም

ድንገትደረትን ስቅዝ አድርጎ የሚይዝ ህመም በአንድ ወይም በሌላ ጊዜ ገጥምዎት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ መሰሉ ምልክት ደገምገም የሚያደርግ ከሆነ ግን ብዙ የሚናገረው የጤና ችግር ስላለ ፈጣን እርምጃ ሊወስዱና ሐኪም ጋር ሊቀርቡም ይገባል ባይ ናቸው ባለሙያዎቹ፡፡ የደረት ላይ ህመም የልብ ድካምን ጠቋሚ ከመሆኑ በተጨማሪ እንደ ኒሞኒያ፣ አስም እንዲሁም ሌሎች ከምግብ መፍጫ ስርዓት ችግሮች ጋር የተያያዘ እክል እየተፈጠረ መሆኑን አመላካች ነው እና ችግሩ ገፍቶ እስኪመጣ መጠበቅና እራሱ በራሱ እንደሚሄድ መገመት ችግርን መጥራት ነው፡፡

3. ተደጋጋሚ ድብርት

ሁላችንም የየራሳችን መጥፎ ቀናት አሉን፡፡ ሰው ማናገር የምንጠላበት፣ የምንወደው ነገር ሁሉ ትርጉም የሚያጣበት እና በአጠቃላይ ሁሉ ነገር የሚያስጠላን ጊዜ አለ፡፡ ነገር ግን ይህ አልፎ አልፎ የሚከሰት እና በዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴያችን ከሚከሰቱ ደስታችንን  ከሚያደምኑ ጉዳዮች ጋር የሚያያዝ እና ችግሮቹ መፍትሄ ሲያገኙ አብሮ የሚፈታ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ አልፎ መደበኛ የህይወት አካል መሆን ሲጀምር ግን ከጀርባው ሌላ ያልተፈታ ስነ ልቦናዊ ወይም ማህበራዊ ችግርን ጠቋሚ ሊሆን ይችላል፡፡

ሴቶች ከወንዶች በተሻለ ድብርትን ለይቶ የማወቅና ምክንያቱን የመፈለግ እንዲሁም ከጓደኛና ቤተሰብ ጋር በመወያየት የመፍታት ተፈጥሯዊ ልምዶች አሏቸው፡፡ ወንዶች በተቃራኒው መጠጥን ትርጉም የሌለው ወሲብን እና እንደ ጫት መቃም የመሰሉ አጉል ልምዶችን በመተግበር ወይም መጠልን በመምረጥ ድብርታቸውን ለማስታገስ ቀዳሚው የባለሙያዎች ምክር ሲሆን ተደጋጋሚ ድብርት ደግሞ ህይወትን እስከማጣት የሚያደርስ ጥፋት ውስጥ ሊከት ስለሚችል በቅድሚያ በቅርብ ላለ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ ችግሩን ማዋራት፣ በዚያ የሚቀል ካልሆነ በአፋጣኝ ወደ ባለሞያ መቅረብና ዘላቂ መፍትሄ ማበጀት ይገባል፡፡ ድብርት ችላ አይበሉ!

ካንሰር በሁለቱም ጾታዎች ተደጋግሞ የሚታይ ችግር ቢሆንም በወንዶች ዘንድ ካንሰር በምርመራ ሲታወቅ ብዙ ጊዜ ዘግይቶ እና ለህክምናም አስቸጋሪ በሚሆንበት ደረጃ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት ከሚነሱ ጉዳዮች ቀዳሚው ወንዶች ዘንድ የአካላቶቻቸውን የተለያዩ ለውጦች አለመከታተላቸውና ችግር ሲኖርም የህክምና እርዳታን አለመሻታቸው ነው ሲሉ ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ፡፡

ሴቶች የጡት ካንሰርን ቀድመው እንዲያውቁ ጡቶቻቸውን በየጊዜው እራሳቸው በእጃቸው እንዲፈትሹ እና የተለየ እብጠት ከተሰማቸው ለባለሞያ እንዲያሳዩ ይመከራል፡፡ በዚህም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሴቶች ካንሰርን በጊዜ መፍትሄ አብጅተውለታል፡፡ በወንዶች ዘንድ ከሚታዩ የካንሰር አይነቶች አንዱ የወንድ ዘር ፍሬ ማምረቻ (ቆለጥ) ውስጥ የሚከሰት ካንሰር ነው፡፡ ይህን የካንሰር አይነት እንደ ሴቶች ጡት ሁሉ ቀላል ፍተሻን ራሳቸው ወንዶች በቆለጦቻቸው ላይ በማድረግ ቀድመው ሊደርሱበትና በባለሞያም እርዳታ ሊያገኙበት ይችላሉ፡፡ ወንዶች ሰውነታቸውን በሚታጠቡበት ወቅት አጠቃላይ ሰውነታቸውን ማስተዋል፣ አልፎ አልፎም በቆለጥ አካባቢ የተፈጠሩ በደንብ የማያስታውቁ አነስተኛ እብጠት መሰል ነገሮች ካሉምመፈተሽ፣ ካንሰሩን ቀድሞ ለመለየት ይጠቅማልና ይህንን ችላ አይበሉ ሲሉ ባለሞያዎቹ ያስረዳሉ፡፡

2. የሆድ ድርቀት

ከምንመገባቸው ጋር በተያያዘ የሚፈጠር የሆድ ድርቀት ጊዜያዊ ችግር በመሆኑ ለወንዶች ብቻ ሳይሆን ሴቶችንም ይህን ያህል ስጋት ላይ የሚጥል ችግር አይደለም፡፡ ነገር ግን በተደጋጋሚ የሆድ ድርቀት ሲከሰት በተለይ ወንዶች ትኩረት መስጠት እና ዋናውን ምክንያት ለይቶ መፍትሄ ማበጀት የግድ ይሆንባቸዋል፡፡ የሆድ ድርቀት መሰረታዊ ምክንያቶች በርካታ ሊሆኑ ቢችሉም የአንጀት ካንሰርን መጠርጠር የብዙ ባለሞያዎች ቀዳሚ ግምት ነው፡፡ የሆድ ድርቀት ከጀርባው ካለው ምክንያት በተጨማሪም በራሱ ሌላ ጣጣንም ይዞ ይመጣል፡፡

የሆ ድርቀት በቀላል መወሰድ የሌለበት ዋና ምክንያት ሄሞሮይድ የተሰኘውና በተለምዶ የፊንጢጣ ኪንታሮት ብለን የምንጠራው በአብዛኛው ወንዶችን የሚያሰቃየውን ህመም ለመከላከል ነው፡፡ ሄሞሮይድ ይህ ነው የተባለ መነሻ ምክንያት ባይቀመጥለትም በሆድ ድርቀት ወቅት አይነምድርን ለማስወጣት በከባድ ማማጥ የግድ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜም የፊንጢጣ አካባቢ ስለ ህዋሳት የመጎዳትና የመድማት አደጋ ይገጥማቸዋል፡፡ ይህ የህዋሳቱ ነርቮቹ መቆጣተ የፊንጢጣ ጫፍ እንዲገለበጥና መቀመጥና መቆም እንዲሁም አይነምድር መውጣት ትልቅ ፈተና እንዲሆን ያስገድዳል፡፡ ለህክምና አስቸጋሪ ከመሆኑ አንፃር አንዳንድ ሰዎች እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ በባህል ህክምና ችግሩን ሳያዳግሙ ለመንቀል ሲጥሩ ለተወሳሰበ ቀውስ የተዳረጉበትን ጊዜ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በቅርብ ያውቃል፡፡ የሄሞሮይድ ህመም እጅግ ከባድና ለማንም አይስጥ የሚባል አይነት ነው፡፡ ለዚህ ነው ረጅም ጊዜ የሚቆይ የሆድ ድርቀትን በባለሞያ እርዳታ በፍጥነት ማስወገድ የሚመከረው፡፡

  1. የወሲብ ችግር

ሁሉም በሚቻል ደረጃ ወንዶች በአንድ ወይም በሌላ ጊዜ ብልታቸውን ለወሲብ ማቆም እና ከዚያም እስከወሲቡ ፍፃሜ የመዝለቅ ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ 70 በመቶው የሚደርስ ለወሲብ ዝግጁ አለመሆን ችግር ከስነ ልቦናዊ ጉዳዮች ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ጠለቅ ያለ ዳሰሳን ይጠይቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ግን የወሲብ ብልት አለመቆም ከበድ ካሉት የልብ ህመም፣ የስኳር ህመም እንዲሁም የደም ቧንቧ ችግሮች ጋር የሚያያዝ በመሆኑ በቀላል መውሰድ እንደማይገባ ባለሞያዎች ያሳስባሉ፡፡

በተፈጥሮ የወንድ ብልት ለወሲብ የሚቆመው ከአዕምሮ በሚሰጥ ትዕዛዝ ይሁን እንጂ ከልብ ተነስተው ወደ ብልት የሚነሳ የደም ቧንቧዎች ከልብ በሚወስዱት ደም ሲሞላ ነው ብልት የሚቆመው፡፡ በመሆኑም ማናቸውም በልብ እና ደም ቧንቧ ህመሞች ላይ የሚከሰት እክል በወሲብ ላይ እክል ያመጣል፡፡ የወሲብ ችግር ከአንድ ሰሞን አልፎ ተደጋጋሚ የሚሆንባቸው እና ብልታቸውን ማስነሳት የሚቸገሩ ሰዎች ችግራቸው ወሲብ ላይ ብቻ ሳይሆን ሰፋ ካሉት ሌሎች አካላትም ጋር ስለሆነ ይህንን ማስጠንቀቂያ የምር ወስደው አስቸኳይ የባለሙያ እርዳታ ማግኘት አለባቸው፡፡

በመነሻችን ታሪካቸውን ያካፈልናችሁ አቶ ግርማ ህይወታቸውን አደጋ ላይ የጣለውን ምልክት ሰዎች ችላ እንዳይሉ ደጋግመው ለወዳጆቻቸው ይነግራሉ፡፡ የትንፋሽ ማጠር ብቻ ሳይሆን ቀደም ብለን ያነሳሳናቸውም ምልክቶች ከበስተጀርባቸው ብዙ የጤና ችግሮቹን ይዘዋልና ትኩረትን ይሻሉ፡፡

Health: ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ ምን ማረጋገጫ አለህ? | 10 መላዎችን ና ተማር

$
0
0

ይህ ጽሁፍ በዘሐበሻ ጋዜጣ ላይም ታትሞ ወጥቱዋል

የቅርብ ጊዜ የስነ ልቦና ጥናታዊ ሪፖርቶች… ሴት ልጅ ለአንተ ልዩ ፍቅርና መውደድ እንዳላትና እንደሌላት አዕምሮዋን በአካላዊ እንቅስቃሴዎቿ በኩል በቀላሉ እንድታነብ ያስችሉሃል!!

አካላዊ እንቅስቃሴዎች ዋነኛዎቹ የመግባቢያ መንገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴና ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴ ይባላሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴዎች በራሳቸው ቋንቋ በመሆን ከንግግርም በላይ በሆነ መልኩ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ እንዲህ አይነት ተግባቦት በአብዛኛው በተቃራ ፆታ ግንኙነት ውስጥ በተለይም በሴቶች ላይ ይስተዋላሉ፡፡
how do u know
ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴ

አንድ ጊዜ ከሴት ጋር አይን ለአይን ከተገጣጠምክ ፊቷን ካዞረች በኋላ ያላትንም እንቅስቃሴዎች አስተውል፡፡ አይናች በመጋጨቱ አፍረት ወይም መጨናነቅ ነገር ከታየበት ተመችተሃታል ወይም ወዳሃለች ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ፀጉሯን እንደማፍተልተል፣ ልብሷን ወይም ጌጣጌጧን ማስተካከል ወይም ደግሞ እጇ ላይ ባለው ነገር መጫወት ከጀመረች እነዚህ ግልፅ የሆኑ ማረጋገጫዎችህ ናቸው፡፡

– ውስጥ እጇን አንብብላት፡- በአጋጣሚዎች እና አንድ ላይ በምትሆኑባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እጇን ብትመለከት እሷም አሳልፋ ውስጥ እጇንና የእጇን አንጓ እንድትነካ ከፈቀደችልህ ሌላው ያንተ እሷን የመመቸት የአዕምሮ ፍቃድ ማሳያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ ‹‹ከፈለከኝ ያንተው ነኝ›› እንደማለት ነው፡፡
– ማጎንበስ፡- በምታጎነብስበት ጊዜ ትከሻዋን ወደ አንተ በመስበቅ ካጎነበሰች ዕድል በእጅህ ገብታለች ማለት ነው፡፡

– እግሮቿን ከፍታ በምትቀመጥባቸው አጋጣሚዎች ካሉ አንተ ጋር በመሆኗ ምቾት ተሰምቷታል ማለት ነው፡፡
– አንድ ሴት አንድን ሰው በምታይበት ጊዜ የአይን ብሌኗ ከሰፋ ያንን ሰው እንደምትወደው በተቃራኒው ደግሞ የአይን ብሌኗን ካጠበበች ለዛ ሰው ጥሩ ስሜት እንደሌላት አንድ መገለጫ ነው፡፡ አይን ለአይን በምትጋጩበት ጊዜ ፈገግታን ከቸረችህ ወደ እሷ ሂድና አነጋግራት፡፡ ሌላው እንደ መልካም ነገር መገለጫ የሚወሰደው አንተ በምታወራበት ጊዜ ለረባ ባልረባው ፈገግ የምትል ወይም ሳቅ የምታበዛ ከሆነ በእርግጠኝነት በደንብ ተመችተሃታል ይሄ ደግሞ የበለጠ የተሻለ ነው፡፡
– በምታወሩበት ጊዜ ሁሉ በተለይ ደግሞ እሷ ስታወራ አንተን በተለያዩ አጋጣሚዎች የምትነካህ ከሆነ መልካም ነገር አለ ማለት ነው፡፡ አይኖቻችሁ በሚጋጠሙበት ጊዜም ምቾት የማይሰጥ ቢሆን እንኳን እንደተፋጠጣችሁ ልትቆዩ ትችላላችሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ላይ መርሳት የሌለብህ ነገር ቢኖር ፊትህን ከማዞርህ በፊት ፈገግ ማለትን ነው፡፡

ይህ ሁኔታ ታዲያ የአንተ እሷን መውደድና መልካም ሰውነት ያሳያል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም በአንዳንድ አጋጣሚዎች እየሰረቀቸፍ ስታይህ ልታጋጥምህ ትችላለች፡፡ ከሁለተኛውና ከሶስተኛው መገጣጠም በኋላ እንድታናግራት መፈለጓን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡
እንደ መልካም ተጫዋችነትህ የጨዋታውን ህግ በማክበር የፈለገችውን ነገር ማሟላት ግድ ይልሃል፡፡
መሽከርከር፡- አንድ ሴት ፀጉሯን አየር ላይ ወርውራ ወዲያው ዞራ ካየችህ አንተ እንድታያት ለማድረግ እየጣረች መሆኑን ማመን ትችላለህ፡፡
ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴዎች

በማንኛውም ሁኔታ ስትመለከታት አይኗን ውስጡን የምታሽከረክረው ከሆነ በአንተ አቀራረብ ማፈሯንና እንዲሁም በአንተ ደስተኛ አለመሆኗን ለሰዎች ለማሳየት እየጣረች መሆኑን ማወቅ አለብህ፡፡ ይህ ነገር ከተፈጠረ እሷን የማግኘት እድልህ ትንሽ በመሆኑ ማድረግ ያለብህ ፊትህን አዙሮ መሄድ ነው፡፡

– በምታወሩበት ጊዜ እጇን ካጣመረች መጨናነቋን ወይም በሁኔታው ምቾት እንዳልተሰማትአመላካች በመሆኑ እስትራቴጂህን ወይም ስልትህን በፍጥነት መቀየር ይኖርብሃል፡፡ ሌላው ከዚሁ ከማጣመር ጎን የሚያያዘው የእግር ማጣመር ነው፡፡ እግር ማጣመር ልክ እጅን የማታመር ያህል መጥፎ ሲሆን ይህን አጋጣሚ የበለጠ መጥፎ የሚያደርገው ደግሞ አንድ ጊዜ እግሯን ካጣመረች እጇንም የማጣመር ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና እግሯን አጣምራም ቢሆን ጉልበቶቿ ወደ አንተ ከዞሩ ትንሽ ከመጨነቋ ውጪ ከአንተ ላይ ፍላጎት እንዳላት ያመላክታል፡፡ ተቃራኒው ሆኖ ጉልበቷ በሌላ አቅጣጫ ከዞረ ግን ችግር ውስጥ ነህ ማለት ነው፡፡

ወደኋላ መሸሽ ወይም መለጠጥ፡- ወንበር ላይ ከአንተ ራቅ ብላ ወይም ተለጥጣ የምትቀመጥ ከመሆን በደንብ የሚስተዋል አንተን ያለመሻቷ መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ምክር የሚሆነው የዚህ አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በምታይበት አጋጣሚ ጨዋታውን ጥሎ መውጣት ብቻ ነው መፍትሄ የሚሆነው በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሴቷን የራሳቸው ማድረግ የሚችሉት ልምዱ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡

የአካላዊ እንቅስቃሴ ማታለያዎች

አንድ ሴት አንተን እየተከታተለችህ መሆኑንና ያለመሆኑን ለማወቅ አንድ የሚያስቅና የሚሰራ ማታለያ ልንገርህ፡፡ እሷ አንተን በምታይበት ሁኔታ ላይ ሆነህ ሰዓትህን እያየህ በዝግታ ከ1-3 ቁጠርና ቀና ብለህ እያት፡፡ እሷም ሰዓቷን እያየች ከሆነ አንተን ስታይህ እንደነበር እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ አንተን የሚወድ ሰው ባህሪ ነው፡፡ ልክ አንተ ሰዓትህን ማየት ስትጀምር እሷም ምን እየጠበክ እንደሆነ በማሰብ ሰዓቷን ታያለች፡፡
ተጨማሪ የአካላዊ እንቅስቃሴ መረጃዎች

1. ፀጉር ማፍተልተል

አብዛኛውን ጊዜ ፀጉሯን የምታስተካክል ወይም የምታፍተለትል ሴት የወንዶችን አይን ለመማረክ የምትሞክረው ናት፡፡ ፀጉር ማፍተልተሏንም ሆነ መነካካቷን በደቂቃ ውስጥ ሶስት ጊዜ የምታደርገው ከሆነ መያዝም ሆነ መታየትን የምትፈልግ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ሌላው ደግሞ ፀጉሯንየምትነካበት መንገድም የራሱ የሆነ መልዕክት እንዳለው መዘንጋት የለብህም፡፡ ይህም ፀጉሯን በቀስታ የምትነካካ ከሆነ የፍቅር ጥበብ እንዳላት ማወቅ የምትችል ሲሆን ከፈጠነች ደግሞ ማፈሯንና ትዕግስት አልባ መሆኗን ማየት ትችላለህ፡፡

2. የብርጭቆ ጠርዝ ላይ እጅን ማሽከርከር

በሲግመንድ ፎርይድ ቲዎሪ መሰረት ይህ ምልክት ለወሲብ የመጋበዝ ያህል ነው፡፡ ይህ አባባል ታዲያ በብዙ ሴቶች ተደግፏል፡፡ ይህን ጊዜ ታዲያ የጣቶቿን እንቅስቃሴ ልብ ማለት አለብህ፡፡ በዝግታ ጣቶቿን የምታሽከረክር ወይም የምታንቀሳቅስ ከሆነ ጥልቅ የሆነ እርጋታን፣ እራስ መቆጣጠርንና ጥበቃን አመላካች ስለሆነ ከጎኗ ልትቀመጥ ትችላለህ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በጥፍሯ ብርጭቆውን መምታት ከጀመረች ለነገሮች ትዕግስት ማጣቷንና መቸኮልን ወይም በሌላ መልኩ በወንድ ጓደኛዋ መናደዷን አመላካች ነው፡፡

3. በክንዷ ስትደገፍ

አሪስቶትል እንዳለው ከሆነ የሴት እጅ ብዙ ነገር ያወራል፡፡ በአካል እንቅስቃሴ ላይ ጥናት አድራጊዎች ደግሞ ሴቶች በእንቅስቃሴያቸው የበለጠ ነገሮችን እንደሚገልፁ ያብራራሉ፡፡ በክንዷ ደገፍ ብላ እጇን አገጯ ስር በማስቀመጥ አይኗ በሀሳብ ከዋለለ ተመስጣብኛለች ብለህ በማሰብ እንዳትሳሳት እንደውም በዛ ሰዓት ላይ እራሷን በመጠየቅ ላይ ስለምትገኝ ትንሽ ታገሳት፡፡ እሷም በዛ ሰዓት እያሰበች ከምትሆናቸው ጥያቄዎች አንዱ ‹‹ለዚህ ሰው እገባዋለሁ?›› ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሴቶች ብዙ ጊዜ ለጥያቄዎቻቸው መልስ የሚፈልጉት በዚህ መልኩ ስለሆነ ነው፡፡ መልሱ ምን እንደሆነ አንተ ታውቀዋለህ፡፡ ስለዚህ በተሳካ ሁኔታ እረጋ በማለትና በቀልድ በማዋዛት ውሳኔዋን ልታስቀይራት ትችላለህ፡፡

4. እጇን በማጣመር ተደግፋ ስትቀመጥ

ይህ አጋጣሚ በጭፈራ ቤትም ሆነ በየትኛውም ቦታ ሴት በማደን ላይ ከሆንክና ካጋጠመህ ዕድለኛ አይደለህም ማለት ነው፡፡ በዚህ አይነት አጋጣሚ ያለች ሴት ሁኔታህ አልተመቻትም ወይም አልተማመነችብህም ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ታዲያ የተዘጋጀህበትም ቀልድም ሆነ ፈርጣማ ሰውነትህ ትርጉም ስለሌላቸው ባትለፋ ይሻላል፡፡ አይ ካልክ ደግሞ ቀለል ያለ የወሬ መጀመሪያ መንገድ ብትፈልግ ያዋጣሃል፡፡

5. ከንፈሯን ስታረጥብ

አንድ ሴት ከአንተ ጋር እያወራች በተደጋጋሚ ከንፈሯን የምታረጥብ ከሆነ ለፍቅር ያላትን ተነሳሽነት ይገልፃል፡፡ የስነ ባህል ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ሴቶች እንደዚህ አይነት ምልክት የሚሰጡት ከንፈራቸው ላይ ሌላ ነገር እንዲቀመጥ ሲፈልጉ ነው፡፡ ምን ሊፈልጉ እንደሚችሉ መቼም ላንተ መንገር የለብኝም፡፡

6. ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ

ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ ከሆነ ነፃነት ያላት ሴት መሆኗን መናገር ይቻላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ውስጥ መቀለድም ሆነ በትልቁ መሳቅ ላይጠበቅብህ ይችላል፡፡ ተነሳሽነቱን እሷ መውሰዷ ካልደበረህ በሁኔታዎቹ አብራችሁ ልትዝናኑ ትችላላችሁ፡፡
7. እግር ማወዛወዝ

እግር ማወዛወዝም ሆነ በፍጥነት ማጣጠፍ ሴቷ ለወሲብ ያላትን ተነሳሽነት ያሳያል፡፡ ይህን አጋጣሚ ደግሞ የበለጠ የሚያበረታታው እግሯን በማንቀሳቀስ ላይ እያለች ሳታስበው የምትከፍት ከሆነ ነው፡፡ በሲግመንድ ፎርይድ ክላሲካል ቲዮሪ መሰረት ይህ አጋጣሚ ለወሲብም ክፍት መሆኗን ጠቋሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሳይነሳ የማይታለፈው የምታደርገው የጫማ አይነት ነው፡፡ የጫማው አይነት ለማውለቅ የበለጠ ቀለል ያለ ከሆነ ለነገሮች ያላትም ተነሳሽነት ቀላል መሆኑን የበለጠ አመላካች ነው፡፡ ለዚህ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው በቤዚክ ኢንስትኒክት /Basic Instinct/ ፊልም ላይ የሻሮን ስቶን እግር አከፋፈት ነው፡፡

8. የጣቶች አይነት

አንድ ሴት ለእጇ ያላት አመለካከት የበለጠ ነገሮችንገላጭ ሲሆን በደንብ የተሰሩ ረጃጅም ጣቶች በጥንቃቄ የተቀለሙ ጥፍሮች መልካም የሆኑ አነቃቂ ነገሮች ናቸው፡፡ ይሁንና ሴቷ እጆቿን የምታንቀሳቅስበት መንገድ የበለጠ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባው ነው፡፡ ለረጅም ሰዓት እጆቿ ላይ በመፍጠጥ ከቆየች መናደዷን መረዳት ትችላለህ /ምናልባት ባንተ?/ ጠረጴዛውንም በጥፍሮቿ የምትመታ ከሆነ ተመሳሳይ መልዕክት ስለያዘ ብታስብበት ይሻላል፡፡

9. ከንፈሯን ከበላች

በመሳሳም ወቅት ከንፈርህን ከነከሰችህ ፍፁም አታቋርጣት፡፡ ምንም መጥፎ የሆነ ነገረ የለም፡፡ ግን እሷ በራሷ የራሷን የምትነክስ ከሆነ ለመጨናነቋ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ለምን? ለሚለው መልስ ምናልባት በጥያቄ አይን አፍጥጠህባት ይሆን?

10. ነፍሷን አዳምጠው

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ መደበኛ ወንድና ሴት ግንኙነት ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ሲሆኑ በወሲብ ላይ ጤናማ የሆነ መልዕክት ያላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህን መልዕክቶች አንብቦ መተርጎምና በእንቅስቃሴው ውስጥ የራስህን ድርሻ መውሰድ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ ሌላው ግን በደንብ እሷን መከታተልና ነፍስያዋ ማዳመጥ ዋናው ነገር ነው፡፡ አንድን ሴት አይተህ ከአንተ ምን እንደምትፈልግ ወሲብ፣ ፍቅር ወይስ ጥልቅ ቅርርብ የሚለውን ነገር ለማወቅ እነዚህን ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ማስተዋልና ነፍሷን ማወቅ ትችላለህ፡፡

ጮክ ብላ የምትስቅ ከሆነ፣ ከንፈሯን ካረጠበች፣ በጡቷ ወይም በዳሌዋ ከገፋችህ፣ በጥልቅ ካዳመጠችህ፣ በኩራት ከተራመደች፣ ዳሌዋን ካማታች፣ የአይን አሰባበሯ፣ እግሯን አጣምራ ወደኋላ ከገፋችው፣ ፊቷን ከሸፈነች፣ በጣቶቿ ፀጉሯን ካበጠረች፣ የማይነኩ የሰውነት ክፍሎችህ ውስጥ እጆቿን ከሰደደች፣ እስቶኪንጓን ካስተካከለች ወይም በሹራቧ ቁልፍ ስትጫወት፣ በጣም ከዘነጠች ከተኳኳለችና ሽቶ ከተጋነነ፣ በጆሮህ በተደጋጋሚ በመምጣት የምታንሾካሹክ ከሆነ ወይም ደግሞ ፍቅራዊ የሆነ ሌላ መንገድ ከተጠቀመች፣ በጥልቀት ካፈጠጠችብህ፣ እንዲሁም በአይኗ መዝናህ ካንተጋር የበለጠ ሰዓት ለማሳለፍ ከፈለገች በነገሮች ላይ እርግጠና ልትሆንና የራስህን ውሳኔና እንቅስቃሴ ልታሳልፍ ትችላለህ፡፡


Health: በወሲብ ምክንያት ወንድ ላስጠላቸው ሴቶች መላው ምን ይሆን?

$
0
0

red card
በወሲብ ጊዜ ከደስታ ይልቅ ህመም፣ ከሰላም ይልቅ ጭንቀት፣ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን የሚያስተናግዱ ሴቶች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ በዚህ የተነሳም ፍቅራቸውና ትዳራቸው የተናጋ፣ ወንድን ወደ መጥላት የተሸጋገሩ ሴቶች አሉ፡፡ የወር አበባዋን ማየት እንዳቆመችና በተለምዶው አባባል የማረጫ ዕድሜዋ ላይ እንደተገኘች አልማዝ (ለዚህ ታሪክ ሲባል ስሟ የተቀየረው)፣ ወሲብ በምትፈፅምበት ወቅት ህመም ይሰማት የጀመረው ብዙም ሳይቆይ እንደሆነ ነው የምትናገረው፡፡

‹‹ከባለቤቴ ጋር ግንኙነት ሳደርግ በውስጤ ስለት ያለው ቢላ ዘልቆ እንደገባ ነው የሚሰማኝ፡፡ ከጎበኘኋቸው የህክምና ባለሙያዎች የሚታዘዙልኝ ቅባቶች ስቃዬን ቢቀንሱልኝም ለሀፍረት መጋለጤ፣ ራሴን መጠራጠሬ፣ ለግንኙነት ስዘጋጅ መሸበሬ አልቀረም..›› ትላለች፡፡

አልማዝ እየተሰማት ባለው ህመምና እሱን ተከትሎም የተቆጣጠራት ፍራቻ ለስምንት ዓመታት አብሯት የቆየ ነው፡፡ የመራቢያን አካል ስለሚያጠናክረውና ስለሚያፍታታው የህክምና ስፖርት ዘግይታ መረዳቷን ነው የምትናገረው፡፡ ዱባይ በመመላለስ ህክምናዋን እንደተከታተለች የምትናገረው አልማዝ የተአምር ያህል በራሷ ላይ ለውጥ ተመልክታለች፡፡

በህክምና ሳይንስ አጠራሩ ‹‹ዲ ስፓራውኒያ›› የሚባለው ቃል፣ ከግሪክ የተወረሰና ትርጉሙም በሚገባ ያልተጣጣመ ወይም ያልገጠመ እንደማለት ነው፡፡ ባለሙያዎቹ ታዲያ በወሲብ ወቅትና በኋላ ላይ በሴቶች የመራቢያ አካል ላይ የሚፈጠረውን ህመም ለመግለጽ ቃሉን ይጠቁመበታል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዓለም ሚሊዮኖች ሴቶች በዚህ ችግር እንደሚሰቃዩ ነው የሚነገረው፡፡ ችግሩ ወሲባዊ ፍላጎትንና በኋላም የሚገኘውን እርካታ የሚከለክል ነው፡፡ ብሎም የሕይወትን መሰረታዊ ጣዕም በመንፈግ ችግሩን ያጎላዋል፡፡ የወር አበባቸውን ማየት ላቆሙት ሴቶች ደግሞ፣ ከዕድሜ ጋር ከሚደረግ ሩጫ ጋር መውደቃቸውን እንዲቀበሉ የሚያደርግ ስነ ልቦናዊ ችግር ከማስከተሉም ባለፈ የሰውት ቅርፅን ሊያበላሽ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

በርካታ ሴቶች በመረጡት ዝምታ፣ ማግኘት የሚገባቸውን እርዳታ ሳያገኙ ይቀራሉ፡፡ በእርግጥ እንደ ገበና የሚቆጠሩትን መሰል ጉዳት ለአደባባይ ማብቃት ባልተለመደባት ሀገራችን ፈተና መሆኑ አይቀርም፡፡

ዲያፓሪውኒያ ምንድነው?

 ዲስፓሪውኒያ በማንኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን፣ በተለየ ሁኔታ የወር አበባ ማየት ባቆሙ/ባረጡ ሴቶች ላይ የሚከሰት ችግር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በጥናት በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ሩብ ያህል ሴቶች፣ በወሲብ ወቅት ህመም የሚሰማቸው ሴቶች እንደሆኑ ተመልክቷል፡፡ ህመሙ አነስ ካለው ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ስቃይ የሚደርስ ሊሆን ይችላል፡፡ ስሜቶችም ማቃጠል፣ ውጋትና መጠዝጠዝ ናቸው፡፡
የህመሞቹ መከሰቻ የሀፍረት ሥጋ ውጪኛው ክፍል ላይ እና የዳሌ አጥንት ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙዎቹ ሴቶች ከመራቢያ አካል ነርቭ በሚያገናኘው ቱቦ ላይ ምቾት ማጣት ይከሰትባቸዋል፡፡ ከዚህም በወሲብ ወቅት መታመሙ በሂደት የሚመጣ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ስለ ወሲብ ማሰብ ጭምር የማይፈልጉና ራሳቸውን ከዚህ ተፈጥሯዊ ተግባር የሚያርቁ ናቸው፡፡

መነሻ ምክንያቶቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

ልንቀበላቸው ከምንችላቸው የችግሩ ምክንያቶች መካከል የመጀመሪያው የሆርሞን ለውጥ ሲሆን፣ እንዲሁም ከስሜት ጋር የተያያዙት ድብርት እና ስጋት ደግሞ ሌሎቹ ናቸው፡፡ በመሀከላቸው የዕድሜ ዘመን ለሚገኙ ሴቶች፣ የመራቢያ አካል መመንመን (Vaginal atrophy) በወሲብ ወቅት ለሚፈጠር ህመም ሌላውና ዋነኛው ምክንያት ተደርጎ በባለሙያዎች ይወሰዳል፡፡

ከስነ ልቦና እና ከስሜት ጋር የተያያዙት ታሪኮቻችንም ወደ ኋላ ለሚመጣው የግንኙነት ወቅት ህመም፣ መነሻ ስለመሆኑ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በመሰረታዊነት የተለዩትም አስገድዶ መደፈር፣ ጭንቀትና ድብርት፣ የጥፋተኝነት ስሜት ወሲብን በህመም የታጀበ የማድረግ አቅም አላቸው፡፡ እንዲሁም በማህፀን ውስጥ የሚከሰት ህመም ምልክትም ሊሆን ይችላል፡፡

ህክምናው ምንድን ነው?

የማህፀን ሐኪሞች በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ናቸው፡፡ ችግሩ በእርግጥም የአንድ ወቅት ብቻ እንዳልሆነና እርዳታ እንደሚያስፈልግሽ ስታምኚ ለሀፍረትና ለመሸማቀቅ ቦታ ሊኖርሽ አይገባም፡፡ ከሌሎቹ ጉዳዮችሽ በላይ ቅድሚያ የምትጪው ጤናሽ በመሆኑ፡፡ ስለዚህ ስለህመም ስሜቱ በቀጥታ ለሐኪም በግልፅ መንገር ይኖርብሻል፡፡ በተለይ እንዴት ጀመረሽ? የት እና መቼ ነው የህመም ስሜቱ የሚሰማሽ? ከስቃዩ ለመውጣት በራስሽ የምትወስጃቸው እርምጃዎች ምንድናቸው? የማህፀን ሕክምና ታሪክሽ እና ስትወልጂ ስለነበሩ ሁኔታዎችና ከፍቅር አጋርሽ ጋር ስላለሽ ግንኙነት ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎች ሊቀርቡልሽ ይችላሉ፡፡ አስፈላጊው ነገርም ራስን ለዕርዳታው ዝግጁ ማድረግ ይሆናል፡፡ አልማዝን ለመሰሉ በወሲብ መደሰት ለሚፈልጉ ሴቶች ግን የማይሳካ ተግባር ይሆናል፡፡ ለሁለቱ ተጣማሪዎች በዚህ ወቅት ሰውነቶቻቸውን በሚፈልጉት መንገድ ምላሽ መስጠት ሳይችል ሲቀር መመልከት ትልቁ የጭንቀታቸውና የፍራቻቸው ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ ከመልካሞቹ የትዳር አጋሮች በመሰል ወቅት ድጋፎቻቸው በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች ከባለሙያ የሚሰጠውን እርዳታ በጋራ ከመከታተል ጀምሮ በከባዱ ጊዜ ጭምር አጋርነታቸውን ያሳያሉ፡፡ ይሄ በኋላ ላይ ለሚፈለገው ውጤት መሰረታዊው ጉዳይ ነው፡፡ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉና ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ሴቶች የወሲብ ወቅት ህመምን እንደሚያዳብሩ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ብዙዎቹንም ለተፈጥሯዊው ተግባር ፍላጎት ወደማጣት ይመራቸዋል፡፡ የህክክና ባለሙያዎች ግን አሁንም የአካል ጉት ወይም ሰፊ ፆታዊ ጥቃት ብቻቸውን የችግሩ ምክንያት ሊሆኑ እንደማይችሉ ያስረዳሉ፡፡ በተደጋጋሚ በመራቢያ አካል ላይ ምርመራ በማድረግ ችግር እንደ ሌለባቸው የተነገራቸው ሰዎች ጭምር በህመሙ ሲሰቃዩ መመልከት የተለመደ በህመሙ ሲሰቃዩ መመልከት የተለመደ በመሆኑ፡፡ እርዳታዎቹ መድሃኒቶች፣ ቴራፒዎችንና ራስን መንከባከብን ሊያጠቃልሉ ይችላሉ፡፡

– ቅባቶች፡- ምንም አይነት ሆርሞን በውስጣቸው የሌለ ቅባቶችና ማለስለሻዎች፣ በግንኙነት ወቅት በሚፈጠር መተሻሸት ሳቢያ የሚከሰትን ህመም ይቀንሳሉ፡፡ ቅባቶቹ ከግንኙነት በፊት ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ለረዥም ጊዜ መፍትሄ ዘወትር የምንጠቀምባቸው ናቸው፡፡ ሰዎች የሚስማማቸውን መርጠው ለመጠቀም ረዥም ጊዜ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ ከአትክልቶች የሚዘጋጁት ዘይቶች ውድ የሚባሉት አማራጮች ናቸው፡፡

– የግንኙነት ልምዶችን መቀየር፡- ከመደበኞቹና ህመም ከሚያስከትሉት የግንኙነት መንገዶች ለየት ያሉ ተግባሮችን መመልከት ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ከጓደኛ ጋር መመካከር የተሻለውን ለመምረጥ ጠቃሚ ነው፡፡

– ንፅህናን በተለየ ሁኔታ መጠበቅ፡- የተለየ ሽታ ያላቸውን ሳሙናዎችንና ቅባቶችን በማስወገድ፣ የመራቢያ አካልን ንፅህና በውሃና በንፁህ ውሃ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ መጠበቅ በባለሙያዎች የሚቀርብ አማራጭ ነው፡፡ ከጥጥ የተሰሩ የውስጥ ልብሶችን መምረጥና ሰውነትን ምቾት ከሚነሱ ልብሶች ማራቅም ጠቃሚ ነው፡፡

– ሌሎች አማራጮች መመልከት፡- ወሲብ ጡንቻዎችን የማጠንከርና የደም ዝውውር ስርዓትን የማሳለጥ ሚና አለው፡፡ ታዲያ ግንኙነቱ የስቃይ ምክንያት ሲሆን ሌሎች አማራጮችን መመልከት ሳይኖርብን አይቀርም ይላሉ ባለሙያዎቹ፡፡

– ቀዶ ጥገና፡- በራሳችን መፍትሄ  ብለን የጀመርናቸው ነገሮች አልሳካ ካሉን ቀዶ ጥገና በአማራጭነት ቀርቧል፡፡ ህክምናው በመራቢያ አካል አካባቢ የተወሰኑ የሰውነት አካላትን በማስወገድ የሚከናወን ነው፡፡ ቀዶ ጥገናው ብዙ ጊዜ የስነ ልቦናውና የመድሃኒት ህክምናው ውጤታማ መሆን ሳይችል ሲቀር የሚገባበት ነው፡፡

– ካውንስሊንግ፡- ስሜትና ስነልቦና ላይ ትኩረት አድርጎ በባለሙያዎች የሚሰጥ ህክምና ነው፡፡ መሰረት ከሌለው ስጋት ጀምሮ ከጓደኛ ጋር ያለው መጥፎ ስሜት በወሲብ ወቅት ለሚፈጠረው ህመም ሌላው መነሻ እንደሀነ ይነገራል፡፡ ይሄ ደግሞ በቀጥታ ትዳርን ወይም የፍቅር ግንኙነትን ሊረብሽ ይችላል፤ ስለዚህ ከሰለጠኑ የምክር ባለሙያዎችና ቴራፒስቶች ጋር ስለጉዳዩ በግልፅ ማውራቱ ብዙ ይረዳል፡፡

Health: 11ዱ የጀርባ ህመም ዋና ዋና ምክንያቶችና 8ቱ ምርጥ የቤት ውስጥ ህክምናዎች

$
0
0

 

back pain

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ ነው:: ደግማችሁ ማተም ለምትፈልጉ የዘ-ሐበሻን ስም በምንጭነት መጥቀሳችሁን አትርሱ::

80 በመቶ የስርጭት አድማስ ያለው የጀርባ ህመም ከበሽታዎች ሁሉ ወደ ሐኪም የሚያመላልስ አስገራሚ ህመም ነው፡፡ አዎን ጥርስዎን ሊነክሱ፣ ፊትዎን ቅጭም ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴም ስራዎን በሰላም ለማከናወን ፈተና መሆኑ አይቀርም፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ህመም ምን አይነት ችግር እንዳስከተለው ላይረዱ ይችላሉ፡፡ የጀርባ ህመም መንስኤው የተለያየ ነው፡፡ ከጀርባ አካባቢ ካሉ የሰውነት ክፍሎች ሊነሳ አልያም ከሰውነት ውስጥ ካሉ አካላት ሊመነጭ ይችላል፡፡ ቀላል የጀርባ ውጥረት አልያም የውስጥ ሰውነት ክፍል ካንሰር ሊሆን ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች፡፡ የአጥንት ችግር፣ የነርቭ ህመም፣ የጡንቻ፣ የጅማት ከኩላሊትና ከማህፀን ግድግዳ፣ እንዲሁም ከሌላ ቦታ የተሰራጨ ካንሰር አሊያም ደግሞ የአጥንት ኢንፌክሽን፡፡

በሁሉም ሰው ላይ ማለት በሚቻል መልኩ በህይወት ዘመን ውስጥ የወገብ ህመም ያጋጥማል የቢሊዮኖች ህመም በመባልም ይታወቃል፡፡ በተለይ የአጥንት ክብደትና ጥንካሬ በዕድሜ ተፅዕኖ መዳከም ሲጀምር ወገብ ለአደጋ ይበልጥ ተጋላጭ እየሆነ ይመጣል፡፡ ለብዙዎች ከአደጋ በፍጥነት አገግሞ የጤነኛ ጀርባ ባለቤት መሆንም እንዲሁ ቀላል የሚባል ሂደት አይሆንም፡፡

እንዲሁም አንዳንድ ያልተለመዱ የጀርባ ችግሮች እንደ ካንሰር ካሉ ጠንከር ካሉ በሽታዎች መነሻነት ይመጣሉ፡፡ ለወራት የሚዘልቁ የጀርባ ህመሞችም የህክምና ባለሙያዎች የተለየ ድጋፍ የሚጠይቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

 

11 ዋና ዋና የጀርባ ህመም ምክንያቶች

  1. ከአቅም በላይ ወይም በተሳሳተ መንገድ ዕቃ ማንሳት
  2. ድንገተኛ አደጋ፤ መውደቅ፣ በስፖርት አማካኝነት የሚመጣ ችግር
  3. የአጥንት መሳሳት
  4. ከልክ ያለፈ ውፍረት በተለይ ደግሞ በመሀከለኛው የሰውነት ክፍል ላይ /ሆድ አካባቢ/ ከፍተኛ ውፍረት መኖር
  5. በየዕለቱ የሚገጥም ጭንቀትና ድብርት
  6. በተሳሳተ መንገድ መተኛት/በተለይ በሆድ በኩል መገኘት/
  7. በተሳሳተ መንገድ መቀመጥና ከተቀመጥንበት መነሳት
  8. ለረዥም ሰዓት መቀመጥ በተለይ ቁጥጥ ማለት እና መቀመጫን የሚቆረቁር ነገር ላይ መቆየት
  9. ከበድ ያለ የእጅ ቦርሳና የጀርባ ቦርሳን መሸከም
  10. ከወገብ ታጥፎ ለረዥም ጊዜ መቆየት
  11. በእርግዝና ወቅት ጡንቻን እና ጅማትን የማሳሰብ እንቅስቃሴ ማድረግ ናቸው፡፡

አይዘናጉ ጀርባዎ ላይ ያልተለመደ ህመም የተሰማዎ ከሆነ የጀመሩትን ስራ ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ወይም ሌሎች ተግባራትን የማቆም እርምጃ ወዲያው ነው መውለድ ያለብዎት፡፡

Back-Pain2በወገብ ላይ የሚገጥም ህመም ለ48 ወይም ለ72 ሰዓታት የሚዘልቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙዎቹ የጀርባ ችግሮች ደግሞ የተወሰኑ ሳምንታትን ይፈልጉ ይሆናል፡፡ የጀርባ ጤና ላይ መሻሻል ከታየ በኋላም ስቃዩ አልፎ አልፎም ቢሆን ሊቀጥል ይችላል፡፡

8 ለጀርባ ህመም የሚወሰዱ የቤት ውስጥ ህክምናዎች

የጀርባ ህመምን የሚያመጡ እና የሚያባብሱ እንቅስቃሴዎችን በማስወገድ እንዲሁም ከታች የተዘረዘሩትን የመፍትሄ አማራጮች በየዕለቱ አልያም ባስቀመጡት ፕሮግራም መሰረት የሚተገበሩ ከሆነ መዳን ከእርሶ ብዙ የራቀ አይሆንም፡፡

በተለይ ትንንሽ የወገብ ወለምታዎችና ህመሞች ላይ ጠንከር ያለ ክትትል በማድረግ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ መዳን ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከበድ ካሉት ብዙዎቹ የጀርባ ችግሮች ሙሉ ለሙሉ ለመፈወስ ወይም ለማገገም ከአራት እስከ ስድስት ሳምንት ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ 12 ሳምንት እንደሚወስዱ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

  1. በረዶ፡ በዋናነት ስቃይን ለመቀነስ የሚመከር ነው፡፡ በበረዶ የታጨቀ ከረጢት ወይም ቦርሳ እንዲሁም በጣም የቀዘቀዙ አትክልቶችን ካዘጋጀን በኋላ የታመሙ የሰውነት ክፍላችን /ጀርባችን/ ላይ ቢያንስ ለ15 ደቂቃ መያዝ፡፡ በሶስት እና አራት ሰዓታት ውስጥም ይህንን ተግባር መደጋገም ታዲያ በረዶውን በቆዳችን ላይ አለማሳረፋችንን እርግጠና መሆን አለብን፡፡
  2. ማረፍ ነገር ግን የተወሰነ መንቀሳቀስ፡ ረዥም የእረፍት ጊዜ ብናገኝ ከገጠመን የወገብ ችግር በፍጥነት ለማገገም ሰፊ ዕድል ይኖረናል፡፡ ነገር ግን ለአንድ እና ለሁለት ቀናት እረፍት ማድረግ የማገገሚያ ሂደቱን ሊያዘገየው ይችላል፡፡

ስለዚህ ጡንቻን ለማጠንከር በሚዳን ሁኔታ ከእረፍቱ ጎንለጎን የተወሰነ እንቅስቃሴ ማድረግ በእጅጉ ይረዳል፡፡

በተረፈ አደጋ ሊያስከትሉ ከሚችሉ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ፡፡ በተለይ ደግሞ ዕቃ ከማንሳት፣ ከማስቀመጥ በተደጋጋሚ ከመተጣጠፍ እና ከመጠምዘዝ በዚህ ጊዜ መራቅ ግድ ይሆናል፡፡

  1. ሙቀትን መተግበር፡ ህመሙ ከተከሰተ ከ48 ሰዓት በኋላ ወይም የህመም ስቃዩ ከራቀ በኋላ የታመመውን የሰውነት ክፍል /ጀርባ/ እና ጡንቻዎችን ለማፍታታትና የቀድሞ ጥንካሬአቸውን ለመመለስ ሙቅ ውሃን በሻወር መልክ፣ በከረጢትና ቦርሳ በማድረግ መታጠብና መያዝ ይመከራል፡፡

ታዲያ ከልክ በላይ በሞቀ ውሃ ቆዳን መጉዳት እንዳይመጣ መጠንቀቅ እንዳይረሳ፡፡

በእርግጥ ከሙቅ ውሃ ይልቅ ቀዝቃዛ ውሃ የማገገም ሂደቱን እንደሚያፋጥነው የታመነ ሲሆን ሁለቱንም በጋራ መጠቀሙ ደግሞ የተሻለ የሚባለው መንገድ ነው፡፡

  1. መዘረጋጋት

የታሰበበት ለመዘረጋጋት እንቅስቃሴ ወገብን በቤት ውስጥ ለማስታመም የሚመከረው አንዱ መፍትሄ ነው፡፡ በመዘረጋጋት ሂደት ግን መጣደፍና መንጠርን የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች የጀርባ ችግር ላለባቸው አካላት በፍፁም አይመከሩም፡፡ ከዚህ ባለፈ በቀን ውስጥ ለ10 እና 15 ደቂቃዎች በፍፁም ህመም የማያስከትል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፈውስን ሊያመጣ ይችላል፡፡

  1. ማሳጅ /ለተመረጠ የጀርባ ችግር/

በተለይ የወገብ ችግሩ የመጣው ጡንቻዎች ስራና ውጥረት ስለበዛባቸው ከሆነ ማሳጅ መፍታታትን በመፍጠር ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል፡፡

  1. ደረጃ ያለው መፍታታት፡ይሄ የመፍታታት ቴክኒክ በርካታ የሰውነታችንን ጡንቻዎች በማፍታት ነው የሚተገበረው፡፡
  2. ዮጋ፡ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ዮጋ የወገብ ህመምን የማዳን ከፍተኛ አቅም አለው፡፡ ሂደቱ በርካታ ወራትን ሊወስድ ቢችልም ችግሩን በዘላቂነት በማጥፋት ግን የተዋጣለት አማራጭ ነው፡፡
  3. መቆም፡መቀመጥና ማንሳት በብልሃት፡- ስንቆም ወገባችንን አጥፈን ሳይሆን ቀጥ ብለን ይሁን፡፡ ስንቆም በፍፁም ትከሻችንን አስቀድመን ሊሆን አይገባም፡፡ ስንቀመጥም የታችኛው የጀርባችን ክፍል በቅድሚያ ወንበር እንዲነካ በማድረግ ይሁን፡፡ የምንቀመጥበት ወንበርም ቢሆን የታችኛውን የወገብ ክፍል የሚደግፍ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡

ዕቃን በማንሳት ሂደትም ዋናውን የሸክም ስራ እግሮቻችን እንዲፈፅሙት እናድርግ ወገብ በፍፁም መታጠፍ የለበትም፡፡

ወደ ሐኪም መሄድ የሚጠይቅ የጀርባ ህመም ደግሞ ይህን ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ህመሙ ወደ እግርዎ ጭምር ከተሰራጨ፣ የጡንቻ መዛል፣ መደንዘዝና እንደመርፌ ጠቅጠቅ የሚያደርግ ህመም አብሮት ካለ፡፡ የጀርባ ህመሙ ከተለወጠ የሰገራ አወጣጥ ለምሳሌ ድርቀት ጋር አልያ የተለየ የሽንት ምልክቶች ካሉ፡፡ እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የክብደት መቀነስና የሰውነት ፍላጎት መቀነስ፣ የክብደት መቀነስና የሰውነት ሙቀት መጨመር አብሮት ካለ፡፡ የአጥንት መሳሳት የረጅም ጊዜ ችግር ካለብዎ፡፡ ህመሙ እየከፋ ከሄደና ከላይ ባሉት ቀላል እርምጃዎች ሊሻልዎ ካልቻለ ወደ ሐኪም በመሄድ ቀጣይ ምርመራ ያድርጉ፡፡

መልካም ጤንነት፡፡

 

 

ከቡና በላይ ሊያነቃቁ የሚችሉ 6 አስደናቂ ነገሮች

$
0
0

chocolate

ከቅድስት አባተ | ዘ-ሐበሻ

በጠዋት መነሳት ለእርስዎ ምን ስሜት ይፈጥርቦት ይሆን? ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የሰው ዘር በጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ የመደበትና የመጫጫን ስሜቶችን ያስተናግዳል፡፡ አንዳንዶቹም ከሀይለኛ የእንቅልፍ ስሜት ለመውጣት ሲቸግራቸው የስራ መስካቸውን እስከ መቀየር ይገደዳሉ፡፡ በንቁነት ጊዜያዊ ፈውስን ይሰጣሉ ተብለው የሚታመንባቸው እፆችንና መጠጦችን መጠቀምም የብዙዎች የዓለማችን ህዝቦች ልማድ እየሆነ መጥቷል፡፡ የቡናና ሻይ መወዳጀትም ለንቃት እንደመፍትሄ ሲቆጠር የነበረ፣ ዛሬም የሚኖር ልማድ ሆኗል፡፡ ምስጋና ለጥናትና ምርምር ይግባውና የሚከተሉት ነገሮች ከቡና ባልተናነሰ መልኩ ለንቃት መፍትሄ እንደሚሆኑ ተረጋግጧል፡፡

1. ፖም

ይህ መልከመልካም የአትክልት አይነት ከምግብነት በተሻለ መልኩ ለብዙ ህመምና ችግሮች በመፍትሄነት ተጠቃሽ ነው፡፡ ፖም በውስጡ ፍሩክቶስ የተሰኘ ንጥረ ነገር ይዟል፡፡ ይህ ንጥረ ነገርም በተፈጥሮ የስኳርነት ባህሪ ያለው በመሆኑ

አዕምሯችን በተፈጥሮው የነቃ እንዲሆን ይረዳል፡፡ ፍሩክቶስ በሰውነታችን ውስጥ ያለምንም መረበሽ በዝግታ በመጓዝ በደረሰባቸው የትኞቹም የአካል ክፍላችን ውስጥ የሚገኙ የደምስሮቻችንና ጡንቻዎቻችንን የማነቃቃት ባህሪ አለው፡፡

2. ጨው ማሽተት

ለወትሮው ከምግባችን ውስጥ የማናጣው የምግብ ጨው ጠቀሜታውን በማስፋት ሊያነቃቃን መጥቶል ሲል ምንኛ ይገርመን ይሆን? መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አብዛኛዎቹ የአሜሪካ ፖሊሶች ከእንቅልፍ በሰዓቱ ለመንቃት ሲሉ ጨውን ተመራጭ ያደርጋሉ፡፡ እንደዘገባው ከሆነ ጨውን በአፍንጫ ማሽተት በድብርት ውስጥ ያለ አዕምሮን በፍጥነት በማንቃት ከእንቅልፍ ስካር ውስጥ መንጥቆ ያወጣናል፡፡ ሆኖም ምንም እንኳን ጨውን በቀላሉ ማግኘትና መጠቀም የሚቻል ቢሆንም በምናሸትበት ወቅት ለሳይነስ በሽታ እና ለአዕምሮ ጉዳት ሊዳርግ የሚችል አቅም ያለው በመሆኑ በተደጋጋሚ ለንቁነት ተብሎ መጠቀም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱን ያመዘነ ያደርገዋል፡፡

3. ሙዝ

ይህ የፍራፍሬ አይነት በዘርፈ ብዙ ጥቅምን የሚሰጥ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በመጠጥ ሀንጎቨር የተደበተ ሰውነትን ለማነቃቃት ከምግብ በፊት ሙዝ መብላት ፍቱን መፍትሄ ነው፡፡ የምግብ ፍላጎትን ማጣትና ማቅለሽለሽ ስሜት የሚሰማው በሽተኛው ሙዝን ቢመገብ ራሱን

ለማረጋጋት የሚጠቅመው ይሆናል፡፡ በተለይም ይህ የፍራፍሬ ዝርያ በብዛት በወሰዱት ቁጥር የማነቃቃት ሀይሉ ይበልጥ የሚጨምር ነው፡፡

4. ውሃ

ውሃ የምግብ ክፍል ውስጥ ይመደባል ብለው የሚከራከሩ ምሁራን ዛሬም ድረስ ምክንያታቸውን በጥበብ ሲያስቀምጡ ይስተዋላሉ፡፡ የስፖርት ሳይንስ ምሁራንም በቀን ውስጥ ብዙ ውሃ መውሰድ ለሰውነታችን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ አበክረው የሚገልፁት እውነት ነው፡፡

ወደ ዛሬው ርዕሰ ጉዳይ ልመልሳችሁና፣ ውሃ ለማነቃቃትም እንደመፍትሄ የሚወሰድ ሆኗል፡፡ መቼም  ፅሑፌን ያስተዋለ የዱር ተማሪ ጥናት ለማጥናት ሲል እግሩን በቀዝቃዛ ውሃ የሚዘፍቅበት ሁኔታ አዕምሮው ላይ ደቅን ሊልበት ይችላል፡፡ ምሁራን የሚሉት ግን ከእንቅልፍ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ ጠጥቶ መተኛተ በጧት ያለችግር ለመንቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ነው፡፡ በተጨማሪም ማታ ላይ በሙቅ ውሃ ሰውነታቸውን ተለቅልቀው የመተኛት ልምድ ያላቸው ሰዎች ወደ ስራቸው በጠዋት ለመውጣት ንቁ የመሆን እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

5. ምግብ

አባቶች የጠዋት ምግብ የሰውነት ምሰሶ ነው ይላሉ፡፡ ሳይንሱም ለአበው አባባል ማረጋገጫውን ከሰጠ አያሌ ዘመናት አስቆጥሯል፡፡ በዘርፉ የተፃፉ ጽሑፎች እንደሚያሳዩት በጠዋት ጥሩ ምግብ የመመገብ ልምድ ያለው ሰው ከሌሎች ሰዎች  በበለጠ ንቁ ይሆናል፡፡ ምሁራኑ ለዚህ ማስረጃነት የሚያቀርቡት የሰው ልጅ በሚርበው ጊዜ መላ ሰውነቱ የመዳከም ስሜት የሚጫጫነው ሲሆን ጥሩ ምግብ ሲያገኝ ግን መላ አካሉ ይበረታታል›› በማለት ነው፡፡

ምሳና ራት ላይ የምንመገባቸው ምግቦች ጣፋጭ መአዛ ያላቸው፣ ከሩቁ የሚጣሩ ከሆነም በአፍንጫችን የሚገባው የምግብ ሽታ ሰውነታችንን የማነቃቃት ሃይል ይኖረዋል፡፡ አትክልትና ፍራፍሬዎችም ለንቁነት ከፍተኛ ቦታ ያላቸው ሲሆን ዓሣና እንቁላልም ተከታዩን ዳራ የሚይዙ የምግብ አይነቶች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ቀድሞውንስ ጆንያም በእህል ይቆማል አይደል የሚባለው፡፡

6. ቸኮሌት

እርግጥ ቸኮሌት ከፍተኛ የሆነ ስብ ስላለው አብዝቶ  መጠቀሙ አይመከርም፡፡ ነገር ግን ለንቃት ይረዳ ዘንድ ቡና በሌለበት አጋጣሚ፣ ቸኮሌትን እንደ አማራጭ ማነቃቂያ መጠቀሙ ምሁራንንም የሚያስማማ ሀቅ ሆኗል፡፡ እንደ ባለሞያዎች ገለፃ፣ ቸኮሌት ስንወሰድ በውስጣችን ከፍተኛ የሆነ የመነቃቃት እና የመመሰጥ ዝንባሌ የሚከሰት ሲሆን ይህም በቀጣይ ለመስራት ባቀድነው ተግባር ላይ በንቃት እንድንከውን ይረዳናል፡፡ ይሁን እንጂ በቸኮሌት የመነቃቃት ሂደቱ ለተወሰነ ጊዜ ስለሚሆን ሌላ የቸኮሌትን ንጥረ ነገር ያካተቱ መጠጦች መጠቀሙ ግድ ሊል ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ጥናቶች እንደሚጠቁሙት፣ ቸኮሌትን መጠቀም የስርዓተ ልመትን ሂደት ከማሳለጥ ባለፈ ለዕድገት እና ለተስተካከለ የአዕምሮ ተግባርም ወሳኝ ነው፡፡ 

Zehabesha.com

Health: ከሰርግዎ በፊትና በኋላ ሊያጠኗቸው የሚገቡ 7 ወሳኝ ጉዳዮች

$
0
0

 

መንገድ ለማቋረጥ ዜብራው ላይ ስደርስ ረዥም ሊሞዚን ሌሎች መኪናዎችን አስከትሎ ያልፋል፡፡ ወደ ኋላ ከተሰደሩት መኪናዎች የሚሰማውን የሰርግ ዘፈን ብሎም በሚኒባስ ሆነው የሚጨፍሩ አጃቢዎችን እየተመለከትኩ እያለ፣ ከጎኔ ያለው ወጣት ‹‹ነገ ሊፋቱ ዛሬ ይህን ሁሉ ወጭ ማውጣት…›› ሲል ዞር ብዬ አየሁት፡፡ 

ከቀናት በኋላ ከአራት ኪሎ ወደ ሜክሲኮ የሚሄድ ታክሲ ውስጥ ተሳፍሬ በሸራተን በኩል ባለው ቁልቁለት መውረድ ስንጀምር፣ ከፊታችን የሰርገኞች መኪኖች በሁለቱም አስፋልት ቆመው ቪዲዮ ይቀርፃሉ፡፡ ፎቶ ይነሳሉ፡፡ ታክሲው ውስጥ ያለን ሰዎች ፀጥ ብለን እስኪጨርሱ ጠበቅን፡፡ ሲጨርሱ አንደኛውን አስፋልት ስለለቀቁልን ሰርገኞቹን አለፍናቸው፡፡ በማለፍ ላይ እያለን ከኋላዬ የተቀመጠ አንድ ግለሰብ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን የወጣቱን አስተያየት የሚመስል አስተያየት አጉረመረመ፡፡ ማግባት እኮ ጥቅም አለው፡፡ ስለጥቅሙስ የተወሰነ ነገር ለምን አልፅፍም ብዙ አሰብኩ፡፡ ስለማግባት የተወሰነ ከፃፍኩ በኋላ ደግሞ መጤን አለባቸው ያልኳቸውን ጉዳዮች አካትቼ የዛሬ ጽሑፌን እንዲህ አሰናዳሁት፡፡

wed

የማግባት ጥቅሞች

በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ መውለድ፣ ማግባትና መሞት የማይቀሩ ወሳኝ ኩነቶች /Standard key events/ ተብለው ቢቆጠሩም ማግባት ግን የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች ማግባትን ከአለማግባት የሚመርጡት በተለያዩ ምክንያቶች ቢሆንም የስነ ልቦና፣ የአንትሮፖሎጂ፣ ሶሲዎሎጂና የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች የማግባት ጥቅሞች ናቸው ያሏቸውን በጥናቶቻቸው አሳይተዋል፡፡

የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች እንደሚያብራሩት፣ ማግባት በኑሮ ሂደት ውስጥ የሚከሰቱብንን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ለማምለጥ የሚጠቅም ኢንሹራንስ ነው፡፡ ባለትዳሮች አጋሮቻቸው ከሚገልፁላቸው ፍቅር፣ ከሚሰጧቸው እውቅና፣ ለንብረቶቻቸውና ለደህንነታቸው ጥበቃ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚያገኙ ሲሆን፣ በዋናነት እነዚህ ተግባራት ውጤታማነታቸውን ያሳድገዋል፡፡ በትዳር አጋሮች መካከል የሚኖረው የኃላፊነት (የሥራ) ክፍፍል ሌላው ኢኮኖሚስቶች የትዳር ጥቅም ብለው የጠቀሱት ጉዳይ ነው፡፡ የባለትዳሮችንና ያላገቡ ሰዎችን የገቢ መጠን ያነፃፀሩ ኢኮኖሚኒስቶች ደግሞ፣  ያገቡቱ ከፍተኛ ገቢ እንዳላቸው ስላገኙ ይህንን ተንተርሰው የገቢ መጨመር ሌላው የማግባት ጥቅም ነው ይላሉ፡፡

የስነ ልቦና፣ አንትሮፖሎጂና ሶሲዎሎጂ ባለሙያዎች ደግሞ ጋብቻ ለማህበረሰብ ወሳኝ ተቋም ነው የሚል የፀና እምነት ያላቸው ሲሆን ማግባት ያለውን ጥቅም በጥናቶቻቸው አስደግፈው ይተነትናሉ፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ (በተለይ ደግሞ ማህበረሰባዊ ባህልን በሚከተሉ ማህበረሰቦች) ያገቡ ሰዎች፣ ካላገቡቱ ይልቅ የኃላፊነት ስሜት አላቸው የሚል እምነት አለ ይላሉ ባለሙያዎቹ፡፡ ይህ ደግሞ ያገቡ ሰዎች ለተለያዩ ማህበራዊ ኃላፊነቶች ተመራጭ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ባዮች ናቸው፡፡ ስለሆነም በማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ የሚገኘው ደረጃ መጨመር የማግባት ማህበራዊ ጥቅም ነው፡፡

በስነ ልቦና ረገድ ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ ያገቡ ሰዎች ካላገቡና ብቻቸውን ከሚኖሩ ሰዎች የተሻለ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጤና አላቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ያገቡ ሰዎች ዝቅተኛ የሱሰኝነት ሁናቴና የድብት መጠን ያላቸው ሲሆን ብቻቸውን ከሚኖሩት ይልቅ ረዥም ዕድሜን ይኖራሉ፡፡ ለባለትዳሮች የአጋሮቻቸው መኖር ከውጥረት ማምለጫ (በተለይም ከስራ ይዘውት የመጡትን ውጥረት) ይሆናቸዋል ይላሉ ተመራማሪዎች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አጋር አለኝ (ብቻዬን አይደለሁም) የሚለው ስሜት፣ ባለትዳሮችን ጠንካራ ማንነት እንዲኖራቸውና ዝቅተኛ የብቸኝነት ስሜት ባለቤት እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡

ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ማግባት ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊና አካላዊ ሁኔታችንን የተሻለ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ይህም ስለሆነ በአሁኑ ጊዜ በየቦታው እየተካሄዱ ያሉ ሰርጎች የሚበረታቱና እሰየው የሚያሰኙ ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ማግባትንና መሰረግን፣ የተመለከቱና ትኩረትን የሚሹ ጉዳዮች አሉና መመልከቱ ጠቃሚ ነው፡፡

በጋብቻ ዙሪያ መጤን ያለባቸው ሁኔታዎች 

1. ያለ ዕድሜ ጋብቻ

በከተሞች የሚደረጉ ጋብቻዎችን በአንክሮ የተመለከተ ሰው፣ በሀገራችን የቤተሰብ ህግ የተቀመጠውን 18 ዓመት የማግቢያ ዕድሜ ያለፉ እንደሆኑ ይታዘብ ይሆናል፡፡ ከዚህም በመነሳት ያለ ዕድሜ ጋብቻ የቀነሰ እንደሆነ ሊያስብ ይችላል፡፡ ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጰያ ፊታችንን ስናዞር ግን አሁንም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ትልቅ ችግር እንደሆነ ማየት ይችላል፡፡ የተለያዩ ጥናቶችም ይህንን ያረጋግጣሉ፡፡ ለአብነት ያህል በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሆኑት ቀረብህ አስረሴና ሙሉነሽ አበበ፣ በምስራቅ ጎጃምና ደቡብ ወሎ የሚካሄዱ ጋብቻዎችን አጥንተው፣ ውጤታቸውንም እ.ኤ.አ በ2014 በHumanities and social sciense ጆርናል አሳትመውታል፡፡ በጥናቱ ውጤት መሰረትም በምስራቅ ጎጃም 87 ከመቶ የሚሆኑቱ ተጋቢዎች፣ በደቡብ ወሎ ደግሞ 80 ከመቶ የሚሆኑቱ ተጋቢዎች ከ18 ዓመት በታች ዕድሜያቸው አግብተዋል፡፡ ሌላው በዚሁ ጥናት የተገኘው ውጤት ያለ ዕድሜያቸው ካገቡት ሰዎች ውስጥ 83 ከመቶ የሚሆኑቱ ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 17 ከመቶ የሚሆኑቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው፡፡ ይህ ውጤት የሚያሳየን አሁንም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ችግራችን መሆኑንና ወንዶችም የችግሩ ገፈት ቀማሾች እንደሆኑ ነው፡፡

2. የተጋቢዎች የደስታ መጠን መቀነስ

ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ማግባት የተለያዩ ጥቅሞች አሉት፡፡ ይህ ሁኔታም ያገቡ ሰዎችን ካላገቡቱ በተሻለ መልኩ ደስተኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሁኔታዎች ተቀይረዋል ይላሉ ስቱትዘርና ፍሬይ የተባሉ ባለሙያዎች በ2006 ባሳተሙት ጽሑፍ፡፡ እንደ ሙያተኞቹ ማህበራሪያ በጭራሽ ያላገቡቱ የደስታ መጠናቸው ከቀድሞው ዘመን በተሻለ እየጨመረ፣ በተቃራኒው ያላገቡቱ የደስታ መጠናቸው ከቀድሞው እየቀነሰ መጥቷል፡፡ እነዚህ ተመራማሪዎች በጀርመን በሚገኙ 15,268 ሰዎች ላይ ከ1984 እስከ 2000 ባደረጉት የ17 ዓመት ጥናት፣ ተጋቢዎች በተጋቡ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ከፍተኛ የደስተኝነት መጠን እንዳላቸው ያም በሂደት እየቀነሰ እንደሚመጣ አይተዋል፡፡

3. የፍቺ መጠን መጨመር

ከተጋቢዎች የደስታ መጠን መቀነስ ጋር ተያይዞ ሌላው ጉዳይ የፍቺ መጠን መጨመር ነው፡፡ ይህ ክስተት ዓለም አቀፋዊ ሲሆን በምዕራቡ ዓለም መጠኑ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በአሜሪካና በካናዳ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሁለት ትዳሮች አንዱ በፍቺ ይቋጫሉ፡፡ ግሎባላይዜሽን እና የግለሰባዊነት ባህል መስፋፋት ይህንን የፍቺ መጠን በምስራቁ ዓለምም እንዲጨምር አድርጎታል፡፡ በእኛም ሀገር ይህ ክስተት መጨመሩን የሚያሳዩ ጠቋሚዎች አሉ፡፡ ለአብነት በማዕከላዊ ስታስታስቲክስ ኤጀንሲ የቀረቡ መረጃዎችን በመተንተን ላቅርብ፡፡

በኤጀንሲው ሀገር አቀፍ ጥናት እንደሚታየው፣ ከ15 እስከ 49 ዓመት ከሚገኙ ሴቶች ውስጥ 61.4 ከመቶ የሆኑቱ ያገቡ ሲሆን 7.7 ከመቶ የሚሆኑቱ ደግሞ የተፋቱ ናቸው፡፡ ኤጀንሲው እ.ኤ.አ በ2011 ወንዶችንም ሴቶችንም ያካተተ ተመሳሳይ ጥናት አካሂዶ የነበረ ሲሆን፣ በንፅፅር ያህል ሴቶቹን የተመለከተውን መረጃ እንመልከት፡፡ በ2011 ወንዶችንም ሴቶችንም ያካተተ ተመሳሳይ ጥናት አካሂዶ የነበረ ሲሆን፣ ለንፅፅር ያህል ሴቶቹን የተመለከተውን መረጃ እንመልከት፡፡ በ2011 በተደረገው ጥናት 58.1 ከመቶ የሚሆኑቱ ያገቡ ሲሆን 5.3 ከመቶ የተፋቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ጥናቶች የሚያሳዩን በ3 ዓመት ውስጥ ያገቡ ሴቶች መጠን ከ58.1 ወደ 61.4 ያደገ ሲሆን፣ የተፋቺዎቹ መጠን በወገኑ ከ5.3 ወደ 7.7 ከመቶ ጨምሯል ማለት ነው፡፡

4. የጋብቻ ወጭ መጨመር

ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ምርምሮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን የሚሰራው ፖፑሌሽን ካውንስል የተባለው ድርጅት እ.ኤ.አ በ2011 ባሳተመው አጭር የምርምር መገለጫ፣ በታዳጊ ሀገራት ለጋብቻ የሚወጣው ወጭ በጣም ጨምሯል፡፡ ይህም ተጋቢዎቹ በዓመት ከሚያገኙት ገቢ በላይ ሆኗል፡፡ ይህንን የጋብቻ ወጭ መጨመር ኢትዮጵያዊ ጥናቶችም አረጋግጠዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 አየለ ተሰማ የተባለ ተመራማሪ ለሶስተኛ ዲግሪ በሰራው ጥናት፣ በወላይታ ዞን ገጠራማ ቦታዎች ስሚከናወኑ የሰርግና የለቅሶ ወጪዎች የሰጠው ትንተና ለዚህ እባባሌ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡

አየለ እንዳረጋገጠው ለሰርግና ለለቅሶ የሚወጣው ወጭ ከፍተኛ ሲሆን የሰርግ ወጭው ለለቅሶ ከሚወጣው ወጭ ይበልጣል፡፡ የሰርግ ወጪውን ሲተነትን የሙሽራውና የሙሽሪት ቤተሰቦች ያጠራቀሙትን የምግብ ክምችት/ገንዘብ ያወጣሉ፡፡ የቤት እንስሳትን ይሸጣሉ ወይንም ያርዳሉ፡፡ ገንዘብ ያበድራሉ፡፡ የእርሻ መሬታቸውን ያከራያሉ፡፡ብሎም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ታዳሚዎች ይጠራሉ፡፡ በምላሹ ታዳሚዎች ስጦታዎችን የሚሰጡ ሲሆን እነዚህ ስጦታዎች ግን ለሰርግ የሚወጣውን ወጭ 20 ከመቶ የሚሆነውን ብቻ ይሸፍናሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አየለ እንደሚያብራራው፣ ከጋብቻው በኋላ የተጋቢ ቤተሰቦች የተለያዩ ነገሮችን (ለምሳሌ ቤት፣ የቤት ዕቃ፣ በሬና ትንሽ መሬት) መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በአጠቃላይም ይላል የአየለ ጽሑፍ ለጋብቻ የሚመጣው ወጭ ከቤተሰቦቹ ዓመታዊ ገቢ ይበልጣል፡፡ ማህበራዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የቤተሰቡን ክብር መጠበቅ/ማጎልበት፣ ከህብረተሰቡ የሚመጡ ጫናዎች፣ ከሌሎች ጋር የሚደረጉ የድግስ ውድድሮችና ከፍተኛ ስጦታ አገኛለሁ ብሎ መጠበቅ፣ ለሰርጎች ትልቅ ወጭ እንዲወጣ የሚያደርጉ ምክንያቶች ሆነው በአየለ ጥናት ተረጋግጠዋል፡፡

ሠርግ በዋናነት የሚከናወነው፣ የተጋቢዎችን ትዳር መመስረት ማህበራዊና ህጋዊ ዕውቅና ያገኝ ዘንድ ነው፡፡ ይህን ለመከወን የሚወጣው ወጭ ሲበዛ፣ በተጋቢዎችም ሆነ በቤተሰቦቻቸው ላይ የራሱ የሆኑ ተፅዕኖዎችን እንደሚፈጥር ይታወቃል፡፡ በማህበረሰብ ደረጃ ደግሞ የሰርግ ወጪዎች መጨመር ሁለት አብይት ተፅዕኖዎች አሉት፡፡ የፓፑሌሽን ካውንስል የ2011 ጥናት እንደሚያሳየው፣ የሙሽሪት ቤተሰቦች የሚያወጡት ወጭ ከፍተኛ በሆነበት ማህበረሰብ (ለምሳሌ ለሙሽራው ቤተሰቦች ስጦታ የሚሰጥበት ባህል) የሰርግ ወጪዎች መጨመር ያላገቡ ሴቶች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል፡፡ በተቃራኒው የሙሽራው ቤተሰቦች የሚያወጡት ወጭ ከፍተኛ የሆነበት ማህበረሰብ ወጣቶችን ከጋብቻ በፊት ወሲባዊ ግንኙነቶችን እንዲፈጥሩና ልጆች እንዲወልዱ አድርጓቸዋል፡፡ በአጠቃላይም የጋብቻ ወጪዎች መጨመር፣ ወጣቶችን ከጋብቻ በፊት ወሲባዊ ግንኙነቶችን እንዲፈጥሩና ያላገቡ ሴቶች ቁጥር እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

ለዚህ ወጭ መጨመር የተለያዩ ምክንያቶች ቢቀመጡም፣ በቁሳዊ ነገሮች ዋጋ የመስጠት ሁናቴ ዋነኛ መንስኤ ነው ባዮች ናቸው ስቱትዘር እና ፍሬይ የተባሉ ባለሙያዎች፡፡ ለዚህም አብነት ሲያቀርቡ በተለያዩ መጽሔቶችና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ውድ የሆኑ የሰርግ ድግሶች ሽፋን ያገኛሉ፡፡ ይህም ሰዎችን ወደ ከፍተኛ ወጭ የሚያስወጡ ድግሶች እንዲያመሩ ያደርጋ፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች ከፍተኛ ወጭ አውጥተው ትዳር የመሰረቱ ሙሽሮች፣ ቆይታቸው አጭር ብሎም ትንሽ አዎንታዊና ብዙ አሉታዊ ግንኙነቶች እንደሚታይባቸው የተለያዩ ቀደምት ጥናቶችን በመጥቀስ ይከራከራሉ፡፡

 

5. ትዳርን/ፍቅርን ዘላቂ ለማድረግ ዝግጁነት አለመኖር

ፍቅርን ብሎም ትዳርን ዘላቂ ለማድረግ፣ ሶስቱም የፍቅር መዋቅሮች (መቀራረብ፣ ስሜታዊ መፈላለግና ዝግጁነት/መስዋዕትነት) መኖር አለባቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ብዙ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች፣ የስሜት ፍቅር መገለጫቸው እየሆነ መጥቷል፡፡ ለዚህ አባባሌ የጅማ ዩኒቨርሲቲው ፈንቴ አምባለው በ2009 የሰራውን ጥናት እንደ ማስረጃ ላቅርብ፡፡ ፈንቴ ጥናቱን የሰራው 828 በሆኑ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ሲሀን፣ በጥናቱ መሰረትም ተማሪዎቹ ከፍተኛ የሆነ የስሜታዊ ፍቅር መጠን ታይቶባቸዋል፡፡ ከእነዚህ ተማሪዎች ውስጥ ደግሞ የፍቅር ፊልሞችን በተደጋጋሚ የሚያዩ፣ ከፍቅር ጋር የተያያዙ ጽሑፎችን የሚያነቡ ወይም ከፍቅር ጋር የተያያዙ የሬዲዮ ፕሮግራሞችን የሚያደምጡ ተማሪዎች ከሌሎች የበለጠ የስሜታዊ ፍቅር መጠን አሳይተዋል፡፡ በመሰረቱ የስሜት ፍቅር መቀራረብና መፈላለግ ያለበት ፍቅር ሲሆን፣ ፍቅርን ለማስቀጠል የሚያስችለውን ዝግጁነት ያልያዘ የፍቅር አይነት ነው፡፡ ይህንን ፍቅር መሰረት አድርገው ወደ ሰርግ የሚዘልቁ ሙሽሮች መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን መገመቱ ደግሞ ቀላል ነው፡፡

6. ግጭቶችን የመፍታት ችሎታ ያላዳበሩ ሙሽሮች

በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ውስጥ ሁሌም ግጭቶች ይኖራሉ፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች በግንኙነቶች መሀል ግጭቶች ከሌሉ መጀመሪያውኑ ግንኙነቱ የለም ማለት ነው ብለው ይከራከራሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ውስጥ ግጭቶች ይኖራሉ፡፡ በዚህ ጊዜም ግጭቶችን የመፍታት ችሎታ ወሳኝ ነው፡፡

መጋባት አንዱ የሁለትዮሽ ግንኙነት አይነት ነውና ይህ ግጭቶችን የምታት ችሎታ ማዳበርን ይጠይቃ፡፡ ሆኖም ግን ይህንን አይነት ችሎታን አዳብረው ወደ ትዳር የሚዘልቁ ኢትዮጵያውያን ሙሽሮች ስንት ይሆኑ ብለን ስንጠይቅጥቂት ይሆናል መልሱ፡፡ ማስረጃ ለማቅረብ ያህል፣ አስካለማርያምና ምን ዋጋው የተባሉ ተመራማሪዎች በአምስት ወረዳዎች የሚታዩ ፍቺዎችን መርምረው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ከ2001 እስከ 2003 ለተፈፀሙ ፍቺዎች ሶት አበይት ምክንያቶችን ሲኖሩ ግጭቶችን የመፍታት ችሎታ አለመኖር አንዱ ነው፡፡

7. የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት

የትዳር አጋር ከመምረጥ ጀምሮ በሌሎች ጉዳዮችም ጭምር፣ የተጋቢ ቤተሰቦች ጣልቃ ገብነት እንደሚታይ የፋፍቻምፕስ እና ኩስምቢንግ የ2002 ጥናት አሳይቷል፡፡ የጣልቃ ገብነቱን ችግር ሲያብራሩ ወላጆች በአጋር መረጣ ላይ ትከረታቸውን ሀብት ላይ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ልጆች ደግሞ የሙያ ወይም የግለሰባዊ ፍላጎቶች መመሳሰል ላይ ትኩረታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ከአጋር መረጣ በኋላም ቢሆን፣ የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት እንዲቀጥል እናም በተጋቢዎቹ ላይ ችግር እንደሚፈጥር ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እላይ የጠቀስኩት የእነ አስካለማርያም ጥናት፣ የፍቺ መንስኤ ብሎ ነቅሶ ካወጣቸው አበይት ምክንያቶች ሁለተኛው የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት ነው (የመነጋገር ችግር ሶስተኛው መንስኤ ነው)፡፡

Health: ስኳርና መዘዙ –አዲስ የስኳር አወሳሰድ መጠን ይፋ ተደረገ

$
0
0

ስኳር የሚጨምርባቸውን ምግቦች እና መጠጦች ለአፍታ እናስባቸው፡፡ ኮስተር ያሉትን ስናዘጋጅ ብቻ ካልሆነ ዕለት ተለት በምንመገባቸውና በምንጠጣቸው ውስጥ ስኳር መጨመርን ለምደነዋል፡፡

diabetes-testing

በባህላዊ መንገድ በሚዘጋጁት ወጦቻችን፣ ጠላዎቻችንና ዳቧችን ሳይቀር እንደ ቀድሞው እናቶቻችን ባልትና የሚጠይቁ አይደሉም፡፡ ይልቁንም ጠቀም ያለ ስኳር ሊሰፈርላቸው ይገባል፡፡ የምግቦቻችንና መጠጦቻችን ቃና ላንቃን በሚያወረዙና ከምላስ በማይወርዱ ጣፋጭነታቸው ብቻ ነው ጥሩነታቸው እየተለካ ያለው፡፡ ከእናት ጡት በቀር ህፃናቶቻችንስ ስኳር ያልተጨመረባቸው ምግብና መጠጦች መች ይቀርብላቸዋል?

 

ስኳርና መዘዙ የዓለም የጤና ተሟጋቾች ትኩረት ከሆነ ሰንብቷል፡፡ ሰሞኑን እንኳን አንድ የእንግሊዝ የተመራማሪዎች ቡድን በእንግሊዝ በአሁኑ ወቅት ጥቅም ላይ የሚውለው የስኳር መጠን ቢያንስ በግማሽ እንዲቀነስ ሐሳብ አቅርቧል፡፡ ተመራማሪዎቹ ስኳር በምግብ ውስጥ የሚመርበት መጠን መወሰን ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አለመሆኑን ነው ያሳሰቡት፡፡

 

የምግብ ባለሙያዎች በቀን ከምንወስዳቸው የካሎሪ መጠን ስኳር ከ5 በመቶ ወይም ከ6 ማንኪያ ከበለጠ አደጋ አለው በሚል ነው ይሄን ዘመቻ አጠናክረው ያስቀጠሉት፡፡ በአሁኑ ወቅት ብዙ ሰዎች ከተጠቀሰው መጠን በእጥፍ የሚልቅ የስኳር ፍጆታ ነው ያላቸው፡፡ የዴቪድ ካሜሮን መንግሥትም ከባለሙያዎቹ የቀረበውን ሐሳብ እንደሚቀበልና በዚህ ዓመት በሚቀርበው የብሔራዊ የህፃናት ውፍረት መካከል እቅድ ውስጥ እንደሚያካትተው አስታውቋል፡፡

 

የአመጋገብ ኮሚቴ ተመራማሪዎቹ ያቀረቡት የቀን የስኳር ፍጆታ (6 ማንኪያ) በግማሽ መቀነስ፣ ከልክ ያለፈ ውፍረትንና የጥርስ ጤንነትን ለመጠበቅ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ነው ያሳሰቡት፡፡ የኮሚቴው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር አያ ማክዶናልድ ‹‹ግኝቱ ከፍተኛ ስኳር ለጤና ጠንቅ መሆኑንና ልማዳችንን ልናስወግድ እንደሚገባ የሚጠቁም ነው ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም ‹‹የምንወስደውን ስኳር መቀነስ የፋይበር ክምችታችንን ከፍ ማድረግና ረዥም ዕድሜ የመኖርንና በጤና የመቆየት ምስጢር ነው›› ብለዋል፡፡

 

የብሪቲሽ የምግብ ተቋም ባለሙያዋ ፕሮፌሰር ጁዲት ቡትሪስ በበኩላቸው፣ እቅዱ ‹‹ከስኳር ነፃ›› የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡ በተፈጥሯአዊዎቹ ምግቦች ማለትም ፍራፍሬዎችና ወተት ውስጥ ያለውን የስኳር ክምችት ሳያጠቃልል ተጨማሪዎቹን በመገደብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው እቅዱ፡፡ በምግብ ውስጥ ዋነኛዎቹ የስኳር መገኛዎች ጣፋጭ መጠጦች፣ ምግቦችና የፍራፍሬ ጭማቂዎች ናቸው ተብለዋል፡፡ አንዳንድ ጋዝ ያለባቸው መጠጦች ብቻቸውን እስከ 9 ማንኪያ ስኳር መገኛ እንደሆኑ ባለሙያዋ ይናገራሉ፡፡

 

የብሪቲሽ የጥርስ ህክምና ማህበር (BDA) መንግሥት የቀረበውን ምክር ከፊት በመሆን እንዲያስፈፅም ጥሪ አቅርቧል፡፡ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሚክ አርምስትሮንግ እንደሚሉት፣ የምግብ ኢንዱስትሪዎች የምርቶቻቸውን ገበያ ለማስፋፋት ከፍተኛ ስኳር ጥቅም ላይ እንደሚያውሉና በአንፃሩ ግን የደንበኞቻቸውን ጤና አደጋ ላይ እየጣሉ እንደሆነ መረዳት አለባቸው ብለዋል፡፡ አንድ ሰው በቀን በሚወስደው ካሎሪ የስኳር መጠኑ ከ5 በመቶ እንዳይበልጥ የቀረበው እቅድ ለምግብ ኢንዱስትሪዎች፣ ለመንግስትና ለማህበረሰቡ ፈተና መሆኑ እንደማይቀር ነው ባለሙያዎቹ ስጋታቸውን መቀየር ይፈልጋሉ? ተፅዕኖውንስ መቋቋም ይችሉ ይሆን? የሚለው ትልቁ የክርክር ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡

 

በሌላ በኩል የምግብ ኢንዱስትሪዎች፣ ስኳርን የመቀነስ ኃላፊነታቸውን መተግበር መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡ የዓም የጤና ድርጅት መመሪያ ደግሞ አዋቂዎችና ህፃናት በቀን ወደ ሰውነታቸው ከሚያስገቡት ኃይል መካከል ስኳር ከ10 በመቶ እንዲያንስ ይመከራል፡፡ በተጨማሪነት ደግሞ የቅነሳ ዘመቻውን በቀን ወደ 5 በመቶ ወይም 6 ማንኪያ ብቻ ወደ መውሰድ ማምራት ጀግንነት ይሆናል ይላል፡፡

 

ስኳር ላይ ታክስ ይጨመር

 

ከምግብ ባለሙያዎች በተጨማሪ የህክምና ዶክተሮችን ጨምሮ ሐሳቡን የሚያራምዱ አካላት፣ በዚህ ሳምንት ስኳር ላይ ታክስ መጨመርን በሚመለከት ድጋፋቸውን አሳይተዋል፡፡

 

የብሪቲሽ የህክምና ማህበር፣ በስኳር መጠጦች ላይ ቢያንስ 20 በመቶ ቀረጥ ቢጣል፣ ውፍረትን ለመዋጋት የተያዘውን የረዥም ጊዜ ግብ ለማሳካት አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ ማለት እንደሚሆን አስታውቋል፡፡ የዴቪድ ካሜሮን መንግስት ግን አሁንም የስኳር ታክስን በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨመር እቅድ እንደሌለው አስታውቋል፡፡

 

የመንግሥት ተወካዩ ሲሞንሰቴቨንስ እንደሚሉትም፣ ቀዳሚ እርምጃ ሊሆን የሚችለው የስኳር መጠጦችን ዋጋ ማናርና የኢንዱስትሪዎቹን ሰራተኞች ደመወዝ ከፍ ማስደረግ ነው፡፡ ይሄም ቤተሰቦችን፣ ህፃናትንና ዝቅተኛ ገንዘብ ተከፋይ ሰራተኞችን የሚደግፍ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከምግብና ከመጠጦች ውስጥ ስኳርን የማስወገድ ወይም የመቀነስ እርምጃው የማይሰራ ከሆነ ተቆጣጣሪ አካል ጣልቃ ለመግባት ይገደዳል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

 

የዓለም የጤና ድርጅት መመሪያ፣ በፍራፍሬና አትክልቶች ውስጥ እንዲሁም በተፈጥሮ ወተቶች ውስጥ የሚገኘው ስኳር በጤና ላይ ስለሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ያለው ነገር የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያየ አጋጣሚ የምንወስዳቸው ስኳሮች በፋብሪካ ውስጥ በተቀነባበሩ ምግቦች ውስጥ በድብቅ ተከማችተው የሚገኙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ አንድ ማባያ ወይም ካችአፕ በትንሹ 4 ግራም ወይም አንድ ማንኪያ ስኳር ይገኝበታል፡፡

 

ከፍተኛ የስኳር ተጠቃሚነት ከልክ ካለፈ ውፍረት እና እሱን ተከትለው ለሚመጡት ተላላፊ ላልሆኑት እንደ ደምግፊት፣ ስኳርና የልብ በሽታ ተጋላጭነት ምክንያት ነው፡፡ በቀን ውስጥ የሚያስፈልገንን ኃይል ለማግኘት የስኳር ሚና ከ5 በመቶ በታች እንዲሆን ወይም ከ3 የሻይ ማንኪያ እንዳይበልጥ ባለሙያዎች አስገንዝበዋል፡፡

Health: በፍቅርና በትዳር ስም የሚፈፀሙ አደገኛ ተግባራት፤ ከፍቅር ወይስ ከእብደት?

$
0
0

Gold Wedding Rings --- Image by © Royalty-Free/Corbis

ከብዙ ዓመታት በፊት የመጀመሪያ ዲግሪዬን ስማር ለካውንስሊንግ ልምምድ ወጥቼ ጊዜ ያጋጠመኝን ጉዳይ በአጭሩ ላካፍላችሁ፡፡

የተመደብኩበት ትምህርት ቤት ካውንስለር ስላልነበረው፣ ዳይሬክተሯን ነበር ያነጋገርኳት፡፡ ‹‹በትምህርቷ ጎበዝ የነበረች ተማሪ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት እጅጉን የሰነፈች ሲሆን አምና ደግሞ ወደቀች፣ ፍቅር ይዞኛል ትላለች›. ብላ ሁኔታውን ካወራችኝ በኋላ ልጅቱን አገናኘችኝ፡፡ ልጅቱ የ17 ዓት ወጣት ነበረች፡፡ ከብዙ መለማመድ በኋላ ሁኔታውን በዝርዝር አጫወተችኝ፡፡ ከክፍለ ሀገር መጥታ አዲስ አበባ ከአክስቷ ጋር የምትማር ልጅ ነች፡፡ በአጋጣሚ የአክስቷን ጓደኛ ባል ወደደችው፡፡ ሰውዬው ትልቅ ፎቅ፣ ውድ መኪና ያለው ሀብታምና የአራት ልጆች አባት ነው፡፡ የሰውዬው ምስል በተደጋጋሚ ይመጣባታል፡፡ መኪና ባየች ቁጥር የሰውዬው ሐሳ ይመጣባታል፡፡ ወንድ አስተማሪ ሲያስተምር የሚታያት ሰውዬው ነው፡፡ ትምህርት ቤትም ሆነ ቤቷ ስትሆን የሰውዬው ምስል ይታያታል፡፡ በሁኔታውም ትጨነቃለች፡፡ ሲጨንቃት ደግሞ የህዝብ ስልክ ባለበት ቦታ ትሄድና ትደውልለታለች፡፡ ሰውዬው በደወለች ቁጥር ይስድባታል፡፡ እሷ ግን ስለደወለች ብቻ ትንሽ ቀለል ይላታል፡፡ ሰውዬው እያስቸገረችው እንደሆነ ለአክስቷ በመናገሩ አክስትየዋ ከቤት አስጣቻት፡፡

ወደ ክፍለ ሀገር ለመሄድ ባለመፈለጓ፣ ከቤተሰቦቿ በሚላክላት 120.00 ብር የአዲስ አበባን ኑሮ ተያያዘችው፡፡ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ግማሹን በስልክ ታጠፋዋለች፡፡ ቀሪው ገንዘብ ስለሚያንሳት፣ ልብሶቿንና ጫማዎቿን ሸጣ የቀራት የተቀዳደዱ ልብሶችና አንድ ነጠላ ጫማ ብቻ ነው፡፡ እሷ ግን ይህ ግድ አይሰጣትም፡፡ ምን አይነት ፍቅር ነው የያዛት ብዬ አሰብኩ፡፡ብዙ አነበብኩ፡፡ በስተመጨረሻ ደረስኩበት፡፡ ይኸው ዛሬ ደግሞ፣ የልጅቱን አደገኛ ተግባራትን ለተመተንተን ፈቀድኩና እንዲህ ጻፍኩት፡፡

‹‹ፍቅር ፍቅር አሉት ስሙን አሳንሰው፣ ከድንጋይ ይበልጣል ለተሸከመው ሰው››

የሚል የዘፈን ግጥም እየሰማን ለኖርን ሰዎች፣ ፍቅር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገንዘብ ቀላል አይደለም፡፡ የግጥሙን ሁለተኛ ስንኝ ስንቃኝ ደግሞ ከድንጋይ የሚበልጥ ነገር እንደሆነ በቀላሉ እንገነዘባለን፡፡ ይህን ስንኝ በጥልቀት ስንቃኘው ምን አይነት ድንጋይ? ትንሽ ወይንስ ትልቅ ድንጋይ? ድንጋዩ ትንሽና በኪሳችን ይዘነው የምንዞር ከሆነ እኮ ፍቅር ቀላል ነው፡፡ በተቃራኒው ድንጋዩ በጣም ትልቅ ከሆነ ደግሞ ፍቅር ልንሸከመው የማንችል ነገር ነው ማለት ነው፡፡

በመሰረቱ ፍቅርን ከባድም ሆነ ቀላል የሚያደርጉ ነገራት አሉ፡፡ ከእነዘህም ውስጥ አንዱ በፍቅር ውስጥ ያሉ ሶስት ምሰሶዎች መዋቅሮች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መዋቅሮች ውስጥ አንደኛው፣ ቅርብ ግንኙነት (intimacy) የሚባለው ሲሆን ይህም በዋናነት የስሜታዊነት ባህሪያትን የሚይዝ ሆኖ መቀራረብ፣ የጋለ ስሜት፣ የመገናኘት እና የመቀራረብ ስሜቶችን የሚያጠቃልል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ጥልቅ ስሜት (Passion) ሲሆን ይህም የተነሳሽነት ሁኔታዎችን የሚይዝ ሆኖ የመሳብ፣ የወሲብ እና ወዘተ ስሜቶችን የሚያካትት ነው፡፡ ሶስተኛው የመስዋዕትነት (Commitment) ሲሆን በአብዛኛው፣ ከአስተሳሰብ ጋር የሚያያዝና ሰዎችን ለመውደድ የምናደርገውን የአጭር ጊዜ ውሳኔ (Short-term decision) እና ፍቅራችንን ለማስቀጠል የምናደርገውን የረዥም ጊዜ ውሳኔ (long-term decision) የሚይዝ ነው፡፡

በመሆኑም ሰዎች በቀላሉ መቀራረብ ከቻሉ፣ የሁለቱም ስሜት ከተቀራረበና አንዱ ለአንዱ መስዋዕት መሆን ከቻሉ፣ ፍቅራቸው ቀላልና ጥሩ የህይወት ቅመም ይሆናል፡፡ በተቃራኒው መቀራረብ የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ከሆኑ፣ ስሜታዊነት በአንደኛው ግለሰብ በቻ ካለ፣ አንዱ ብቻውን መስዋዕት የሚከፍል ከሆነ፣ በሁለቱም ግለሰቦች ዘንድ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ካልሆኑ ወዘተ… ፍቅር የተባለው ነገር የተጓደለ ብሎም ለመሸከም ከሚከብድ ድንጋይ ጋር የሚነፃፀርና ከባድ ይሆናል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አንዳንዶቹ ፍቅር ውስጥ ያሉ እየመሰላቸው ነገር ግን የፍቅር ሱስ ብዬ የምጠራው አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነው፣ ራሳቸውም ሆነ አፈቀርኩት/ኳት ከሚሉት ግለሰብ ላይ ጉት ሲያደርሱ እናስታውሳለን፡፡ በቀላል አገላለፅ በፍቅር ሱስ ተጠምደው በፍቅር ስም አደገኛ ተግባራትን ይፈጽማሉ፡፡

1. የፍቅር ሱስ (Obsessive love)

የፍቅር ሱስን ለማብራራት ከመሞከሬ በፊት አንድ የአዕምሮ ህመምን ላብራራ፡፡ ይህም በእንግሊዝኛው ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲዝኦርደር (Obsessive-compulsive disorder) በአማርኛ ደግሞ ‹‹በሐሳብ የመወጠርና የግዳጅ ተግባር ህመም›› ብዬ የተረጎምኩት፡፡ የስነ ልቦና እና የሳይካትሪስት ባለሙያዎች በዋናነት የሚቆሙበት የDSM ማኑዋል እንደሚያብራራው፣ ይህ ህመም ከጭንቀት ችግሮች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን፣ ህመሙ ላለበት ሰውን ለመለየት የሚያስችሉ 5 መሰረታዊ መስፈርቶች አሉት፡፡

– በሌሎች ሐሳቦች መሀል ጣልቃ የሚገባ ወይም ከፍተኛ ጭንቀት የሚፈጥር ሐሳብ ወይም ምስል በተደጋጋሚ መከሰት (obsession)

– ተደጋጋሚ የሀሳብ ምልልሱን ለማጥፋት ወይም ለመቀነስ በተደጋጋሚ የሚከወን ተግባር መኖር፤

– የጭንቀት መጠኑ ደግሞ የዕለት ተዕለት ተግባራችንን እስከማዛባት ሲደርስ፤

– ተደጋጋሚ ሐሳቡ እና ተግባሩ በአንድ ቀን ውስጥ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት የሚታይ ከሆነ፤

– ተደጋጋሚ ሐሳቡ ወይም ድርጊቱ መከሰት ከጀመረ ግለሰቡ እያሰበ ያለው ሐሳብ ወይም እየከወነ ያለው ተግባር፣ በቂ ምክንያት የሌለው ወይም የተሳሳተ ነው ብሎ የሚያምን ከሆነ (ይህን መስፈርት ለማያሟሉ ግለሰቦች ደግሞ ደካማ እይታ ያላቸው መሆናቸው ይፈተሽና እንደ መስፈርት ይወሰዳል)

በአጭሩ በዚህ ችግር የተያዙ ሰዎች፣ የሆነ ሐሳብ ወይም ምስል በየሐሳቦቻቸው መሀል እየመጣ ጭንቀት ይፈጥርባቸዋል፡፡ ከጭንቀት ለመገላገል ደግሞ የሆነን ተግባር በተደጋጋሚ ይከውናል፡፡ በምሳሌ ለማስረዳት ያህል እንደ ካውንስሊንግ የምሰጠው ግለሰብ በተደጋጋሚ ቤቴን አልቆለፍኩትም የሚል ሐሳብ ይመጣበታል፡፡ ጭንቅ ሲለውም የቤቱን ቁልፍ በተደጋጋሚ በመሄድ ያረጋግጣል፡፡

እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ዝም ብለው የሚከሰቱ ሁኔታዎች ሳይሆኑ በተለያዩ አነሳሽ ነገሮች (triggers) የሚከሰቱ ናቸው፡፡ አነሳሽ የሚባሉት በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ሐሳቦችን የሚፈጥሩ ክስተቶች ወይም ፍንጮቹ ናቸው፡፡ ለምሳሌ እላይ የጠቀስኩት ግለሰብ፣ ቤቴን አልቆለፍኩም የሚል ሐሳብ የሚያስታውሰው የቤቱን ቁልፍ ማየት እና ስለ ጓደኛው ወሬ መነሳት ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት አንድ ጓደኛው ቤቱን ሳይቆልፍ አድሮ ሌቦች ገብተው እንደ ዘረፉት ካወራው ወዲህ፣ ቁልፍ ባየ ቁጥርና ሰዎች ስለጓደኛው የሆነ ወሬ ባወሩ ቁጥር ወይም ስለጓደኛው ባሰበ ቁጥር ቤቴን አልቆለፍኩም የሚለው ሐሳብ ይመጣበታል፡፡ ሌላ ስራ እየሰራም ሆነ ሌላ ሐሳብ እያሰበ፣ ይህ ሐሳብ ከተከሰተበት ወዲያውኑ ወደ በሩ በማምራት ቁልፉን ያረጋግጣል፡፡

በአጠቃላይም በዚህ ህመም የተያዙ ግለሰቦች በተለያዩ ሀገራት አነሳሽነት ወደ ህመሙ የገቡ ናቸው፡፡ አነሳሽ የሚባሉት ነገሮች አንዱ ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ አንድ ግለሰብ የተፈቀረው ግለሰብ ሁኔታ ወይም ምስል በሌሎች ሐሳቦች መሀል እየመጣ ድቅን ይልበታል፡፡ ይህ ሁኔታም ጭንቀትን ይፈጥርበታል፡፡ ጭንቀቱ ደግሞ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ማስታጎል ይጀምራል፡፡ ይህንን ጭንቀት ለማስወገድ ወይም ለመቀነስ የተለያዩ ተግባራትን በተደጋጋሚ ይከውናል፡፡ በምሳሌ ለማስረዳት፣ በመግቢያዬ የጠቀስኳት ወጣት የወደደችው ሰውዬ ምስል በተደጋጋሚ ይከሰትበታል፡፡ ጭንቀትመወ ጥር ያደርጋታል፤ ይህ ጭንቀቷም ትምህርቷን እንዳትማር ያደርጋታል፡፡ ከዚህ ጭንቀት ለመውጣትም በተደጋጋሚ ስልክ ትደውላለች፡፡

ይህ ማለት ይህቺ ወጣት፣ በሐሳብ የመመሰጥና የአስገዳጅ ተግባር ህመም ይዟታል ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይም ይህቺው ወጣትና በዙሪያዋ ያሉ ሰዎች፣ ልጅቱ ከሰውዬው ጋር ፍቅር እንደያዛት ያምናሉ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ የፍቅር ሱስ (obsessive love) የሚባለው፡፡ በእንደዚህ አይነት ሱስ ያሉ ግለሰቦች ያፈቀሩት ሰው ምስል ወይም ሁኔታ በተደጋጋሚ በሐሳቦቻቸው መሀል ድቅን ይልባቸዋል፡፡ በዚህ ሐሳብም ይመሰጣሉ፤ ጭንቀት ይፈጥርባቸዋል፤ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውም ይስተጓጎላል፡፡ እናም ጭንቀቱን ለማስወገድ ተደጋጋሚ ተግባራት ይፈጽማሉ ወይም ሐሳቡ የሆነ ተግባር እንዲፈጽሙ ያስገድዳቸዋል፡፡

ችግሩ የሚመጣው የሚከውኑት ተግባር ምንነት ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሚያፈቅሩት ሰው ሃሳብ/ምስል በተደጋጋሚ ሲመጣባቸው፣ ተፈቃሪው/ተፈቃሪዋ ያለበት/ያለችበት አካባቢ በመሄድ የመመልከት ተግባር ያከናውናሉ፡፡ በመግቢያዬ የጠቀስኳት ወጣት ደግሞ፣ የሰውዬው ሐሳብ ሲመጣባት ስልክ የመደወል ተግባርን በተደጋጋሚ ታከናውናለች፡፡ እዚህ ላይ ነው እንግዲህ በፍቅር ስም የሚከወኑ ህገወጥ ተግባራት የሚመጡት፡፡ ያፈቀሯት ሴት ምስል በተደጋጋሚ ሲከሰትብዎት፣ የሚፈጠረውን ጭንቀት ለማስወገድ ተፈቃሪዋን ማስገደድ፣ መማታት፣ አሲድ መድፋትና መግደልን የመሳሰሉ ተግባራት የሚፈጸመው፡፡ ሴቶችም ማስፈራራት፣ በተለያዩ ነገራት የመጠምዘዝ ተግባር መከወን፣ ማስመታት፣ ዐዋቂ ቤት ሄዶ የመስተፋቅር መድሃኒት በመፈለግ ማጥቃት፣ መግደል፣ ማስገደልን የመሳሰሉ ተግባራት የሚፈጽሙት፡፡

2. ተግባራቱ ፍቅርን ይገልፃሉ ወይ?

ፍቅር ምሉዕ የሚባለው ወይም እውነተኛ ፍቅር የሚባለው፣ ሶስቱንም የፍቅር ምሰሶዎች/መዋቅሮች አጣምሮ ሲይዝ ነው፡፡ በዚህ መነፅር የመወጣጠር ፍቅርን ስንቃኘው፣ የተወሰኑት ስሜታዊነትንና መስዋዕትነት የሚይዙ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ስሜታዊነትን ብቻ የሚይዙ ናቸው፡፡ ጠቅለል አድርገን ሁሉም የመወጣጠር ስሜታዊነት የሚታይባቸውና ምንም አይት የመቀራረብ መዋቅር የሌላቸው ናቸው፡፡

በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ የመወጣጠረ ፍቅር ውስጥ ያሉ ሰዎች የተሟላ ፍቅር ውስጥ አይደሉም የሚል ድምዳሜ መድረስ ይቻላል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ በመወጣጠር ፍቅር ውስጥ የሚካሄደው ተግባር መቀራረብን በስሜታዊነት ለማምጣት የሚደረግ ስራ ነው፡፡ በመሰረቱ መቀራረብ ስሜታዊነትን ይፈጥራ እንጂ ስሜታዊነት መቀራረብን መፍጠር እንደማይችል የስነ ልቦና ባለሙያዎች በጥናቶቻቸው አረጋግጠዋል፡፡ እኛም በገሃዱ ዓለም እንመለከተዋለን፡፡ አንድን ሰው በማጨናነቅ እንዲቀርበን አድርገን እኛን የመቅረብ ስሜት እንዲሰማው፣ እኛን የመውደድ ስሜትና ራሱን ለእኛ መስዋዕት እንዲያደርግ ማድረግ አይቻለንም፡፡

በሶስተኛ ደረጃ ማየት ያለብን ሁኔታ፣ ተደጋጋሚ ሐሳብ (ምስል ሲከሰትብን፣ ጭንቀትን ይፈጥራል፣ ጭንቀቱን ለማስወገድ የተለያዩ ተግባራት ይከውናሉ፡፡ ይህ ክስተት ደግሞ ቀደም ብለን የጠቀስናቸው ተግባራት የሚሰሩት ጭንቀትን ለመቀነስ/ለማስወገድ እንጂ ለፍቅር የሚደረጉ ተግባራት አይደሉም፡፡

በመሆኑም ከእነዚህ ሁኔታዎች በመነሳት፣ የመወጣጠር ፍቅር በያዛቸው የተለያዩ ተግባራትን የሚከወኑ ግለሰቦች የአዕምሮ ጤና ችግር እንጂ እውነተኛ ፍቅር የሚገልፁ አይደሉም፡፡

3. መለያየት

በፍቅር ስም የሚፈፀም አንደኛ ተግባር ደግሞ በፍቅር ኖው የተለያዩ ሰዎች የሚፈጽሟቸው ተግባራት ናቸው፡፡

ጥንዶች በፍቅር ሲኖሩ ተቀራርበዋል፡፡ በስሜት ተፈላልገዋል፣ አንዱ ለአንዱ መስዋዕት ሆነዋል፡፡ እነዚህ ጥንዶች በተለያዩ ምክንያቶች ተለያዩ፡፡ በዚህ ጊዜም መቀራረባቸው፣ ስሜታዊነታቸውና መስዋዕትነታቸው የመክፈል ሁኔታቸው ይቀንሳል/ይጠፋል፡፡ ታዲያማ እዚህ ላይ ችግሮች የሚፈጠሩት፣ አንዳንዶች የተለያቸውን ሰው ወደ ማጥቃት ሁኔታ ወይም ስሜት ይጓዛሉ፡፡ የቀድሞ ፍቅረኛውን ሆቴል ወስዶ በጩቤ ወጋግቶ የገደለ ወጣት ታሪክ ሰምተናል፡፡ ለአነሳሁት ሐሳብም ከበቂ በላይ ምሳሌ ይሆናል፡፡

የዚህ አይነት ሁኔታዎችን ጠለቅ ብለን ብንመለከት ደግሞ የአስተሳሰብ ክፍተትን እንመለከታለን፡፡ ሁለት ግለሰቦች አንድን ሁኔታ በተለያየ መንገድ ይገነዘቡታል፡፡ በምድብ ከፍለን ስንመለከት ደግሞ አንዳንዶቹ ሁኔታውን በአሉታዊነቱ ሲያስቡት ሌሎቹ ደግሞ ሁኔታውን በአሉታዊነት ያስቡታል፡፡

ጥንዶች በፍቅር ለመዝለቅ፣ የመቀራረብ የመፈላለግና የመስዋዕትነት ሁኔታው አብሮ መዝለቅ አለበት፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ መዝለቅ ካልቻለ በመጀመሪያ የተዛባውን ምሰሶ ለማስተካከል መሞከር ወሳኝ ነው፡፡ ሙከራው ካልተሳካ ደግሞ በመነጋገርና በመስማማት መለያየት ይቻላል፡፡ በአዎንታዊ አስተሳሰብ የሚያስቡ ሰዎች ጎዶሎ ፍቅር ይዞ ከመቀጠል፣ ተለያይቶ ሙሉ ፍቅርን ማምጣት እንደሚቻል ሲያስቡ፣ አሉታዊ አስተሳሰብ ያላቸው ደግሞ ሲጀመር የተወላገደ ጎደሎ ፍቅሩን ለማስተካከል አይሞክሩም፡፡ ሲቀጥሉም መለያየትን ልክ እንደ አብሮ መኖር ሁሉ አንድ አማራጭ አድርገው አያስቡም፡፡ በአንድ አብነት ለማስረዳት ልሞክር፡፡

ሁለት ግለሰቦች በፍቅር አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች፣ በሁለቱ መካከል የነበረው ፍቅር እየቀዘቀዘ መጣ፡፡ እንዲያውም አንዴ ወንዱ ለጥቂት ሴቷ በቢላዋ ልትወጋው ስትንደረደር በሰራተኛዋ ዋይታ ለጥቂት ተረፈ፡፡ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ተደጋጋሚ ጥረቶች አደረጉ፡፡ በስተመጨረሻም በመተማመን ለመለያየት ወሰኑ፡፡ ለእኔ በገረመኝ ሁኔታ ሴቷ ከእንደዚህ አይነት ፍቅር መለያየት ጥሩ ነው የሚል አስተሳሰብ ብትይዝ፣ ወንድየው በተቀራኒው ከእሷ መለየት መሞት ማለት ነው የሚል አስተሳሰብ በመያዝ ራሱን ለማጥፋት እስከማሰብ ደረሰ፡፡

ከመለያየት ጋር የተያዘ ሌላው ተግባር ደግሞ፣ እኔ የፈለኩት ካልሆነ የሚል ሁኔታና የፈለጉት ሳይሆን ሲቀር ወደ ጎጂ ተግባራት የማምራት ሁኔታ ነው፡፡ በፍቅር ውስጥ አንዱ ምሰሶ መስዋዕትነት ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በተቻለ መጠን ያፈቀርነውን ግለሰብ ፍላጎት ለማርካት መጣር ነው፡፡ ይህንን የማናደርግ ከሆነ ደግሞ ያፈቀርነው ራሳችንን እንጂ ሌላ ሰው ለማለት ይከብዳል፡፡ ምሳሌ ልስጥ፣ ሁለት ፍቅረኞች ተለያዩ፡፡ ከቆይታ በኋላ ወንዱ ሌላ ፍቅረኛ ያዘ፡፡ ከተለያዩ በግምት ከዓመት በኋላ ከአንድ ወንድ ጋር ስትሄድ አያት፡፡ በዚህ ጊዜ ወንዱ አፍቃሪ፣ ጓደኞቹን በመሰብሰብ ሌላ ወንድ ጋር ላይሽ አልፈልግም በሚል ፈሊጥ የቀድሞ ፍቅረኛውንና አብሯት የሚሄደውን ልጅ መቀጥቀጥ ጀመሩ፡፡ ተደባዳቢው አፍቃሪ፣ ሌላ ፍቅረኛ መያዙና የቀድሞ ፍቅረኛው ጋ እየሄደ ያለው ልጅ ምን እንደሆነ አለማረጋገጡን ልብ ይሏል፡፡

በመለያየት ዙሪያ አንድ ሌላ ጉዳይ ልጨምር፡፡ የዚህ ጉዳይ መነሻ ችግር ጥንዶች በፍቅር አብረው በነበሩበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የራሳቸውን ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ በመገደብ የፍቅረኞቻቸውን ፍላጎት ብቻ ለማርካት ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ በፍቅረኞቸው ላይ ጥገኛ ያደርጋሉ፡፡ እንዲዘሀ አይነት ሰዎች ደግሞ መለያየት ሲመጣ ራሳቸውን ችለው ለመቆም ሲቸገሩ እናያለን፡፡

ይህን ሁኔታ በበኩሉ ፍቅረኞቸው ላይም ሆነ ራሳቸው ላይ አደገኛ ነገራትን እንዲፈጽሙ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ በመሰረቱ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እንደሚያብራሩት፣ የበሰሉ ፍቅረኞች (Mature lovers) ብዙ ጊዜያቸውን ከፍቅረኞቻቸው ጋር የሚያሳልፉ ሲሆን እንደ ግለሰብ ደግሞ የራሳቸው ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡

ይህ ደግሞ ለራሳቸው አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን ለመከወን የሚያስችላቸው ከመሆኑም በላይ ራስን ችሎ የማስተዳደር ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ በተቃራኒው በፍቅር ስም ራሳቸውን ለፍቅረኞቸው ሙሉ ለሙሉ አሳልፈው የሚሰጡ ፍቅረኞች ይህ ስሜት የላቸውም፤ ስለሆነም መለያየት ሲመጣ ለችግር ይጋለጣሉ፡፡ በፍቅረኛዋ ጠያቂነት ከቤተሰቦቿና ከጓደኞቿ ራሷን አግልላ የኖረች ሴት፣ ባሏ ሌላ ሴት አፍቅሮ ከቤት ሲያስወጣት ወደ ሆቴል በማምራት፣ ሴተኛ አዳሪ የሆነች ሴት ታሪክ ጋዜጣ ላይ አንብቤያለሁ፤ ላነሳሁት ሐሳብም ምርጥ ምሳሌ ነው፡፡

4. ፍቺ

ቀደም ብዬ በመለያየት ዙሪያ ያነሳኋቸው ጉዳዮ በትዳር/በጋብቻ ተሳስረው የነበሩና የተለያዩ/የተፋቱ ጥንዶች ጉዳዮች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ፍቺ ከፍቅረኞች መለያየት የሚለዩት ሁለት አበይት ሁኔታዎች ስላሉት፣ በትኩረት ለማየት ያስችለን ዘንድ ራሱን እንዲችል አድርጌ እቃኘዋለሁ፡፡

አንደኛው ሁኔታ ሰዎች/ጥንዶች በሚጋቡበት ሰዓት የሁለት ቤተሰቦች ጥምረት ተፈጥሯል፡፡ ሕግና ደንብ ሲጥሱ የሚጠብቃቸው ቅጣት ራሳቸውን ዝግጁ ስለሚያደርግ፣ በውስጣቸው ጥላቻን ሲያሳድሩ አይስተዋሉም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስነ ምግባራቸውን ለማበረታታት ወላጆች የተለያዩ ስጦታዎችን ያበረክቱላቸዋል፡፡ ሚዛናዊ አስተዳደግን በሚጠቀም ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ልጅ በአብዛኛው፡፡

– ደስተኛ እና ስኬታማ ይሆናሉ፡፡

– ከፍተኛ የሆነ የውሳኔ ብቃት ሲታይባቸው፤ በውሳኔ ጊዜም የተለያዩ አማራጮችን መመልከትና ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችንም ቀድመው ለመገመት ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡

– በሕይወታቸው ላይ ኃላፊነትን የሚወስዱ ግለሰቦች ይሆናሉ፡፡

– ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ይታይባቸዋል፡፡

– ራሳቸውን መግጽ ይችላሉ፡፡

– የሰውን ሐሳብ የመቀበል ችግር አይኖርባቸውም፡፡

– በአጠቃላይ ለህይወት በጎ የሆነ እይታ ያዳብራሉ፡፡

– በቀላሉ ራሳቸውን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር ማለማመድ ይችላሉ፡፡

5. ነፃ አስተዳደግ

ይህን የአስተዳደግ ዘዴ የሚጠቀሙ ቤተሰቦች፣ ምንም አይነት ህግ እና ደንብ ለቤታቸው አያወጡም፡፡ ለልጆቻቸው ያስፈልጋሉ ያሉትን ቁሳቁስ በራሳቸው ተነሳሽትም ሆነ በልጆቹ ጠያቂነት ከማሟላት ወደኋላ አይሉም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ‹‹ልጆች ልጆ›› ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ ጥፋታቸውም ከልጅነታቸው ጋር የተያያዘ እንጂ በወደፊት ህይወታቸው ላይ ሊያመጣ የሚችለውን የባህሪ ብልሹነት አይቀበሉትም፡፡  ሁሉንም ነገር ሲያድጉ ይተውታል ብለውም ያስባሉ፡፡ ከልጆቸው ጋር ሊወያዩ የሚችሉት ምናልባት እቤት ውስጥ ከባድ የሚባል ችግር ሲፈጠር ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ቢሆን የተፈጠረውን ችግር ወይም ልጁ የሚያንፀባርቀውን መልካም ያልሆነ ባህሪ ለማስተካከል ብዙም ጥረት አያደርጉም፡፡ ከልጆቻቸው ጋር የሚኖራቸውም ግንኙነት የወላጅ እና የልጅ ሳይሆን የጓደኛ አይነት ነው፡፡

ነፃ አስተዳደግን በሚጠቀም ቤተሰብ ውስጥ የሚያድግ ልጅ የሚያንፀባርቃቸው ባህሪዎች በአብዛኛው፡፡

– ከልክ ያለፈ በራስ መተማመን ይስተዋልባቸዋል፡፡

– በሚፈልጉት ጊዜ ማንኛውንም ነገር እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡

– ሕግና ደንብን ያለማክበር ችግር ይታይባቸዋል፡፡

ወላጆቻቸው ሁሉንም ነገር እየሰጡ ስላሳደጓቸው፤ በትምህርት ህይወታቸውም ሆነ ስራ ላይ፤ ይሄ ነው የሚባል ጥረት ስለማያሳዩ እኔ ብቻ የተሻልኩ ነኝ ብለው ስለሚያስቡ ስኬት ሲርቃቸው ይስተዋላል፡፡ ዝቅተኛ የሆነ የድብርት መጠን ይስተዋልባቸዋል፡፡

6. ቸልተኛ

እነዚህ አይነት ቤተሰቦች በአብዛኛው፣ የልጆቻቸውን መሰረታዊ ፍላጎት እንኳን በአግባቡ የማያሟሉ ናቸው፡፡ የእነሱ እምነት ልጅ በዕድሉ ያድጋል የሚል ሲሆን በራሳቸው ተፍጨርጭረው ህይወታቸውን እንዲለውጡ ይጠብቃሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ልጆች በስራና በሌላው ህይወታቸው በጣም የተዋጡ ወይም ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የሱስ ተጠቂዎች፣ የአዕምሮ በሽተኞች ወይም ደግሞ በልጅነት ዘመናቸው ከቤተሰባቸው ወይም ከማህበረሰቡ መልካም እንክብካ ያልተደረገላቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥናቶቹ ያመለክታሉ፡፡ እንደ ጥናቱ ምናልባት ልጆቹ የተፈጠሩት ሁለቱም ወላጆች፣ ልጅ ወልደው ለማሳደግ ዝግጁ ሳይሆኑ ወይም በአንደኛው ወገን ግፊትና ፍላጎትም ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል፡፡

እንደዘህ አይነት ባህሪ በሚንፀባረቅበት ቤተሰብ ያደጉ ልጆች በአብዛኛው

– ለመኖር አስፈላጊ የሆነ የህይወት ልምድና ክህሎት ማጣት ይስተዋልባቸዋል፡፡

– በሱስ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

– የወላጆቸውን በቂ ፍቅርና አትኩሮት ሳያገኙ ያደጉ ስለሆነ፣ ካደጉ በኋላም የሰውን አትኩሮት የመሳብ ይስተዋልባቸዋል፡፡

– ዕድሜያቸው ለተቃራ ፆታ ፍቅር ሲደርስም፣ ተፈላጊነታቸውን ለማረጋገጥ ከቀረቧቸው ሰዎች ጋር ሁሉ በቀላሉ በፍቅር የመውደቅ አባዜ ይስተዋልባቸዋል፡፡

– በአብዛኛው ወንጀል በመፈፀም የሚታወቁ ግለሰቦች ከዚህ አይነት ቤተሰብ እንደመጡ ይኸው ጥናት ያመለክታል፡፡

7.ምን ይደረግ?

ከላይ በመግቢያችን የጠቀስናት ተመራማሪ በጥናቷ ያሰፈረችው፣ ልጆችን በማሳደግ አስፈላጊ የሆነው ነጥብ ኃላፊነትን መወጣትና ከልጆች መጠበቅ የሚል ሲሆን፣ ከዚህ እሴት አኳያ እያንዳንዱን የአስተዳደግ ዘዴ እናያለን፡፡ ፈላጭ ቆጭ የልጅ አስተዳደግ ዘዴ (demanding not responsive) ተብሎ የሚፈረጅ ሲሆን፣ እንዲከበርለት የሚፈልጋቸውን የቤተሰብ እሴቶች ከመዘርዘር ውጪ ልጁ ከቤተሰቡ  የሚፈልጋቸውን ቅድመ ሁኔታ ስለማያሟላ፣ ተመራጭ ያልሆነ የልጅ አስተዳደግ መሆኑን ትገልፃለች፡፡

ነፃ የሆነ የቤተሰብ አስተዳደግን ስንመለከት ደግሞ (Responsive but not demanding) (ሚዛናዊ) የሚባለው የአስተዳደግ አይነት ‹‹Both responsive and demanding›› በመሆኑ፣ እጅግ ተመራጭና ለልጁ ሁለንተናዊ ዕድገት አዎንታዊ የሆነ ተፅዕኖ የሚያሳድር፣ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ወላጆች ቢከተሉት መልካም ውጤት እንደሚያመጣ ይታመናል፡፡ እንግዲህ የዛሬው ህፃን፣ የነገው አባወራና ሀገር ተረካቢ ነውና በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፣ ልጆቻችንን በማሳደግ ሂደት ውስጥ ለምናከናውናቸው ተግባሮች ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ልጆች የምንፈልገውን ነገር እንዲያደርጉ ከመናገር ይልቅ፣ ምሳሌ ሆኖ መገኘቱ ከሁሉም በላይ ተመራጭ ስለሆነ፣ የመልካም ባህሪ ባለቤትነት ፈርቀዳጅ በመሆን የመልካም ቤተሰብ ባለቤት መሆን ይቻላል እላለሁ፡፡

በኢትዮጵያ በካንሰር የሚያዙ ህፃናትና አዋቂዎች ቁጥር ለምን ጨመረ?

$
0
0

ካንሰር ከ100 በላይ የሚሆኑ በሽታዎች የጋራ መጠሪያ ሲሆን በሰውነት ውስጥ አንዱ ሴል ብቻውን ሲስፋፋ የሚመጣም ችግር ነው፡፡ ለዓመታት በኢኮኖሚ ረገድ ዕድገት ያሳዩ ሀገራት ችግር ብቻ ተደርጎ ሲቆጠር የቆየው ካንሰር፣ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዝቅተኛና መካከለኛ የዕድገት ደረጃ ባላቸው ሀገራትም ዋነኛው የጤና እክል ሆኖ ቀጥሏል፡፡
Cancer
እናም በኢትዮጵያ በካንሰርና ተያያዥ በሽታዎች የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ በሆነ መልኩ መጨመሩን የፌዴራል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ እንደተናገረው በየዓመቱ ከ60 ሺ በላይ ዜጎች የካንሰር ተጠቂ እየሆኑ ይገኛል፡፡ በመጪዎቹ 10 ዓመታትም ማለትም በ2025 አሃዙ ወደ 100 ሺ የማደግ ስጋት ጥሏል ብለዋል፡፡ በሁሉም የካንሰር አይነቶች በኢትዮጵያ 45 ሺ ሰዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡ ነው የሚገመተው፡፡ በተለይ በገዳይነታቸው በቀዳሚነት የሚቀመጡት የጡትና የማህፀን በር ካንሰር ብቻቸውን፣ ከ12 ሺ በላይ ዜጎቻችንን ህይወት በየዓመቱ ይቀጥፋሉ፡፡
በአሁኑ ሰዓት በዜጎች ላይ የሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች የጡት፣ የማህፀን በር ጫፍ፣ የሽንት ፊኛ መግቢያ ካንሰርና የአንጀት ካንሰር እንደ አደገኝነት ደረጃቸው ተዘርዝረዋል፡፡ ከፕሮስቴት ካንሰር ውጪ ባሉት ሶስቱ የካንሰር አይነቶች ሴቶች በይበልጥ እንደሚጠቁ ነው መረጃዎች የሚናገሩት፡፡ በዚህ መሰረት ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በካንሰር የመያዝ ዕድላቸው 67 በመቶ እንደደረሰ ጠቅሰዋል፡፡ በሌላ በኩል በሂውማን ፓፒሎማ (HPV) ቫይረስ አማካኝነት የሚተላለፈው የፕሮስቴት ካንሰርም በርካታ ወንዶችን ለሞት እያበቃ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

በአንፃሩ እንደ ሌሎች ሀገራት የትንባሆ አጫሾች ቁጥር፣ በኢትዮጵያ ከ20 በመቶ የማይበልጥ መሆኑን ተከትሎ በሳንባና ተያያዥ የሰውነት አካላት ላይ የሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች ዝቅተኛ መሆኑ ታውቋል፡፡ ነገር ግን ይሄ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለካንሰር በሽተኞች ሞት የ20 በመቶ ድርሻ አለው፡፡ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለሞት ከሚዳርጉ ምክንያቶች መካከል ካንሰር የ40 በመቶ ድርሻ ይዟል፡፡

በ2030 ደግሞ የመሪነት ድርሻውን እንደሚይዝ ተጠብቋል፡፡ ያም ቢሆን ብዙዎቹ የካንሰር በሽታዎች ሊታከሙና ፈውስ ሊገኝላቸው የሚችሉ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ በኢትዮጵያ ትልቁ ችግር የሆነውም የካንሰር ስጋት ያላቸው ሰዎች፣ በጊዜ ወደ ጤና ተቋም አለመምጣታቸውና ተገቢውን የባለሙያ እርዳታ አለማግኘታቸው ይገለፃል፡፡

በሀገራችን ለ90 ሚሊዮን ሕዝብ የካንሰር በሽታ ህክምና የሚሰጠው፣ በጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል ብቻ ነው፡፡ ከአዲስ አበባና ከክልል ከተሞች ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡትም ህክምና ለማግኘት ቢያንስ የአንድ ዓመት ቀጠሮ መጠበቅ አለባቸው፡፡ የዚህን ችግር መኖር የሚያረጋግጡት ዶ/ር ኩኑዝ፣ ከበሽታው ባህሪ አንፃር ጊዜ ሲሰጠው፣ በሰውነት ውስጥ ለማሰራጨት ዕድል የሚያገኝ በመሆኑ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡
በካንሰር ህክምና ስፔሻላይዝድ አድርገው፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና ሲሰጡ ከነበሩ አራት ባለሙያዎች መካከል አንዱ በጡረታ መገለላቸውን ተከትሎ፣ በቀሪዎቹ ሶስት ዶክተሮች ብቻ የካንሰር/የጨረር ህክምና ይሰጣል፡፡ የህክምና መሳሪያው ውድነትም አገልግሎቱን በማዳረስ ረገድ ፈተና መፍጠሩን ዶ/ር ኩኑዝ አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም የካንሰር በሽታ ህክምናን ፍለጋ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚመጡና የገንዘብ አቅሙ ኖሯቸው ማረፊያ ያላገኙ ሰዎች በየኮሪደሩ ለመተኛትና ወረፋቸውን ለመጠበቅ ተገደዋል፡፡ አንድ ለእናቱ የሆነው የጤና ተቋም/ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል/ ከአቅሙ በላይ ከሆነው ችግር ጋር እየታገለ እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ ነገር ግን በሽታው በየዕለቱ በውስጣቸው እየተሰራጨና እያዳከማቸው ተራቸውን የሚጠባበቁት ዜጎችም ተስፋ ብቻ ይመስላል ስንቃቸው፡፡

እ.ኤ.አ  በ2012 ብቻ በዓለም 14 ሚሊዮን ሰዎች አዳዲስ የካንሰር ተጠቂዎች ሆነው ሲመዘገቡ፣ በተመሳሳይ ዓት 8.2 ሚሊየኖች ደግሞ በዚህ በሽታ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በቀጣዮቹ ሁለት አስርት ዓመታትም ይሄ መጠን በ70 በመቶ ሊያድግ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ በካንሰር ሳቢያ ለሚከሰቱ ምቶች አምስቱ ተጠያቂ ምክንያቶችን ዘርዝሯል፡፡ እነርሱም ከፍተኛ ክብደት፣ ዝቅተኛ አትክልትና ፍራፍሬ ተመጋቢነት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አለማድረግ፣ ሲጋራ ማጨስና አልኮል ማዘውተር እንደሆኑ አስቀምጧል፡፡

በኢትዮጰያ የህፃናት ካንሰር በሽታ ለምን ጨመረ?

በኢትዮጵያ የካንሰር በሽታ ጭማሪ ለማሳየቱ የተወሰኑ ምክንያቶችን ይዘረዘራሉ፡፡ የታሸጉ ምግቦችና መጠጦች መበርከት፣ ኢንፌክሽን (በተለይ ከHPV ጋር በተገናኘ) የአካል ብቃት አለማድረግ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ እንዲሁም በሽታው ዕድሜያቸው በገፉ ሰዎች ላይ የመከሰት ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ተጠቅሷል፡፡ በህፃናት ላይ የሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች በአዋቂዎች ላይ ከሚከሰቱት አንፃር የተለዩ መሆኑን ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ የደም ካንሰር፣ የዕጢ ካንሰርና የአጥንት ካንሰር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ የካንሰር አይነቶች በህፃናት ላይ ያለመከሰት ዕድል ቢኖራቸውም አልፎ አልፎ ተከስተው ይታያሉ፡፡

የአጥንትና የደም ካንሰር የሆነው ሉኪሚያ/Leukemia/ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ በህፃናት ላይ የመከሰት ዕድሉ 30 በመቶ ሆኗል፡፡ በሽታው በፍጥነት የመሰራጨትና በህመምተኛው ላይ ድካም፣ መድማት፣ ክብደት መቀነስ፣ የአጥንት ህመምና ሌሎች ምልክቶች አሉት፡፡ በሽታው መኖሩ እንደታወቀም በአፋጣኝ የኬሞቴራፒ ህክምናን መከታተል መጀመር እንዳለባቸው ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ የደምና የአጥንት ውስጥ ካንሰር የሆነው ሉኪሚያ ደግሞ በኢትዮጵያ የህፃናቱ ዋናው የጤና እክል ነው፡፡

በመሆኑም በዚህ በሽታ ተይዘው የሚመጡ የህፃናት ቁጥር መጨመሩን ነው የተነገረው፡፡ ዶ/ሮች እንደሚሉት ‹‹ወላጆች በህፃናት አመጋገብ ላይ ትኩረት እስካላደረጉ ድረስ በአሳሳቢነቱ መቀጠሉ አይቀርም፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው ትኩስና አዳዲስ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ ይልቅ፣ የታሸጉ መጠጦችንና ምግቦችን ማስለመዳቸው ለካንሰር መስፋፋት ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡

በህይወት ዘመናቸው ከሶስት ሴቶች አንዷና ከአምስት ወንዶች አንዱ በካንሰር የመያዝ ዕድል እንዳላቸው አለምአቀፍ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ከዚህ አንጻር ወንዶችን በብዛት የሚያጠቁና ወዲያው ቢታወቁ ለመክሰም የሚችሉ የካንሰር አይነቶችን እንዲመረመሩ ይመክራል፡፡ በተለይም ወንዶች ከ50 ዓመት በኋላ፣ ሴቶች ከ35 ዓት ዕድሜ በኋላ የካንሰር ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡ ወንዶችን በተመለከተ የሳንባ ካንሰር፣ የትልቁ አንጀት ካንሰርና ፕሮስቴት ካንሰር ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ፣ ሴቶችን በተመለከተ ደግሞ የጡት ካንሰር፣ የማህፀን በር ካንሰር፣ የሳንባ ካንሰር፣ የትልቁ አንጀት ካንሰር፣ የማህፀን ጋን ካንሰር፣ የዕንቁላል ዕጢ (ኢቫሪያን) ካንሰርና የቆዳ ካንሰር ተጠቃሽ ናቸው፡፡
 


Health: ሙሉ ጨረቃና እብደት፣ ራስን ማጥፋትና የእንቅልፍ እጦት ምን አገናኛቸው?

$
0
0

የእኛ ምላሽ!
በጠፍ ጨረቃ ደጃፌ ላይ ቁጭ ብያለሁ፡፡ ቤት መግባት ያሰኘኝ አይመስለኝም፡፡ ብቻ የጨረቃዋ ድምቀት ፍጥጥ አድርጎኝ ቁጭ ብያለሁ፡፡ እንቅልፍ ያስፈለገኝ አይመስለኝም፡፡ ነገሩ ደግሞ ጥሎብኝ ነው መሰል፣ ከዋክብትንና ጨረቃን ለስለስ ባለ ነፋሻ አየር መታደም እጅግ ሐሴትን ይሰጠኛል፡፡ ዛሬ ግን በጠራው ድቅድቅ ጨለማ ወለል ብላ የምትታየኝ የኛዋ ብቸኛዋ ጨረቃ ናት፡፡ በእርግጥ ከቅርብ ርቀት እነ ኔቡላን የመሰሉ የሰማዩ ግርማዎች ሲንቦገቦጉ ይታዩኛል፡፡ በዚህ ትዕይንት መሀል ግን ትኩረቴን ስቦት እያነበብኩት ያለ ነገር አለ፡፡ ጆርናል ኦፍ ሳይካትሪ ሰርቪስስ፣ በመድረ አሜሪካ የሳይንሳዊ ጥናት ጆርናል፡፡ ከዚህ ጆርናል ላይ አንድ ትኩረቴን የሳበ ጥናት ይገኛል፡፡ በጨረቃና በሰው ልጅ መካከል ያለ ጥብቅ ቁርኝት፡፡ ወደድንም ጠላንም ጨረቃ በእኛ ላይ የማይካድ ተፅዕኖ አላት ብለን እንድናስብ የሚያደርጉ ነገሮችን አስፍሯል፡፡
ask your doctor zehabesha

እርግጠኛ ነኝ፣ ብዙዎቻችን በተለይም የሆሊውድ ፊልም ያየን ሰዎች በአስፈሪና አስደንጋጭ ዘውግ ፊልሞቻቸው፣ ጨረቃና የሰው ልጅ ምትሃታዊ ለውጦችን በብዛት አይነት ይሆናል፡፡ ነገሩ ከፊልምነት የዘለለ ነገር የለውም ብለንን እናልፍ ሆናል፡፡ ሆኖም ግን ትንሽ ቢሆን አሊያም እንደ ፊልሙ የተጋነነ ባይሆንም ጨረቃና እኛን የሚያቆራኙን፣ ብዙ ጉዳዮች መኖራቸው እውነትነት አለው የሚሉ ወገኖች መኖቸው እሙን ነው፡፡

ጨረቃና አደጋዎቿ

ብታምኑም ባታምኑም ሙሉ ጨረቃ በምትውልበት ወቅት፣ ሰዎች እንቅልፍ በአግባቡ ለመተኛት ያቅታቸዋል ይለናል ጆርናል ኦፍ አፌክቲቭ ዲስ ኦርደርስ በ1999 ላይ ደረስኩበት ባለው ጥናት፡፡ አስገራሚው ቁም ነገር ደግሞ ለዚህ ምክንያት ነው ብሎ ያስቀመጠው ትንታኔ፣ የፊዚክስ እውነታዎች ላይ ተመርኩዞ መሆኑ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ምድር ላይ ያሉ የውሃማ አካላትን ወጀብ (ማዕበል) የሚፈጥሩት ፀሐይና ጨረቃ ናቸው፡፡ ይህ የወጀብ እንቅስቃሴም ወደ ጨረቃ አቅጣጫ ያለ ውሃማ አካልን በስበት ኃይል ወደ ጨረቃ ስለሚጎትት፣ ወጀቡ ይፈጠራል ወደ ፀሐይ አቅጣጫ ያለውም ውሃማ አካል እንዲሁ ወደ ፀሐይ ይሳባል፤ ይህም (ታይዳል ዌቭ) በአማርኛችን ስንመልሰው ወጀብ ይፈጠራል፡፡ ሆኖም የሰው ልጅ አካል 75 በመቶው ውሃ በመሆኑ፣ ሙሉ ጨረቃ በሚሆንበት ወቅት ይኸው የስበት ኃይል ተፅዕኖ ሳይፈጠርብን እንደማይቀር ይገመታሉ፡፡

በምድረ አሜሪካ 11940 የደረሱ አደጋዎች ላይ ያተኮረ ጥናት፣ በኮሎራዶ ቬቴሪናሪ ሜዲካል ሴንተር ተመራማሪዎች ሲያካሂዱ፣ ደረስንበት ያሉት መረጃ እንደሚያሳየው ዘወትር ከሚደርሰው ውድመቶች ላይ 23 በመቶ የመጎዳዳት አደጋ በዚህ የሙሉ ጨረቃ ወቅት ደርሷል፡፡

የአሜሪካ አብስቴትሪክስና ጋይናኮሎጂ ጆርናል ጥናት ደግሞ፣ በሴቶች የወር አበባ ላይ አተኩሮ በሙሉ ጨረቃ ወቅት ያለውን ሁኔታ ከተለመዶው ምሽት ጋር አነፃፅሮ አጥንቷል፡፡ በእርግጥ የሴቶች የወር አበባ አመጣጥ በራሱ የሚለያይና ቋሚ ሂደት የሌለው የተፈጥሮ ክስተት ነው፡፡ ክስተቱም በየ28 ቀናት ውስጥ የሚከሰትና ከእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ በአንዱ ሊመጣ የሚችል ቢሆንም፣ በሙሉ ጨረቃ ዕለት ግን በ29 እና 30 ቀናት ውስጥ መከሰቱ፣ ይህም የተከሰተባቸው 60 በመቶ የሚሆኑት ጥናት የተካሄደባቸው ሴቶች መሆናቸው ነው፡፡

ሙሉ ጨረቃ ስትሆን ራስ ህመም ይበረታል፣ እንቅልፍ ቶሎ አይመጣም አንዳንዶችንም ታሳብዳለች?

ሙሉ ጨረቃ በምትታይበት ወቅት፣ አንዳንድ ግለሰቦች ሊያብዱ ይችላሉ የሚለውን የቆየ እምነት ለመፈተን፣ ቆርጠው ከተነሱ ተመራማሪዎች መካከል የፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲው፣ ጀምስ ሮትንና የሳስካችዌን ዩኒቨርሲቲው ኢቫን ኬሊ ናቸው፡፡ በ37 ተመሳሳይ ጥናቶች ላይ ተመርኩዘው ለረጅም ጊዜ ጉዳዩን መረመሩት፡፡ የአእምሮ ህመምተኞች ሆስፒታሎችንም ሁኔታ አጠኑ፡፡ ነገር ግን ሰዎች እንደሚያስቡት፣ ጨረቃ ያን ያህል ለእብደግ አታደርስም አልያም ተጋንኖ የሚታየን በጨረቃ ወቅት ነው እንጂ፣ በሌላ ጊዜያትም ሰዎች በተመሳሳይ ቁጥር እንደሚያብዱ ጥናታቸው ይጠቁማል፡፡ ራስ ህመምንም ቢሆን የተለየ ራስ ህመም ምልክቶችን በዚህ ወቅት እንዳላዩ ጥናታቸው ይናገራል፡፡ ሰዎች ቀደም ሲሉ ሙሉ ጨረቃ ስትውል ችግሩ እንደሚባባስ ስለሚያስቡ፣ በሙሉ ጨረቃ ዕለት ችግሩ እንደተከሰተባቸው አድርገው ስለሚያስቡ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ያምናሉ፡፡

እንቅልፍ እጦትን በተመለከተ ግን ሙሉ ጨረቃ በምትውልበት ወቅት ሰዎች ቶሎ እንደማይተኙ ጥናታቸው ያትታል፡፡ እንደነ ጀምስ ሮተን እምነት ይህ ሊሆን የሚችለው፣ የጨረቃዋ ረጅም ሰዓት ደምቃ መታየት ሰዎች ቶሎ እንዳይተኙ የሚመች ሁኔታዎችን ስለምትፈጥር ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ፡፡ እናም ሰዎች በነፋሻ አየርና በደማቅ የጨረቃ ብርሃን ታግዘው፣ እንቅልፋቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደሚያርቁት ይታሰባልም፡፡

ሁለት ጥናቶች እርስ በእርሳቸው እንዳይስማሙ ያደረገ ክስተት ደግሞ በእንስሳቶች ላይ የሚታየው ሁኔታ ነው፡፡ በእንግሊዝ የተደረገ አንድ ጥናት በ2001 ላይ በብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል ላይ ለህትመት ሲበቃ፣ ውሾች በሙሉ በጨረቃ ወቅት ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ ያደርሳሉ፡፡ ውሾች ቀዳሚዎች ሆነው በጥናቱ ላይ ተመዝግበዋልም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአውስትራሊያ የተደረገ ጥናት በዚሁ ጆርናል ላይ ታት እንደሚነበበው፣ ውሾች በማንኛውም ምሽ ሰዎች ላይ ጉዳት የማድረስ እድላቸው ሰፊ እንደሆነ በመረጃ የተደገፈ ነገር አሳይቷል፡፡ ይህ ጥናት እንደሚያምነው፣ ውሾች ምሽት ከሆነ በማንኛውም ወቅት አደጋ የማድረስ እድላቸው ከቀን ይበልጣል፡፡ በመሆኑም የውሾች አደጋ ከጨረቃ ጋር ምንም እንደማያያይዘው ጥናቱ ይደመድማል፡፡

በተደጋጋሚ ከሚነሱ ቆየት ያሉና ጥናታዊ ግምቶች መካከል፣ ጨረቃና እብደትን የሚያይዙ አመለካከቶች ናቸው፡፡ ከ2004 ጀምሮ በምድረ ካናዳ ጥናት ያካሄዱ ሳይንቲስቶች፣ በጆርናል ኦፍ ኢፔሌፕሲና ቢሄቪየር ላይ እንዳሰፈሩት ሰዎች እንደሚያምኑት፣ ሙሉ ጨረቃ በምትውልበት ወቅት ምንም አይነት የተለየ የአዕምሮ ችግር እንደሌለ እና ጥናታቸውም የሚፈራውን ነገር ማግኘት እንዳልቻለ ያትታል፡፡

አሜሪካዊው የሳይንስ ጋዜጠኛና የባድ ሳይንስ አምደኛ፣ ‹‹ፖሊሶችም ሆኑ ነዋሪው በሙሉ ጨረቃ ወቅት ከባድ አደጋ ይደርሳል አልያም ያጋጥመናል ብለው ካመኑ ብዙ ችግሮችና አደጋዎች ከወትሮው በተለየ ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ይህ ማለት ሙሉ ጨረቃ ስለዋለች ሳይሆን፣ ሰዎች አመለካከታችን ውሏችንን ስለሚፈጥረው ነው፡፡ የምናስበው ነገር የምንፈልገውን ክስተት ተፅዕኖ ውስጥ ያሳድረዋል…›› ይላል፡፡

እውነቱ ወዴት ይሆን?

ሳይንስ እርስ በእርሱ መስማማት ያልቻለበት ጉዳይ ይመስላል፡፡ በተለይም እንቅልፍ ላይ ሙሉ ጨረቃ በምትውልበት ምሽት፣ ተፅዕኖ እንዳለው የሚያምኑ ሳይንቲስቶች መኖራቸውና በተቃራኒው ደግሞ፣ ይህን የሚቃወሙና ከጨረቃ ጋር ምንም የሚያያይዘው ጉዳይ እንደሌለ የሚጠቁሙ ሳይንቲስቶች በሌላኛው ወገን ሆነው እሰጥ አገባቸውን የቀጠሉ ይመስላል፡፡

አብዛኞቹ ሳይንሳዊ ጥናቶች፣ የመረጃ አሰባሰባቸው ተቀራራቢ በመሆኑ ደግሞ ጉዳዩን እንቆቅልሽ ያደርገዋል፡፡ ሆኖም ግን አብዛኞቹ ተመማሪዎች ጠንከር ያለው አመለካከቶች ላይ አንድ አቋም ያላቸው ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ያህል ከሌላው ጊዜ በተለየ ለአዕምሮ ህመም የሚጋለጡ ሰዎች፣ ሙሉ ጨረቃ ወቅት ያብዳሉ አልያም አቅላቸውን ስተው፣ ጨርቃቸውን ጥለው ጎዳና ይወጣሉ የሚባለው የቆየ አመለካት እውነት እንዳልሆና፣ እስካሁን ድረስ ሳይንስ ይህን ነገር ባያረጋግጥም እውነት የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ወደፊትም ጥናቶች የዚህ አመለካከትን እውነትነት አልያም ውሸትነት ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ነገር ግን ትልቁ ጉዳይና ብዙዎቹን ሳይንቲቶች አላግባብ ያለው አመለካከት ሙሉ ጨረቃና የሰዎች እንቅልፍ ዑደት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይም ሳይንቲስቶች ለሁለት ተከፍለዋል፡፡ እንቆቅልሽ የሆነው ጉዳይ ደግሞ፣ ሁለቱም ጎራዎች የተለያዩ ጥናቶችን አድርገው ደረስንበት ያሉት ውጤት ተቃራኒ የማያስማማ መሆኑ ነው፡፡

ሆኖም የሰሞነኛ ጨረቃችን፣ የበልግ ዝናባችን እንደቀረ ምልክት መሆኑን ደግሞ የተለያዩ የስፔስ ሳይንስ፣ የአየር ንብረት ጥናቶችን ተመርኩዘን መገመት እንችላለን፡፡ በእርግጥም ዘንድሮ የበልግ ዝናብ፣ በብዙዎቹ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም ሙሉ ጨረቃ በታየችባቸው አካባቢዎች አለመኖሩ እሙን ነው፡፡
መቼም ይቺ ሙሉ ጨረቃ የማታመጣብን የለምና፣ ከዝናብ እጥረት አልፎም ጤናችን ላይ ታሳድራለች የተባለው ተፅዕኖም እውነት ይሆን? በእርግጥ ጨረቃ የሰውን ልጅ የማሳበድ አቅም ይኖት ይሆን? ሰዎችንስ እንቅልፍ የምትነሳበት ወቅት አላት ይሆን? ጊዜና ሳይንስ ይፍቱት እላለሁ፡፡

Health: ድንገተኛ የእንቅስቃሴ ላይ የሞት መንስኤዎችና ሊወሰዱ የሚገባቸው 5 እርምጃዎች!

$
0
0

ሰዎች ስፖርት እየሰሩ ራሳቸውን ስተው ስለምን ይወድቃሉ?

እንቅስቃሴ የሚያደርጉና የተስተካከለ አካላዊ ቁመና ያላቸው ሰዎች፣ ከልብ ጋር ተያይዘው ለሚመጡ በሽታዎችና ለሞት የመጋለጥ ዕድላቸው በተቃራኒው ካሉት አንፃር እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች በእንቅስቃሴ ወቅት ከሚመጣ አደጋና ሞት ሙሉ ለሙሉ የተጠበቁ አለመሆናቸው ነው፣ ዘ ሳይንስ ኦፍ ስፖርት ባሰፈረው ጥናታዊ ጽሑፍ የሚያስረዳው፡፡
excersise

ስፖርተኞች በምንልበት ጊዜ የግድ በአትሌቲክስ በሩጫና ውርወራ እንዲሁም በእግር ኳስና በቦክስ ጨዋታዎች ውስጥ የሚሳተፉትን ብቻ የሚመለከት አይደለም፡፡ ክብደት ለመቀነስ ወይም የኮሌስትሮል መጠንን ለማስተካከል አልያም የደም ውስጥ ደም ግፊትንና የስኳር መጠንን ለማስተካከል ሰዎች በራሳቸው ተነሳሽት ወይም በሐኪም ትዕዛዝ ዕለታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ይሰራሉ፡፡ በተለይ የልብ ፍጥነትን የሚጨምሩ ስፖርቶች በየዕለቱ ወይም ከአንድ ሰዓት በላይ በተሰሩ ቁጥር እንዲህ መሰል ሰዎችን በድንገተኛ ለሚጥሉ ወይም ለሚገድሉ ህመሞች ይጋለጣሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የዘርፉ ባለሙያዎች ስፖርተኞችን በድንገት ሊጥሉ ወይም ሊገድሉ ይችላሉ የሚሏቸው ህመሞች ውስጥበዋናነት ከልብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ናቸው፡፡ የጡንቻ መጠን መተለቅ ችግር ወይም በህክምና ቋንቋው ‹‹Hypertrophic cardiomyopathy›› አንዱ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ደምን ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚረጨው የግራው የታችኛው ልብ ክፍል ጡንቻ በወፈረ ቁጥር ድንገት ደም መርጨትን ሳይታሰብ በመግታት አንድን ሰው በድንገት ጠብ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ከልብ ጋር የተያያዘው ሁለተኛ ገዳይ ደግሞ በማህፀን ውስጥ አንድ ፅንስ የተለያዩ አካላቶችን ሲያዘጋጅ የአፈጣጠር ዝግጅት ሊከሰት በመቻሉ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በልብ አፈጣጠር ወቅት የሚከሰት ዝንፈት ‹‹Congenital malformation›› ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ እንዲሁም ልባችን ኤሌክትሪካዊ የአሰራር ፍሰት ያለው ሲሆን በሆነ አጋጣሚ ይህ መሰሉ የኤሌክትሪክ ፍሰት እክል ‹‹Electrical abnormalities of the heart›› ሌላው ለድንገተኛ ሞት የሚያጋልጥ ነው፡፡ የልብ ምት መዛባት ማለትም ከወትሮ የልብ ፍጥነት በላይ ወይም ከወትሮው የልብ ፍጥነት በታች አልያም የልብ ፍጥነት መጨመርና ወጥነት ማጣት በቀላሉ የሚታዩ አይደሉም፡፡

ከልብ ችግር ወጣ ስንልም በተለይ አስም በመባል የሚጠራው የመተንፈሻ አካል ህመም ያለበት አንድ ሰው በድንገት የአየር ቧንቧው በመጥበቡ ትንፋሽ ሊያጥረውና ሊሞት የሚችል በመሆኑ እንዲህ መሰል ችግር ያለባቸው ሰዎች ስፖርት ከመስራታቸው በፊት ሐኪማቸውን ቢያማክሩ ወይም እንደ ቬንቶሊን አይነት የአየር ቧንቧ ማስፊያ መድሃኒቶችን ቢይዙ መልካም እንደሆነ ይጠቆማል፡፡

የስኳር ህመም ሌላኛው በድንገት ራስን ለመሳት የሚያጋልጥ ህመም ነው፡፡ በዚህ ረገድ የደም ውስጥ ግሉኮስ መውረድ ወይም ከልክ በላይ መውጣት አንድን የስኳር ህመምተኛ ራሱን ስቶ እንዲወድቅ ወይም ደግሞ በድንገት እንዲሞት ሊያደርገው የሚችል በመሆኑ የስኳር ህሙማን በተቻለ መጠን ከሐኪማቸው ጋር በመወያየት ስፖርታዊ እንቅስቃሴን መስራት ወይም ከስፖርት በፊትና በኋላ የደም ውስጥ ግሉኮስን በመለካት በጣም ካነሰ ተጨማሪ ካሎሪ የመውሰድና ከጨመረ ደግሞ ስኳር አውራጅ ኢንሱሊን (መድሃኒት) መውሰድ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ዞሮ ዞሮ በስፖርት ጊዜ የደም ግሉኮስ መመርመሪያ፣ ጣፋጭ ምግብ፣ እንዲሁም ኢንሱሊን መያዝና የስኳር ህመምተኝነትን የሚገልፅ ምልክት በእጅ ላይ ማሰር ወይም መታወቂያ ካርድ መያዝ ጠቃሚ ይሆናል፡፡

‹‹Heat Stroke›› በመባል የሚጠራው ችግር ደግሞ ሙቀትን ተከትሎ በሚመጣ ላብ ሳቢያ አንድ ሰው ራሱን ሊስት ይችላል፡፡ ከፍተኛ ፈሳሽ በላብ መልክ ሲወጣ በሚጠጣ ውሃ ወይም ማዕድን በሚተኩ መጠጦች የሚተካ ባልሆነ ቁጥር ይህ መሰል ችግር ሊከሰት ይችላልና ነገሩን ከዚህም አንፃር ማጤን መልካም ነው፡፡ ከደም ግፊት ጋር የተያያዘ ስትሮክም እንዲሁ በጭንቅላት ውስጥ የደም መፍሰስን የሚያስከትል በመሆኑ የደም ግፊት ህሙማን ሐኪማቸውን ያማክሩ፡፡

እንደሚታወቀው ስፖርተኞች በውድድር አልያም በልምምድ ላይ ሳሉ በድንገት ሲሞቱ፣ የሚዲያዎችና በአጠቃላይ የዓለማችን ዋና ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ መነጋገሪያነቱ ከፍ ይላል፡፡ ፍጥነትና ጉልበት በሚፈልጉ የሜዳ እና የጎዳና ላይ ስፖርታዊ ውድድሮች ከፍተኛ ስም ያተረፉ ስፖተኞች በድንገት ህይወታቸው አልፏል፡፡

በእንቅስቃሴ ላይ ሳሉ በድንገት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች፣ ስር የሰደደ የልብ ችግር እንዳለባቸው ቀድመው ምንም አይነት መረጃ የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በእንቅስቃሴ ወቅት ከልብ ችግሮች አይነቶች ጋር የተያያዙ በሽታዎች ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ፣ የእነዚህ በሽታዎች በአትሌቶች ላይ በድንገት የመከሰት ዕድላቸው እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ ጥናቶች ችግሩ ከ10 ሺ ወይም ከ20 ሺ አትሌቶች በአንዱ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ያስገነዝባሉ፡፡ ነገር ግን አሃዙ ስፖርትን በሚያዘወትሩ፣ ያለ ቅድመ ዝግጅት ስፖት በሚጀምሩበት እንዲሁም ወጣ ገባ በሚሉት ላይ እጅጉን ከፍ ይላል፡፡

በየዕለቱ የሚደረግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ልባችንን በሚገባ ይጠብቅልናል፣ የተመታጠነ ኮሌስትሮል በሰውነታችን ውስጥ እንዲኖር፣ ልባችን ስራውን እንዲያቀላጥፍ እንዲሁም ህይወታችን የተሻለ እንዲሆንና ዕድሜአችንን ለመጨመር የማይተካ ሚና አለው፡፡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በራሱ እጅግ ጠቃሚ እንጂ አደገኛ አይደለም፣ ጥቅሞቹም በፍፁም መዘንጋት እንደሌለባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

በድንገተኛ ሞት ላይ የሚወጡ ጥናቶች፣ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ወቅት ለሚከሰተው ድንገተኛ ሞት፣ እንቅስቃሴ በራሱ ተጠያቂ ነው አልያም ሌሎችም ምክንያት ይኖራሉ ሲሉ ሐሳብ ያቀርባሉ፡፡ ነገር ግን አሁንም በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወቅት ሳይታሰብ ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቀደም ሲል የሚያውቁት ወይም የማያውቁት በተለይ የልብ ችግር ዋነኛው ምክንያታቸው ሊሆን እንደሚችል አፅንኦት ይሰጣሉ፡፡ ሌሎች መረጃዎች መካከለኛ እንቅስቃሴ ለድንገተኛ ሞት ምክንያትነቱ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያሉ፡፡ በአንፃሩ ማራቶንና ሀገር አቋራጭ ሩጫዎች ደግሞ ከ5-7 እጥፍ አደጋውን ሊያባብሱት ይችላሉ፡፡ የቀድሞው ዝነኛ የማራቶን ሯጭ አልቤርቶ ሳላዛር፣ በልብ ድካም ሳቢያ በልምምድ ላይ ሳለ ህይወቱ ያለፈ ታላቅ አትሌት ነው፡፡
በስፔን ላሊጋ (የእግርኳስ ውድድር)፣ በፕሮፌሽናልነት ደረጃ ሲጫወት የነበረው የ22 ዓመቱ፣ አንቶኒዩ ፑየርታ ጨዋታ ላይ ራሱን ስቶ በመውደቁ ህይወቱን አጥቷል፡፡ ክስተቱ መላውን የዓለም የእግርኳስ ተመልካች ሐዘን ውስጥ የጣለ ሆኖ አልፏል፡፡ ሌላው ካሜሮናዊ ኢንተርናሽል ቪቪየን ፎዬ በሜዳ ላይ በድንገት ተዝለፍልፎ በመውደቁ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም፣ ልቡ መስራት አቁማለችና የትኛውም የህክምና ባለሙያ ህይወቱን ሊታደጋት ያልቻለ እግርኳስ ተጨዋች ነበረ፡፡ የዝነኛው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የቀድሞ ባለቤትም እንዲሁ በልምምድ ላይ ሳለች በድንገት ህይወቷ ያለፈች ሌላኛዋ አትሌት ናት፡፡

እነዚህን ጨምሮ የአንድ ወቅት መነጋገሪያ የነበሩ የስፖርተኞችን የሜዳ ላይ ሞት ሰምተናል፣ ነገር ግን ማናችንም ይሄ ተከስቷል ብለን ስፖርትን ከማዘውተር አላገደንም፡፡ በእርግጥ ክስተቱ በእኛ ላይ የመፈጠር ዕድላቸውን በማጤን ለጥንቃቄ እንደመነሻ አገልግለውን ይሆናል፡፡

እግርኳስን ጨምሮ፣ የዓለማችን ትልልቅ የስፖርት ክለቦች ለሚገዟቸው ስፖርተኞች ጤንነት ትልቅ አፅንኦት ይሰጣሉ፡፡ የልብ አልያም ሌላ መሰረታዊ የጤና ችግር ጋር የሚገኝን ስፖርተኛ አያስተናግዱም፣ ወይም እጅግ ጉልበትና ፍጥነት በሚጠይቅ የውድድር መድረክ ላይ እንዲወክላቸው ዕድል አይሰጡም፡፡ በዚህም ስፖርተኞች ሙሉ የጤና ምርመራን እንዲያልፉ ያስገድዳሉ፡፡ በተለይ በአውሮፓ የእግርኳስ ሊጎች ውስጥ ብዙ ጊዜ ድንገተኛ የስፖርተኞችን ሞት የማንመለከተውም፣ በጤና ምርምር ላይ ያላቸው ጥብቅ አቋም ነው፡፡

በእንቅስቃሴ ወቅት ሊኖር የሚችልን ድንገተኛ ሞት በምን መልክ ልናስወግድ እንችላለን?

1. ትምህርት፡- ስለልብም ሆነ በእንቅስቃሴ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን በተመለከተ፣ ራስን ለመረጃ ማብቃት መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ አደገኛው ክስተት ከመፈጠሩ በፊት በሰውነታችን ላይ የተለያዩ ምልክቶችን ልንመለከት እንችላለን፡፡ በተለይ ራስን መሳት፣ የአተነፋፈስ ችግር ወይም የትንፋሽ እጥረት፣ የደረት ላይ ህመምና ድብርት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህንና ሌሎች ምልክቶች በሚገባ መረዳት፣ በእንቅስቃሴ ውስጥ ሳለን ማወቅ የሚገባን ይሆናል፡፡

2. ምርመራ፡- ብዙዎቹ የአደጋው ምልክቶች በቀላሉ የሚደርስባቸው አይደሉም፡፡ ብዙዎች አጠቃላይ የጤና ምርመራ የማድረግን ከፍተኛ ጥቅም ትኩረት አይሰጡም፣ ተጨማሪ ወጪ አድርገውም ይወስዱታል፡፡ ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታ (ለጤና አልያም ለውድድር) ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ስንጀምር፣ የልባችንን ጨምሮ፣ የግፊት፣ የስኳር፣ የሳንባና የመላ ሰውነታችን የጤና ሁኔታ በምርመራ ማወቅ ያስፈልገናል፡፡
3. የቤተሰብን የጤና ታሪክ ማወቅ

ስፖርተኞችም ሆነ እንቅስቃሴን በየዕለቱ መከወን የሚፈልጉ ሰዎች፣ በቅድሚያ ማድረግ ካለባቸው ተግባር መካከል በጤና ዙሪያ የቤተሰቦቻቸውን ታሪክ ማወቅ ነው፡፡ ልብ እና ሌሎች የመተንፈሻ አካላት ችግሮች የቤተሰቦቸው ጉዳይ ከነበሩ፣ የእኛም ችግር የመሆን ዕድል ይኖራቸዋልና ለምርመራ የህክምና ባለሙያ እርዳታ ያስፈልገናል፡፡ (የልብ ችግሮች፣ የስኳርና የደም ግፊት ችግሮች በዘር ይወረሳሉ)

4. ከሚታወቅ ህመም ጋር ወደ እንቅስቃሴ የሚመጡ ሰዎችም፣ ህመማቸው እስከሚፈቅድላቸው ርቀት ድረስ ብቻ መንቀሳቀስ እንዲሁም ቅድመ ሁኔታዎችንም መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡ ከሐኪሞቻቸውም ጋር መመካከራቸውን መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ለምሳሌ ከስኳር ህመም ጋር እያሉ እንቅስቃሴ የሚጀምሩ ሰዎች፣ በበቂ ሁኔታ ምግባቸውንና መድሃኒታቸውን መውሰዳቸውን እርግጠኛ መሆን አለባቸው፡፡

5. ድንገተኛ ራስን መሳት በሚያጋጥም ጊዜ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ እንደተጠበቀ ሆኖ በቦታው የሚደረግ የህይወት አድን ስራም ወሳኝ ነው፡፡ ለምሳሌ ደረትን በመዳፍ ጫን ጫን የማድረግና በአፍ በኩል የሚሰጥ የትንፋሽ እገዛ ግድ ነው፡፡ ግለሰቡ አየር እንዲያገኝ ማድረግ፣ ምላሱ ጉሮሮውን ታጥፎ እንዳይዘጋው ምላስን በጣት መዘርጋትን ማረጋገጥ፣ በፍጥነትም አምቡላንስ መጥራት የሚመከሩ ናቸው፣ መልካም ጤንነት፡፡

Health: የመገጣጠሚያ አካላት የህመም ስሜቶችና መፍትሄዎቻቸው

$
0
0

 

ከዶ/ር ቁምላቸው አባተ (ሜ/ ዶክተር)

ከመቶ በላይ የሚሆኑ የመገጣጠሚያ ህመሞች አሉ፡፡ የመገጣጠሚያ ህመም ሲባል በጥቅሉ በሰውነት የሚገኙ ትናንሽም ይሁኑ ትላልቅ መገጣጠሚያዎችን ያማከለ በዋነኝነት እብጠትና የመጠዝጠዝ ስሜት የሚያስከትል ህመም ሲሆን መጠኑ፣ ዓይነቱን ተከትሎ የሚከሰተው ችግር ይለያይ እንጂ ልጅ አዋቂ ሳይል በማንኛውም እድሜ ክልል ፆታና ዘርን ሳይለይ ይከሰታል፡፡ በመሰረቱ የመገጣጠሚያ ህመም ሲባል የግድ መነሻው መገጣጠሚያ ነው ማለት አይደለም፡፡ ማንኛውም በሽታ የመገጣጠሚያ ህመም አያስከትልም ባይባልም አብዛኛውን ጊዜ የአጥንት፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመሞች መገለጫ ሊባል ግን ይችላል፡፡ ቀላል ወይም ከባድ የጤና ችግር የሚያስከትሉ የመገጣጠሚያ ህመሞች ባጀማመራቸው ተመሳሳይ ምልክቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡

bone

ለመገጣጠሚያ ህመሞች የሚደረግ ምርመራ አፋጣኝ ምላሽ ማግኘት የሚገባቸውን፤ በጊዜ ሂደት ሊፈቱ ከሚችሉት ለመለየት ያስችላል፡፡ የመገጣጠሚያ ህመም መነሻ ምንድን? የሚለውን ለመመለስ ሙሉ የጤና ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም፡፡ ለባለሙያ በሚነገረው የምልክት ይዘት፣ ሂደት፣ ተከታታይ ስሜቶች ወዘተርፈ የህመሙን ክብደት መገመት ይቻላል፡፡ ቀጥሎ ሊከወን የሚገባውንም የአካል ምርመራ እንዲሁም ትኩረት የሚሹ የላቦራቶሪና ተያያዥ ምርመራዎች ለመምረጥ አቅጣጫ መተለሚያ ነው፡፡ አንድ ታማሚ ሊገልፃቸው የሚገቡ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትት ይገባል፡፡ የመገጣጠሚያ አካላት አካባቢ ያሉ ማናቸውም የህመም ስሜቶችን (ለምሳሌ መጠዝጠዝ)፣ የታመሙ መገጣጠሚያዎች ቁጥር፣ የህመሙ አስከፊነት፣ድግግሞሽ፣ ቆይታ እንድሁም ጠቅላላ ይዘት (አልፎም መዘርዘር የሚገባቸው እውነታዎች ቢኖሩትም) መገለፅ ይገባዋል፡፡ የእብጠቱም እንዲሁ ሂደቱ፣ ቆይታው፣ የእብጠቱ ሙቀት፣ እብጠቱን የሸፈነው ቆዳ መልክ ለውጥና የመሳሰሉትም በተመሳሳይ መገለፅ ይኖርባቸዋል፡፡

• ህመም፣ እብጠት በዚህም የተነሳ መገጣጠሚያን ማጠፍ መዘርጋት አለመቻል፡ ፡ እብጠትን እንጂ የህመምን ልክ በወጉ ለመግለፅ ሊከብድ ይችላል፡፡ የሆነው ሆኖ አስቀድሜ ከጠቀስኳቸው ምልክቶች ባሻገር የታመመው መገጣጠሚያ፣ የህመሙ ክስተት ፍጥነት እንዲሁም አጠቃላይ ህመሙን የሚያባብሱ ወይም የሚያሻሽሉ ነገሮች መገለፅ ይገባቸዋል፡፡

• የህመሙን የክፋት ልክ በወጉ መግለፅ ከባድ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡

ህፃናት (በተለይ በለጋ ዕድሜ ያሉት ህመማቸውን በወጉ መግለፅ ስለማይችሉ) የበለጠ ሊያስቸግር ይችላል፡ ፡ ለማንኛውም የመገጣጠሚያ ህመሙ ምንም ዓይነት ስራ ለማከናወን የማይቻልበትን ሁኔታ ካስከተለ አሳሳቢ እንደሆነ መረዳቱ ፈጣን ምላሽም እንደሚያሻው አያጠራጥርም፡፡ ለእንዲህ ዓይነት መገጣጠሚያዎች እብጠት፣ ቃንዣ፣ ማጠፍ፣ መዘርጋት አለመቻል መነሻዎች አጥንት ወይም መገጣጠሚያ በባክቴሪያ ወይም በካንሰር ህመም ተይዞ መሆኑን ጠቋሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ መስራት አለመቻል፣ የታመመውን የአካል ክፍል ጨርሶውኑ አለማንቀሳቀስ፣ እንቅልፍን ማጣጣም አለመቻል ወዘተ የህመሙን ክብደት ማሳያዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ • የታመሙትን መገጣጠሚያዎች ማወቅ (የትኛውን መገጣጠሚያ ነው የሚያመኝ? ምን ያህል መገጣጠሚያዎችን?….ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት፣ በቀጣይነት መወሰድ የሚገባቸውን ምርመራዎች እንዲሁም ሊሰጥ የሚገባውን ህክምና ፈር ማስያዣ ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አንድ መገጣጠሚያ ሲታመም ፈጣን ምላሽ ሊያሻው እንደሚችል መገመት መልካም ነው፡፡ • የህመሙ ተከታታይነት፣ አልፎ አልፎ መከሰት፤ አለበለዚያም ካንድ መገጣጠሚያ ወደ ሌላ መዛወሩ መነሻ ምክንያቱን ጠቋሚ በመሆኑ አፋጣኝ ህክምና ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ለምሳሌ ፋታ የማይሰጥ፤ ተከታታይ ህመም ባንፃሩ አሳሳቢ መነሻዎች አሉት፡፡ ህመሙ የሚባባስበት ሰዓትም እንዲሁ የህመሙን አስከፊነት መገመቻ ነው፡፡

አንዳንድ የመገጣጠሚያ ህመሞች ጧት ሰላም ሆነው ቀኑ እየገፋ ሲሄድ የሚባባሱ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በተቃራኒው ቀን ምንም ሳይሉ ሌሊት አያስተኙም፡፡ ህመሙ የተስተዋለበት ፍጥነትም በተመሳሳይ ሁኔታ ለህመሙ መሰጠት የሚገባውን ትኩረት ያመላክታል፡፡ የሚያባብሱ ሁኔታዎች በእርግጥ በአካል ላይ የሚደርሱ አደጋዎች የመገጣጠሚያ ህመሞች ብቸኛ መነሻ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በሌላ የሰውነት ክፍል ላይ የተስተዋሉ ቁስለቶች፣ ህመሞች ወዘተ፤ ከህመሙ በፊት የነበረው ያጠቃላይ የሰውነት እንቅስቃሴ ይሄን ለመገመት ያስችላል፡፡ በዘር የሚተላለፉ የመገጣጠሚያ ህመም መነሻዎችም እንዳሉ ማስታወሱ የግድ ነው፡፡ በእህት፣ ወንድም ብቻ ሳይሆን በብዙ ዘመዶችም የሚስተዋል ሊሆን ይችላል፡፡ አጠቃላይ የአካል ክፍሎችን መመርመር ለምሳሌ ትኩሳት፣ ቁስለት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የሆድ ቁርጠት፣ እንዲሁም የዓይን ህመም መኖር አለመኖሩን መርምሮ ማወቅ መሰረታዊ ነው፡፡ መገጣጠሚያዎች ሊያብጡ፣ሊቀሉ፣ ሲነኩ የህመም ስሜት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ የመገጣጠሚያ አካላቱ ከትንሽ ጀምሮ አስከ መካከለኛ ከዚያም ሲብስ ባጠቃላይ አካላትን ማንቀሳቀስ ሊያቅት ይችላል፡፡ የመገጣጠሚያ እብጠት ወይም ህመም መነሻ የሆኑ ብዙ የሰውነት ክፍል ህመሞች ስላሉ አነዚህን የአካል ክፍሎች ያማከለ ምርመራ ማድረግ ይገባል፡፡ (ለምሳሌ የሳንባ፣ የልብ፣ የአንጀት ወዘተ) በባለሙያ በሚታዘዙ ምርመራዎች በመገጣጠሚያዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት መጠን ወይም ዓይነት ማወቅ ይቻላል፡፡ የራጅ ምርመራ እንዲሁም የተለያዩ የደም ምርመራዎች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ ከመገጣጠሚያ እባጮችም ፈሳሽ ተቀድቶ የላቦራቶሪ ምርመራ ይደረጋል፡፡

 

ህክምና እንግዲህ ታማሚው በሚናገረው፣ በአካላዊም ይሁን በሌላ ምርመራ በሚገኘው ውጤት መሰረት የተለያዩ ህክምናዎች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ በመሰረቱ ለመገጣጠሚያ ህመም የሚደረግ ህክምና ዓላማዎች ህመም(ቃንዣ) ለመቀነስ፣ የተጎዳውን መገጣጠሚያ ስራ ለማሻሻል እንዲሁም የመገጣጠሚያ ህመም የጎንዮሽ ጉዳትን ለመቀነስ ነው፡፡ በአብዛኛው (ለማስታወስ ያህል ከመቶ ያላነሱ ምክንያቶች ስላሉት) መነሻ ምክንያቱን ማዳን ይከብዳል፡፡ ያኗኗር ዘይቤን ማሻሻል /መለወጥ/ እርስዎ መገጣጠሚያዎትን ካመመዎት ከህክምና ባለሙያ ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት አጥንት እና መገጣጠሚያ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማስታገስ ብዙ መፍትሄዎችን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ለማጠፍ ለመዘርጋት ያስቸገረ መገጣጠሚያን፣የህመም እና የድካም ስሜቱን ለማስታገስ የጡንቻን እና የአጥንትን ጥንካሬ ለማሻሻል እንቅስቃሴ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ ሊደረግ የሚገባው የእንቅስቃሴ ዓይነት እንደ ተጎዳው አካል ይለያያል፡ ፡ ለማጠፍ ለመዘርጋት፣ለጥንካሬ ወዘተ፡፡

ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ እንደ ህመሙ አይነት ሊመከሩ የሚችሉበት አጋጣሚም ይኖራል፡፡ በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ የተጎዳውን መገጣጠሚያ አንድ ቦታ ላይ ለረዥም ጊዜ አለማቆየት ፣ በእንቅስቃሴም ይሁን በሌላ አጋጣሚ የተጎዳው መገጣጠሚያ ላይ ጫና አለማሳረፍ እና የመሳሰሉት ለህመሙ በጊዜ መሻር የራሳቸውን አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ ለፈውስ ወይም ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት የተለያዩ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ፡፡ አንድ ጊዜ የታዘዙ መድሃኒቶችን በራስ ተነሳሽነት እየገዙ ከታቀደለት ጊዜ በላይ መጠቀም መጥፎ ነው፡፡ እንደሚታወቀውም ያለ ባለሙያ ትዕዛዝ የሚወሰዱ ብዙ የዕውነትም ጥሩ መድሃኒቶች ቢኖሩም ሊያስከትሏቸው የሚችሏቸው ብዙ ችግሮች ስላሉ ከመውሰድዎ በፊት ባለሙያ ያማክሩ፡፡ ለማንኛውም መድሃኒትዎትን ባለሙያ ባዘዘው ልክ ላዘዘው የጊዜ ርዝማኔ ያህል ብቻ ይውሰዱ፡፡ ሌሎች የሚወስዷቸው መድሃኒቶችም ካሉ ለሚከታተለዎት ባለሙያ ያሳውቁ፡፡ ለአንዳንድ የመገጣጠሚያ ህመሞች ሌሎች የህክምና አማራጮች ካልተሳኩ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልግበት አጋጣሚም አለ ፡፡ በመገጣጠሚያዎች ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለመቀነስ ሳይዘገዩ ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡ ፡ ስለሆነም ከሚከተሉት የህመም ስሜቶች አንዱን ካስተዋሉ ባለሙያ ከማማከር አይቦዝኑ፡-

• የመገጣጠሚያ ህመምዎ ከ3 ቀናት በላይ ከቆየብዎት

• ሊገልፁት የማይችሉት ህመም ካለብዎት

• መገጣጠሚያዎትን ማንቀሳቀስ ካልቻሉ

• የታመመው መገጣጠሚያ ቆዳ ከቀላ፣ ከሞቀ

• ትኩሳት ካለብዎት እንዲሁም ክብደት ከቀነሱ ወዘተርፈ ባለሙያ ያማክሩ፡፡ በቸር እንሰንብት!!!

 

Source: Enku Magazine

Sport: የምርጥ ስብዕና ባለቤት የሆነው –ሁዋን ማታ

$
0
0

 

በማንችስተር ከተማ ፉትቦል ሆቴል ሁዋን ማታ ኦልድ ትራፎርድ እና የሰር ማት በስፒን ጎዳና እየቃኘ ተመስጧል፡፡ በቅርቡ 28ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከበረው ስፔናዊው አማካይ እግርኳስን በደስታ ስሜት ውስጥ ሆኖ እየተጫወተ ይገኛል፡፡

Juan matta

እግርኳስ ተጫዋቾች በዚህ ወቅት የሚያገኙት ደመወዝ ከፍተኛ ነው ሲባል እርሱ ግን ይሄንን አመለካከት የሚቀይር አስተያየትን ይሰጣል፡፡ ማታ በኦልድ ትራፎርድ ሳምንታዊው 150 ሺ ፓውንድ ማግኘቱ ከከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋቾች መሀከል አንድ ቢያደርገውም እርሱ ግን ያን ያህል የተደነቀ አይመስልም፡፡

‹‹ከቀሪው ማህበረሰብ አንፃር የሚከፈለን ክፍያ በጣም ትንሽ ነው›› የሚል አስተያየትን የሚሰጠው ማታ፣ ‹‹ነገሩ ተጋንኖ መቅረቡ ተገቢ አይደለም›› በማለት ይናገራል፡፡

በመንገድ ላይ እግርኳስ የሚከፈለን ክፍያ በጣም ትንሽ ነው›› የሚል አስተያየትን የሚሰጠው ማታ፤ ‹‹ነገሩ ተጋንኖ መቅረቡ ተገቢ አይደለም›› በማለት ይናገራል፡፡

በመንገድ ላይ እግርኳስ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ግሎባል አምባሳደር መሆኑ ደግሞ ምን ያህል ለእግርኳስ የቀረበ ስሜት እንዳለው ማረጋገጫ ነው፡፡ ማታ ነገሮችን የሚመለከተው በጣም በጥልቀት ነው፡፡

የምርጥ ስብዕና ባለቤት የሆነው የቀድሞው የቫሌንሲያ ኮከብ በሜዳ ውስጥ ደግሞ እግርኳስን ውብ አድርጎ መጫወት ይችልበታል፡፡ አማካዩን የእግርኳሱ ዓለም በከፍተኛ ክፍያ ያበደ ነው? የሚል ጥያቄ ስታነሱበት በጣም በተረጋጋ ስሜት ውስጥ ሆኖ ‹‹የምሰጠው አስተያየትን የመሰለኝን እንጂ ምላሽ ለማግኘት ፈልጌ አይደለም፤ ስለ እግርኳስ እና ህይወት ስጠየቅ የመሰለኝን ምላሽ እሰጣለሁኝ፡፡ እግርኳስን በጥልቀት እረዳለሁኝ፡፡ ይሄንን ስፖርት በሚገባ እረዳለሁኝ፤ ህይወቴን እወደዋለሁኝ፡፡ እግር ኳስን መጫወትም ያስደስተኛል፤ እግርኳስ ተጨዋቾች የሰው ልጆች ናቸው፤ ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ሰብዕና አለው፤ ሁላችንም የራሳችን የሆነ እይታ አለን፡፡ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የምገኝ ተጨዋች እንደሆንኩኝ አላውቅም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ራሴን መሆን እፈልጋለሁኝ፡፡ የምሰጠው አስተያየት ምላሽ ካለው ምክንያቱ አስተያየቱ የተለየ በመሆኑ ሊሆን ይችላል›› የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

ማታ ባለፈው ሐሙስ በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል የልደት በዓሉን ኬክ በመቁረስ ሲያከብር ከቆየ በኋላ ምሽት ላይ ከቡድን ጓደኞቹ ጋር ራት ለመመገብ ወደ ማንቸስተር ከተማ ወጣ ብሏል፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ወደ ማንቸስተር ከተማ ወጣ ብሏል፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሉዊ ቫን ሃል ወደ ዋናው ቡድን ያሳደጓቸው ተጨዋቾች ስጋት ቢሆንም ግን ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓ እና ዓለም ዋንጫ ያነሳው ማታ በቀጣይ አቅሙን አውጥቶ በመጠቀም በቋሚነት መጫወት እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡

‹‹በቀጣይ የእግርኳስ ብቃቴ ጫፍ ላይ እንደምገኝ ተስፋ አደርጋለሁኝ›› ይላል በጃንዋሪ 2014 ከቼልሲ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ሲዘዋወር 37.1 ሚሊዮን ፓውንድ የወጣበት አማካይ፣ ‹‹ከ27-30 ዓመት የአንድ ተጨዋች የብቃቱ ጫፍ መገኛ ዕድሜ ነው፡፡ ከምንም በላይ በዚህ ዕድሜህ ከፍ ያለ ልምድ ታገኛለህ፤ ተደጋጋሚ ጨዋታዎችን ታከናውናለህ፤ በእግርኳስ ህይወቴ ጠንከር ያለ ጉዳት አለማስተናገድ በጣም ያስደስታል፡፡ በቀጣይ የተሻለ ብቃት ማግኘት እንደምችል ተስፋ አደርጋለሁኝ፡፡

mata juan

‹‹እስካሁን በተጫወትኩባቸው ክለቦች ቫሌሲያ እና ቼልሲ እንዲሁም ብሔራዊ ቡድን በዕድሜ ትንሹ እኔ ነበርኩኝ፤ በአሁኑ ሰዓት በ1995 እና 1996 የተወለዱ ተጨዋቾችን በቡድናችን ውስጥ እየተመለከትኩኝ ነው፡፡ እኔ የተወለድኩት ደግሞ በ1988 ነው፡፡ ይሄ የህይወቱ ጉዳይ ነው፡፡ እያወራን ያለነው ስለ እግርኳስ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ዕድሜዬ እየገፋ እንደሆነ አውቃለሁኝ፡፡

‹‹አሁን በምገኝበት ሁኔታ የእግርኳስ ህይወቴ መጠናቀቂያ ላይ እገኛለሁኝ ብዬ አላስብም፡፡ ምክንያቱም ሁልጊዜም ልምምድ እሰራለሁኝ፡፡ እጫወታለሁኝ፤ አስደሳች ህይወትን እየመራሁኝ እገኛለሁኝ፡፡ በልምምድ ሜዳ ላይ ጠንክሬ መስራቴ ተጠቃሚ አደርጎኛል፡፡

በማንቸስተር ዩናይትድ ህይወት ለማታ ቀላል ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስፔናዊው በቫን ሃል ሁለተኛ ዓመት ውጤታማ ለመሆን የተቸገረው ቡድን አባል በመሆኑ እያንዳንዱ ውጣ ውረድ ፍፁም አደጋች ነው፡፡ ለከርሞ በቻምፒዮንስ ሊጉ የሚያሳትፈውን ውጤት ለማግኘት እየታገለ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ በኤፍኤካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ሜይ 21 ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይጫወታል፡፡

ማታ በሌይስተር ሲቲ ብቃት በጣም ተገርሟል፡፡ ዘንድሮ የአሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒዮሪ ቡድኑ በማይዋዥቅ አቋም ስኬታማ ሆኗል፡፡ ስፔናዊው አማካይ ‹‹ሌይስተር ሲቲዎች ዘንድሮ በጣም ጥሩ ናቸው፡፡ የእነርሱ ሻምፒዮን መሆን ያን ያህል አስገራሚ አይደለም፡፡ በጣም መኩራት አለባቸው›› የሚል መረጃን ሰጥቶ፤ ‹‹እርግጥ ነው ይሄ የውድድር ዓመት ለእኛ ቀላል አይደለም፡፡ በተለይ ዲሴምበር እና ጃንዋሪ ላይ ተደጋጋሚ ሽንፈት አስተናግደናል፡፡ ነገር ግን እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ አይነት ትልቅ ክለብ ውስጥ ስትጫወት ሁሉም ነገር ፈታኝ ነው፡፡ ሆኖም ጫናውን በሚገባ መቋቋም ግድ ይልሃል፡፡ ተደራራቢ ጨዋታዎችን ስታሸንፍ ሁሉም ነገር አስቸጋሪ ነው፡፡ ቀሪዎቹን ጨዋታዎች በሙሉ በድል ይዘን እንፈፅማለን፡፡ ይሄንን አሳክተን ለጥቂት ዓመታት ያጣነውን የኤፍኤ ካፕ ዋንጫ ብናነሳ የስኬት ዓመት ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡ ይሄንን ዋንጫ ካነሳን 12 ዓመታት ተቆጥሯል›› ይላል፡፡

የጆዜ ሞውሪንሆ ስም ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር መያያዙን ተከትሎ ከስታምፎርድ ብሪጅ ለመሰናበት ምክንያት ስለሆኑት አሰልጣኝ ጥያቄ ስታስከትሉ፤ ‹‹በቀጣይ ሊሆን ስለሚችል ነገር ማውራት ፍትሃዊ አይደለም፤ ከፊታችን ወሳኝ ጨዋታዎች ይጠብቁናል፤ ይሄ ለአሰልጣኙ ክብር መንፈግ ነው፡፡ ይሄንን ጉዳይ ለማውራት ጊዜው አሁን አይደለም የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

 

 

Health: ስትሮክ ሊመታኝ ነው እያልኩ እየተረበሸኩ ነው፤ ምን ይሻለኛል?

$
0
0

የደም ግፊት በሽተኛ ነኝ፡፡ በተለያየ ጊዜ ብታከምም ልድን አልቻልኩም፡፡ አሁን አሁን ደግሞ በሽታው ለተለያዩ ህመሞች ያጋልጣል የሚል ወሬ ሰምቻለሁ፡፡ ታዲያ ከዚህ መሰል ችግር ራስን ነፃ ለማድረግ በየጊዜው ምርመራ ማድረግ እንዳለብኝ በዚሁ ህመም የ10 ዓመት ተሞክሮ ያለው አንድ ታካሚ ባልደረባዬ አጫውቶኛል፡፡ ለመሆኑ እንዴት አይነትና በየስንት ጊዜው መመርመር ይኖርብኝ ይሆን? የትስ ቦታ ብመረመር ይሻላል ትላላችሁ? ይኸው አንድ ቀን ያልሆነ ቦታ ሊጥለኝ ይችላል እያልኩ እየሰጋሁ ነው፡፡ በተለይ ትንሽ ድክም ሲለኝ፣ ራሴን ጭው ሲያደርገኝ፣ ድንገት እግሬ ከዳ ሲያደርገኝ ከአሁን አሁን ስትሮክ ሊመታኝ ነው እያልኩ እረበሻለሁ፡፡ ስለዚህ መልሳችሁን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡
መሐመድ ነኝ

ask your doctor zehabesha

ውድ ጠያቂያችን መሐመድ በእውነቱ ከህመሙ በላይ የጎዳህ ጭንቀትህ ይመስለኛል፡፡ ስትሮክ ሳይከሰትብህ በየቀኑ በራስህ ጭንቀት ራስህ ላይ እየጠራኸው ነው፡፡ የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል እንደሚባለው ጥንቃቄ በሚገባ መተግበር እንጂ ትንሽ እንከን በተሰማህ ቁጥር መበርገጉ ራሱን የቻለ ህመም ነው፡፡ ከደም ግፊት የልቅ የጭንቀት ግፊቱ የበዛብህ ነው የሚመስለው፡፡

ውድ ወንድማችን መሐመድ ከድር መቼም አንድን ህገወጥና ተቀባይነት የሌለውን ድርጊት የፈፀመ ወንጀለኛ መንጥሮ ለማውጣት ፖሊሲው ምርመራ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም፡፡ ድርጊቱን የፈፀመውም እጁን ካልሰጠ በቀር ታዲያ ፈልጎ ለማግኘት ብዙ ጥረትን ይጠይቃል፡፡ ከቀላል የምስክር ቃል የሚጀምረው ይህ ውስብስብ ምርመራ እስከ ዲኤንኤ ምርመራ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ይህ እንግዲህ የፖሊሶችን ጥልቅ ምርመራ ይመለከታል፡፡ ለከፍተኛ ደም ግፊትስ?

ከፍተኛ ደም ግፊትን ያክል በቀላል የማይታይ በደል በአንድ ሰውም ላይ ሲፈፀም ከከባድ ወንጀል ተነጥሎ የማይታይ ነውና ምርመራው እስከ ወዲያኛው ድረስ ሳይቋረጥ ሊቀጥል ይችላል፡፡ የምርመራው አብይ አላማዎችም ሁለት ናቸው፡፡ አንዱ ህመሙን ያስከተለው ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ/ወንጀል ፈፃሚው መሆኑ ነው/ ሲሆን ሌላው ደግሞ ህመሙ በራሱ ከተከሰተ በኋላ በሌላው የአካል ክፍል ላይ ያደረሰው አደጋ ካለ ለመለየት ነው፡፡ የህመሙ መንስኤ ከተገኘ መንስኤውን በማስወገድ ህመሙን ማስወገድ ወይም ማስተካከል እንዲቻል ያግዛል፡፡ ምርመራው በሌላ የሰውነት ክፍሎች የማስተካከያ እርምጃ/ተግሳፅ/ ለመውሰድ ወሳኝ ይሆናል ማለት ነው፡፡

የምርመራውን ጥቅምና አስፈላጊነት በአጭሩ እንዲህ ከተረዳን ታዲያ እንደ አንተ ያለ ግለሰብ በሐኪም የሚያደርግለት ወይም ሊደረጉለት የሚገቡ ምርመራዎች የትኞቹ ናቸው? ላልከው ጥያቄ እንዲህ አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

1. የደም ሴሎች ምርመራ (CBC Count)፡- ይህ ምርመራ የቀይ የደም ሴሎች፣ የነጭ የደም ሴሎችና የፕላትሌቶች ቁጥርን ማወቂያ ሲሆን ጤናማ ቁጥር እንዲኖራቸው ይጠበቃል፡፡

2. የሰውነት ማዕድን ምርመራ (Serum Electrolytes)፡- ሰውነታችን ውስጥ በፔሬዲክ ቴብል ውስጥ ካሉት ከ110 በላይ ማዕድኖች (Elements) ውስጥ የማይገኙት ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ በዋናነት ግን የደም ውስጥ ሶዲየም፣ ክሎራይድ፣ ፖታሲየም፣ ካልሲየም፣ ፎስፎረስ ጤናማ መጠን እንዲኖራቸው ይጠበቃል፡፡

3. የኩላሊትን ጤናማነት መለያ ምርመራ (Renal Function Tests or RFT)፡- ከፍተኛ ደም ግፊትን በማስከተል ረገድ አንዱ ምክንያት ኩላሊት ሊሆን ሲችል ከፍተኛ ደም ግፊትም በራሱ በኩላሊት ላይ ጫና በማድረስ በመጨረሻ ለኩላሊት ድክመት ያጋልጣል፡፡ በመሆኑም የኩላሊትን ጤናማነት ከምንለይባቸው የደም ምርመራ አይነቶች ውስጥ ‹‹ክሬያቲኒን›› እና ‹‹ዩሪያ›› ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እንዲሁም የኩላሊትን አካላዊ ጤናማነት ለመመልከት ልዩ የኩላሊት ራጅ ምርመራ (IVP RENAL ANGIOGRAPHY) ሊያስፈልጉ ይችላሉ፡፡

4. የደም ስኳር መጠን (Blood glucose test):- ከፍተኛ ደም ግፊትና ስኳር ህመም 50 በመቶ በሆነ ዕድል በጣምራነት የሚከሰቱ ህመሞች ናቸው፡፡ በመሆኑም ለየትኛውም የደም ግፊት ህሙማን የደም ስኳር ጤናማነቱ መታየት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡

5. (Urinalysis)፡- ይህ ምርመራ በሽንት ውስጥ የሚኖሩ ኬሚካላዊ ለውጦችን የሚቃኝ ሲሆን በዋናነትም ‹‹albumen›› እና ‹‹glucose›› ለማየት ያግዛል፡፡ በሽንት ምርመራ በተለይ ‹‹albumen›› ከታየ የኩላሊት ህመም መከሰቱን ይጠቁማል፡፡

6. (Lipid Profile):- በምግባችን ይዘት ከፊል ካርቦሃይድሬት፣ ከፊል ፕሮቲንና ከፊል ቅባት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ካርቦሃይድሬትና ፕሪቲን ባመዛኙ ወደ ግሉኮስነት /ስኳርነት/ በመቀየር ለሰውነት የኃይል ምንጭ ሲሆኑ የቅባት ምግቦች ደግሞ ወደ ትራይግሊስራይድስ /ቅባትነት/ በመለወጥ ነው ለኃይል ምንጭነት የሚጠቅሙት፡፡ ከፍተኛ የደም ቅባት ክምችት መኖር ለከፍተኛ ደም ግፊትና ስኳር ከማጋለጡም አልፎ ተርፎ የህመሞቹን አደጋም ይጨምራል፡፡ በመሆኑም የእነዚህን የቅባት ክምችቶች ከምናውቅባቸው የምርመራ አይነቶች ‹‹total cholesterol, low density lipoprotein (LDL), High density lipoprotien (HDL) and Triglycerides›› ተጠቃሽ ናቸው፡፡

7. የታይሮይድ ዕጢ ምርመራ፡- ታይሮይድ ዕጢ የሰውነትን አጠቃላይ አሰራር /ሜታቦሊዝም/ በበላይነት የሚቆጣጠር ሲሆን ከዚህ አብጥ ስራውም ከወትሮ ከፍ ወይም ዝቅ ካለ ለደም ግፊት ህመም ያጋልጣል፡፡ ስለሆነም የዚህን ዕጢ አሰራር የሚጠቁሙ ምርመራዎች እንዳስፈላጊነቱ ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ እነሱም (T3/T4 and TSH) በመባል ይታወቃሉ፡፡

8. የልብ ምርመራ፡- ከፍተኛ ደም ግፊት ተፅዕኖ ከሚያሳድርባቸው የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ልብ ግንባር ቀደም ተጠቃሹ ነው፡፡ በመሆኑም የልብን ጤናማነት ከሚያሳውቁ ምርመራዎች ውስጥ ‹‹ኢሲጂና ኢኮካርዲዮግራፊ›› ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይ በኢኮካርዲዮግራፊ ምርመራ የግራው የልብ ክፍል ላይ ችግር ከታየ ለደም ግፊት ህመሙ ወዲያው መድሃኒት እንዲጀምር ያስገድዳል፡፡

9. የዓይን ምርመራ፡- ይህ ምርመራ ደም ግፊት በዓይን ካሜራ ክፍል ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመለየት የሚያግዝ ሲሆን አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄያዊ እርምጃ ለመውሰድም ይጠቅማል፡፡

ውድ ወንድማችን መሐመድ ከድር መቼም እንደህመም ተቆጥሮ የማይታከም ነገር ቢኖር ፍቅር ብቻ ነው ይባል እንጂ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ግን ራሱንየቻለ ህክምና ያለው ነው፡፡ ያውም ከአንድ አይሉ ብዙ አይነት ህክምናዎች አሉት፡፡ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር አይደል የሚባለው፡፡ ምንም እንኳን መቶ በመቶ ባይፈውሱም፡፡ እናም ታዲያ አማራጩ ብዙ ነው፡፡

እንግዲህ የደም ግፊት ህመም አንድና አንድ የሆነ መድሃኒት የለውም፡፡ የሚዋጡም ሆነ የማይዋጡ መፍትሄዎች ያሉት ነው፡፡ ካለ መድሃኒት አስፈላጊነት የሚታከም የደም ግፊት ህመም አለ፡፡ በአንድ አይነት መድሃኒት ብቻም ይሁን ከአንድ በላይ ጣምራ መድሃኒቶች የማያስፈልጉትም የደም ግፊት ህመም አለ፡፡ ሁሉም እንደየአይነታቸው ህክምናቸው ይለያያል፡፡ የሀገሩን በሬ በአገሩ ሰርዶ እንዲሉ፡፡

መድሃኒት ሁሉ እንደስሙ አይደለም፡፡ የራሱ የሆነ ጉዳትም አለው፡፡ ጉዳቱ ከጥቅሙ ስለሚያንስ ግን እንወስደዋለን፡፡ ከመድሃኒት ሌላ መዳኛ ወይም በሽታውን ማስተካከያ መንገድ ካለ ግን መድሃኒቱን ለመውሰድ በጨረታው አንገደድም፡፡ የግድ መወሰድ ካለበት ወይም አማራጮች ከሌሉ ግን የጎንዮሽ ጉቱን ተቀብለን እንወስደዋለን፡፡ ነገሮች እንዲህ ከመሰሉ ታዲያ የደም ግፊት መጠንህን በአመጋገብ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስተካከል አንዱ መላ ሲሆን ነገር ግን በመድሃኒት የግድ መታከም አለባቸው የሚባሉ ህመምተኞች የሚከተሉት ናቸው፡፡

የታችኛው የግፊት መጠን ከ90mmhg ቢሆንም የግድ ህክምናው ያስፈልገዋል፡፡

አንድ የደም ግፊት ህመም ታካሚ የግፊት መጠኑ እስከ 140 በ90 mmhg ዝቅ እንዲያደርግ ይመከራል፡፡ ለሁሉም አይነት ህሙማን ግን አይደለም፡፡ አንድ ደባል የስኳር ህመም ያለበት ሰው የደም ግፊት መጠኑ እስከ 130 በ85 mmhg ያህል እንዲወርድ ይመከራል፡፡ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንዳመለከቱትም የትኛው /ዲያስቶሊክ/ የግፊት መጠን ከ90 mmhg እንዳይበልጥ ተደርጎ ቁጥጥር ስር ከዋለ በህመሙ የመሞት ዕድሉ እጅግ አናሳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በተለይ ደግሞ የላይኛውን የግፊት መጠን 120 mmhg ላይ ካደረስከው እጅግ የተዋታለት ቁጥጥር በመባል ይጠራል፡፡

ስለሆነም ወንድማችን ከላይ የተጠቀሱት ምርመራዎች በተለይ ከልብና ከዓይን ምርመራዎች ውጭ በየትኛውም ቦታ የሚታዩ ናቸው፡፡ የምርመራ ጊዜው እንደ ህክምና ታሪክህና ዕድሜህ የሚወሰን በመሆኑ ከሐኪምህ ጋር ቀርበህ ተነጋገርበት፡፡ እነዚህ ምርመራዎች እንዳስፈላጊነቱ ሊደረጉ የሚችሉ እንጂ ለሁሉም የግድ ሊደረጉ የሚገባቸው ናቸው ለማለትም ስላልሆነ የትኞቹ መቼ ሊደረጉ እንደሚገባ ሐኪምህ የበለጠ ግልፅ ሊያደርግልህ ይችላል እላለሁ፡፡ በተረፈ አላህ ከስትሮክ የፀዳ አስተሳሰብ ይስጥህ እያልኩ ልሰናበትህ፡፡

Viewing all 384 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>