Quantcast
Channel: ጤና – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 384 articles
Browse latest View live

Health: ከባድ ላብ የጤና ነው? | Hyperhidrosis

$
0
0

Lab

ዶክተር ዓብይ ዓይናለም | ለዘ-ሐበሻ ጤና ዓምድ

<<ከፍተኛ የሆነ የላብ ችግር አለብኝ፡፡ ብብቴ ውስጥ፣ በግንባሬ ላይ በተለይም በመዳፌ ላይ እንደ ውሃ ይቀዳል፡፡ እግሬም እንደዚሁ በጣም ያልበኛል፡፡ ከሰው መቀላቀል ትቻለሁ፡፡ እባካችሁን ከዚህ እግር ከወርች ከያዘኝ የከባድ ላብ ችግር መፍትሄ ካለ ጠቁሙኝ፡፡>> ሲል አንድ የዘ-ሃበሻ አንባቢ በስልክ ያቀረበልንን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ጉዳዩን የዛሬ የጤና አምዳችን ጉዳይ አድርገነዋል፡፡

ላብ ሰውነታችን ራሱን የሚያቀዘቅበት ተፈጥሯዊ መንገድ ነው፡ ፡ አብዛኛው ይህ ሁኔታ ተፈጥሯዊ እና የጤንነት ምልክት ነው፡፡ አ ንዳንድ ሰዎች ግን ተደጋጋሚ እና የማያቋርጥ ላብ ይታይባቸዋል እ ና ይህ ሁኔታ በህክምና ቋንቋ ሃይፐርሃይድሮሲስ/Hyperhidrosis/ ይባላል፡፡

ሃይፐርሃይድሮሲስ/ከባድ ላብ/ በላብ ዕጢዎች የሚመረተው ላ ብ ሰውነት ራሱን ለማቀዝቀዝ ከሚፈልገው በላይ ነው፡፡ ይህ በሽታ በ አብዛኛው መዳፍንና የእግር ስርን እና ብብትን ያጠቃል፡፡ የዕለት ተዕ ለት ስራን ከማወኩም በተጨማሪ ከባድ ላብ ማህበራዊ ጭንቀት እና የመሸማቀቅ ስሜት ብሎም ራስን ማግለል ሊያስከትል ይችላል፡፡

ጥሩው ነገር ግን ይህንን ችግር ለማከም የተለያዩ ዘዴዎች መኖራ ቸው ነው፡፡ ከባድ ላብ እጅግ ከባድ ሲሆን እስከ ቀዶ ጥገና የሚያደር ስ ህክምና አለው፡፡ ምንም እንኳን መቼ የት እና ምን ያክል ያልበናል የሚለው በስፋት ቢለያይም አብዛኛው ሰው ከበድ ያለ የጉል በት ስራ ሲሰራ፣ ሞቃታማ ቦታ ሲሆን፣ ድንጋጤ ወይም ጭ ንቀት እና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲሆን ያልበዋል፡፡ ከባድ ላብ ሃይፐርሃይድሮሲስ ያለበት ሰው የላብ ሁኔታ ግን ከላይ ከ ተጠቀሰው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው፡፡

የከባድ ላብ ዋና ዋና ምልክቶች ቶሎ ቶሎ መምጣቱ የሚ ታይ ከሚገባው በላይ የሆነ እና ብብትን የሚያበሰብስ ሲሆን ነው፡፡ ከሚገባው በላይ የሆነ የሚያስጨንቅ የላብ መኖር በ ተለይም በእግር ስር፣ በብብት፣ በራስ እና በፊት ላይ የሚታ ይ ሲሆን፣ የቆዳ ማጣበቅ ወይም ከእጅ መዳፍና ከእግር መር ገጫ ጠብ ጠብ የሚል ላብ ሲታይ ነው፡፡

ሃይፐርሃይድሮሲስ የሚለው ስያሜ የሚሰጠውን የተቸ ጋሪውን የዕለት ተዕለት ስራን የሚያደናቅፍ ከፍተኛ የላብ መ ጠን/ከባድ ላብ ሲኖር ነው፡፡ ይህ ክስተት ያለ ምንም በቂ ም ክንያት ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ይታያል፡፡ ለእነዚህ ሰዎ ች ከባድ ላብ የማህበራዊ ህይወትን ያውክባቸዋል፡፡

እጃቸው ያለማቋረጥ ስለሚረጥብ ስራ መስራትም ሆነ መዝናኛ ቦታ ራሳቸውን ማዝናናት ይሳናቸዋል፡፡ በዚህም ም ክንያት ከሰው ጋር ሲጨባበጡ በእጃቸው ላብ ምክንያት እ ና ሸሚዛቸው የላብ ቅርፅ ስለሚያሳይ አንዳንዴ ላቡ ጠረን ስለሚኖረው በዚህ በሚፈጠርባቸው መሸበር ራሳቸውን ከ ሰው ያገላሉ፡፡

እንደዚህ ያለ ችግር ያለበት ሰው ከተለመደው በላይ ድ ንት ከፍ ያለ ላብ ሲያይ፣ ላብ የዕለት ተዕለት ስራውን ሲያደ ናቅፍበት፣ እና የሌሊት ላብ ያለ በቂ ምክንያት ሲኖረው ሐኪ ም ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የብርድ ላብ የታየበት ማንኛ ውም ሰው ሐኪም ዘንድ መቅረብ አለበት፡፡ በተለይም ደግ ሞ ሁኔታው ከጭንቅላት ቅል መቅለል እና የደረት ወይም የ ሆድ ህመም ስሜት ጋር አብሮ ከመጣ የልብ በሽታ፣ የጭንቀ ት ወይም የሌላ ከፍተኛ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊ ዜ ሊሰጠው አይገባም፡፡

የከባድ ላብ ምንጩ ሰውነታችን ሙቀቱን ከሚቆጣጠርበት የቁጥጥር ስርዓት ይመነጫል በተለይ ደግሞ የላብ ዕጢዎች ቆዳችን ሁለት አይነት የላብ ዕጢዎች አሉት፡፡ አንደኛው ኢክራይን ዕጢ ሲባል ሌላኛው ደግሞ አፓክራይን ዕጢ ሲባል ሌላኛ ው ደግሞ አፓክራይን ዕጢዎች ይባላሉ፡፡ ኢክራይን ዕጢዎች በአብ ዛኛው ሰውነታችን ውስጥ ሲገኙ በቀጥታ አፋቸው ወደ ቆዳ ላይኛው ክፍል ይከፈታል፡፡ አፓክራይን ዕጢዎች ግን የሚገኙት በብዛት ፀጉር በሚሸፍናቸው የቆዳ ክፍሎች ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ የራስ ቅል፣ ብብት እና ጭገር አካባቢ ነው፡፡

የሰውነታችን ሙቀት ሲጨምር አውቶኖሚክ ነርቨስ ሲስተም የ ተባለው የአዕምሮ ክፍል እነዚህን ዕጢዎች ላብ ወደ ቆዳ የላይኛው ክፍል እንዲለቁ ያደርጋል፡፡ ላቡም ሰውነታችንን ከቀዘቀዘ በኋላ ይ ተንና ቆዳችን ይደርቃል፡፡ ይህ ላብ በውስጡ በአብዛኛው ውሃ እ ና ጨው ይይዛል አልፎ አልፎ ደግሞ ሌሎች ኬሚካሎችም በተጨ ማሪ ይይዛል፡፡

ከባድ ላብ በአንድ ቦታ የተወሰነ ወይም ጠቅላላ ወይም በርካታ ሰውነታችንን የሚያካትት /generalized hyperhidrosis/ በመባል ይከፋፈላል፡፡ የመዳፍና የእግር ከባድ ላብ በአብዛኛው ቀን ቀን የሚ ከሰት ነው፡፡ አንዳንዴም በብብት አካባቢም ይታያል፡፡ ይህ ላብ ሌሊ ት በአመዛኝ አይታይም፡፡ በሁለቱም የሰውነታችን ክፍል በእኩል መ ልኩ ይታያል፡፡ ይህ አይነት ከባድ ላብ ወደ ሃያው የዕድሜ ክልል አ ካባቢ በአብዛኛው ይጀምራል፡፡ ከሌላ በሽታ ጋር ግንኙነት የሌለውና ራሱን የቻለ ችግር ነው፡፡ ትክክለኛው ምክንያት ወይም መነሻ ገና አይታወቅም፡፡ ነገር ግን በዘር የመምጣት አዝማሚያም ይኖረዋል፡፡ በርካታ የሰውነት ክፍልን የሚያጠቃው የከባድ ላብ ችግር አይነ ት በድንገት የሚጀምር ነው፡፡ በርካታ የሰውነት ክፍልን ያጠቃል፡፡ በ አብዛኛው ሌላ ምክንያት አለው፡፡ ለምሳሌ የመድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳ ት፣ የበሽ ምልክት፣ የማረጥ ምልክት፣ የስኳር መጠን በደም ውስጥ ዝ ቅ ማለት፣ የታይሮይድ በሽታ፣ የደም ካንሰር በሽታ፣ የልብ ድካም በሽ ታ ወይም የአንድ ወይም የሌላ ኢንፌክሽን በሽታ ምልክት ሊሆን ይ ችላል፡፡ በዚህ ጊዜ አስፈላጊውን መድሃኒት በመውሰድ ወይም መንስ ኤውን በሽታ በማከም ላቡን ያጠፋዋል፡፡

በከባድ ላብ መንስኤነት የሚመጡ በርካታ የአካልና የስነ ልቦና ች ግሮች መካከል የፈንገስ ኢንፌክሽን፣ በባክቴሪያ ምክንያት የቆዳ እና የቆዳ ፀጉር አካባቢ ኢንፌክሽን በእግር ጣቶች አካባቢ የሚመጡ ኢ ንፌክሽኖች፣ የጎዳ ኪንታሮት /warth/ በሽታ ወይም ኪንታሮት ሲታ ከም ቶሎ ያለመዳን ችግር፣ በቆዳ ላይ በሙቀት የሚመጡ ሽፍታዎች መብዛት፣ እና ማህበራዊ መገለል ከላይ እንደተጠቀሰው ግለሰቡ ራሱ

ጥ መግባት አንባቢያን ማደናገር ነው፡፡ ይህም ዘዴ እንደየሁኔታው ባ ደጉ ሀገራት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ለአንዳንድ ከባድ ላብ ላላባቸው ሰዎች መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ ከፋርማሲ በሚገዛ ላብ መከላከያ ሊቆም ይችላል፡፡ እነዚህ የላብ ማቆ ሚያ መድሃኒቶች የላብ መተላለፊያ መንገዶችን በመዝጋት ይህንንም በአልሙኒየም ጨው አማካኝነት ወደ ቆዳ የሚደርሰውን የላብ መጠ ን ይቀይሳል፡፡ ማስታወስ ያለብን ላብ መከላከያ ላብ ሲከላከል ዲኦራ ንት ደግሞ የላብን መጥፎጠረን ብቻ ነው የሚከላከለው፡፡

ከላብ መከላከያ በተጨማሪ የሚከተሉትን ማድረግ ላብን ለመቀ ነስና ከላብ ጋር ለተያያዙ የሰውነት መጥፎ ጠረን ጠቃሚ ነው፡፡

1. ቢቻል በየቀኑ መታጠብ ይህ በቆዳችን ላይ ያሉ ባክቴሪያዎ ችን ይቀንሳል

2. ከመታጠብ በኋላ እግርን በፎጣ በደንብ ማድረቅ፡፡ ይህም ን ማግለል የመጀመር ሁኔታ ይታያል፡፡

በከባድ ላብ ምክንያት ወደ ሐኪም ዘንድ ሲቀርቡ ሐኪሙ የተ ለያዩ የበሽታ ታሪኮችን ይጠይቃሉ፡፡ የአካል ምርመራም ያደርጋሉ፡ ፡ የደምና የሽንት ምርመራ በማዘዝ በሽታው በምን ምክንያት እንደ መጣ ለማወቅ ይሞክራሉ፡፡ ከተገኘም ሐኪምዎ ቴርሞ ሬጉሌተር ቴ ስት ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

የተለያዩ ምርመራዎች ካደረጉ በኋላ ሐኪሙ የተለያዩ የህክምና ዘዴዎችን ሊጠቀም ይችላል፡፡ ሐኪምዎ እንደ አልሙኒየም ክሎራይ ድ የመሰሉ የመድሃኒት ይዘት ያላቸውን ሊይዙ ይችላሉ፡፡ ይህ መድ ሃኒት ከቀላል እስከ መካከለኛ ደረጃ ሃይፐርናይድሮሲስን ለማከም ወ ይም ለመቀነስ ይችላል፡፡ ይህ መድሃኒት ከተገኘ ጥሩ ውጤት ለማግ ኘት ላብ በሚበዛበት አካል ላይ ሌሊት ሌሊት ማድረግ ነው፡፡ መድሃ ኒቱ ቆዳን የማሳበጥ፣ የማቅላት እና የማሳከክ ፀባይ ያለው ጠንካራ ኬ ሚካል ነው፡፡ ይህንን ለመከላከል ጠዋት በደምብ ማጠብ ያስፈልጋ ል፡፡ በርካታ የሰውነትን ክፍሎች የሚያጠቃልል የላብ ችግር ከሆነ ሐ ኪምዎ አንቲ ኮለነርጂክ መድሃኒቶችን ሊይዙ ይችላሉ፡፡ ይህም መድ ሃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት፡፡ የቆዳ ሐኪሞች ደግሞ አዩንቶፎረሲ ስ በሚባል ዘዴ ያክሙታል፡፡ ከዚህም ሌላ በቶሊየም ቶክሲን የተባለ መድሃኒት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ ይህ ኬሚካል የተወሰኑ ጡ ንቻዎችን ፓራላይዝ በማድረግ የቆዳን የእርጅና ገፅታ ለማጥፋት ባደ ጉት ሀገሮች ጥቅም ላይ የሚውልበት ጊዜ አለ፡፡ይህም የሚደረገው ላ ብን በሚመለከት አዕምሮ ወደ ላብ ዕጢዎች የሚመጣውን የነርቭ ሂ ደት በማቋረጥ ነው፡፡ ወደዚህ ቀዶ ጥገና አሰራር ዝርዝር ሂደት ውስ ባክቴሪያዎች እና ሌላ ጀርሞች ለመራባት የሚያመቻቸውን እርጥበ ት ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም እርጥበት የሚመጥ ፓውደር መጠቀም ይቻላል፡፡

3. ከተፈጥሮ ማቴሪያል የተሰሩ ጫማ እና ካልሲ መጠቀም ከ ቆዳ የተሰራ ጫማ እግራችን አየር እንዲያገኝ በማድረግ የእግር ላብ ን ይቀንሳል፡፡

4. ጫማ ውስጡ ቶሎ ስለማይደርቅ እያቀያየሩ /በየቀኑ/ ማድረ ግ ላብ በብዛት ያለበት እግርን ችግር ይቀንሳል፡፡

5. የጥጥና የሱፍ ካልሲ በመጠቀም እግርን እርጥበት ስለሚመጥ በተለይ ደግሞ ሯጭ ሰው እርጥበት መጣጭ ስፔሺያል ካልሲ እንዲ ጠቀም ይመከራል፡፡

6. ካልሲን በየቀኑ መቀየር ቢቻል በቀን ሁለቴ በመቀየር ካልሲ በ ተደረገ ቁጥር ታጥቦ እና በደንብ እግርን እንዲደርቅ በማድረግ ተጨ ማሪ መፍትሄ ይሆናል፡፡

7. እግርን ማናፈስ ከተቻለ በባዶ እግር መሄድ ካልሆነም ቶሎ ቶ ሎ እግርን እያወጡ ማናፈስ (ቢቻል በቀን ለ30 ደቂቃ እግርን ከጫ ማ አውጥቶ ማናፈስ ቢቻል)

8. በአጠቃላይ የተፈጥሮ ክር ልብሶች መልበስ /የጥጥ የሱፍ እና የሀገር ልብሶች ሰውነት በቂ አየር እንዲያገኝ ያደርጋሉ/

9. አንድ ዮጋ፣ ሜዲቴሽን ወዘተ… የመሳሰሉ ዘዴዎችን በመጠቀ ም ጭንቀትን በማስወገድ የላብ መከሰትን መቀነስ ይቻላል፡፡

ስለዚህ ጠያቂያችን ከላይ የተጠቀሱትን በማድረግና መፍትሄ ካ ልሆኑ ወደ ሐኪም ዘንድ በመሄድ መፍትሄ መሻት ይመከራል፡፡


Health: ኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም (ሆርሞን) – ከወሲብ ፍላጎት ማጣት እስከ መካንነት (ከዶክተሩ ጋር የተደረገ ልዩ ቃለምልልስ)

$
0
0

 

 

የኤስትሮጅን ንጥረ ቅመም (ሆርሞን) ሴትነትን ከመወሰን በተጨማሪ በተለያየ መልክ የሚገለፅ ተፅዕኖ አለው፡፡ ይህ ሆርሞን በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው መጠን በላይ ሲመረት ወይም ዝቅተኛ ሲሆን፣ አልያም ጭራሹን ሳይመረት ሲቀር የተለያዩ የጤና ችግሮችን ያስከትላል፡፡ በኤስትሮጂን ሆርሞን (ንጥረ ቅመም) ምንነት፣ በጥቅሙ፣ እሱን ተከትለው በሚከሰቱ የጤና ችግሮችና በመፍትሄያቸው ዙሪያ አንድ የማህፀንና ጽንስ ስፔሻሊስትን አነጋግረንልዎታል፡፡

Making-Love

ጥያቄ፡ኤስትሮጂን ሆርሞን (ንጥረ ቅመም) ምንድነው? የሚመረተውስ እንዴት ነው?

ዶ/ር፡- ኤስትሮጂን ሆርሞን በሴቶች ሰውነት ውስጥ ከሚመነጩ ሆርሞኖች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ሆርሞን ጋር የመተጋገዝ ስራ የሚያከናውን ፕሮጀስትሮን የሚባል ንጥረ ቅመም አለ፡፡ እነዚህ ንጥረ ቅመሞች በስነ ተዋልዶ ጤና ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ናቸው፡፡ የምናተኩረው በኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም ላይ በመሆኑ፣ ይህ ንጥረ ቅመም በተፈጥሮ የሚመነጭ ነው፡፡ ሆርሞኑ E, E2 እና E3 ተብለው በሶት ይከፈላሉ፡፡ የሚመነጨውም በአብዛኛው በሴቶች የዕንቁላል ማፍሪያ ክፍል ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በእርግዝና ወቅት በእንግዴ ልጅ አማካኝነት፣ ንጥረ ቅመሙ የሚመረትበት ሁኔታ አለ፡፡ ሆርሞኑ የሚመረተው ሴቶች ለአቅመ ሔዋን ሲደርሱ ነው፡፡

በደም ውስጥ ከሚገኙ ቅባቶች አንዱ የሆነው ኮሌስትሮል፣ በተለያዩ አብላይ ኢንዛይሞች አማካኝነት በቅድሚያ አንድርስቶንና ቴስቴስትሮን ወደተባለ የወንድነት ሆርሞኖች ይለውጣል፡፡ ቀጥሎም የተለያዩ የኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም አይነቶች ይመረታል፡፡ የመመረት መጠናቸውም የአንዲትን ሴት የወር አበባ ዑደትን ተከትሎ ይለያያል፡፡ በተለይም በወር አበባ መምጫ 12ኛውና 13ኛው ቀን አካባቢና የሁለተኛው ወር አበባ ሊመጣ ሲል የኤስትሮጂን ምርቱ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የወር አበባን ለአራት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

  1. ደም የሚታይበት ጊዜ
  2. እንቁላል ከመውጣቱ በፊት ያለው ጊዜ
  3. እንቁላል የምትወጣበት ጊዜ እና
  4. እንቁላል ከወጣ በኋላ ያሉት ጊዜያት ተብለው በአራት ይከፈላሉ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የአስትሮጂን መጠን ከፍ የሚልበትና ዝቅ የሚልበት ሁኔታ አለ፡፡ መጠናቸውን በተመለከተ እንቁላል ሊወጣ ሲል 380 ማይክሮ ግራም ሲሆን፣ በሚቀጥለው የወር አበባ ጊዜ ደግሞ 250 ማይክሮ ግራም ዝቅ ይላል፡፡ መጠኑ ሲቀንስ እስከ 36 ማይክሮ ግራም ዝቅ የሚልበት ሁኔታ ይኖራል፡፡

አንዲት ሴት በፅንስ ላይ እያለች 7 ሚሊየን የሚሆኑ ዕንቁላሎች በተፈጥሮ ይኖሯታል፡፡ በውልደት ጊዜ የዕንቁላል መጠኑ ከ1 እስከ 2 ሚሊየን ዝቅ ይላል፡፡ ይህ ቁጥር ከውልደት በኋላ በየጊዜው እየቀነሰ በመሄድ፣ በ14ኛ ዕድሜዋ አካባቢ ከ300 እስከ 400 ሺ ይደርሳል፡፡ ወደ ጉርምስና ዕድሜዋ ስትገባ የኤስትሮጂን ሆርሞን በሚፈለገው መጠን መመረት ይጀምራል፡፡ ይህ ሁሉ ትዕዛዝ የሚመጣው ከአእምሮ ነው፡፡

አዕምሮ ውስጥ ሃይፓታለመስ እና ፒቱታሪ ግላንድ የሚባሉ ክፍሎች አሉ፡፡ ቀጥሎም የእንቁላል መስሪያው ክፍል አለ፡፡ እነዚህ ሶስት የአካል ክፍሎች በቅንጅት በመስራት፣ አዕምሮ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በጉርምስና ዕድሜ ላይ እንቁላል ጊዜውን ጠብቆ መምረት ይጀምራል፡፡ የተሟላ ጤንነት ላይ ያለች ሴት በየወሩ በግራ እና በቀኝ ሁለት እንቁላሎችን ታኮርታለች፡፡

የተመረተው እንቁላል እንደወጣ ከወንድ ዘር ፍሬ ጋር ከተገናኘ ፅንስ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ፅንስ ከሌለ የተዘጋጀው የማህፀን ግድግዳ፣ በሚቀጥለው 28 ቀን የንጥረ ቅመሞች ድጋፍ ስለማይኖረው ይፈርስና ደም ሆኖ ይወጣል፡፡ አንዲት ሴት በየወሩ መጠኑ ከ3 እስከ 80 ሚሊ ሊትር ሊሆን የሚችል የወር አበባ ታያለች፡፡ የወር አበባ ዑደቱ የሚከናወነው፣ በኤስትሮጅንና በፕሮስቴስትሮን ሆርሞኖች መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ይሆናል፡፡

 

ጥያቄ፡ኤስትሮጂን ከላይ ከተገለፁት ተግባራት ባሻገር ሌሎች ጠቀሜታዎች ካሉት ብናይ?

ዶ/ር፡- ኤስትሮጂን የሚባለው ንጥረ ቅመም፣ የወር አበባ ዑደትን የተሳካ ለማድረግ ከሚሰጠው ጠቀሜታ ባሻገር ሌሎች ጥቅሞችም አሉት፡፡ ዋና ዋና የሚባሉትን ቀጥለን እናያለን፡፡

– በጡቶቿ ላይ በጉርምስና ዕድሜዋ ላይ ለውጦች እንዲመጡ ያደርጋል፤

– በጡት ውስጥ የወተት ማምረቻ ቧንቧዎች እንዲወፍሩና እንዲበዙ ያደርጋል፤

– የጡት ጫፍ ጥቁር እንዲልና የተለየ ቀለም እንዲኖረው የሚያደርግ ነው፤

– በብብትና በብልት አካባቢ ፀጉር እንዲወጣ የሚያደርግ ነው፤

– የወር አበባ ዑደት እንዲጀመር የሚያደርግ ነው፤

– አንዲት ሴት የሴትነት አካላዊ ቅርፅ እንዲኖት ያደርጋል፤

– በሴቶች ጡትና መቀመጫቸው አካባቢ የቅባት መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

– ሴቶች ድምፃቸው ቀጭን እንዲሆን ያደርጋል፤

– በሰውነታቸው ላይ ሴቶች ፀጉር እንዳይኖራቸውና የጭንቅላታቸው ፀጉር ግን እየበዛና እየተለቀ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡

– ማህፀን መጠኑን ጠብቆና ዳብሮ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡ በአጠቃላይ ኤስትሮጂን ሆርሞን ለሴቶች ከላይ የዘረዘርናቸውን ጥቅሞች ያስገኝላቸዋል፡፡

 

ጥያቄ፡የኤስትሮጂን ሆርሞንን መጣባት እንዲከሰት የሚያደርጉ ምክንያቶች ምንድናቸው?

ዶ/ር፡- የተለያዩ ምክንያቶች አሉ፡፡ ዋና ዋና የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡

– ዕድሜ በመግፋቱ ምክንያት በቂ የኤስትሮጂን መጠን አለመመረቱ፤

– ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በደም አማካኝነት የሚመጡ ኢንፌክሽኖች የዕንቁላል ማኳራቸውን ማጥቃታቸው፤

– በቀዶ ህክምና ኦቫሪ ሲወጣ፤

– በተፈጥሮ ኦቫሪው ኤስትሮጂን ማምረት አለመቻሉ፤

 

ጥያቄ፡የኤስትሮጂን ሆርሞን መዛባት መኖሩን የሚጠቁሙ ምልክቶች የትኞቹ ናቸው?

ዶ/ር፡- ተለዋዋጭ የሰውነት ሙቀት፣ ላብ ጥምቅ ጥምቅ ማድረግ፣ የወር አበባ መዛባት፣ የብልት መድረቅ፣ የአጥንት መሳሳት፣ በወሲብ ወቅት ህመም መከሰትና የሆድ መነፋት በቀዳሚነት የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡

 

ጥያቄ፡ከሴቶች ጡት ማነስ እና ፀጉር ዕድገት ጋር የኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም ያለው ግንኙነት ምን ይሆን?

ዶ/ር፡- የጡት ማነስም ሆነ መተለቅ ቀጥታ ከኤስትሮጂን ሆርሞን ጋር ብቻ የሚያያዝ አይደለም፡፡ ኤስትሮጂን አንዱ መንስኤ ይሁን እንጂ ሌሎች ሆርሞኖች በተጣጣመ መልኩ የማይሰሩ ወይም ደግሞ መጠናቸውን የማይጠብቁ ከሆነ የአስትሮጂንን ጤናማ ተግባር ያበላሹታል፡፡ ስለዚህ የአንዲት ሴት ሆርሞን መጠኑ ከፍ ካለ ፂም ሊኖራት ይችላል፤ ስለዚህ የጡት ማነስ (መተለቅ) የፀጉር ዕድገት መቀጨጭና የሴትነት መለያ ባህሪያት መዛባት የሚከሰተው፣ በኤስትሮጂን ማነስና በሌሎች ሆርሞኖች መብዛት ምክንያት ነው፡፡

 

ጥያቄ፡የኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም ከወሲብ ፍላጎት መቀነስ /መብዛት/ ጋር የሚያያዝበት ሁኔታ አለ?

ዶ/ር፡- በእርግጥም ይገናኛል፡፡ የኤስትሮጂንና የቴስቴስትሮን ንጥረ ቅመሞች አለመመጣጠን፣ በሴቶችም በወንዶችም የወሲብ ፍላጎት መቀነስና መጨመር ሁኔታዎችን ያሳያል፡፡ ሆርሞኑ ብቻውን ሳይሆን በአካባቢ ሁኔታዎችና ከበሽታዎች ጋር በተገናኘ መልኩ፣ በሴቶች የወሲብ ፍላጎት ማጣት ላይ አልያም መብዛት ምክንያት ይሆናል፡፡

 

ጥያቄ፡የንጥረ ቅመሙ አለጊዜው መመረት፣ ማነስና መብዛትን ተከትለው የሚከሰቱ የጤና ችግሮች የትኞቹ ናቸው?

ዶ/ር፡- ዕድሜያቸው ከ10 በላይ ሲሆን የጉልምስና ምልክት መታየት ሲገባው አስቀድሞ በ5 እና በ6 ዕድሜያቸው ጡት ማውጣት፣ ዳሌአቸው ሰፋ ማለትና የወር አበባ መታየት ቢያጋጥማቸው ይሄ የኤስትሮጂን መጠን በተፈጥሮ በብዛት መመረቱን ያሳያል፡፡ አልያም ደግሞ ሳይታወቅ በመድሃኒት መልክ ኤስትሮጂን ሆርሞን ከውጭ መወሰዱን ያመላክታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኤስትሮጂን ማነስ ካለ ደግሞ የጉርምስና ዕድሜያቸው ይዘገያል፡፡ ይህም ማለት 18 ዓመታቸው ድረስ ጡታቸው ላያድግና የወር አበባ ላያዩ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኤስትሮጂን ሆርሞን መብዛት በሚከሰትበት ወቅት፣ የወር አበባ መብዛትና መርዘም እንዲሁም የማህፀን ዕጢዎችና የተለያዩ ቦታዎች ላይ ፀጉር የመውጣት ሁኔታ ይከሰታል፡፡ እንደዚሁም የማህፀን ግድግዳ እና የኦቫሪ ካንሰር ይከሰታል፡፡ በሰውነት ውስጥ የቴስቴስትሮን ሆርሞን በብዛት ስለሚመረት፣ የቅርፅ መበላሸትን በተለይም የወንድነት ባህሪን መላበስ፣ ያልተፈለገ ቦታ ላይ ፀጉር መውጣት እና ድምፅ እንደ ወንድ የመወፈር ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

ሆርሞኑ በማይመረትበት ጊዜ ደግሞ ሌሎች ችግሮችን ያስከትላል፡፡ ለምሳሌ አንዲት ሴት በ51 ዓመቷ የወር አበባ ማቆም ሲገባት በ28 እና በ30 ዕድሜዋ የወር አበባ ሊጠፋባት ይችላል፡፡ ከዕድሜ የቀደመ የዕንቁላል ማፍሪያ አካል ስራውን የማቆም ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ በዚህ ወቅት መውለድ አይችሉም፡፡ ያለማቋረጥ ትኩሳትና በብዛት ላብ የመፈጠር ሁኔታ ይከሰታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በረጅም ጊዜ የአጥንት መሳሳትና የልብ ነክ ጤና ችግሮች ይፈጠራሉ፡፡ እንደዚሁም የአጥንት ጥንካሬ ማጣት፣ ከዕድሜ ቀድመው የእርጅና ምልክቶች እና ከዕድሜ የቀደመ ማረጥ ይከሰታል፡፡

 

ጥያቄ፡በንጥረ ቅመሙ አለመመረት ወይም የመጠን ማዛባት የበለጠ ተጋላጭ የሚሆኑ ሴቶች ይኖሩ ይሆን?

ዶ/ር፡- ይኖራሉ፡፡ የሥራ ውጥረት ያለባቸው፣ ለረጅም ጊዜ የሚሮጡ፣ በትላልቅ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያሉ ሴቶች ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ የሚሆኑበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ የስኳር፣ የቲቢ፣ ኤች.አይ.ቪ የጭንቅላት ዕጢዎች፣ የእንቅርትና መሰል ለረጅም ጊዜ የሰውነት ጤናን የሚያውኩ በሽታዎች ሴቶችን የኤስትሮጅን ሆርሞን መዛባት ያስከትላሉ፡፡ በዚህም ሳቢያ የወር አበባ ዑደት መዛባትም ሊፈጠርባቸው ይችላል፡፡ ሌላው የዕንቁላል ማፍሪያው አካባቢ ያለው ክፍል በጨረር፣ በኢንፌክሽን በዘር የሚተላለፍ የጤና ችግር ያጋጠማቸው ሴቶችም፣ የሆርሞን አለመመረት ወይም የመጠን መዛባት ሊገጥማቸው ይችላል፡፡

 

ጥያቄ፡የሆርሞን መዛባቱን ለማረጋገጥ የሚዳረጉ ምርመራዎች ምንድናቸው?

ዶ/ር፡-በደም አማካይነት የሆርሞን ምርመራ በማድረግ ማነሱንም ሆነ ከሚጠበቀው መጠን በላይ መመረቱን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኤስትሮጅን ሆርሞን መዛባትን ተከትሎ፣ ሌሎች የጤና ችግሮች መከሰታቸውንና ያስከተሉት ጉዳት መኖሩን ለማወቅ የአልትራ ሳውንድ ምርመራ እናደርጋለን፡፡

 

ጥያቄ፡ከኤስትሮጂን ሆርሞን ሚዛን መሳት ጋር በተያያዙ ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄው ምንድነው?

ዶ/ር፡- ከሁሉም የሚቀድመው የሆርሞን ባለመመረት አልያም ደግሞ ከመጠን መዛባት ጋር በተያያዘ፣ የሚከሰቱ የጤና ባለሙያን ማማከር ተገቢ ነው የሚሆነው፡፡ ሐኪሙ በሚያደርገው ሁሉ አቀፍ ምርመራ ችግሩ ከተለየ በኋላ የመውለድ ችግር ከሆነ፣ የወር አበባ መቋረጥና ሌሎች መሰል ችግሮች ከሆኑ እንደየባህሪያቸው በህክምናው የሚሰጡ መፍትሄዎች አሉ፡፡ በሌላም በኩል የወር አበባ መዛባት ካለ የሆርሞን ችግር ብቻውን ሳይሆን፣ ከሌሎች የጤና ችግሮች ጋር የሚቆራኝበት ሁኔታ ስላለ የሌሎች ጤና ችግሮች ምርመራ ተደርጎ መፍትሄ ይሰጠዋል፡፡

የኤስትሮጅን ሆርሞን ማነስ ሲኖር በመድሃኒት መልክ የኤስትሮጅን ሆርሞን በመስጠት እናክማለን፡፡ በአጠቃላይ ከሆርሞን መዛባት ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች በህክምና መፍትሄ የመስጠት ሥራ በመስራት መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡

 

 

 

Health: 11ዱ የጀርባ ህመም ዋና ዋና ምክንያቶችና 8ቱ ምርጥ የቤት ውስጥ ህክምናዎች

$
0
0

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም | ለዘ-ሐበሻ ጤና

80 በመቶ የስርጭት አድማስ ያለው የጀርባ ህመም ከበሽታዎች ሁሉ ወደ ሐኪም የሚያመላልስ አስገራሚ ህመም ነው፡፡ አዎን ጥርስዎን ሊነክሱ፣ ፊትዎን ቅጭም ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴም ስራዎን በሰላም ለማከናወን ፈተና መሆኑ አይቀርም፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ህመም ምን አይነት ችግር እንዳስከተለው ላይረዱ ይችላሉ፡፡ የጀርባ ህመም መንስኤው የተለያየ ነው፡፡ ከጀርባ አካባቢ ካሉ የሰውነት ክፍሎች ሊነሳ አልያም ከሰውነት ውስጥ ካሉ አካላት ሊመነጭ ይችላል፡፡ ቀላል የጀርባ ውጥረት አልያም የውስጥ ሰውነት ክፍል ካንሰር ሊሆን ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች፡፡ የአጥንት ችግር፣ የነርቭ ህመም፣ የጡንቻ፣ የጅማት ከኩላሊትና ከማህፀን ግድግዳ፣ እንዲሁም ከሌላ ቦታ የተሰራጨ ካንሰር አሊያም ደግሞ የአጥንት ኢንፌክሽን፡፡

በሁሉም ሰው ላይ ማለት በሚቻል መልኩ በህይወት ዘመን ውስጥ የወገብ ህመም ያጋጥማል የቢሊዮኖች ህመም በመባልም ይታወቃል፡፡ በተለይ የአጥንት ክብደትና ጥንካሬ በዕድሜ ተፅዕኖ መዳከም ሲጀምር ወገብ ለአደጋ ይበልጥ ተጋላጭ እየሆነ ይመጣል፡፡ ለብዙዎች ከአደጋ በፍጥነት አገግሞ የጤነኛ ጀርባ ባለቤት መሆንም እንዲሁ ቀላል የሚባል ሂደት አይሆንም፡፡

እንዲሁም አንዳንድ ያልተለመዱ የጀርባ ችግሮች እንደ ካንሰር ካሉ ጠንከር ካሉ በሽታዎች መነሻነት ይመጣሉ፡፡ ለወራት የሚዘልቁ የጀርባ ህመሞችም የህክምና ባለሙያዎች የተለየ ድጋፍ የሚጠይቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

Back Pain

11 ዋና ዋና የጀርባ ህመም ምክንያቶች

1. ከአቅም በላይ ወይም በተሳሳተ መንገድ ዕቃ ማንሳት

2. ድንገተኛ አደጋ፤ መውደቅ፣ በስፖርት አማካኝነት የሚመጣ ችግር

3. የአጥንት መሳሳት

4. ከልክ ያለፈ ውፍረት በተለይ ደግሞ በመሀከለኛው የሰውነት ክፍል ላይ /ሆድ አካባቢ/ ከፍተኛ ውፍረት መኖር

5. በየዕለቱ የሚገጥም ጭንቀትና ድብርት

6. በተሳሳተ መንገድ መተኛት/በተለይ በሆድ በኩል መገኘት/

7. በተሳሳተ መንገድ መቀመጥና ከተቀመጥንበት መነሳት

8. ለረዥም ሰዓት መቀመጥ በተለይ ቁጥጥ ማለት እና መቀመጫን የሚቆረቁር ነገር ላይ መቆየት

9. ከበድ ያለ የእጅ ቦርሳና የጀርባ ቦርሳን መሸከም

10. ከወገብ ታጥፎ ለረዥም ጊዜ መቆየት

11. በእርግዝና ወቅት ጡንቻን እና ጅማትን የማሳሰብ እንቅስቃሴ ማድረግ ናቸው፡፡

አይዘናጉ ጀርባዎ ላይ ያልተለመደ ህመም የተሰማዎ ከሆነ የጀመሩትን ስራ ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ወይም ሌሎች ተግባራትን የማቆም እርምጃ ወዲያው ነው መውለድ ያለብዎት፡፡

በወገብ ላይ የሚገጥም ህመም ለ48 ወይም ለ72 ሰዓታት የሚዘልቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙዎቹ የጀርባ ችግሮች ደግሞ የተወሰኑ ሳምንታትን ይፈልጉ ይሆናል፡፡ የጀርባ ጤና ላይ መሻሻል ከታየ በኋላም ስቃዩ አልፎ አልፎም ቢሆን ሊቀጥል ይችላል፡፡

8 ለጀርባ ህመም የሚወሰዱ የቤት ውስጥ ህክምናዎች

የጀርባ ህመምን የሚያመጡ እና የሚያባብሱ እንቅስቃሴዎችን በማስወገድ እንዲሁም ከታች የተዘረዘሩትን የመፍትሄ አማራጮች በየዕለቱ አልያም ባስቀመጡት ፕሮግራም መሰረት የሚተገበሩ ከሆነ መዳን ከእርሶ ብዙ የራቀ አይሆንም፡፡

በተለይ ትንንሽ የወገብ ወለምታዎችና ህመሞች ላይ ጠንከር ያለ ክትትል በማድረግ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ መዳን ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከበድ ካሉት ብዙዎቹ የጀርባ ችግሮች ሙሉ ለሙሉ ለመፈወስ ወይም ለማገገም ከአራት እስከ ስድስት ሳምንት ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ 12 ሳምንት እንደሚወስዱ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

1. በረዶ፡ በዋናነት ስቃይን ለመቀነስ የሚመከር ነው፡፡ በበረዶ የታጨቀ ከረጢት ወይም ቦርሳ እንዲሁም በጣም የቀዘቀዙ አትክልቶችን ካዘጋጀን በኋላ የታመሙ የሰውነት ክፍላችን /ጀርባችን/ ላይ ቢያንስ ለ15 ደቂቃ መያዝ፡፡ በሶስት እና አራት ሰዓታት ውስጥም ይህንን ተግባር መደጋገም ታዲያ በረዶውን በቆዳችን ላይ አለማሳረፋችንን እርግጠና መሆን አለብን፡፡

2. ማረፍ ነገር ግን የተወሰነ መንቀሳቀስ፡ ረዥም የእረፍት ጊዜ ብናገኝ ከገጠመን የወገብ ችግር በፍጥነት ለማገገም ሰፊ ዕድል ይኖረናል፡፡ ነገር ግን ለአንድ እና ለሁለት ቀናት እረፍት ማድረግ የማገገሚያ ሂደቱን ሊያዘገየው ይችላል፡፡

ስለዚህ ጡንቻን ለማጠንከር በሚዳን ሁኔታ ከእረፍቱ ጎንለጎን የተወሰነ እንቅስቃሴ ማድረግ በእጅጉ ይረዳል፡፡

በተረፈ አደጋ ሊያስከትሉ ከሚችሉ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ፡፡ በተለይ ደግሞ ዕቃ ከማንሳት፣ ከማስቀመጥ በተደጋጋሚ ከመተጣጠፍ እና ከመጠምዘዝ በዚህ ጊዜ መራቅ ግድ ይሆናል፡፡

3. ሙቀትን መተግበር፡ ህመሙ ከተከሰተ ከ48 ሰዓት በኋላ ወይም የህመም ስቃዩ ከራቀ በኋላ የታመመውን የሰውነት ክፍል /ጀርባ/ እና ጡንቻዎችን ለማፍታታትና የቀድሞ ጥንካሬአቸውን ለመመለስ ሙቅ ውሃን በሻወር መልክ፣ በከረጢትና ቦርሳ በማድረግ መታጠብና መያዝ ይመከራል፡፡

ታዲያ ከልክ በላይ በሞቀ ውሃ ቆዳን መጉዳት እንዳይመጣ መጠንቀቅ እንዳይረሳ፡፡

በእርግጥ ከሙቅ ውሃ ይልቅ ቀዝቃዛ ውሃ የማገገም ሂደቱን እንደሚያፋጥነው የታመነ ሲሆን ሁለቱንም በጋራ መጠቀሙ ደግሞ የተሻለ የሚባለው መንገድ ነው፡፡

4. መዘረጋጋት

የታሰበበት ለመዘረጋጋት እንቅስቃሴ ወገብን በቤት ውስጥ ለማስታመም የሚመከረው አንዱ መፍትሄ ነው፡፡ በመዘረጋጋት ሂደት ግን መጣደፍና መንጠርን የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች የጀርባ ችግር ላለባቸው አካላት በፍፁም አይመከሩም፡፡ ከዚህ ባለፈ በቀን ውስጥ ለ10 እና 15 ደቂቃዎች በፍፁም ህመም የማያስከትል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፈውስን ሊያመጣ ይችላል፡፡

5. ማሳጅ /ለተመረጠ የጀርባ ችግር/

በተለይ የወገብ ችግሩ የመጣው ጡንቻዎች ስራና ውጥረት ስለበዛባቸው ከሆነ ማሳጅ መፍታታትን በመፍጠር ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል፡፡

6. ደረጃ ያለው መፍታታት፡– ይሄ የመፍታታት ቴክኒክ በርካታ የሰውነታችንን ጡንቻዎች በማፍታት ነው የሚተገበረው፡፡

7. ዮጋ፡ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ዮጋ የወገብ ህመምን የማዳን ከፍተኛ አቅም አለው፡፡ ሂደቱ በርካታ ወራትን ሊወስድ ቢችልም ችግሩን በዘላቂነት በማጥፋት ግን የተዋጣለት አማራጭ ነው፡፡

8. መቆም፡ መቀመጥና ማንሳት በብልሃት፡- ስንቆም ወገባችንን አጥፈን ሳይሆን ቀጥ ብለን ይሁን፡፡ ስንቆም በፍፁም ትከሻችንን አስቀድመን ሊሆን አይገባም፡፡ ስንቀመጥም የታችኛው የጀርባችን ክፍል በቅድሚያ ወንበር እንዲነካ በማድረግ ይሁን፡፡ የምንቀመጥበት ወንበርም ቢሆን የታችኛውን የወገብ ክፍል የሚደግፍ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡

ዕቃን በማንሳት ሂደትም ዋናውን የሸክም ስራ እግሮቻችን እንዲፈፅሙት እናድርግ ወገብ በፍፁም መታጠፍ የለበትም፡፡

ወደ ሐኪም መሄድ የሚጠይቅ የጀርባ ህመም ደግሞ ይህን ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ህመሙ ወደ እግርዎ ጭምር ከተሰራጨ፣ የጡንቻ መዛል፣ መደንዘዝና እንደመርፌ ጠቅጠቅ የሚያደርግ ህመም አብሮት ካለ፡፡ የጀርባ ህመሙ ከተለወጠ የሰገራ አወጣጥ ለምሳሌ ድርቀት ጋር አልያ የተለየ የሽንት ምልክቶች ካሉ፡፡ እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የክብደት መቀነስና የሰውነት ፍላጎት መቀነስ፣ የክብደት መቀነስና የሰውነት ሙቀት መጨመር አብሮት ካለ፡፡ የአጥንት መሳሳት የረጅም ጊዜ ችግር ካለብዎ፡፡ ህመሙ እየከፋ ከሄደና ከላይ ባሉት ቀላል እርምጃዎች ሊሻልዎ ካልቻለ ወደ ሐኪም በመሄድ ቀጣይ ምርመራ ያድርጉ፡፡

መልካም ጤንነት፡፡

 

Health: የደም ቧንቧ መስፋት በሽታ –መንስኤው፤ መፍትሄውና መከላከያው

$
0
0

 

ሁለት አይነት የደም ቧንቧዎች አሉ፡፡ ኦክስጅን የተሸከሙና ደምን ከልብ ወደ ሌላው የሰውነት ክፍል የሚወስዱ የደም ቧንቧዎች አርተሪ ይባላሉ፡፡ ጥቅም ላይ የዋለውን ደም ከሌላው የሰውነት ክፍል ወደ ልብ የሚመልሱ ቧንቧዎች ደግሞ ቬን ይባላሉ፡፡ 

ደም መልሶችም ሆኑ ደም ቅዳ ቧንቧዎች በሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች የሚገኙ ናቸው፡፡ ደም ቧንቧን እንደ አንድ ፕላስቲክ ቲዩብ ወስደን መሀል ላይ ቆርጠን ብናየው ግድግዳውን ማየት እንችላለን፡፡ ደም ቅዳ ቧንቧ ግድግዳው ወፍራም ነው፡፡ የውስጠኛው፣ መካከለኛውና የላይኛው ተብለው የሚከፋፈሉ ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡ በሌላም በኩል ደም መልስ ቧንቧዎች ግድግዳቸው ቀጭን ነው፡፡ ለዚህ ይመስላል፣ ከደም ቧንቧ መስፋት ጋር ለተያያዙ የጤና ችግሮች የተጋለጡ የሚሆኑት፡፡

ዛሬ በዚህ የደም ቧንቧ መስፋት ችግር ዙሪያ ለአንባቢዎቻችን ሰፋ ያለ መረጃ ለመስጠት ፈልገን አንድ የቀዶ ጥገና ህክምና ስፔሺያሊስትን ማብራሪያ ጠይቀናቸው ነበር፡፡ እንዲያነቡት ጋብዘናል፡፡

blood

ጥያቄ፡የደም ቧንቧ መስፋት ራሱን የቻለ በሽታ ነው ወይስ የሌሎች በሽታዎች ምልክት ነው? መንስኤውስ ምንድነው ይላሉ?

ዶ/ር፡- የደም ቧንቧ መስፋት (ማቆር) ራሱን የቻለ በሽታ ነው፡፡ ደም በታችኛው የሰውነት ክፍላችን ወይም ከእግራችን አካባቢ በፍጥነት ወደ ሳንባና ልብ መመለስ ሲገባው፣ ለረዥም ጊዜ እግራችን ውስጥ ከቆየ የደም ቧንቧውን እየለጠጠው እና እያሰፋው ይሄዳል፡፡ ቀላል የሆኑ  በቆዳ ላይና ከቆዳ ስር ትናንሽ ሽንትርትር ነገሮች በተለይ ሴቶች ላይ በታፋና በእግር ጀርባ አካባቢ ይታያሉ፡፡ ከዚህ ተነስቶ ከእግራችን ጀርባ አረንጓዴ (ሰማያዊ) የሆኑ ትላልቅ እብጠቶችን የሚያመጡ የደም ቧንቧዎች መቋጠር ይታያል፡፡ ይህ ችግር ገፍቶ ከፍተኛ ደረጃ በሚደርስበት ጊዜ አልሰር እስከ መፍጠር እንዲሁም የእግሮቻችንን ከለር እስከ መቀየር ሊደርስ ይችላል፡፡

የደም ቧንቧ መስፋት የራሱ የሆኑ መንስኤዎች ያሉት በሽታ ነው፡፡ ከመንስኤዎቹ አንፃር ዋና ዋና የምንላቸውን እንይ፡-

– ደም መልስ ቧንቧዎች ደምን ወደ ታችኛው የአካል ክፍል እንዳይመለስ የሚያደርጉ ቫልቮች አሏቸው፡፡ እነዚህ ቫልቮች ብዙውን ጊዜ በተፈጥሮ አለመኖር፣

– ደምን ወደታችኛው የአካል ክፍል እንዳይመለስ የሚያደርጉ ቫልቮች በተፈጥሮ ደካም በሚሆኑበት ጊዜ፤

– ለረዥም ጊዜ ቁሞ መስራት ደም እግራችን አካባ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ ስለሚያደርገው ደም መልስ ቧንቧዎች እየተለጠጡ ይሄዳሉ፤

– በእርግዝና ወቅት የተለያዩ አካላዊና የሆርሞን ለውጦች ይከሰታሉ፡፡ በዚህ ምክንያት በእርግዝና ወቅት የደም ቧንቧ መለጠጥ ይከሰታል፤

– ለረዥም ጊዜ የቆየ ጉበት በሽታ የደም ቧንቧ መስፋትን ያጣል፤

– የፊንጢጣ ኪንታሮት፡፡

ጥያቄ፡ከፆታ አንፃር በጤና ችግሩ የበለጠ ተጋላጭ ማነው?

ዶ/ር፡- በደም ቧንቧ መስፋት ከወንዶች ይልቅ ሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው፡፡

ጥያቄ፡ምልክቱ ምንድነው?

ዶ/ር፡- የደም ቧንቧ መስፋት ብዙ ምልክቶችን አያሳይም፡፡ ነገር ግን ችግሩ እየጨመረ ሲመጣ ለረዥም ሰዓት በሚቆምበት ጊዜ የተወሰኑ ምልክቶችን ያሳያል፡፡

– ከፍተኛ የእግር ህመም ስሜት ይኖራል፤

– እብጠት ይኖራል፤

– ውሃ መጠራቀም ይከሰታል፤

– በተለይ ሴቶች ላይ በመቀመጫና በእግር ጀርባ አካባ ሸንተረር የመሰሉ ነገሮች በብዛት ይታያሉ፡፡

– የቆዳ ከለሩ ስለሚቀየር ለእይታ የሚማርክ አይሆንም፤

– ችግሩ መፍትሄ ካልተሰጠውና እየቆየ የሚሄድ ከሆነ እግር አካባ አልሰር ይፈጥራ፡፡

– የቆዳ ቀለም መዥጎርጎር

– የደም ዝውውር መስተጓጎል

– የተለያዩ ቁስሎች ሲፈጠሩ አለመዳን

– የቆዳ መብለጭለጭ

ጥያቄ፡ደረጃ ካለው ብናየው?

ዶ/ር፡- የደም ቧንቧ ጥበት በሽታ ራሱን የቻለ 4 ደረጃዎች አሉት፡፡ ደረጃቸውን ቀለል ባለ መልኩ ለመግለፅ የጠና ችግሩ እያለ ምንም አይነት ምልክት ሳይኖር ሐኪሙ ብቻ ሲመረምር የሚያገኘው ከሆነ ደረጃ አንድ እንለዋለን፡፡ በሽታው ደረጃ ሁለት ላይ ከደረሰ በእንቅስቃሴ ወቅት ብቻ እገራችንን የህመም ስሜት የሚሰማን ይሆናል፡፡ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል የምንለው፤ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳይኖር በረፍት ላይ ሁነን የህመም ስሜት መሰማት ከመረ አስጊ ሊባል የሚችል ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላክታል፡፡ ከዚህ ከፍ ሲልም እግር ላይ ቁስለት ሊፈጥር ይችላል፡፡ እዚህ ከደረሰ የከፋ የሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል፡፡

ጥያቄ፡የደም ቧንቧ መስፋት (ማቆር) በሽታ የተከሰተ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚካሄደው ምርመራ ምንድነው ይላሉ?

ዶ/ር፡- በሽታው መከሰቱን ለማወቅ ምንም የሚያስቸግር ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ደም መልስ የሚባሉ የደም ቧንቧዎች ከውጭ በግልፅ የሚታዩ በመሆኑ በዓይናችን በማየት ብቻ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ ለደም ቧንቧ መስፋት ምንም አይነት የማረጋገጫ ምርመራ ማድረግ የሚያስፈልገው አይደለም፡፡

ጥያቄ፡በህክምና ያለው መፍትሄ ምንድነው?

ዶ/ር፡- ለደም ቧንቧ መስፋትን እያንዳንዱ ሰው በቤቱ ውስጥ ሊያደርገው የሚገባ መፍትሄ ይኖራል፡፡ ለምሳሌ ለረዥም ሰዓት አለመቆም፣ ስራ መስራት ካለብን ቶሎ ቶሎ እየተቀመጡ እረፍትን ልምድ ማድረግና ስንቀመጥ እግራችንን ከፍ አድርገን መቀመጥ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ወፈር ያሉ ስቶኪንጎችን በመጠቀም፣ የሰፋውን የደም ቧንቧ ጨምቀው እንዲይዙትና ደም እንዳያቁር ማድረግ ይቻላል፡፡ በእነዚህ ሁኔታዎች የማይመለስ ከሆነ፣ በህክምናው ያለው የመፍትሄ አማራጭ በቀዶ ህክምና የሰፋውን የደም ቧንቧ ቆጦ ማውጣት ብቻ ነው፡፡

ጥያቄ፡የደም ቧንቧ መስፋት በወቅቱ ካልታከመ የሚያስከትለው ጉዳት ምንድን ነው?

ዶ/ር፡-የማይድን አልሰር ወይም ሰፊ ቁስል ይፈጥራል፡፡ የተፈጠረው ቁስል የማያቋርጥ ስቃይ ያመጣል፡፡ መራመድን መከልከልና የእግር ውበትን ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም ጫማ አድርጎ ለመጓዝ ያስቸግራል፡፡ በስተመጨረሻም የአጥንት ኢንፌክሽን ያመጣል፡፡

ጥያቄ፡እንዴት እንከላከለዋለን?

ዶ/ር፡- ህብረተሰቡ ስለደም ቧንቧ መስፋት (ማቆር) በሽታ መኖሩንና ችግሩ በቀላሉ ሊታይ የሚችል እንዳልሆነ እንዲገነዘብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውጭ የደም ቧንቧ መስፋትን ለመከላከል የሚያስችሉ ብዙ ነገሮች የሉም ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የባታችንን ጡንቻዎች የሚያጠነክሩ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን መስራት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ አዘውትሮ በእግር መራመድ፣ በስራ ቦታ ብዙ ከመቀመጥና ከመቆም በተወሰነ ጊዜ ውስጥ መንቀሳቀስ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ በስተመጨረሻ ሁሉም ሰው በእግር አካባቢ የህመም ሆነ የቆዳ ለውጦች ሲኖሩ በቀላሉ ማለፍ የለበትም፡፡ ሁልጊዜም የደም ቧንቧ መስፋትን ማሰብ ይኖርበታል ለማለት እወዳለሁ፡፡

Health: ‹‹እናቴ የሞተችው በልብ ህመም ነው፤ ስለዚህ ተጠንቀቅ ተብያለሁ››

$
0
0

ስሜ ዮሴፍ ማሞ ይባላል፡፡ የ20 ዓመት ወጣት ስሆን የ12ተኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተማሪ ነኝ፡፡ ተወልጄ ያደግኩት አዲስ አበባ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከቤተሰቦቼ ጋር የምኖረው መቂ ከተማ ነው፡፡ እናቴ የሞተችው በልብ ህመም ነው፤ እናም ላንተም ያሰጋሃል ተጠንቀቅ ስላሉኝ ስለ ልብ በሽታ ግልፅ የሆነ መረጃ ብትሰጡኝና አሁን ላይ ከሚሰማኝ ጭንቀት ነፃ እንድታወጡኝ እለምናችኋለሁ፡፡

ask your doctor zehabesha

መልስ

በአሁኑ ጊዜ በበለፀጉ ሀገሮች ውስጥ ከልብና ደም ስር ችግሮች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ይህን የጤና ችግር በሞት መንስኤነቱ ቀዳሚውን ስፍራ እንዲይዝ አድርጎታል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ እያደጉ ባሉ ሀገሮች ይኸው የልብ የደም ስር ችግር የሚያጠቃው የሰው ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሄዷል፡፡ ምንም እንኳን ለዚህ ህመም መነሻነት በዘር ሐረግ የሚወረሱ አጋላጭ ክስተቶች ቢኖሩምአብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት ግን ከአኗኗር ዘይቤ ጋር ተያይዘው የሚመጡ መንስኤዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ የአኗኗር ዘይቤን ጤናማ በማድረግ ከልብና ደም ስር በሽታዎች ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የሞት ቁጥር በጣም መቀነስ ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ቀድሞ በማወቅና አስፈላጊውን የህክምና እርዳታ በማድረግ ስቃይንና ሞትን መቀነስ እንደሚችል ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

አብዛኞቹ ለልብና ደም ስር ችግሮች መንስኤ መሆናቸው የታወቁት አጋላጭ ክስተቶችን የመከላከያ እርምጃ በመውሰድ የማያስከተሉትን አሉታዊ ተፅዕኖ መለወጥ ይቻላል፡፡ ይኸውም የአኗኗር ዘይቤን ጤናማ በማድረግና በጥናት ጥቅም እንዳላቸው የተረጋገጡ መድሃኒቶችን በመውሰድ ነው፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እርምጃዎችን በመውሰድ ለልብና ደም ቅዳ ጥበት ችግር የሚያጋልጡ ዋና ዋና አጋላጭ ክስተቶች የሚያስከትሉትን አሉታዊ ተፅዕኖ መቀየር ስለሚቻል እነዚህን እርምጃዎች ሁሉም ሰው ተግባራዊ እንዲያደርገው ያስፈልጋል፡፡

1. አመጋገብ፡ ጤናማ አመጋገብ የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ አትክልትና ፍራፍሬን መመገብ፣ ስኳርነት ያላቸውን ምግቦች መቀነስ፣ የደም ኮሌስትሮልን ከፍ የማያደርጉ የቅባት አይነቶችን (Monounsaturated fats) መጠቀም፣ ፋይበር ያላቸውን ምግቦች መጠቀም እና ኦሜጋ 3 የቅባት አይነቶችን ከአሳ መጠቀም ይገኙበታል፡፡

ጥናቶች በተከታታይ እንዳመለከቱት፣ ይህ አይነት የአመጋገብ ስርዕት ያላቸው ሰዎች በልብና ደም ስር የመጠቃት እድላቸው ይቀንሳል፡፡

2. ማጨስ፡– ማጨስ ከሚያስከትላቸው የጤና ጠንቆች ሌላ፣ እንደ ሲጋራም ሆነ ሌላ ለጤና ጠንቅ የሆኑትን እንደ ሺሻ፣ ፒፓ የማያጨስ በድንገተኛ የልብ ህመም የመያዝ ዕድሉ ከሚያጨሱት በዘጠኝ እጁ የጨመረ ይሆናል፡፡ ሲጋራ በውስጡ ኒኮቲን እና ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ የተባሉት ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮችን የልብን የተጣራ የደም አቅርቦት በተለያዩ ምክንያቶች ይቀንሳሉ፣ የልብ ሞት መጠንም ይጨምራሉ፡፡ የደም ግፊት መጠንን ከፍ ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም ደምን ያወፍራሉ፡፡ ይህንን የሚያደርጉትም የደም መርጋትን የሚከለካከሉ ፕሌትሌት የተባሉትን ንጥረ ነገሮች እንቅስቃሴ ስለሚያውኩ ነው፡፡

እዚህ ላይ በጣም ልንገነዘብ የሚገባን ነገር ደህና ነው ለክፉ አይሰጥም የሚባል ሲጋራ እንደሌለ ነው፡፡ የሲጋራው ፊልተር መኖር ልብ ላይ የሚፈጠረውን ጫና በፍፁም መቀነስ አይቻልም፡፡ በቅርቡም በተደረገው ጥናት ብዙም የሚያጨሱ በትንሹም ቀንሰው የሚያጨሱ ጉዳቱ እኩል እንደሆነ ታውቋል እናም መፍትሄው ማቆም ብቻ ነው፡፡

ስለዚህም የሚያጨሱ ሰዎች ከዚህ ሱስ እንዳላቂ አስፈላጊው ምክርና የህክምና እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የማያጨሱ ሰዎች በተለይም ወጣቶች ሲጋራ ማጨስ እንዳይለምድ መምከል ያስፈልጋል፡፡

3. የደም ግፊትን መቆጣጠር፡ የደም ግፊት ለልብና ደም ስር ችግር ከሚያጋልጡ መነሻዎች መሀከል አንደኛው ነው፡፡

ስለሆነም ከልብ ድካም፣ ከአንጎል ጉዳት ከኩላሊት መድከም (Renal failure) ከልብ ደም ስር መጥበብ ጋር በተያያዘ ለሚደርስ ስቃይና ሞት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ የደም ግፊት (hypertension) አለ የሚባለው በመለኪያ መሳሪያው ከ140/90 ሚ.ሜ ሜርኩሪ በላይ ሲሆን በአጠቃላይ የደም ግፊት ከዚህ መጠን በላይ እንዳይሆን እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው፡፡ ለስኳር ታካሚዎችና የኩላሊት ችግር ላላቸው ሰዎች ግን የደም ግፊታቸው የላይኛው ጣራ ከላይ ከተጠቀሰው ቁጥር ያነሰ እንዲሆን ይመከራል፡፡ ሁሉም የደም ግፊት  ያላቸው ሰዎች በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ፣ የምግብ ጨው እንዲቀንሱ፣ ውፍረት ካለ እንዲቀንሱ እና ከመጠን በላይ አልኮል እንዳይጠቀሙ ይመከራል፡፡ በእነዚህ መንገዶች የደም ግፊት መጠን ከመነሻውም በጣም ከፍተኛ ከሆነ በሐኪም ክትትል የደም ግፊት መድሃኒቶችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ እንደታካሚው ሁኔታ፣ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር በአብዛኛው ጊዜ በአንድ በላይ መድሃኒት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

4. ደም ውስጥ ያለ ቅባትን መቆጣጠር፡– ከፍ ያለ የደም ውስጥ ቅባት ያላቸው ሰዎች ተከታታይነት ያለው የሰውነት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ፣ ውፍረት ካላቸው እንዲቀንሱ እና ጤናማ የሆነ አመጋገብ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን እርምጃዎች በመውሰድ የቅባት መጠን የሚፈለገው ደረጃ ላይ ካልደረሱ በሐኪም ክትትል ቅባት የሚቀነሱ መድሃኒቶችን መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

የቅባት መጠናቸው ለጤና ተስማሚ ከሆኑ ምግቦች መሀከል አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቅጠላ ቅጠል፣ ቅባቱ የተቀነሰለት ወተት፣ እርጎ፣ አሳ እና ሌሎች የባህር ውስጥ ምግቦች ያልተፈተጉ ጥራጥሬዎች፣ የገብስ ዳቦ፣ የወይራ ዘይት፣ አኩሪ አተር፣ ባቄላ፣ አተር እና የዶሮ ምርቶች የተወሰኑት ሲሆኑ በሌላ በኩል ግን ለልብና ደም ስር ችግር ሊያጋልጥ የሚችል ቅባት ከሚገኝባቸው የምግብ አይነቶች መካከል የእንስሳት ስብና ቀይ ስጋ፣ ቅቤ፣ የሚረጋ ዘይት፣ ማርጋሪን፣ አይስክሬምና ቅባቱ ያልተቀነሰ ወተት ዋናዎቹ ስለሆኑ ከእነዚህ የምግብ አይነቶች መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡

5. የአካል እንቅስቃሴ፡- ተከታታይነት ያለው የአካል እንቅስቃሴ ከልብ ችግር ጋር የተያያዘ ስቃይንና ሞትን እንደሚቀንስ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ተግባራዊ ሊሆኑ ከሚችሉ መመሪያዎች መሀከልም በቀን ውስጥ ከ30-60 ደቂቃ ወይም በድምሩ በሳምንት ቢያንስ ለ150 ደቂቃ የሚደርስ እንቅስቃሴ በሳምንት ውስጥ ከ4-6 ቀን እንዲደረግ ይመከራል፡፡ የሰውነት እንቅስቃሴዎቹም የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡፡ ፈጠን ያለ የእግር ጉዞ፣ መደነስ፣ ሶምሶማ ሩጫ፣ ብስክሌት መጋለብ፣ መዋኘት፣ ኤሮቢክ እንቅስቃሴ ይገኙበታል፡፡ ጥሩ የሆነ የእንቅስቃሴ ደረጃ ላይ መድረሱን በትንፋሽ ማጠር፣ በድካም ወይም ላብ ሲኖር ለማወቅ ይቻላል፡፡

6. ክብደት መቀነስ፡– ከልክ ያለፈ ውፍረት ለደም ግፊት፣ ለስኳር ህመም፣ ለደም ውስጥ ቅባት መጨመርና መዛባት ያጋልጣል፡፡ ስለሆነም ይህ ችግር ያለባቸው ታካሚዎች ክብደት ለመቀነስ ፈቃደኛና ዝግጁ ከሆኑ አመጋገብን፣ የባህሪ ለውጥንና የአካል እንቅስቃሴን አስመልክቶ መረጃ ሊያገኙ ይገባል፡፡

7. ጭንቀት፡- ለጭንቀት የተጋለጡ ሰዎች ከላይ ለተመለከተው አትሮስከለሮሲስ ለተባለው ሂደት ይጋለጣሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በተፈጥሯቸው በትንሹ የሚጨነቁ ሰዎች በስራ ጫና እንዲሁም ማህበራዊ ህይወት የተወሳሰበ ኑሮ የሚያሳልፉ ሰዎች ከሌሎች በበለጠ ለልብ ህመም የተጋለጡ ናቸው፡፡ በአብዛኛው ጊዜ የሚወገዱ እና የሚያመጣውንም ነገር ለይቶ በመገንዘብ መከላከል የሚቻሉ ናቸው፡፡ ሁልጊዜ ማድረግ ያለብንን ነገር ጭንቀት ወይም ሃሳብ ካበዛን ለቅርብ ሰው ማማከር የተሻለ መሆኑን ነው፡፡

8. አስፕሪን መጠቀም፡ ድንገተኛ የልብ ደም ስር መድፈን የሚያመጣውን የልብ ጡንቻ ጉዳት ለመከላከል ለዚህ ችግርተጋላጭነት ያላቸው ታካሚዎች አስፕሪን ቢተቀሙ ችግሩ የሚከሰትበትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ነገር ግን አስፕሪም አንድ አንድ ያልተፈለጉ ውጤቶች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል የዋነኛው ሆድ ዕቃ ውስጥ የደም መፍሰስ ነው፡፡ ስሆነም አስፕሪን ለልብ ደም ስር መዳፈን ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ለሆኑ ታካሚዎች ብቻ መሰጠት አለበት፡፡  እነዚህን ታካሚዎች ለይቶ ለማወቅ በቁጥር የሚቀመጡ መመዘኛዎች ይላሉ ይህ ውሳኔ በሐኪሞች ሚደረግ ይሆናል፡፡ ስለዚህ አስፕሪን መውሰድዎት ለልብና ደም ስር እንደሚጠቀምዎት ለማወቅና አስፕሪን እንዳይወስዱ የሚያግድዎት የህክምና ሁኔታ እንዳለ ለመረዳት የልብ ሐኪምዎትን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

9. አልኮል ማስወገድ፡ ከመጠን በላይ የሆነ የአልኮል አጠቃቀም በተለያየ ምክንያት የሚመጣ የሞት ቁጥርን ይጨምራል፡፡ ከዚህም መካከል አንድና ዋነኛው ከልብና ደም ስር ጋር የተያያዘ ሞት ነው፡፡ ምንም እንኳን የአልኮል አወሳሰድ መጠን ችግር አያመጣም የሚል ዝቅተኛ ገደብ በእርግጠኝነት ሊቀመጥለት ባይቻልም የሚከተሉት ሁኔታዎች ምንም አይነት አልኮል እንዳይወሰድ ይከለክላሉ፡፡ እነሱም እርግዝና፣ ከዚህ በፊት ያ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ፣ የጉበት ወይም የቆሽት ችግር፣ በግል ወይም በቤተሰብ ያለ የአልኮል ሱሰኝነት እና አደገኛ መሳሪያ ወይም ማሽን ላይ የሚሰራ ግለሰቦችን ይመለከታል፡፡ በመጠጥ ውስጥ ለምሳሌ አንድ ቢራ፣ አንድ ብርጭቆው ወይን ወይም አንድ ብርጭቆ የተደባለቀ መጠን ከ10-15 ግራም አልኮል ይገኛል፡፡ አሁን ባሉ የህክምና መመሪያዎች መሰረት ወንዶች በቀን ከሁለት ብርጭቆ መጠን እንዲሁም ሴቶች ደግሞ ከአንድ ብርጭቆ መጠን የበለጠ እንዳይጠቀሙ ይመከራል፡፡ ነገር ግን ይህ መጠን እንደየሰዉ የጤና ሁኔታ ስለሚለያይ ሐኪምዎን በቅድሚያ ስለ አልኮል አጠቃቀም መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡

ለማጠቃለል ከላይ የተዘሩትን እርምጃዎች በመውሰድ የልብና ደም ስር ችግሮችን ለመቀነስ ስለሚቻል እርስዎ ላይ ሊያገኙት የሚችሉት አጋላጭ ክስተቶችን ቀድሞ ለማወቅና በቅድሚያ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ሐኪምዎን ዛሬውኑ ያማክሩ፡፡

በእርግዝና ወቅት መመገብ የሌለብዎ ምግቦች

$
0
0

fast

በማስረሻ መሀመድ

በእርግዝናዎ ወቅት መመገብ/መዉሰድ የሌለብዎን የምግብ አይነት ማወቅ ለእርስዎና ለልጅዎ ጤናማ ምርጫ እንዲያደረጉ ያግዝዎታል::

በደንብ ያልበሰለ/ጥሬ ስጋ፣የዶሮ ዉጤቶችን(የዶሮ፣ ስጋና እንቁላል) ያለመጠቀም

በእርግዝናዎ ወቅት ነፍሰጡር ካልሆኑት አንፃር ሲታይ በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሰት የምግብ መመረዝ የመጋለጥ እድልዎ ከፍ ያለ ነዉ:: ስለሆነም ከምግብ ወለድ ህመሞች እራስን ለመከላከል

· ሁሉንም የስጋና የዶሮ ተዋፅኦዎችን ከመመገብዎ በፊት በሚገባ ማብሰል

· እንቁላል ነጩና አስኳሉ በደንብ እስኪጠነክሩ ድረስ በደንብ መቀቀል፡- ጥሬ እንቁላል አደገኛ በሆኑ ባክቴሪያዎች ሊበከል ይችላል:: ስለሆነም ከጥሬ ወይም በደንብ ካልበሰ እንቁላል የተዘጋጁ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ

ፓስቸራይዝድ ያልተደረጉ ምግቦችን ያለመመገብ

ብዙዎቹ መጠነኛ ስብ የያዙ እንደ ክሬም የወጣለት ወተትና ማንኛዉም ፖስቸራይዝድ ያልተደረገ ወተት የያዙ ምግቦችን መመገብ ለምግብ ወለድ ህመሞች ሊዳርግዎ ይችላል፡

በደንብ ያልታጠቡ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ያለመጠቀም

ጤናዎን ሊጎዱ ከሚችሉ ባክቴሪያዎች እራስን ለመከላከል በደንብ ያልታጠቡ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ያለመመገብ

ከመጠን ያለፈ ካፊን/ caffeine/ ያለመጠቀም

ካፊን የእንግዴ ልጁን በማለፍ በማህፀንዎ ዉስጥ ያለዉን ፅንስ ሊጎዳ ይችላል:: ምንም እንኳ ተጨማሪ ጥናት ቢያስፈልግም አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከመጠን ያለፈ ካፊን ያላቸዉን ነገሮች መጠቀም ለዉርጃ የመጋለጥ እድሉን ሊጨምር እንደሚችል ያሳያል::

መጠጥ ያለመጠጣት

ምንም እንኳ ትንሽ አልኮሆል መጠጣት ፅንሱን ይጎዳል ተብሎ ባይታመንም፤ ምን ያህል አልኮሆል ቢወሰድ ፅንሱን እንደሚጎዳና እንደማይጎዳ በጥናት የተረጋገጠ ነገር የለም ጽንሱን ሊጎዳ የሚችል ትንሹ የአልኮሆል መጠን

ምን ያህል እንደሆነ በጥናት የተረጋገጠ ነገር የለም/የሚታወቅ ነገር የለም:: ስለሆነም የሚሻለዉ በእርግዝናዎ ወቅት ምንም አይነት አልኮሆል ከመዉሰድ/ ከመጠጣት መቆጠብ ነዉ:: አልኮሆል የሚጠጡ እናቶች ለዉርጃና ፅንሱ በሆዳቸዉ ዉስጥ ሞቶ የመወለድ እድላቸዉ በጣም ከፍተኛ ነዉ:: በእርግዝና ወቅት ከመጠን ያለፈ አልኮሆል መዉሰድ ፅንሱን ለፋታል አልኮሆል ሲንድረም የማጋለጥ እድሉ ከፍ ያለ ነዉ:: ይህ መጠን

በፅንሱ የፊትና ልብ ላይ ተፈጥሮያዊ ችግሮችና ለአእምሮ ዘገምተኝነት ይዳርገዋል:: ሌላኛዉ ነፍሰጡር እናቶች መካከለኛ አልኮሆል ጠጪ ቢሆኑም እንኳን አልኮሆሉ በፅንሱ የአእምሮ እድገት ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል::

ጥሬ የሆኑ፣በደንብ ያልበሰሉ ወይም የተበከሉ

ጎጂ ከሆኑ ባክቴሪያና ቫይረሶች እራስን ለመከላከል

· ጥሬ አሳ ያለመመገብ

·በፍሪጅ የቆየ ወይም በደንብ ያልበሰለ የባህር ምግቦችን/ seafood/ ያለመመገብ

· የባህር ምግቦችን በደንብ ማብሰል

የባህር ምግቦችን ያለመጠቀም/ከመጠቀም  መቆጠብ

Health: አለሌነት ከወላጆች የሚወረስ ባህሪ ነውን? |ሊነበብ የሚገባ ጥናት

$
0
0

cheating

ሲወለዱ ጀምሮ በፍቅርና ትዳር አጋራቸው ላይ የሚወሰልቱ ሰዎች መኖራቸውን እና ይህም ከወላጆቻቸው በዘርየወረሱት ሊሆን እንደሚችል በዚህ ዙሪያ የተደረገ ጥናት አመለከተ፡፡ ይህም ማለት ውስልትና በዘር የሚተላለፍ እንዲሆን አድርጎታል ይላል ጥናቱ፡፡ በጥናቱ ላይ የተገኘው ነገርም ‹‹ORD4›› በመባል የሚጠራው ልዩ ዘር ሲሆን ያለባቸው ሰዎች የበለጠ በስሜት የሚነቃቁ እና ከፍተኛ ደስታን የሚሰጠው ዶፓሚን የተባለ ቅመም ከሌሎች አስበልጠው የሚያመነጩ ናቸው፡፡

በጥናቱ ላይ እንደ አንድ ባለታሪክ የቀረበውን ታዋቂው የጎልፍ ተጨዋች ታይገር ውድስ ሲሆን ውድስ በሚስቱ ላይ መወስለቱን ተከትሎ አባቱ በእናቱ ላይ ላደረገው ይቅር እንደማይለው በአንድ ወቅት መግለፁ ይታወቃል፡፡

ሰዎች ለአካባቢያቸውና ለዓለም ባላቸው አስተሳሰብ ቀናነት በሁለት ይከፈላሉ ለማለት ይቻላል፡፡ እነሱም ቀና አስተሳሰብ ያላቸውና ፀለምተኛ አስተሳሰብ ያላቸው የሚሉት ናቸው፡፡ ቀና አስተሳሰብ ስንል የሰዎች አካባቢያቸውን ወይም ዓለምን በመልካም እና በበጎ መልኩ መመልከት ሲሆን ፀለምተኛ አመለካከት ማለት ደግሞ በጭፍኑ ለአካባቢ ወይም ለዓለም የሚንፀባረቅ ክፉ እና ጠማማ አስተሳሰብ ነው፡፡ በእርግጥ እነዚህ ሙሉ ለሙሉ ተቃራኒ የሆኑ የአመለካከት ገፅታዎች በስነ ልቦና ባለሙያዎች ዘንድ ፖዘቲቭ ቲንከርስ እና ኔጋቲቭ ቲንከርስ በማለት የምንጠራቸው ናቸው፡፡

ቀና ያልሆነ ወይም ፀለምተኛ ወይም ጤናማ አመለካከት ያለው ሰው በመልካምና በጥሩ ሁኔታዎች ውስጥ የተከበበ ቢሆንም እንኳን ይህ ክፉ አመለካከቱ አይለቀውም፡፡ መልካሙን ነገር አጨልሞ የሚመለከት በመሆኑም የዓለምን ጨለማ ክፍል ብቻ ነጥሎ የሚመለከት በመሆኑ አካባቢው የለገሰውን መልካም አጋጣሚ ሊጠቀምበት አይችልም፡፡ እንዲያውም ጠማማ እና ፀለምተኛ አስተሳሰብ ከራሱ አልፎ ወደ አካባቢውም ስለሚንፀባረቅ ከጊዜ በኋላ ብሩህ የነበረውን አካባቢ ጨለማ እንዲወርሰው ያደርገዋል ማለት ነው፡፡

በእርግጥ ፀለምተኞች እና ጠማማ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በጣም አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ይህ አመለካከታቸው ከእነርሱም አልፎ ወደ ሌሎች ሰዎች ስለሚተላለፍ ነው፡፡

ጠማማው አስተሳሰባቸው ሌሎችን ቀና አስተሳሰብ ይበክለዋል፣ ታዲያ ከዚህ አኳያ የፀለምተኛ ሰዎች መሰረታዊ ባህሪይ ራሱን የቻለ ከባድ በሽታ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ልክ እንደ ተላላፊ በሽታ ከበሽተኛው ወደ ጤናማው የሚተላለፍ ህመም ነው፡፡ ፀለምተኛ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ገንቢ ሊባል በሚችል መልኩ ለታላቅ ደረጃ ሊደርሱ ወይም ሊበቁ የሚችሉ አይደሉም፡፡ በእርግጥ ለታላላቅና ሊበቁ ቢችሉ እንኳን በአፍራሽ መልኩ ብቻ መሆን አለበት፡፡ በአጠቃላይ የሚሰማሩባቸው የሥራ መስኮች እንኳን በንግድም ሆነ በምርት ላይ ቢሆን ከገንቢነታቸው ይልቅ አፍራሽነታቸው የሚያመዝን ነው፡፡ እናም በስራ ላይ ቢሰማሩም እንኳን ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናል ማለት ነው፡፡

አለበለዚያ ግን ይህን መሰል አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች በአጠቃላይ በማህበራዊ ህይወታቸው ተረብሸው የሚረብሹ ሲሆኑ በተለይም ሽብርንና ረብሻን በሚጤቁ ተግባራት ላይ ቢሰማሩ እጅግ በጣም የተዋታላቸው ይሆናሉ፡፡ በእርግጥ እነዚህ ግለሰቦች በማህበረሰቡ ዘንድ ‹‹ትንሽ ሰዎች›› በመባል የሚፈረጁ ናቸው፡፡ ትንሽ ያስባላቸውም የአስተሳሰባቸውና የአመለካከታቸው ትንሽነት ነው፡፡

የእነዚህ ሰዎች ሌላው ጉልህ ባህሪያቸው ደግሞ የወጣላቸው አጭበርባሪዎች መሆናቸው ነው፡፡ ጉዳዩ ጠቀማቸውም አልጠቀማቸውም መዋሸትና ማጭበርበር ይወዳሉ፡፡

እንዲያውም በታማኝነታቸው እና በቀናነታቸው በብዛት ከሚጠቀሙ ይልቅ በአጭበርባሪነታቸው እና በጠማማነታቸው በትንሹ ብቻ ቢጠቀሙ ይመረጣሉ፡፡

ታላቁ ግድፈታቸው ግን ታማኞች አለመሆናቸው ነው፡፡ ፍፁም ታማኞች አይደሉም፡፡ የተሳካ ማህበራዊ ህይወት እና የተዋጣለት ስራ እንዳይኖራቸው የሚያደርጋቸውም ይኸው ነው፡፡

አሁን አሁን እየተሰሩ ያሉ ጥናቶች እንደጠቆሙት ከሆነ ግን ያለመታመን ባህሪ በዘር አማካኝነት የሚተላለፍ ችግር መሆኑ ነው፡፡ ማለትም በክርሞዞሞች ውስጥ ባሉት ጂኖች ውስጥ የተቀመረ ነው፡፡ ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች እንዳይታመኑ የሚያደርጓቸው ጂኖች አሏቸው ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ በሴት የሜዳ አህዮች ላይ የተከናወነው ጥናት እንደሚጠቁመው ከሆነ አህዮቹ በሴት ጓደኞቻቸው ላይ የመወስለት ሁኔታ ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ታዲያ ይሄን የሚያደርጉት ግን በዲኤንኤ ውስጥ ባሉትለየት ያሉ ጂኖች የተነሳ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ማለትም ይህ ልዩ ጂን ያለባቸው ወንድ የሜዳ አህዮች ናቸው ለሴት ጓደኛው ያለመታመን ሁኔን የሚያሳዩት፡፡

በዝርያ ላይ የተከናወኑ ጥናቶች እንዳመለከቱትም በአንድ ሴት ያለመወሰን ሁኔታ በተለይ በከፍተኛ ሁኔታ በዝርያ የሚተላለፍ ነው፡፡ ይህም ፕሮሚስኪዩቲ (Promiscuity) እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡ እነዚህ ጥናቶች ጨምረው እንዳመለከቱት ከሆነም በአንድ ሴት ላይ የማይወሰኑ ወንዶች ይሄን ለየት ያለ ባህሪይ በዘር ለተተኪው ትውልድ ሊያስተላልፉ የሚችሉ ሲሆን ዝርያውን የሚያስተላልፉትም ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ ነው፡፡ እናም በአንድ ሴት ያለመወሰን ሁኔታ ሴቶች እንኳን የሚወርሱት ከእናቶቻቸው ይልቅ ከአባቶቻቸው ነው ማለት ነው፡፡ ያው እንግዲህ ሴት ልጅ አባቷን ትመስላለች እንደሚባለው አይደል?

ታዲያ እነዚሁ ተመራማሪዎች ጨምረው ለማጥናት እንደቻሉት ከሆነም በባለትዳሮች መካከል ያለመታመን ሁኔታ መከሰቱ በልጆቸው ላይ ታላቅ ቅያሜን ነው የሚፈጥረው፡፡

ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነም የፕሮሚስኪዩቲ ጂን ያለባቸው እንስሳትም ሆኑ ሰዎች ይሄንኑ ዝርያ በዘር የማስተላለፍ ባህሪ አላቸው፡፡ እናም እንግዲህ የአተራማሽ ልጆች እነሱም ቢሆኑ አተራማሾች ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ የአተራማሽት በእርጥ ከበርካታ ሴቶች ልጆችን የማግኘት ዕድሉን የሚፈጥር በመሆኑ ይሄን መሰሉ ጂን ያለባቸው ሰዎች ዝርያቸውን የማሰራጨት እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም ዝርያቸው ከምድረገፅ በቀላሉ እንዳይጠፋ ያደርገዋል ማለት ነው፡፡ ቻርለስ ዳርዊን ሰርቫይቨር ኦቭ ዘ ፊተስት የሚለው መርህም እዚህ ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

 

 

Health: የፀጉርዎ ነገር! ሳይንስ ስለፀጉርዎ የሚለውን እንንገርዎት

$
0
0

 

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም | ለዘሐበሻ

ዘመናዊ ሰዎች የሌሎች ሰዎችን ፀጉር ሲያደንቁ ይስተዋላሉ፡፡ ፀጉራቸውን ለመስተካከል/ለመስራት ሲሯሯጡም እናያለን፡፡ በፀጉር አምሮና ተውቦ ለመገኘት ሁሉም እንደየአቅሙ ሲሟሟት ይታያል፡፡ ግን ለምንድነው ሰዎች ፀጉራቸውን የሚንከባከቡት? ለፀጉር የሚጠፋው ገንዘብና ጊዜ ቀላል ነው? ነጋ ጠባ ፀጉር እያደገ፣ እየተስተካከለ፣ እየተበጠረ የሚኖር መሆኑ አያናድድም? ያለማቋረጥ የሚያድግ ፀጉር ባለቤት በመሆን ረገድ፣ የሰው ልጅ ብቸኛ ፍጡር ነው፡፡ እኮ ለምን?

hair

ከአንድ ሁለት ዓመት ወዲህ ፀጉርን በሚመለከት ሳይንሳዊ አመለካከቶች እየተንፀባረቁ ናቸው፡፡ እንደሚባለው ከሰው በስተቀር ሌሎች ፍጡራን አንዴ ፀጉር ከተላበሱ በኋላ ዕድገቱ ይቆማል፡፡ የእኛ ፀጉር ግን ሲሻው ዕድሜ ልክ ሲያድግ፣ ሲመዘዝ ይባጃል፡፡ ለምንድነው የሰው ፀጉር ያለማቋረጥ ለማደግ የቻለው? በእንክብካቤ ብዛት ወይስ በተፈጥሮ? ለዚህ አስተማማኝ ምላሽ ለመስጠት ይከብድ ይሆናል፡፡

በደንብ የሚታወቀው ሁለት አይነት ፀጉር ያለን መሆኑ፡፡ ዋነኛው የጭንቅላት፣ የቅንድብና የሽፋሽፍት፣ ሌላው በሌሎች የሰራ አካላታችን የሚገኙት ናቸው፡፡ እነዚህም እንደየሰዉ ዕድሜ፣ ፆታና ተፈጥሮ ይብዛ ይነስ እንጂ የብሽሽት፣ የብብትና የጢምንም ጨማምሮ ዘጠኝና አስር አይነት ይሆናሉ፡፡ በትከሻ ላይ ዝቅ ብሎ አምሮ የሚታየውም ሆነ በእግር ጣቶች ላይ የምትበቅለዋ ስስ የሆነች ፀጉር፣ ሁሉም እስከሚረግፉ እኩል ይበቅላሉ፡፡ በወር ከአንድ እስከ 1.5 አፅቅ (ሳ.ሜ) የበቀለ ፀጉር አድጎ ሲያበቃ ይረግፋል፡፡ የፀጉር ዕድገት ጊዜም እንደ ፀጉሩ አይነት ይለያያል፣ ርዝመቱም በዚያው ይወሰናል፡፡ ለምሳሌ የእግር ፀጉር ዕድገቱን በሁለት ወራት ያቋርጣል፣ የብብት ፀጉር ለስድስት ወራት፣ የራስ ፀጉር ግን ያለማቋረጥ ዕድገቱ ከስድስት ዓመት በላይ ይዘልቃል፡፡

እጅግም የማይታወቀው የፀጉራችን አስተዳደግ ስልተ ምስጢሩ ሲሆን ወደፊት ግን የሚደረስበት ይሆናል፡፡ ለመሆኑ መቼ ነው የሰው ልጆች የራስ ፀጉር በማያቋርጥ ሁኔታ ማደግ የጀመረው? ተብሎ ሲጠየቅ የዛሬ 240,000 ዓመታት፣ የሰው ልጅ እሳት ማቀጣጠል ከጀመረበት ጊዜ በኋላ ነው ይባላል፡፡ እናም ከብርድ መከላከያ ብልሃት እስካገኘበት ጊዜ ድረስ በፀጉሩ ላይ የአይነትም ሆነ የመጠን/የብዛት ለውጥ ማስከተሉና፣ በለውጡም የማይፈለግ ቦታ የበቀለ ፀጉር ከጊዜ ወደ ጊዜ መርገፉ/መሳሳቱ የዝግመት ለውጥ ሀቅ እንደሆነ ይታሰባል፡፡

የፀጉር መሳሳት በበኩሉ አያሌ ጠቀሜታዎች እንዳሉትም አለመዘንጋት ነው፡፡ ይኸውም ፀጉር ውስጥ ተደብቀውና ተራብተው በሽታ አምጪ የሆኑ ተባዮችን መቀነሱ፣ ከአስቸጋሪው የጫካ ኑሮ ወደ ሜዳማ፣ ሙቀታማና ወደ ባህር አካባቢዎች ሲጠጋ ከፀሐይ ከሚከላከልበት የራስ ፀጉር በስተቀር፣ ራሱን ለማቀዝቀዝ የፀጉሩ ከቀድሞው መቀነስ ላብ በብዛት ለማመንጨት ረድቶታል፡፡ በዚያ ላይ ሰው ልጅ ፀጉሩ እያነሰ በሄደና፣ ለስላሳ ቆዳ በኖረው ቁጥር ይበልጥ ለፍቅር እየተፈላለገ፣ ባለ አናሳ ፀጉሮቹ እየተራቡ፣ ፀጉራሞቹ በብዛት እየቀነሱ እንደሄዱ ይገመታል፡፡ በተባይ አምጪነቱም ይሁን በሌላ ምክንያት የማይፈለግ የነበረው ፀጉር፣ አሁን ደግሞ በአንፃሩ ምን እየተደረገ ነው?

በአሁኑ ጊዜ፣ ፀጉራችንን እጅግ ሲበዛ እንንከባከበዋለን፡፡ ፀጉር የማንነት መገለጫ ሆኗል፡፡ በወጉ የተሰራ ፀጉር አደባባይ ሲወጣ ያስከብራል፣ አድናቂዎችም ያስገኛል፡፡ ሰው ፀጉሩን አበጣጥሮ የሚወጣው ወድዶ አይደለም፡፡ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሰውም፣ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለራሱም ሲል ነው፡፡ ያለበለዚያ ፀጉሩን አንጨባሮ/አንጨፍሮ የወጣ ሰው ምንም ብሩህ አዕምሮ ቢኖው፣ የውስጡን የሚያውቅለት ስለሌለ በቦዘኔነት ወይም ግዴየለሽነት ይፈረጃል፡፡

ፀጉርን አሳምሮ ሽክ ማለት እኮ ብዙ ይናገራል፣ ያናግራልም፡፡ ‹‹ፀጉሯ ወርዶ፣ ወርዶ!›› እየተባለ ይዘፈን የለም? ይሄ እኮ ዛሬ ተጀመረ ሳይሆን ጥንት ጥንታውያንም ያደርጉት ነበር፡፡ የጥንት ሰዎች (አሁንም እንደ ጥንቱ መለመላቸውን በሚኖሩ ማህበረሰቦች ውስጥ እንደሚታየው) የተዋበ የፀጉር አሰራር ዘዴ አላቸው፡፡ የፀጉራቸው አሰራር ዝርያቸውን ወይም ማህበራዊ ማንነታቸውን ገላጭ ነው፡፡ በአገራችንም እንደየአካባቢው ጎገሬ፣ ቁንጮ፣ ጋሜ፣ ጉድሮ፣ ሽሩባ ወዘተ… ወይም ‹‹ፍሪዝ›› የሚሰጠው ትርጉም እንዳለ ሁሉ፣ በሌላው ዓለምም ‹‹እንቁላል ራሶችን››፣ ‹‹ራስ ተፈሪያንስን›› እና የመሳሰሉትን መጠቃቀስ ይቻላል፡፡

የሰው ልጅ ከ2300 ዓመታት በፊት የፀጉር ቅባት፣ ከ8000 ዓመታት በፊት ደግሞ ማበጠሪያ ይጠቀም እንደነበር በጥናት ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ ሰዎች የፀጉር ማስዋብን ዘዴ ይጠቀሙ የነበረው ጊዜ ርቀት በ10 ሺዎች ዓመታት እንደሚቆጠሩ ከተገኙ ቅርሶች ታውቋል፡፡ አሁን ላይ ቆመን ጥንተ ጥንታውያን የዋሻ ሰዎች፣ እንዴት እንደኖሩ በዓይነ ህሊናችን መዳሰስ እንችል ይሆናል፡፡

ፀጉራቸውን ለመንከባከብና ለማስዋብ በቂ ጊዜ እንደነበራቸው እንገምታለን፡፡ እነሱ ቀልጣፎች ነበሩ፤ በቀላሉ የማደንና ምግብ የመሰብሰብ ብቃት ነበራቸው፡፡ ስለሆነም ለማህበራዊ ክንውኖች በቂ ትርፍ ጊዜ ነበራቸው፡፡ ለመዋቢያ፣ ማስዋቢያ ቁሳቁሶችን ለመስራት ጭምር ኋላ ቀር ከተባለ ማህበረሰብ ጀምሮ እስከ ዘመኑ የቁንጅና ሳሎኖች ድረስ፣ የፀጉር እንክብካቤ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ በሂደት አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የላቁ እንደሚሆኑና የበለጠ ተረፈላጊነት እንደሚኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ የፀጉር ማስዋብ ስራ እጅግ ጥንታዊ ከሆኑት የሙያ መስኮች አንዱ እንደሆነ አይጠረጠርም፡፡

ስለ ፀጉራችን ለምን እንጨነቃለን?

በርካታ ሰዎች የፀጉራቸውን ሁኔታ በመስተዋት እያዩ በየቀኑ ብዙ ሰዓት ያሳልፋሉ፡፡ ስለ ፀጉር ማሰብ ወንድ ሴት የማይል ከመሆንም በላይ ትልቅ ጭንቀት የሚፈጥርበት ጊዜም አለ፡፡

ስለ ፀጉርህ ሁኔታዎች እወቅ

በራስ ቅል ላይ በአማካይ 100,00 የሚደርሱ ፀጉሮች እንዳሉ ይገመታል፡፡ አንድ ነጠላ ፀጉር የሚያድገው  ዕድሜ ልክ ሳይሆን ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ይረግፍና ከጥቂት የሽግግር ጊዜ በኋላ ከዚያው ቀዳዳ አዲስ ፀጉር መብቀል ይጀምራል፡፡ አንድ ነጠላ ፀጉር የራሱ የሆነ የአስተዳደግ ኡደት አለው፡፡ በዚህ ኡደት ምክንያት ምንም አይነት የፀጉር ችግር ከሌለበት ሰው እንኳን በእያንዳንዱ ቀን ከ70 እስከ 100 የሚደርሱ ፀጉሮች ይረግፋሉ፡፡

የፀጉር ቀለም የሚለያየው በምን ምክንያት ነው? ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒዲያ እንዲህ በማለት ያብራራል፡፡ ‹‹የፀጉር ቀለም በአብዛኛው የሚወሰነው ሜላኒን የተባለው ጥቁር ቡናማ ቀለም ባለው ስርጭትና መጠን ነው›› ሜላኒን በፀጉር፣ በቆዳና በዓይን ውስጥ የሚገኝ የተፈጥሮ ቀለም ነው፡፡ የቀለሙ መጠን በጨመረ መጠን ፀጉርም ጠቆር እያለ ይሄዳል፡፡ የሜላኒን መጠን እያነሰ ሲሄድ ደግሞ የፀጉር ቀለም ከጥቁር ወደ ቡናማነት ወይም ወደ ቢጫነት ያደላ ይሆናል፡፡ ፀጉር ምንም ሜላኒን ከሌለው ግን ሙሉ በሙሉ ነጭ ይሆናል፡፡

ከፎረፎር ሌላ ብዙዎችን የማያሳስባቸው የፀጉር መርገፍ አለዚያም የፀጉር መሸበት ነው፡፡

የፀጉር አስተዳደግ

የፀጉራችን አስተዳደግ የራሱ ዑደት አለው፡፡ ፀጉር የማደጊያ፣ የመሸጋገሪያና የማረፊያ ጊዜ አለው፡፡ ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒዲያ እንዲህ በማለት ያብራራል፡፡ ‹‹ፀጉር በማረፊያ ጊዜ ማደጉን ያቆማል፡፡ በዚህ ጊዜ አሮጌው ፀጉር የማደጊያው ጊዜ እስኪ ደርስ ድረስ በስሩ ላይ እንዳለ ይቆያል፡፡ በማደጊያ ጊዜ አሮጌው ፀጉር ይረግፍና አዲስ ፀጉር ከስር ይወጣል፡፡ ‹‹በማንኛውም ወቅት ከ85 እከ 90 በመቶ የሚደርስ ፀጉር በዕድገት ላይ ሲሆን ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነው በማረፊያ፣ በመቶ የሚሆነው በመሸጋገሪያ ጊዜ ላይ ይሆናል፡፡

ፀጉርህ ሸብቷል?

ሽበት ብዙውን ጊዜ የእርጅና እና የአረጋዊነት ምልክት ተደርጎ ይታያል፡፡ እርግጥ ነው፣ ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ፀጉር ይሸብታል፡፡ ይሁን እንጂ ሽበት የሚመጣው በእርጅና ምክንያት ብቻ አይደለም፡፡ ሽበት ጠቆር ያለ ፀጉር ባላቸው ላይ ጎልቶ የሚታይ ይሁን እንጂ ፆታም ሆነ የፀጉር ቀለም አይመርጥም፡፡

አንዳንዶች በመሸበታቸው ምክንያት ከዕድሜያቸው በላይ ያረጁ መስለው ሊታዩና ይህም አሳሳቢ ሊሆንባቸው ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ባለመሸበታቸው ምክንያት ትክክለኛው ዕድሜያቸውና መልካቸው አለመመሳሰሉ የሚያሳስባቸው ሰዎችም አይጠፉም፡፡

ፀጉር ከሸበተ ሞተ ማለት አይደለም፡፡ እርግጥ ነው በዓይን የሚታየው ውጪያዊ የፀጉር ክፍል በድን ነው፡፡ የእያንዳንዱ ፀጉር ስር ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ህይወት ያለው የፀጉር ክፍል ይህ ብቻ ነው፡፡ የፀጉር ስር እንደ ፀጉር ፋብሪካ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በስሩ ውስጥ ያሉት ሌሎች በብዛት ተራብተው ፀጉር ሲፈጠር የቀለም ሴሎች የሚሰሩትን ሜላኒን ይቀባል፡፡ በዚህም የተነሳ የቀለም ሴሎች ሜላኒን መስራት ካቆሙ ፀጉር ነጭ ይሆናል፡፡

የቀለም ሴሎች በድንገት ሜላኒን መስራታቸውን የሚያቆሙት ለምን እንደሆነ ማንም የማያውቅ የለም፡፡ በዚህም ምክንያት ለሽበት የሚሆን አስተማማኝ መድሃኒት ሊገኝ አልተቻለም፡፡ በተጨማሪም ስራቸውን አቁመው የነበሩ የቀለም ሴሎች እንደገና መስራት ሊጀምሩ እንደሚችሉ ተደርሶበታል፡፡

አንዳንዶች ሜላኒን እንደመወጋት ያሉትን አዳዲስ ህክምናዎች ይሞክራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ፀጉራቸውን ቀለም ይቀባሉ፡፡ ይህም ቢሆን ዛሬ የመጣ ልማድ አይደለም፡፡ የጥንቶቹ ግሪካውያንና ሮማውያን ፀጉራቸውን ቀለም ይቀበሉ ነበር፡፡ የጥንት ግብፃውያን በበሬ ደም ፀጉራቸውን ያቀልሙ ነበር፡፡

ይሁን እንጀ በየጊዜው ቀለም መቀባት ጊዜና ጥረት የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ የአንዳንዶችን ቆዳ ሊያስቆጣ ወይም ሊያቆስል ይችላል፡፡ ሽበትን በቀለም ማጥቆር ብንወስንም መቀባትን ለማቆም የምንፈልግበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከስር የሚያድገውን ሽበት መሸሸግ አስቸጋሪ ይሆንብናል፡፡ ሽት በአዎንታዊ ጎኑ የሚያምርና ከዚህ በፊት ያልነበረህን ግርማ ሞስ የሚያስገኝልህ ሊሆን ይችላል፡፡

የፀጉር መሳሳትና ራስ በራነት

ሌላው የተለመደ የፀጉር ችግር የፀጉር መሳሳትና ራሰ በራነት ነው፡፡ እነዚህም ችግሮች ቢሆኑ ዛሬ የተፈጠሩ አይደሉም፡፡ በጥንቷ ግብፅ ለራስ በራነት ከአንበሳ፣ ከጉማሬ፣ ከአዞ፣ ከድመትት ከእባብና ከዝይ ስብ የተቀመመ መድሃኒት ይሰጥ ነበር፡፡ በዛሬው ጊዜ ራስ በራነትንና የፀጉር መሳሳት ይከላከላሉ የሚባሉ በርካታ ሸቀጦች ሲኖሩ ለእነዚህ ሸቀጦች በየዓመቱ የሚፈሰው ገንዘብ በጣም ብዙ ነው፡፡

በራነት የሚጀምረው ትክክለኛው የፀጉር አበቃቀል ሲዛባ ነው፡፡ ትክክለኛው የፀጉር አበቃቀል በምግብ አለ መመጣጠን፣ ረዥም ጊዜ በሚቆይ ትኩሳት ወይም በቆዳ በሽታ ባሉ ምክንያት የተነሳ ሊዛባ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የፀጉር አበቃቀል እንደ እርግዝናና ልጅ መውለድ ባሉ ምክንያቶች ስለሚዛባ አዲስ ፀጉር መበቀል ከመጀመሩ በፊት ብዙ ፀጉር ሊረግፍ ይችላል፡፡ የፀጉሩን አስተዳደግ ያዛባው ምክንያት ሲወገድ ግን እንዲህ ያለው የፀጉር መርገፍ ይቆምና ወደ መደበኛው ሁኔታ ይመለሳል፡፡

ሌላው አይነት የፀጉር መርገፍ ደግሞ ላሽ ይባላል፡፡ ይህ ችግር በሚኖርበት ጊዜ በአንዱ አካባቢ ያለ በርካታ ፀጉር አንድ ጊዜ ይረግፋል፡፡ ላሽ የሚመጣው በሰውነት የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ላይ በሚደርስ ቀውስ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር በቅርቡ የተደረጉ የህክምና ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

በጣም የተለመደው የፀጉር መርገፍ በወንዶች ላይ የሚደርሰው የራስ በራነት አይነት ነው፡፡ ከፊት ያለው ፀጉር ገባ ገባ በማለት ወይም መሀል አናት ላይ ሳሳ በማለት ይጀምርና ቀስ በቀስ እየተባባሰ ይሄዳል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ያለው የፀጉር እድገት የተዛባ ሆኖ ከቆየ በኋላ ቀስ በቀስ ጨርሶ ወደ ማቆም ይደርሳል፡፡ ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ በማለት ያብራራል- ‹‹በራነት በጀመረው አካባቢ በነበረው ረዥም፣ ጠንካራና ባለቀለም ፀጉር መብቀል ይጀምራል›› የፀጉር ዕድገት እየቀጠለ ሲሄድ እየሳሳና ዕድሜው እያጠረ ሄዶ ምንም ፀጉር ከማይበቅልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡ ይህ የሚሆነው በዘር ውርሻና በወንዶች ሆርሞኖች ምክንያት ነው፡፡

የወንዶች ራስ በራን  ከአፍላ የጉርምስና  ዕድሜ አንስቶ ሊጀምር ቢችልም አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምረው በ30ዎቹ ዓመት መገባደጃና በ40ዎቹ ዓመታት ዕድሜ ነው፡፡ እንዲህ ያለው የፀጉር መርገፍ በብዙ ወንዶች ላይ የሚደርስ ቢሆንም መጠኑ ከዘር ወደ ዘርና ከግለሰብ ወደ ግለሰብ ይለያል፡፡ ያም ሆነ ይህ ለዚህ ችግር የተረጋገጠ መድሃኒት ማግኘት አልተቻለም፡፡ አንዳንዶች በራቸውን ለመሸፈን ሰው ሰራሽ ፀጉር ለማድረግ ወይም በቀዶ ህክምና ፀጉር ለማስተካከል ይመርጡ ይሆናል፡፡ ለተቀረው ፀጉር ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ ፀጉር እንዳይረግፍ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡

የአንድ ሰው ፀጉር አንዴ መሳሳት ከጀመረ ጨርሶ ይመለጣል ማለት አይደለም፡፡ ነጠላ ፀጉሮች በመቅጠናቸው ምክንያት ሳስቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለመሆኑ የፀጉር ውፍረት ምን ያል ነው? አንድ ጥናት እዳመለከተው ከ50 እስከ 100 ማይክሮ ሊደርስ ይችላል አንድ ሰው እያረጀ ሲሄድ ፀጉሩ ይቀጥናል፡፡ የጥቂት ማይክሮኖች መቀነስ ብዙም ለውጥ የሚያመጣ ላይመስል ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ 100,000 የሚያክሉ ፀጉሮች መኖራቸውን አትዘንጉ፡፡ ስለዚህ ነጠላ ፀጉሮች በትንሹ እንኳን ቢቀጥኑ በጠቅላላው የፀጉር ብዛት ላይ የሚያስከትለው ለውጥ ከፍተኛ ይሆናል፡፡

ለፀጉር እንክብካቤ ማድረግ

ፀጉር በየወሩ 10 ሚሊ ሜትር ያህል ያድጋል፡፡ ፈጣን ዕድገት ካላቸው የሰውነት ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ የሰውነት ፀጉሮች ዕድገት በሙሉ አንድ ላይ ቢጀመር በየቀኑ 20 ሜትር ያህል ያድጋል ማለት ነው፡፡

ለሽትና ለራስ በራነት ፍቱን የሆነ መድሃኒት ገና ያልተገኘ ቢሆንም ያለንን ፀጉር ለመንከባከብ ብዙ ልናደርግ የምንችለው ነገር አለ፡፡ በቂና የተመጣጠነ ምግብ መመገብና የራስ ቅል በቂ የደም ዝውውር እንዲያገኝ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከመጠን በላይ ምግብ መቀነስ ወይም የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ ሽበትና የፀጉር መሳት ሊያፋጥን ይችላል፡፡ አዘውትረን ፀጉራችንን መታጠብና የራስ ቅል ቆዳን በጥፍር ሳይቧጥጡ ጥሩ አድርጎ ማሸት ጥሩ እንደሆነ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ይህን ለማድረግ የራስ ቅል ጥሩ የደም ዝውውር እንዲያገኝ ያስችላል፡፡ ፀጉራችሁ በሳሙና ወይም በሻምፖ ከታጠባችሁ በኋላ ጥሩ አድርጋችሁ አለቅልቁት፡፡

ፀጉራችሁን በኃይል አታበጥሩ፡፡ ፀጉራችሁ ረዥም ከሆነ መጀመሪያ ላይ ከስራ ጀምሮ እስከጫፍ አለማበጠር ጥሩ ይሆናል፡፡ ከዚህ ይልቅ በመጀመሪያ ፀጉራችሁን መሀል ላይ ይዛችሁ ጫፍ ጫፉን በማበጠር አፍታቱት፡፡ ቀጥላችሁ ከመሀል አንስታችሁ እስከ ጫፍ አበጥሩ፡፡ በመጨረሻም ፀጉራችሁን ወደታች ልቀቁትና ከስር እስከ ጫፍ አበጥሩት፡፡

ፀጉራችሁ ሸብቶ ስታዩት ወይም ሲረግፍ ሊያሳስባችሁ ይችላል፡፡ ቢሆንም የፀጉራችሁ ሁኔታ አብዛኛውን ጊዜ እናንተን የማያሳስባችሁን ያህል ሌሎችን እንደማያሳስብ አስታውሱ፡፡ ፀጉራችሁን ቀለም መቀባት፣ ሰው ሰራሽ ፀጉር ማድረግ ወይም ህክምና ማድረግ ተፈልጎ ይሆናል፡፡ እንዲህ ማድረጉ ለእናንተ የተተወ ነው፡፡ የፀጉራችሁ ቀለም ምንም አይነት ይሁን ወይም ምንም ያህል ፀጉር ይኑራችሁ ዋና አስፈላጊው ነገር በንፅህናና በስርዓት መያዛችሁ ነው፡፡


Health: ኮሌስትሮልን መቀነሻ ክትባት እየመጣ ነው

$
0
0

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም | ለዘ-ሐበሻ

በልብና ደም ቧንቧ ጤንነት ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያመጣውን ኮሌስትሮልን ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ ሲውል ለዓመታት የቆየውን ስታቲን የተሰኘ መድሃኒት ያስንቃል የተባለ መድሃኒት ከወራት በፊት ይፋ ተደርጎ ነበር፡፡
cholestrol vaccin
ይህ ዜና ሳይበርድ ከሰሞኑ ደግሞ፣ በኮሌስትሮል ላይ የተጀመረውን ዘመቻ የበለጠ ያጠናክራል የተባለ የምርምር ዜና ወጥቷል፡፡ መጥፎ የሚባለውን የኮሌስትሮል አይነት ለመቆጣጠር የሚያስችል ክትባት ለሰዎች ለማቅረብ ጫፍ መድረሳቸውን ተመራማሪዎች አስታውቀዋል፡፡ የዝግጅት ክፍላችንም አዲሱን ተስፋ ከቀደሙት የኮሌስትሮል መፍትሄዎች ጋር አዋህዶ እና ዘላቂ ኮሌስትሮልን የመከላከያ መፍትሄ ሐሳቦችን ጨምሮ ተከታዩን ፊቸር አዘጋጅቷል፡፡

የኮሌስትሮል ጣጣዎች
ኮሌስትሮል በተፈጥሮው ክፋት ያለው ቅባት አይደለም፡፡ የተለያዩ የጾታዊ ሆርሞኖችን ጨምሮ ሌሎችም የሚዘጋጁበት ንጥረ ነገር በመሆኑ፣ ለሰውነታችን እጅግ በጥቂት መጠኑ ያስፈልገዋል፡፡ ኮሌስትሮል ከተለያዩ ምግቦች ወደ ሰውነት ዘልቆና ከመጠን አልፎ ሲጠራቀም ግን የደም ቧንቧዎች ግድግዳና መንገዳቸው ላይ በመለጠፍና መንገዱን በማጥበብ፣ ደም እንደልቡ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንዳይደርስ ያግዳል፡፡ በዚህ ምክንያትም ለህዋሳቶች በህይወት መቆየት ወሳኝ የሆኑት ንጥረ ነገሮችና ኦክስጅንም አይሄዱም ማለት ነው፡፡
በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስና ኦክስጅን ማጠርን ተከትሎ የሚመጣው ስትሮክ፣ ከፍተኛ የደም ግፊትና ተያይዘው የሚመጡት እንደ ኩላሊት ድክመት አይነት ክፉ ህመሞችም ከሚከሰቱባቸው መንስኤዎች ዋነኛውም ይኸው የኮሌስትሮል ጠንቅ ነው፡፡ በዋናነት ሁለት አይነት የኮሌስትሮል መልኮች ያሉ ሲሆን፣ ከፍተኛ ግዝፈት ያለውና ዝቅተኛ ግዝፈት ያለው ኮሌስትሮል ተብለው ይከፈላሉ፡፡ ለጤና አደገኛ የሚባለው ዝቅተኛ ግዝፈት ያለው (ሎው ዴንሲቲ ሊፖፕሮቲን) የሚባለው ነው፡፡

የቀደሙት መድሃኒቶች
መጥፎ የሚባለው የኮሌስትሮል አይነት እንዲቀንስ በማድረግ፣ ከፍተኛ አስተዋፅኦን ለህሙማን ለመስጠት ከገበያ የተቀላቀለው ስታቲን የተሰኘው መድሃኒት የበርካቶች መድን ሆኖ ቆይቷል፡፡ በአንዳንድ ባለሞያዎች ከካንሰርና ሌሎች ጤና ችግሮች ጋር የተያያዘ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዳሉት እየተገለፀ ሲፃፍ የቆየ ቢሆንም፣ ከሚሰጠው ከፍተኛ ጥቅም አንፃር የሚነሱት የጎንዮሽ ጉዳቶች እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም ሲሉ በተቃራኒው የሚሞግቱት በርካታ ናቸው፡፡

ሳኖፊና ሪጂነሮን የተሰኙት የመድሃኒት አምራቾች ያቀረቡት፣ አዲሱ የኮሌስትሮል መድሃኒት ኮሌስትሮልን በከፍተኛ ፍጥነት የመቀነስ አቅሙ በስፋት እየተወሳ ነው፡፡ በመድሃኒቱ ቅመማው ሂደት በተደረጉ ጥናቶች መድሃኒቱ የኮሌስትሮል መጠንን እስከ 40 በመቶ በመቀነስ አቅሙን አሳይቷል፡፡ መጥፎ የሚባለውን አይነት መጠን ከደም ውስጥ በፍጥነት መቀነስና የመልካሙን ኮሌስትሮል አይነት መጠን መጨመር በዋናነት መድሃኒቱ የሚሰራው ተግባር ነው፡፡ ከእነዚህ መድሃኒቶች ተከትሎ የመጣውና በተለይ ከስታቲን ጋር ቢሰጥ ውጤቱ እጅግ አመርቂ ይሆናል የተባለ ክትባትን የማግኘቱ ዜና ከፍተኛ ትኩረትን ከሰሞን አግኝቷል፡፡

አዲሱ የክትባት ተስፋ
ከሰሞኑ ቫክሲን በተባለው የምርምር ጆርናል ላይ በወጣ ጥናታቸው፣ የክትባት ተስፋን ይዘው የመጡት በኒው ሜክሲኮ ዩኒርሲቲ የሞለኪውላር ጀነቲክስ ሳይንቲስቶች የክትባት ሐሳቡን በአይጦችና ጦጣዎች ላይ ሞክረው፣ ኮሌስትሮልን በመቀነስ መልካም ውጤት መገኘታቸውን አብስረዋል፡፡ ከጥናቱ መሪዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ብራይስ ቻከሪያን እንደሚገልጡት፣ ለበርካታ ህመሞች መንስኤ የሆነው ዝቅተኛ ግዝፈት ያለው፣ ኮሌስትሮልን ተሸካሚ ለፓፕሮቲን ወይም በተለምዶ ኤል.ዲ.ኤል የሚባለውን ጠንቅ ከደም ውስጥ በመቀነስ ላይ ያተኩራል፡፡ ይህን ለማድረግም የኮሌስትሮል መጠንን የሚቆጣጠር ፕሮቲንን ታሳቢ ያደረገ ክትባት በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ፡፡
የክትባት ዝግጅት ሂደቱ በቀጣይነት ማለፍ ያለባቸው ሂደቶች ሁሉ የሚሳኩ ከሆነ፣ በርካቶች በአነስተኛ ዋጋ የኮሌስትሮል መቀነሻ የህክምና መፍትሄን ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ ይህን ሐሳብ የሚያብራሩት የጥናቱ ባለሞያ ዶ/ር ብራይስ፣ ‹‹ከልብና ደም ቧንቧ ህመሞች በአብዛኛው ያደገው ሀገር ችግር ተደርገው ይቆጠሩ ነበር፡፡ በገቢም የተሻሉ ስለሆኑ እነዚህ ሰዎች እንደ ስታቲን እና መሰል መድሃኒቶችን በውድ ዋጋ ለመግዛት የሚችሉ ናቸው፡፡ በአዳጊ ሀገራት ግን ይህ ፈታኝ ነው፡፡ ክትባቱ ሲቀርብ በአነስተኛ ዋጋ ስለሆነ የዋጋ ጫናን ጭምር ለአዳጊ ሀገራት ይቀንሳል›› ይላሉ፡፡

አጠቃላይ ምክሮች
– በኮሌስትሮል ምክንያት የሚመጡ ህመሞች ተጋላጭነትዎን መቀነስ ይችላሉ፡፡ ይህን ለማሳካት ከሚያስችልዎት እርምጃ መካከልም ሲጋራ አለማጨስ፣ በሚችሉት ጊዜ ሁሉ የአካል እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት ማድረግ፣ አልኮል መጠጦችን አለመዳፈር፣ በተለያየ መልክ ቅባት ያላቸውን ምግቦች በልክ ማድረግን በዋናነት በባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡

– በየጊዜው የኮሌስትሮል መጠንዎን ከአጠቃላይ የጤና ምርመራ ጋር በማድረግ፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል ያሰጋዎት እንደሆነ መረዳትና ከሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ምክሮች ከባለሞያ የመድሃኒት ትዕዛዝ ጋር በመውሰድ፣ በጊዜ ችግሩን መግታት የሚችሉበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡
 
 

Health: ህፃናት ከልክ በላይ መወፈራቸው ለምን ያሳስበናል? |ለህፃናት የሚመከሩ ምግቦች

$
0
0

 

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም | ለዘ-ሐበሻ

ዛሬ ላይ ሰዎች በሽታዎችና አደጋዎች ከሚያመጡባቸው ችግሮች እኩል ውፍረት ህይወታቸውን ሌላ መልክ እያስያዘው ይገኛል፡፡ እንደ አሜሪካ ባሉ ሀገራት ደግሞ የዜጎቸውን ህይወት በመንጠቅ ከቀዳማዊ ችግሮች አንዱ  ነው፡፡ ሰዎችን በተለይ አዋቂዎቹን ከቤት ውስጥ በማዋልና ተስፋ በማስቆረጥና በሌሎች ተፅዕኖዎቹ ከልክ ያለፈ ውፍረት ዋነኛው የዓለማችን ማህበራዊ ችግር ወደ መሆን እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡ ችግሩ አሁን ላይ የወጣቶችና የህፃናትም ጭምር መሆኑ ነው አሳሳቢው ጉዳይ፡፡

baby fat

አንድ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ከ5 እስከ 11 ዓመት በሆናቸው ህፃናት መሀከል ከሚገኙ 3 ህፃናት ውስጥ አንዱ ከልክ ካለፈ የውፍረት ችግር ጋር የሚኖር መሆኑን አመልክቷል፡፡ ታዳጊዎች ከልክ በላይ በወፈሩ መጠን የዕድሜ እኩዮቻቸው ብዙ ጊዜ ተጋላጭ ባልሆኑባቸው አንዳንድ በሽታዎች የመጠቃት እድላቸው በእጅጉ ይጨምራል፡፡ እንደ ወላጅ ወይም እንደ አሳዳጊና እንደ መምህር በአንድ ህፃን ህይወት ላይ ሚናቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች አሉ በተለይ ጤናማና የተስተካከለ ክብደት እንዲኖራቸው ለማድረግ፡፡ በዚህ ረገድ ህጻናቱ ጤናማ ምግብ መመገባቸውን እርግጠኛ መሆንና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በማበረታታት ሊሆን ይችላል ሚናቸውን የሚወጡት፡፡

የህፃናት ውፍረት አደጋ በኢትዮጵያ

ልጅን በሚገባ ለማሳደጋቸውና የሚፈለገውን ለማሟላታቸው ብዙ ጊዜ ወላጆች እንደምስክርነት የሚያቀርቡት ድንቡሽቡሽ ያሉትንና ከልክ በላይ የወፈሩትን ልጆቻቸውን ነው፡፡ ታዛቢውም ቢሆን ‹‹እንዴት ቢንከባከቡት ነው እንዲህ የፋፋ ልጅ ያደረሱት?›› የሚለውን ጥያቄ መሰንዘሩ አይቀርም፡፡ በአጠቃላይ አቅሙና አቅርቦቱ እስካልተስተጓጎለ ድረስ ልጅን ማደለብ ባህል እንደሆነ አለ፡፡

በሀገራችን ወላጆች በውፍረት ሳቢያ በልጆቻቸው ላይ ሊመጡ ስለሚችሉ አካላዊና አዕምሯዊ ችግሮች ላይ በቂ ትኩረት ይሰጣሉ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከልክ በላይ የወፈሩ በርካታ ህፃናትን እንደልበ እንድንመለከት ምክንያት እንደሆነ ነው የፊትነስና የጤናማ አመጋገብ ባለሙያዋ የትናየት ታምራት የምትናገረው፡፡ በግል የማማከርና ተግባር ልምምዶችን ስትሰጥ በቆየችባቸው ባለፉት 6 ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንኳን እርዳታዋን የሚፈልጉ ከልክ በላይ የወፈሩ ህፃናት ቁጥር በአስደንገጭ ቁጥር ጨምሯል፡፡ ወላጆች ግንዛቤ ጨምሯል፡፡ ወላጆች ግንዛቤ ኖሯቸው ይሁን ሳይኖራቸው ለልጆቻቸው ጤናማ አካላዊ ገፅታ ከፍተኛ ትኩረት እየሰጡ አይገኙም፡፡

ህፃናት ከልክ በላይ መወፈራቸው ለምን ያሳስበናል?

ልጆቻቸው ከልክ በላይ መወፈራቸውን ተከትሎ ወላጆችን ሊያሳስባቸው የሚገቡ በርካታ ተያያዥ ጉዳዮች አሉ፡፡ በከፍተኛ ውፍረት ውስጥ የሚመደቡት ህፃናት የመገጣጠሚያ እና የመተንፈሻ አካላት ችግሮች ይገጥሟቸዋል፡፡ በተለይ እነዚህ የጤና እክሎች ህፃናቱ እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው ማንኛውንም ተግባር እንዳሻቸው እንዳይፈፅሙ በመከልከል ከባዱ የአዕምሮ ችግር ውስጥ ይከታቸዋል፡፡

አንዳንዱ ህፃናት ደግሞ ከከፍተኛ ውፍረት ጋር ቀጥታ ተዛምዶ እንዳላቸው ለሚታወቁት የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ ደም ግፊት እና ከፍተኛ ኮሌስትሮል ይጋለጣሉ ዕድሜአቸው በተወሰነ ደረጃ እየጨመረ በመጣ ጊዜም የልብ ችግር እና በርካታ የካንሰር አይነቶች የጤና ስጋቶቻቸው ይሆናሉ፡፡

ህፃናት ጤናማ አመጋገብን እንዲዋሃዱ ምን ማድረግ ይገባል?

– የህፃናትን የተበላሸ የሚባል የአመጋገብ ልማድ ወደ ጤናማ መስመር ለማምጣት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴም እንዲያዘወትሩ የወላጆች እና የአሳዳጊዎች ሚና ዋነኛው ነው፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን ተግባራት መፈፀም ይመከራል፡፡

– ምሳሌ ሆኖ መቅረብ የህፃናት አዕምሮ ያየውን ለመቀበል እና ለማመስመሰል የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለዚህ ወላጆችና አሳዳጊዎች በህፃናቱ ፊት ጤናማ የሚባሉትን ምግቦች ማዘውተራቸው በህፃናቱ አዕምሮ ላይ የሚፈለገውን ለውጥ ለማተም ይረዳል፡፡

– ሁሉንም ቤተሰብ ማሳተፍ፡- ከልክ በላይ ውፍረቱ የአንድ ህፃን ችግር ቢሆንም ዘላቂ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ ከሆነ ሁሉንም የቤተሰብ አባላት ያሳተፈ የአመጋገብ ባህል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ነው፡፡

– ከህፃናት ሊርቁ የሚገባቸው ምግቦችን መለየት

– በካሎሪ፣ ስኳር እና ጨው ክምችታቸው ከፍተኛ የሚባሉትን ምግቦችና መጠጦች ለምሳሌ ቺፕስ፣ ኩኪሶች፣ ጥብሶችና ከረሜላዎች የተቀነባበሩ ጣፋጭ መጠጦች ይገኙበታል፡፡ ከዚህ ባለፈ በፋብሪካ የተቀነባበሩትን እንደሩዝ እና ፓስታ ያሉትን ምግቦችም ህፃናቱን ማራቅ ይመከራል፡፡

ለህፃናት የሚመከሩ ምግቦች

ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶች፣ ለውዝ እና ዝቅተኛ ፉት ያላቸውን ወተቶች እና የወተት ውጤቶች፣ ካልሲየም እና ቫይታሚን ‹‹ዲ›› የተጨመረባቸው ቢሆኑ ደግሞ ይበልጥ ይመከራል፡፡ ከዚህ ውጪ ስለ የሚባሉ ስጋዎችን አሳና ሌሎች የባህር ውስጥ ምግቦችን፣ ባቄላ፣ አኩሪአተር እና እንቁላልን ህፃናቶች እንዲያዘወትሩ ማድረግ በጤናቸውና አካላቸው ላይ የምንፈልገውን ለውጥ እንድንመለከት ይረዳል፡፡

ህፃናት ጤናማ አመጋገብን እንዲመርጡ እነዚህ የተቀመጡ አማራጮች ናቸው፡፡

– ህፃናት ስላጠኑ ወይም ለፈፀሙት አንድ ተግባር እንደማበረታቻ ሁልጊዜ ምግብን ባንጠቀም ይመከራል፡፡ ይሄ በተለይ ከልክ ያለፈ ውፍረት ለሚያሰጋቸው ህፃናት ይሰራል፡፡ በምግብ ማበረታታቱ አስፈላጊ ከሆነም ጤናማዎቹን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ለህፃናቱ በሽልማት መልክ ኬክን ጨምሮ ጣፋጮችን ማቅረቡ ከፍተኛ ችግር ያስከትላል፡፡

– ምግብን በትልቁ ከማቅረብ አነስ ባለ መጠን መጀመር፡፡ ህፃናቱ ተጨማሪ ምግብ ካስፈለጋቸው ጥያቄው ከእነርሱ እንዲመጣ መጠበቅ፡፡

Health: ትዳር በሚያስቡ ፍቅረኞች መሀከል የዕድሜያቸው ልዩነት ስንት ይሁን?

$
0
0

በዕድሜ ጎዳና የሚደረግ ጉዞ ከልጅነት እስከ እርጅና ይዞን ይዘልቃል፡፡ በዚህ ሂደትም አንዱን የህይወት ምዕራፍ አጠናቀን ወደ ሌላው ስንሻገር ትዳር የመያዝ ወይም ያለመያዝ አማራጭ በጉዟችን ላይ ይገጥመናል፡፡ በሀገራችን በወርሀ ጥርና በወርሃ ሚያዚያ ብዙ ጥንዶች በዕድሜ ጎዳናቸው እኩሌታ ላይ ከጋብቻ ፌርማታ በመሆን ወደ ትዳር ለመሳፈር ዝግጁ የሚሆኑበት ወቅት ነው፡፡ ተፈጥሮ፣ ባህል፣ አቅም፣ ብስለት እንዲሁም ኃላፊነትን የመሸከም ዝግጁነት ሴቶችና ወንዶች ለትዳር የተለያየ አመለካከት እንዲኖራቸው አድርጎናል፡፡

Maza-wedding-bands

ሴቶች በሀገራችን በአብዛኛው ለመውለድ አልያም ‹‹ቆሞ ቀር›› ለሚባለው አሉታዊ የባህል ተፅዕኖ ላለመዳረግ ሲሉ ዕድሜያቸው 30 ከመሆኑ በፊት ትዳር የመያዝ ፍላጎት አላቸው፡፡ የትዳር ኃላፊነትን ከመሸከም አንጻር ወንዶች ከሴቶች ዘግይተው የመብሰል ነገር ስለሚስተዋልባቸው የወንደላጤነትን ነፃነት ላለማስረከብ ሲሉ እንዲሁም በየትኛውም የዕድሜ ክልል ልጅ መውለድ የመቻልን የተፈጥሮ ስጦታን ከቁጥር በማስገባት፣ ብዙ ወንዶች ትዳርን በለጋ ዕድሜ ከመያዝ ይቆጠባሉ፡፡

የህይወት መሰረታዊ ውሳኔ የሚባለው ትዳርም በሁሉም እምነቶች ዘንድ አይነተኛ ቦታ አለው፡፡ የትዳርም ትርጓሜ ሁለት የሚፋቀሩ ሰዎች ለመዋደድ፣ ለመደጋገፍ እና እስከ ህይወት ፍፃሜ አብሮ ለመኖር በሚያመልኩት ፈጣሪ ፊት ቃል የሚገቡበት እንዲሁም በህግ ፊት አስፈላጊውን ኃላፊነት ለመውሰድ ግዴታቸውን የሚቀበሉበት የጋራ ስምምነት ነው፡፡ በሰዎች ታሪክም የትዳር ፌርማታ አዲስ ገቢዎችን እንደሚያስተናግድ ሁሉ ጉዞን በቃል የሚሉ መንገደኞችንም ያስወርዳል፡፡ የትዳር ጓደኛ በአንድ ሰው የግል ምርጫ የሚወሰን ቢሆንም በአብዛኛው በፍቅር ምሰሶ የተዋቀረ ትዳር ዘላቂነት ይኖረዋል፡፡ በጥንዶች መካከል ያለ አካላዊ ግንኙነት ትዳር ውበቱ ሳይደበዝዝ እንዲቆይ ሲያደርግ የሥጋ ግንኙነትም በትዳር ውስጥ ብቸኛ ሳይሆን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ በአጠቃላይ ያለው ተፈጥሯዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ሁኔታ ወንዶች ትዳር እንዲፈሩና ሴቶች ጋብቻ እንዲፈልጉ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በሴቶች ፍለጋ እንዲሁም በወንዶች ማመንታት የሚፈጠርን ክፍተት ፍቅር፣ ፍቅረ ነዋይ ወይም የጋብቻ አባዜ በማጥበብ ሴቶችና ወንዶች ለጋብቻ ይበቃሉ፡፡

የሴቶች የዕድሜ ጣሪያና ዝቅታ!

ሴቶች በጋብቻ ውስጥ ቤተሰብን ማፍራት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ ስለሆነ ልጅ መውለድ በሚችሉበት የዕድሜ ክልል የሚወዱትን የህይወት አጋር ማግኘትና ማግባት ይፈልጋሉ፡፡

ተፈጥሮ እንደ ወንዶች ለሴቶች በመሆኗ ትዳር በሴቶች ዘንድ 22-30 ባለው የዕድሜ ክልል እንዲፈፀም ይመከራል፡፡ የሴቶች የጋብቻ ዕድሜ እንደ ጊዜው እና እንደ አንድ ሀገር ባህል እሴት አንፃራዊ ነው፡፡ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ጥሩ የጋብቻ ዕድሜ ተብሎ የሚታሰበው 15 ዓመት እስከ 24 ዓመት ሲሆን፣ 22 ዓመቷ ያላገባች ሴትም ‹‹ቆሞ ቀር›› ትባላለች፡፡ በአንፃሩ በከተማው አንዲት ሴት ለምሳሌ 22 ዓመቷ ትዳር ብትይዝ ‹‹አልቸኮልሽም?›› ትባላለች፡፡ ስለዚህም 22-30 ያለው የሴቶች የጋብቻ ጊዜ በከተማ የሚስተዋል የአሁን ዘመን አማካይ ዕድሜ ሲሆን፣ 30 ገደብ እስከ 35 ሊበልጥም ይችላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለች ሴት ትምህርት በመሟሯ፣ በስራ ዕድል ተወዳዳሪ በመሆኗ እና የራሷን ገቢ ማግኘት በመቻሏ በወንዱ ላይ ሊኖራት የሚችለውን የገንዘብ ጥገኝነት በከፊል ቀንሶላታል፡፡ ስለሆነም በስራዋ ማግኘት የምትፈልገውን የስኬት ደረጃ ላይ እስከምትደርስ የአሁኗ ዘመን ሴት በአንጻሩ እንደ በፊት ዘመን ሴቶች ትዳርን የማስቀደም አዝማሚያ ብዙም አታሳይም፡፡ በየተያያዥም 21ኛው ክፍለ ዘመን ካፈራቸው እሳቤዎች መሀከል አንዱ የሆነው የሴቶች ከወንዶች የእኩልነት ሃሳብ በሴቶች የጋብቻ ዕድሜ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ ጋብቻ ምርጫቸው ላልሆኑ ሴቶችም እንደ ድሮ ‹‹ቆሞ ቀር›› ከመባልም ይህ እሳቤ ገላግሏቸዋል፡፡ አንዲት ሴት የገንዘብ ነፃነቷን ካረጋገጠች በጋብቻ መታሰርን እና ነፃነቷን ልክ እንደ ወንዱ ላለማጣት ከፈለገች ትዳርን ያለመያዝ ወይም ‹‹ምን አጨቃጨቀኝ፣ እራሴን መቻል እንደው አይሳነኝ›› ብላ ትዳርን በተፈለገው አጋጣሚ የማፍረስ እድሉን የነጻው ኢኮኖሚ ነፃ አስተሳሰብ አመቺ አድርጎታል፡፡ በጥቅሉ ከባህልም፣ ከተፈጥሮም ከብስለትም አንፃር 22-30 ያለው ጊዜ ለሴቶች ወደ ትዳር የሚሳፈሩበት የዕድሜ ፌርማታ መሆኑን ብዙዎች የሚስማሙበት ሃሳብ ነው፡፡ 20ዎቹ፣ 30ዎቹ እንዲሁም 40ዎቹ የዕድሜ ክልል ጋብቻን ፈፅሞ ትዳር መያዝ በሴቶች ላይ የሚያደርሰው ጉዳትና ጥቅም አለው፡፡ 20ዎቹ መጀመሪያ ከወሊድ ጋር ተያያዥ ችግሮች በአነስተኛ ደረጃ ስለሚከሰቱ ለሴቶች የጋብቻ እንዲሁም ለወሊድ አመቺ ዕድሜ ተብሎ የሚታሰበው 24 ዓመት ነው፡፡ ሆኖም 20ዎቹ የዕድሜ ክልል ማግባት ለሴቷ የራሱ ተግዳሮቶች አሉት፡፡ አንዲት ሴት ከጋብቻ በኋላ 20ዎቹ መጀመሪያ ልጅ ብትወልድ ለራሷ ህይወት የምትሰጠውን ትኩረት በመቀነስ ወደ ህፃኑ ታደላለች፡፡ የኋላ ኋላ በባሏ የገንዘብ ድጋፍ ስር ትወድቃለች፡፡ ብዙሃኑ የጋብቻ ስነ ልቦና ባለሞያዎች የሚስማሙበት ግንባር ቀደም የፍቺ መንስኤ የገንዘብ ጉዳይ ነው፡፡ 20ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚከወነው ትዳር ለወሊድ ጥቅም ሲኖረው በተለይ በእኛ ሀገር ያሉ ልጅን የማሳደግ፣ ባልን የመንከባከብ እንዲሁም ትዳርን በፍቅር የማቆየት ኃላፊነቶች እጅጉን ፈታኝ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ 30ዎቹ የዕድሜ ክልል ማግባት ለሴቷ ከወሊድ አንፃር እንደ 20ዎቹ የዕድሜ ክልል ሁሉ የወሊድ ሁኔታዎች ብዙም አመቺ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ሴቷም 20ዎቹ አንፃር በዕድሜ ስለምትበስል በቤት አያያዝና በስረዋ ዙሪያ ጥሩ ብቃት ይኖራታል ተብሎ ይታሰባል፡፡ 40ዎቹ እና ከዛ በላይ የሚፈፀሙ ጋብቻዎች ለሴቷ ከትዳር ከምትፈልገው ስኬት አንፃርም ሆነ ከወሊድ በአብዛኛው ተመራጭ አይሆንም፡፡

የወንዶች የዕድሜ ጣሪያና ዝቅታ

የወንዶች የጋብቻ ዕድሜ 24 አንስቶ የመጨረሻው ወሰን ገደብ የለሽ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ግማሾቹ ሴቶች ወንዶች ማግባት አለባቸው ብለው የሚያምኑት ዕድሜ 30-45 ዓመት ያለውን ጊዜ ነው፡፡ ወንዶች 20-30 ባለው ዕድሜ ትኩረት የሚሰጡት ጉዳይ ለትዳር ሳይሆን በተሰማሩበት ስራ ስኬታማ መሆን የሚያስችላቸውን የገንዘብ አቅም ነፃነታቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ 20-30 ያለው የዕድሜ ክልል ከሴቶች ትዳር የመያዣ ጊዜ ሲሆን፣ ለወንዶች ደግሞ የማንነት ጥያቄ የሚጎለብት መሆኑ በዕድሜ ጎዳና ላይ ሴቶችና ወንዶች ወደ ትዳር የሚያደርጉት አካሄድ አሰነዛዘሩና ፍጥነቱ እንዲለያይ አድርጎታል፡፡ ሴቶች የወንዶች ኃላፊነት የመውሰድ ዝግጁነት ብስለታቸው የሚመጣው በዕድሜ ሳይሆን በአፈጣጠራቸው እና በአስተዳደጋቸው ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ወንደላጤ ሆኖ መቆየት ለበሽታ ከማጋለጡ አንፃር ሲታይ አንዳንድ ወንዶች በጋብቻ የመወሰን ጥቅምን ተረድተው 20ዎቹ አጋማሽ ትዳር በመያዝ በለጋ ዕድሜያቸው አግብተው ስኬታማ ሲሆኑ የሚስተዋሉ ወጣት አባወራዎች አሉ፡፡ ከትዳር ጋር በተያያዘ የብዙዎቹ ወንዶች ጥያቄ የአቅም ጉዳይ ነው፡፡ በሴት እጅ መኖር አልፈልግም የሚል በማህበረሰባችን የሰረፀ አመለካከት በመኖሩ ሳቢያ ማንም ወንድ ትዳር ለመመስረት ብቁ የሚያደርገው የገንዘብ አቅም እስከሌለው ድረስ ጋብቻን ለመፈፀም ያመነታል፡፡ ወንዶች 30-45 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ጋብቻ ቢፈፅሙ ትዳሩን ስኬታማ ከማድረግ አንፃር ጠቀሜታ እንዳለው ብዙ የትዳር ስነ ልቦና ባለሞያዎች ይስማማሉ፡፡ ከዘመነኝነት ጋር በተያያዘ የሴት ዕድሜ በመልኳ፣ የወንድ ዕድሜ በአመለካከቱና በአኗኗር ዘዬው ይለካል ብለው የሚያምኑ ወንዶች 40 ዓመትን እንደ 30 50 ዓመትን እንደ 40 በመቁጠር እና ‹‹50 ዓመቴ እንደ 30 ዓመት ወጣት ማሰብ እስከቻልኩ ችግር የለውም›› በማለት ትዳርን ማዘግየት ይመርጣሉ፡፡ እንደ መደመር የስሌት ህግ ህይወት አንድ ሲደመር አንድ ሁለት ስለመሆኑ እርግጠኛ የማይኮንበት አጋጣሚን ስለሚፈጥር አንዳንድ ሴቶች 35-45 ባለው የዕድሜ ክልል ትዳርን ሲይዙ አንዳንድ ወንዶች 19 ዓመታቸው ወይም 60 ይፈፅማሉ፡፡

በትዳር አጋሮች መሀከል ሊኖር የሚገባ የዕድሜ ልዩነት ስንት መሆን አለበት?

በወንዶችና በሴቶች መሀከል በትዳር ውስጥ ሊኖር የሚገባው የዕድሜ ልዩነት እንደ ሰው ምርጫ ይለያያል፡፡ በሴቶች ዘንድ ተለቅ ያለን ወንድ የማግባት አዝማሚያ በፊትም እንዲሁም አሁን ላይ ያለ ድርጊት ነው፡፡ በፊት ጠና ያለ ወንድ የትዳር አጋር የሚሆንበት አጋጣሚ የባህል ተፅዕኖ ሲሆን በአሁኑ ዘመን ሴቷ ለስኬት፣ ለፍቅር ወይም የተደላደለ ህይወት ፍለጋ ከእርሷ ጠና ያለን ወንድ ለትዳር የምትመርጥበት አካሄድ ይስተዋላል፡፡ በጥቅም የሚመሰረት ትዳርም እድሜን ታሳቢ አያደርግም፡፡ የሀገራችን የቤተሰብ ህግ ‹‹ሀብትሽ ሀብቴ›› የሚል አሰራር ስላለው፣ ህጉም በጋብቻ ወቅት ያለውን የወንዱን ንብረት ሴቷ ከጋቻ በኋላ በሚኖረው ፍቺ እኩል የመካፈል መብትን ይሰጣታል፡፡ በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ ወጣት ሴቶች 20 ዓመት ታላቃቸው ጋር በፍቅር ጭምብል ሽፋን ለገንዘብ ብለው ትዳር ይፈጽማሉ፡፡ በሌላ እይታ ፍቺንና የንብረት ክፍፍልን ሰንቆ የተነሳ ትዳር መጨረሻው ምን እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡

ሆኖም በትዳር አጋሮች መሀከል ያለ የዕድሜ ልዩነት በትዳር ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ወንዱና ሴቷ ከተለያየ ትውልድ ውስጥ ከሚመደብ የዕድሜ ክልል ከሆኑ በቀላሉ ለመግባባት ይቸግራቸዋል፡፡ በፊተኛው ትውልድ ውስጥ ከሚመደብ የዕድሜ ክልል ከሆኑ በቀላሉ ለመግባባት ይቸግራቸዋል፡፡ በፊተኛው ትውልድ ውስጥ የነበረ ቀልድ በአሁኑ ትውልድ አመለካከት ከአዝናኝነቱ ይልቅ አናዳጅነቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ሌላው ችግር በወሲብ አለመጣጣም ሲሆን ለምሳሌ ያህል ሴቷን ወደ ሌላ የዕድሜ አቻዋ እንድታዘነብል ሊያደርጋት ይችላል፡፡ ይህንን ከግምት በማስገባት በትዳር አጋሮች መሀከል በአማካይ 3-5 ዓመት የዕድሜ ልዩነት ቢኖር ይመረጣል፡፡ በሴቶችም ዘንድ በዕድሜ የሚልቁትን ወንድ የማግባት አዝማሚያ አለ፡፡ በማዘዝና በመፍራት ያደገች ሴት ከእድሜ ታላቅ ይልቅ ታናሽዋን ለማግባት ትመርጣለች፡፡ ለአንዳንዶቹ ዕድሜ የብስለት መለኪያ ሲሆን ለአንዳንዶች ዕድሜ አንድ ብሎ እስከ መቶ እንደሚቆጠር አሃዝ ነው፡፡ በተለያየ የአመለካከት አድማስ ስር ባሉ ሰዎች ዘንድ በአሁኑ ጊዜ ዕድሜ ትዳርን ከመያዝ አኳያ ይህን ያህል ቦታ አይሰጠውም፡፡ ህይወት በቀመር ተካፍሎ ተባዝቶ ተደምሮና ተቀንሶ በትክክል የሚመጣ አይደለም ብለው ስለሚያምኑ አንዳንዶች ትዳርን ብዙሃኑ በሚስማማበት የወንድና የሴት የዕድሜ ክልል ጋብቻ ለመፈፀም አይጨነቁም፡፡ የህይወት ፍሰት በራሱ ጊዜ ከጋብቻ ፌርማታ አድርሶ ወደ ትዳር ዓለም ያሳፍራል ብለው ስለሚያምኑ ትዳርን በተጠቀሰው የዕድሜ ክልል ጋብቻ ለመፈፀም አይጨነቁም፡፡ የህይወት ፍሰት በራሱ ጊዜ ከጋብቻ ፌርማታ አድርሶ ወደ ትዳር ዓለም ያሳፍራል ብለው ስለሚያምኑ ትዳርን በተጠቀሰው የዕድሜ ክልል ለመያዝ ሃሳብ አይገባቸውም፡፡

ከአሸወይና ማዶ

የሴቶችን እንዲሁም የወንዶችን አማካይ ዕድሜ ባገናዘበ ይሁን ባላገናዘበ መልኩ በአገራችን የሚስተዋለውን የጋብቻ ተሳፋሪዎች ቁጥር ማስተዋልአዳጋች አይሆንም፡፡ ይህም ቁጥር በተጨባጭ የሚታየው በየዓመቱ በየዕድሜያችን ጎዳና የሚፈራረቁት የወርሃ ጥር እና የወርሃ ከሚያዝያ የጋብቻ ፌርማታ ተሳፋሪዎች ብዛት ነው፡፡ በመኪና ጢሩንባ፣ በእጅ ጭብጨባ እና እልልታ እንዲሁም በሃይማኖታችን እስከ ህይወታችን ፍጻሜ በታማኝነት፣ በመቻቻል፣ በመደጋገፍ በመዋደድ ለመጽናት ምለን ጋብቻችን እንፈጽማለን፡፡ ከአሸወይናው ማዶ ያለውን የትዳር የህይወት ጎዳናን ፍቅር እና መቻቻል የተቃና እንዲያደርገው ከአባትና ከእናቶቻችን የምንለማው ነገር ነው፡፡

በዕድሜ፣ በፍቅር፣ በአመለካከት የልባችን ምርጫ የሆነችን እንዲሁም 20 ዓመታት በኋላም ቢሆን ልናፈቅራቸው እንደምንችል እርግጠኛ የምንሆንበትን አጋር ማግባት ትዳርን እንዲጸና ከማድረጉ ባሻገር በትዳር ፌርማታ ተሳፍረን ባለመግባባት ፌርማታ ከመውረድ ይታደገናል፡፡

Health: የትልቁ አንጀት ካንሰር ምልክቶችና ህክምናው

$
0
0

 

colon cancer

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም |  ለዘ-ሐበሻ

የትልቁ አንጀት ካንሰር እንደ ሌሎች ካንሰሮች ሁሉ፣ ራሱን ሰውነት ውስጥ በማባዛትና በማሰራጨት ሌሎች አካላቶቻችን ስራ እንዳይሰሩ በሚያደርግበት ጊዜ የሚከሰት ነው፡፡

የትልቁ አንጀት ካንሰር በአመዛኙ፣ ከ50 እስከ 70 ዓመት ዕድሜ በሆኑ ሰዎች ላይ የሚታይ ሲሆን፣ አንዳንዴ ከዚህ የዕድሜ ክልል ዝቅ ብሎም ሊከሰት ይችላል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ከ20 እስከ 40 ዓመት ዕድሜ በሆኑ ወጣቶች ላይ በብዛት እየታየ ነው፡፡ ለዚህ መንስኤው ምን እንደሆነ በጥናት የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡ ወደፊት ሰፊ ጥናት ተደርጎ ምክንያቱን ማወቅና መጠንቀቅ ያስችለናል ብዬ አስባለሁ፡፡

የትልቁ አንጀት ካንሰር በአደጉት ሀገራት ከሴቶች የጡት ካንሰር በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ በወንዶች ላይ በአንደኝነት በሴቶች ላይ ደግሞ በአራተኛ ደረጃ ይከሰታል፡፡

በዓለማችን በአማካይ በዓመት አንድ ሚሊየን ሰዎች በበሽታው ይጠቃሉ ተብሎ ሲገመት፣ ከእነዚህም ግማሽ የሚሆኑት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከበሽታው ይድናሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡

አጋላጭ ምክንያቶቹ

ዕድሜ በጨመረ ቁጥር ለበሽታው የመጋለጥ ዕድል አለ፡፡ ስለዚህም ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ግለሰቦች ሁሉ ቅድመ ካንሰር ምርመራ ቢያደርጉና በሽታው ሊሆኑ የሚችሉ ምልክቶችን ካስተዋሉ ቶሎ ሐኪም ዘንድ ቀርበው መታየትና በግልፅ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡

የትልቁ አንጀት ካንሰር ሴቶችም ወንዶችም ላይ ቢከሰትም፣ ከሴቶች ይልቅ በብዛት በወንዶች ላይ ይከሰታል፡፡

አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረትና አመጋገብ፣ እንደ ማንኛውም ያለፈ ውፍረትና አመጋገብ፣ እንደ ማንኛውም ካንሰር ትልቁን አንጀት ለካንሰር ሊያጋልጠው ይችላል፡፡

በበሽታው የተጠቃ የቤተሰብ ወይም የቅርብ ዘምድ መኖር ወይም የረዥም ጊዜ የአንጀት ቁጣ መደጋገም በበሽታው አማጭነት ይታወቃል፡፡

ምልክቶቹ

የትልቁ አንጀት ካንሰር ምልክቶች እንደ በሽታው ደረጃ እና በሰውነታችን ውስጥ ባለው የስርጭት መጠን ይለያያል፡፡

በሽታው ሲጀማምር ከተለመደው ወጣ ያለ የሆድ ድርቀት፤

የሰገራ መቅጠን ወይም ደም እና ንፍጥ የቀላቀለ የረዥም ጊዜ ተቅማጥ

በእርግጥ እነዚህ ምልክቶች በሌላ በሽታ ምክንያት ለምሳሌ በአንጀት ውስጥ ትላትሎች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ምልክቶቹ ታዩ ማለት የትልቁ አንጀት ካንሰር ነው ማለት አይደለም፡፡ ባለሙያ ጋ ቀርቦ በአግባቡ መታየትና መመርመር ያስፈልጋል፡፡

– ከሰገራ በኋላ ደም መኖር

– የሆድ እብጠት፣

– ከፍተኛና ተደጋጋሚ ቁርጠት፣

– ደረጃው እየገፋ በሚሄድበት ጊዜ የምግብ ፍላጎትና የክብደት መቀነስ፣

– የድካም ስሜት

– የጀርባ ህመም እና ሰገራ ለመቀመጥ መቸገር ሊኖር ይችላል፡፡

ህክምናው

አንድ ታማሚ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶችን ሲያሳይና፣ የህክምና ባለሙያው የትልቁ አንጀት ካንሰር ሊሆን ይችላል ብሎ ካሰበ፣ ይሄን ለማረጋገጥና ደረጃውን ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራዎችን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም ከዕጢው ላይ ናሙና ወስዶ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ይሄን ለማድረግም በፊንጢጣ በኩል የሚገባ መሳሪያ ወይም ቀዶ ጥገና ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ቀዶ ጥገናው አንድም በሽታውን ለማረጋገጥ እንዲሁም በሽታውን ለማከም ይረዳል፡፡

በሽታው ከተረጋገጠ በኋላ ደረጃውን ለማወቅና ህክምና ለማስጀመር ተጨማሪ ምርመራዎችን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ እነዚህም፡-

– የሆድ አልትራሳውንድ

– ሲቲስካን

– ኤም አር አይ

– የደረት ራጅ

– የተለያዩ የደም ምርመራዎች

የትልቁ አንጀት ካንሰር ህክምና፣ እንደ በሽታው ደረጃ የናሙና ውጤት፣ እንደ በሽተኛው ዕድሜና አቋም እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች ይለያል፡፡ ስለዚህ የተለያዩ የህክምና ዘዴዎች ሲኖሩት ከኦፕሬሽን በተጨማሪ ኬሞቴራፒ፣ የጨረር ህክምና እንዲሁም በሀገራችን ባይለመድም ታርጌትድ ቴራፒ የተባ ህክምናዎች አሉ፡፡

የትኛውን ህክምና መጠቀም አለብን ለሚለው፣ እንደ በሽታው ደረጃ፣ እንደ ባለሙያውና እንደ በሽተኛው ውሳኔ ይለያያል፡፡ ባለሙያው እና በሽተኛው ስለ ጉዳዩ በጥልቀት መወያየትና በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

በሽታው ደረጃ አንድ ወይም ሁለት በሚሆንበት ጊዜ ኦፕሬሽን በቂ ሲሆን፣ የናሙናው ውጤት ታይቶ እንደ አስፈላጊነቱ ኬሞቴራፒ ሊጨመር ይችላል፡፡

ደረጃ ሶስት ላይ በብዛት ኦፕሬሽን በኋላ ደግሞ ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ ያስፈልገዋል፡፡

በሀገራችን ህክምና አሁን በደረሰበት፣ ደረጃ አራት የአንጀት ካንሰር በሽታን ሙሉ በሙሉ ማዳን ይከብዳል፡፡ እነዚህ በሽተኞች በዋነኛነት የሚታከሙት ኬሞቴራፒ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ህመሙን ለመቀነስና በሽታውን ለመቆጣጠር Radiotherapy Surgery የህክምና አማራጭ ልንጠቀም እንችላለን፡፡

እዚህ ጋ መገንዘብ ያለብን፣ የትልቁ አንጀት ካንሰር በቶሎ ከተገኘ /ደረጃው ሳይገፋ/ እና አስፈላጊው ህክምና ከተደረገለት እንደ ማንኛውም በሽታ ሙሉ በሙሉ መዳንይችላል፡፡ ይሄ እንዲሆን ደግሞ የበሽታው ምልክት ከታየ ቶሎ በሐኪም መታየትና የቅድመ ካንሰር ምርመራ (screening) ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

እንዴት መከላከል እንችላለን?

የትልቁ አንጀት ካንሰርን ለመከላከል፣ በተቻለ መጠን ጤናማ የአመጋገብ እና የህይወት ዘይቤ መከተል ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ ይኼም ማለትየአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ክብደትን መቆጣጠር፣ አልኮልን አብዝቶ አለመጠጣት፣ አለማጨስ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አዘውትሮ መመገብ ማለታችን ነው፡፡

በእኛ ሀር ባይለመድም ቅድመ ካንሰር ምርመራ በኋላ ሊመጣ ከሚችል በሽታ እጅግ ተመራጭ ቅድመ ጥንቃቄ ዘዴ ነው፡፡

Health: በወንድ ዘር ፍሬ ማመንጫ ላይ የሚከሰት እብጠት (ለወንዶች ብቻ!!)

$
0
0

ask your doctor zehabesha

መንስኤውና መፍትሄው ምንድን ነው?

(ከባለሙያ ጋር የተደረገ ውይይት)

 

በወንድ የዘር ፍሬ ማመንጫዎች (ቆለጥ) ላይ የሚፈጠር እብጠት በሽታ ወይስ የበሽታ ምልክት? በሽታ ከሆነ መንስኤው ምንድነው? በሀገራችንና በዓለምአቀፍ ደረጃ የችግሩ ስፋት በምን ሁኔታ ላይ የሚገኝ ነው? የጤና ችግሩ በህክምናው ዘርፍ መፍትሄ አለው ወይ? በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ አንድ የህክምና ባለሙያን አነጋግረናል፡፡

 

ጥያቄ፡ስለወንድ ብልት አካላት የተወሰኑ ሐሳቦችን ለውይይት መነሻነት ብናነሳ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡

ዶ/ር፡- ከውጪ የሚታዩት የወሲብ አካላት የወንድ ብልትና ሁለቱን ፍሬዎች ያቀፈው ቆዳ ናቸው፡፡ ከቆዳው ስር ሁለት ፍሬዎች እና በፍሬዎቹ የሚመረተውን የወንድ ዘር (ስፐርም) የሚያቁሩና የሚያስተላልፉ የተጠማዘዙ ቱቦዎች (ኤፒዲዲሚስ) አሉ፡፡ ከሰውነት ውስጥ ደግሞ የፕሮስቴት ዕጢ፣ ቫዝ ደፈረንስ እና የሴሚናል ቬሲክል ዕጢዎች ናቸው፡፡

ብልት ዋና የወሲብ አካል ሲሆን ያልቆመው ብልት በአማካይ 9 ሣንቲ ሜትር ይረዝማል፡፡ ወደ ጎን ደግሞ 3 ሣ.ሜትር ይሆናል፡፡ በደንብ በሚቆምበት ጊዜ ደግሞ በአማካይ እስከ 13 ሣንቲ ሜትር ርዝመት ወደ ጎን ደግሞ እስከ 4 ሣንቲ ሜትር ይሰፋል፡፡ ይሄ በአማካኝ ሲሆን ከዚህ ያጠረም ወይም የረዘመው ብልት ያላቸው ይኖራሉ፡፡ በብልቱ ውስጥ ያሉት ደም ስሮች በወሲብ ጊዜ በደም ስለሚሞሉ መቆምን ወይም መገተርን ያስከትላሉ፡፡

ሁለቱ የሴሚናል ቬሲክል ዕጢዎች እና የፕሮስቴት ዕጢ የሚያመርቱት ፈሳሽ ከፍሬዎቹ ከሚመረተውና በቫዝ ዲፍረንስ ቱቦ በሚጓጓዝ ስፐርም ጋር በመቀላቀል በወሲብ ጊዜ በብልቱ የሚወጣውን ፈሳሽ (ሲመን) ይፈጥራሉ፡፡ የዚህ ፈሳሽ ሁለት በመቶ የስፐርም ህዋሳት ሲሆኑ 98 በመቶ ደግሞ በሁለቱ ዕጢዎች የተመረተው ፈሳሽ ነው፡፡ ሁለቱ ፍሬዎች ስፐርም ከማምረታቸውም ሌላ ቴስቴስትሮን የሚባል ኬሚካልም በማምረት የወንድ ባህሪን እንዲጎለብት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡

 

ጥያቄ፡በወንዶች የዘር ፍሬ ማመንጫ ላይ የሚከሰተው ካንሰር ያልሆነ እብጠት ራሱን የቻለ በሽታ ነው ወይስ የሌሎች በሽታዎች ምልክት ነው?

ዶ/ር፡- በሽታ የሚባለው ነገር የአንድን ሰው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚያውክና ስቃይ ያለው ህመምን የሚያመጣ ነገር ነው፡፡ በቆለጥ ላይ በአንድ በኩል ከራሱ የሚነሳ ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶች ይፈጠራሉ፡፡ የዘር ፍሬ ላይ የሚፈጠሩ እብጠቶች የሰዎችን የጤና ሁኔታ ያቃውሳሉ፡፡ የዕለት ተዕለት ስራንም ያውካሉ፡፡ ከዚህ መሰረታዊ ሁኔታ በመነሳት የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ የሚከሰቱ ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶች ራሳቸውን የቻሉ በሽታዎች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከሌሎች የአካል ክፍሎች የሚነሱ የጤና ችግሮች በዘር ፍሬ ማመንጫዎች ላይ እብጠትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

 

ጥያቄ፡በወንዶች ዘር ፍሬ ማመንጫ ላይ ከሚከሰቱ ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶች ዋና ዋና የሚባሉትን ቢገልፁልኝ?

ዶ/ር፡- ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶች በዘር ማመንጫ ፍሬዎ ላይ ይከሰታሉ፡፡ ዋና ዋና የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡

– አንጀትን ሰብስቦ የሚይዘው ሽፍን ላይ ክፍተት ሲፈጠር አንጀት የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎቹን ወደሚይዘው ከረጢት ውስጥ በመግባት እብጠት እንዲፈጠር ያደርጋል፤

– የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎችን የሚይዘው ከረጢት በተለያዩ ፍሳሾች ሲሞላ በየጊዜው መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ እብጠትን ያመጣል፤

– በቫይረስ፣ በፈንገስና በባክቴሪያ አማካኝነት የተለያዩ ኢንፌክሽኖች በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ ሲከሰት እብጠት ይፈጠራል፤

– በመኪናም ሆነ በሌላ ምክንያት የሚመጣ የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ መመታትን (መቀጥቀጥን) ካደረሰ እብጠት ሊከሰት ይችላል፤

– ለብዙ ሰዓት የሚቆሙ ወይም እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ላይ በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ውስጥ ያሉ ደም መላሽ ደም ስሮች ተቋጥረው እብጠትን ያመጣሉ፡፡

– የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎቹ በራሳቸው ተሽከርካሪው በመታነቃቸው ምክንያት የደም ዝውውር ስርዓቱ ይታወካል፡፡ በዚህ ጊዜ እብጠት ይከሰታል፡፡

– በኢንፌክሽን ምክንያት የዘር ፍሬዎች መሸፈኛ ከረጢት ሊያብጥ ወይም መግል ሊይዝ ይችላል፡፡

– የዘር ፍሬው መንጭቶ ወደ ማጠራቀሚያው እስኪደርስ ድረስ ያለው ቱቦ (ቧንቧ) ካንሰር ያልሆኑ ዕጢዎች ሊበቅሉበት ይችላል፤

– የዘር ፍሬ ማስተላለፊያ ቱቦ በተለያዩ ምክንያቶች ሲቆጣ እብጠት ይፈጠራል፡፡ በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ ከላይ የዘረዘርኳቸው ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶች ይፈጠራሉ፡፡

 

ጥያቄ፡የእብጠቱ መንስኤ ምንድነው ይላሉ?

ዶ/ር፡- ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶች በዘር ማመንጫ ፍሬዎች ላይ እንዲፈጠሩ መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮች ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያለማቋረጥ በብዛት የሚስሉ፣ ከፍተኛ ጉልበትን በሚጠይቁ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ እና በዕድሜ ምክንያት ሽንት እምቢ ሲላቸው የሚያምጡ ሰዎች፣ አንጀታቸው ከእምብርት በታች ያለውን አጠንት አልፎ ወደ ዘርፍሬ ከረጢት ውስጥ በመግባት እብጠት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በቫይረስ፣ በፈንገስ እና በባክቴሪያ አማካኝነት በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎና በከረጢቱ ላይ ኢንፌክሽን ይከሰታል፡፡ በዚህም ሳቢያ እብጠት፣ ውሃ መቋርና መግል የመፍጠር ሁኔታ ይኖል፡፡ በተለያየ ምክንያት የሚከሰት አደጋም በዘር ፍሬዎች ላ ካንሰር ያልሆነ እብጠት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል፡፡ ለረዥም ሰዓት መቆም እንዲሁም ለረዥም ሰዓት መንቀሳቀስና ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቁ ስራዎችን አዘውትሮ መስራት ለእብጠቱ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮች ናቸው፡፡

 

ጥያቄ፡እብጠቶች ሲከሰቱ የሚያሳዩት ምልክት ምንድነው?

ዶ/ር፡- ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶች በዘር ማመንጫ ፍሬዎች ላይ ሲከሰቱ የተወሰኑ ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡

– የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ያብጣሉ

– ቀስ በቀስ እየጨመረ የሚሄድ ህመም ይኖራል

– የዘር ፍሬ ከረጢቱ በየጊዜው በመጠኑ እየጨመረ የሚሄድ ውሃ ይቋጥራል

– ሽንት ሲሸና የማቃጠል ስሜት ይኖል

– የሽንት ማጣደፍ ስሜት ይኖራ እና

– ሽንት አሁንም አሁንም መጣሁ መጣሁ የማለት ስሜት መከሰት ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶች በዘር ማመንጫ ፍሬዎ ላይ ሲከሰቱ ከሚታዩ ምልክቶች ዋና ዋና የሚባሉት ናቸው፡፡

 

ጥያቄ፡በወንዶች ዘርፍሬ ማመንጫ ላይ ከሚከሰቱ ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶች ከግብረ ስጋ ግንኙነት ጋር ያላቸው ግንኙነት ምንድነው?

ዶ/ር፡- አንዳንድ ሰዎች በአንድ ጊዜም ይሁን በተለያዩ ቀናት ደጋግሞ ወሲብ መፈፀም የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎችን ያሳብጣል ብለው ያምናሉ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ትክክል አይደለም፡፡ ወሲብን ደጋግ መፈፀም ከዘርፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች እብጠት ጋር የሚገናኝበት ሁኔታ የለም፡፡ ነገር ግን በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ኢንፌክሽን ካለ የዘር ፍሬዎችንም ሆነ የዘር ፍሬ ከረጢቱን ማጥቃቱ የማይቀር እንደሆነ መገንዘብ ጠቃሚ ይሆናል፡፡

 

ጥያቄ፡የበሽታው ስርጭት በአገራችንና በዓለም አቀፍ ደረጃ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

ዶ/ር፡- በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ የሚከሰት ካንሰር ያልሆነ እብጠት በሀገራችን ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታይ የጤና ችግር ነው፡፡ በሽታው በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚከሰት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሃያዎቹ የዕድሜ እርከን አካባቢ በአሉ እና ዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ሰፋ ባለ መልኩ የሚታይ የጤና ችግር ነው፡፡ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ደግሞ የዘር ፍሬ ከረጢት ውሃ የመቋጠር በአብዛኛው በህፃናት ላይ የሚታይ ችግር ነው፡፡

 

ጥያቄ፡ይህ የጤና ችግር በትክክል መኖሩን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ምርመራዎች የትኞቹ ናቸው?  

ዶ/ር፡- አብዛኛውን ጊዜ የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ የሚከሰቱ ካንሰር ያልሆኑ እብጠቶችን ምንነትና መንስኤ ለመለየት የሚደረገው ምርመራ የሚመሰረተው ህመምተኛው ስለበሽታው በሚናገረውና በአካላዊ ምርመራ ላይ ነው፡፡ ከበሽተኛው እና ከአካላዊ ምርመራው የተገኘውን መረጃ መሰረት በማድረግ የሽንትና የአልትራ ሳውንድ ምርመራ ይደረጋል፡፡ በእነዚህ የምርመራ ሂደቶች የችግሩን ምንነትና መንስኤ ለይቶ ማወቅ ይቻላል፡፡

 

ጥያቄ፡ህክምናውስ ምንድነው?

ዶ/ር፡- ህክምናው እንደ ችግሩ መንስኤ፣ አይነትና ደረጃ የተለያየ ነው፡፡ ነገር ግን ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ እንደ በሽታው ሁኔታ በመድሃኒትና በቀዶ ህክምና በማከም ለጤና ችግሩ መፍትሄ መስጠት ይቻላል፡፡ ይህ አቅም በአገራችንም በተሟላ መንገድ አለ፡፡

 

ጥያቄ፡በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ የሚከሰት ካንሰር ያልሆነ እብጠት በወቅቱ ካልታከመ የሚያስከትለው በጉዳት ምንድነው?

ዶ/ር፡- ማንኛውም የጤና ችግር በወቅቱ ካልታከመ የሚያደርሰው ጉዳት በዚያው ልክ እየጨመረ የሚመጣ ነው የሚሆነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ የሚከሰት ካንሰር ያልሆነ እብጠት በወቅቱ ካልታከመ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍ ያለ ነው፡፡ የህመም ስሜቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የዘር ፍሬ ከረጢቱ በየጊዜው እያበጠ ስለሚመጣ፣ ልብስ ለብሶ ለመንቀሳቀስም ሆነ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለማድረግ ያስቸግራል፡፡ በማህበራዊና በስነ ልቦና ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖም ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ እብጠቱ የመጣው በኢንፌክሽን አማካኝነት ከሆነና በወቅቱ ካልታከመ በጊዜ ሂደት ወደ ካንሰርነት የመለወጥ ዕድል ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም ችግሩ ያጋጠመው ግለሰብ ከነገ ዛሬ እያ ጊዜ ከማቃጠል በፍጥት ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ መፍትሄ መፈለግ ይኖርበታል፡፡

 

ጥያቄ፡ችግሩን እንዴት እንከላከል?

ዶ/ር፡-

– የግልና የአካባቢ ንፅህናን አዘውትሮ በመጠበቅ ኢንፌክሽኖችን መከላከል ይቻላል

– ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ አለመፈፀም

– በተቻለ መጠን ራስን ከየትኛውም አደጋ መጠበቅ

– የሽንት ማማጥና መሰል ችግሮች ሲከሰቱ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ መፍት መፈለግ ያስፈልጋል

– በአብዛኛው ግን በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ የሚከሰትን ካንሰር ያልሆነ እብጠት ለመከላከል አስቸጋሪ ነው፡፡ በመሆኑም ችግሩ ሲከሰት በፍጥነት ህክምና ማግኘት ይገባል ለማለት እወዳለሁ፡፡

 

ይህ አስተማሪ ቃለምልልስ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል::

 

Health: ከምግብ ዝርዝራችን ውስጥ ልንሰርዛቸው የሚገባ 6 ምግቦች!!

$
0
0

 

በርካታ የምግብ ጤና ባለሙያዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ምግቦች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ማስወገድ ላይ ጥርጣሬ የላቸውም፡፡

ምግቦቹ ሆድን ከመሙላትና የረሃብ ስሜትን ከማስታገሳቸው ጎን ለጎን የጤና ጠንቅነታቸው በተለይም ሰውነት ለቁጥጥር እስኪከብድ ድረስ በማደለባቸው ከምግብ ዝርዝራችን ውስጥ ልንሰርዛቸው እንደሚገባ በቂ ምክንያት ነው፡፡ አንዳንዶቹን ስማቸውንም መጠራት ከቶ አያስፈልግም፡፡ ብዙዎቹ የምግብ አይነቶች በሁሉም የሀገራችን ኩሽና በቀላሉ የሚዘጋጁ ካለመሆናቸው ጋር ብዙ ሰዎችም በሚገባ ላያውቋቸው ይችሉ ይሆናል፡፡

የሆቴሎችና የሬስቶራንቶች መስፋፋት ግን ከባህር ማዶ የአመጋገብ ባህል ጋር ጥሩ አድርገን እየተወዳጀን እንደመጣን መታዘብ ይቻላል፡፡ ስለምንመገባቸው ምግቦች ይዘትም በቂ መረጃ ማወቅ ይኖርብናል፡፡

  1. ካርቦን ብቻ የካበቱ ምግቦች፡-

High-Carbohydrate-Foods ስንመገብ ሰውነታችን በእነዚህ ምግቦች ውስጥ ያለውን ካርቦን ወደ ስኳርነት ይቀይረዋል፡፡ ከዛም በቀጥታ ወደ ሰም ትቧችን ይወስደዋል፡፡ ለመነጨው ስኳር ምላሽ ትቧችን ይወስደዋል፡፡ ለመነጨው ስኳር ምላሽ በመሆን መልኩም አሁንም ሰውነታችን ተጨማሪ ኢንሱሊን ለማምረት ይገደዳል፡፡ በተቻለ መጠን ስኳሩን ለመምጠጥ ነው ይሄን የሚያደርገው፤ ችግር የሚሆነውም ሂደቱ ውስጣችን ያለ በቂ የደም ስኳር እንዲቀየር በማድረግ ለተመሳሳይ ምግብ ነው እንድንራብ ምክንያት ስለመሆን ነው፡፡ ‹‹እርግጥ ነው ከካቦርን ምግቦች ርቆ መኖር አይቻልም›› የሚሉት በፊላደልፊያ የክብደት ቅነሳ ባለሙያዋ ዶ/ር ቻርሊ ሴልትዘር ናቸው፡፡ ‹‹ያለካርቦን ሕይወትን ማሰብ›› እብደት ነው ይላሉ፡፡ ልንገነዘበው የሚገባው መሰረታዊው ጉይ እነዚህ ምግቦች የካርቦብ፣ የፋትና በሰውነታችን ውስጥ ለመፈጨት ጊዜ የሚወስዱ ፕሮቲኖች ስብጥር መሆናቸው እንደሆነ ዶ/ር ቻርሊ ይናገራሉ፡፡

2. ከፍተኛ ፋይበር ያለባቸው ምግቦች፡

እውነት ነው ማንኛውም ሰው ፋይበር ያስፈልገዋል፡፡ ነገር ግን መጠናቸው ላይ እንድንጠነቀቅና በቂ ፋይበር ብቻ ለሰውነታችን የሚሰጡትን ምግቦች ፋይበር ብቻ ለሰውነታችን የሚሰጡትን ምግቦች ለይተን እንድንጠቀም ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

3. ዝቅተኛ ስብ ያለባቸው ምግቦች፡– 

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ ሰዎች የሚመገቡት ምግብ ዝቅተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑን ከተረዱ በ30% ተጨማሪ ምግቦችን ይበላሉ፡፡ ይሄም ከፍተኛ መጠን የመመገብ ልምድ እንዲኖር በማድረግ ክብደት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ያስተጓጉላል፡፡ ባሙያዎችም ስብ የሌለባቸውን ምግቦች ሲያዘጋጁ ብዙ ጊዜ ስቡን ከምግብ ይለያሉ፡፡ በሂደቱ የግብአቱን ጣዕም ጭምር ሊያስወግዱ ይችላሉ፡፡ ለማካካስ በሚል በተወገደው ስብ ምትክ ደግሞ ስኳር ሲጨምሩበት በጤናም ሆነ በክብደት ላይ የከፋ ችግር ያስከትላሉ፡

carb4. አርቴፊሻል ጣፋጭ መጠጦች፡

ምንም አይነት የካሎሪ ክምችት የሌለባቸው ጣፋጮቹ የሶዳ እና ሌሎች ባለጣዕም መጠጦችን አሁኑኑ ማሰናበት እንደሚኖርብን ዶ/ር ሴልትዘር ያስገነዝባሉ፡፡ እነዚህን መጠጦች የመጠጣት ልምዳችን በቀላሉ የሚላቀቁት አይነት ካልሆነብን ደግሞ ቢያንስ በውሃ እና በሎሚ መበረዝ አለብን ይላሉ፡፡

5. በትልቅ ዕቃ የሚቀርቡ ምግቦች፡

በትልቅ ዕቃ በቀረበ ምግብ ሳቢያ ሰዎች በ200% በላይ ጭማሪ እንዲመገቡ ምክንያት እንደሚሆን ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ በኮርኔል ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ጥናቱ፣ ሰዎች ሊገቡት የሚችሉት ከፍተኛ ምግብ መኖሩን ሲረዱ ከአቅማቸውም በላይ ለመመገብ ራሳቸውን እንደሚያዘጋጁ አረጋግጧል፡፡ ስለዚህ ይሄ ልምድ ከልክ ያለፈን ክብደት ለማስወገድ የጀመርነውን ጥረት እንዳያስተጓጉልብን ዛሬውኑ መቀየር ይኖርብናል፡፡

6. አስካሪ መጠጦች፡-

መጠጦች ዝቅተኛ የካሎሪ ክምችት ስላላቸው ብቻ ክብደት ለመቀነስ ይጠቅሙን ይሆናል ብለን ብናስብም፣ እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ስለመሆኑ ነው ዶ/ር ሴልትዘር የሚናገሩት፡፡ አልኮል የክብደት ቅነሳ እቅዳችንን አያግዝልንም፡፡ በብዙዎቹ መጠጦች እንደውም ምንም አይነት የሰውነት ጉልበት የሚሰጥ ማዕድን በውስጣቸው የሌለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ምንም የማይጠቅሙንም በመሆኑ የአልኮል መጠጥን የምናስወግድበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው፡፡

 

Health: ስለኪንታሮት በሽታ ማወቅ ያሉብን ወሳኝ ቁምነገሮች

$
0
0

የኪንታሮት ህመም በታችኛ የትልቁ አንጀትና ፊንጥጣ አካበቢ ያሉ የደም መልስ ( veins) የደም ቧንቧዎች በሚያብጡበትና በሚቆጡበት ወቅት የሚከሰት የህመም አይነት ነዉ፡፡ የኪንታሮት ህመም ሰገራ በሚወጡበት ወቅት ሲያምጡ፣ ወይም በፊንጥጣና በታችኛዉ የትልቁ አንጀት አካበቢ ባሉ የደም ስሮች ላይ እንደ እርግዝናና ሌሎች ጭነትን ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት የሚከሰት ነዉ፡፡ ኪንታሮት በታችኛዉ የትልቁ አንጀት ዉስጥ የሚገኙ የዉስጠኛዉ ኪነታሮት (internal hemorrhoids) ወይም በፊንጥጣ ዙሪያ ባለዉ ቆዳ ስር የሚታይ የዉጨኛዉ ኪንታሮት (external hemorrhoids) አይነት በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡ በሌላ በኩልም የኪንታሮት ህመም  piles በመባልም ይጠራል::
hemroides

የህመሙ ምልክቶች
• የኪንታሮት ህመም ምልክቶች እንደኪንታሮቱ ቦታ የሚወሰን ሲሆን የዉስጠኛዉ የኪንታሮት አይነት ብዙዉን ጊዜ በአይን የማይታይ ቢሆንም በሚፀዳዱበት ወቅት ማማጥ ካለዎ የደም ስሮቹ ሊቆጡና በቀላለ ሊደሙ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ በሚያምጡበት ወቅት የዉስጠኛዉ ኪንታሮት አይነት ወደታች በመምጣትና በፊንጥጣ ዉስጥ በማለፍ ህመምና የመቆጥቆጥ ስሜት ሊኖረዉ ይችላል፡፡
• የዉጪኛዉ የኪንታሮት አይነት በፊንጥጣ ዙሪያ ባለዉ ቆዳ ስር የሚገኝ ሲሆን የደም ስሮቹ በሚቆጡበት ወቅት ሊያሳክኩ ወይም ሊደሙ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ ደም በዉጭኛዉ ኪንታሮት ዉስጥ በመጠራቀምና በመርጋት ከፍተኛ ህመም፣ እብጠትንና መቆጣትን/መለብለብን ሊያመጣ ይችላል፡፡
• በሚፀዳዱበት ወቅት/ሰገራ በሚወጡበት ወቅት ከፊንጥጣ የሚወጣ ህመም የሌለዉ ደም/መድማት፡- ይህን ክስተት በመፀደጃ ሳህን ላይ ወይም በሶፍት ላይ ሊያዩ ይችላሉ፡፡
• በፊንጥጣ አካባቢ የማሳከክ ወይም የማቃጠል ስሜት ካለዎ
• በፊንጥጣ አካባቢ ህመም ወይም ምቾተ ያለመሰማት ካለዎ
• በፊንጥጣ ዙሪያ እብጠት ካለዎ
• የሰገራ ማምለጥ ካለዎ

የህክምና ባለሙያ ማየት የሚገባዎ መቼ ነዉ?
ምንም እንኳ ለኪንታሮት ዋነኛ ምልክቱ በሚፀዳዱበት ወቅት የደም መፍሰስ ቢሆንም በፊንጥጣ ደም መምጣት ሁሌ ከኪንታሮት ጋር ብቻ የተያዘ ሳይሆን እንደ የትልቁ አንጀት ካንሰር ወይም የፊንጥጣ ካንሰር ምልክትም ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
• ኪንታሮት ህመም ካለዉ፣ በተደጋጋሚ ወይም በጣም የሚደማ ከሆነ፣ወይም በኪንታሮት ማስታገሻ ህመሙ የማይሻሻል ከሆነ
• ከኪንታሮት የህመም ምልክቶች ጋር አስፋልት/ሬንጅ የመሰለ ሰገራ ካለዎ፣የረጋ ደም ካለዎ፣ከሰገራዎ ጋር ደም ካዩ
• በጣም ከፍ ያለ የደም መፍሰስ ካለዎ፣ የመደበር ወይም የማዞር ስሜት ካለዎ

የኪንታሮት ምክንያቶች
ኪንታሮት በፊንጥጣ ዙሪያ ባሉ የደም መልስ ላይ ጫና በሚበዛበት ወይም በሚፈጠርበት ወቅት የደም ስሮቹ ስለሚያብጡና ስለሚወጠሩ የህመሙ ምልክቶች ይታያሉ፡፡ በደም ስሮቹ ላይ ጫና እንዲጨምር ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ
• በሚፀዳዱበት ወቅት ማማጥ ካለ
• መፀዳጃ ላይ ለረጅም ጊዜ መቀመጥ
• ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት ረዘም ላለ ጊዜ ከነበረዎ
• ውፍረት መኖር
• እርግዝና
• የፋይበር መጠናቸዉ አነስተኛ ወይም ፋይበር የሌላለቸዉን ምግቦች ማዘዉተር ናቸዉ፡፡

የኪንታሮት ህመም ጉዳቶች
• የደም ማነስ እንዲከሰት ያደርጋል
• የኪንታሮት መታነቅ/ Strangulated hemorrhoid

ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች
• የህክምና ባለሙያዎ አካላዊ ምርመራ በፊንጥጣዎ ላይ ሊያደርጉልዎ ይችላሉ
• የህክምና ባለሙያዎ የሚከተሉት ችግሮች ሊኖረዎ ይችላሉ ብለዉ ካሰቡ እንደ ኮሎንስኮፒ ያሉ ከፍ ያለ ምርመራ ሊያደርጉልዎ ይችላሉ
-ከኪንታሮቱ በተጨማሪ ሌላ የትልቁ አንጀት ችግር ይኖራል ብለዉ ካሰቡ
-ለትልቁ አንጀት ካንሰር ተጋላጭነት ካለዎ
-እድሜዎ ከ50 አመት በላይ ከሆነና በቅርቡ የኮሎንስኮፒ ምርመራ አድርገሁ የማያዉቁ ከሆነ

ለኪንታሮት ህመም ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
ብዙዉን ጊዜ ለኪንታሮት ህምመ ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ እንደ የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ያሉና እርስዎ በራስዎ ሊተገብሩት የሚችሉ እርምጃዎችን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡አንዳንዴ ደግሞ ለኪንታሮት የሚሰጡ መድሃኒቶችንና መለስተኛ የቀዶ ጥገና የህክምና ዘዴዎች ሊደረጉልዎ ይችላሉ፡፡

መድሃኒቶች
የኪንታሮት ህመምዎ መጠነኛ የሆነ ምቾት ያለመሰማት ወይም መጠነኛ ህመም ብቻ ከሆነ ያለዉ በኪንታሮቱ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ወይም በፊንጥጣ ሊደረጉ የሚችሉ ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ መድሃኒቶች ህመሙን ለተወሰነ ጊዜ ስለሚያስታግሱልዎ ገዝተሁ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የህክምና ባለሙያዎ ካላዘዘልዎ በስተቀር ያለሀኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ መድሃኒቶች እንደ የቆዳ መሳሳሰትን፣ የቆዳ መቆጣትንና ሽፍታን የመሳሰሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊያመጡ ስለሚችሉ ከአንድ ሳምንት በላይ መጠቀም የለብዎትም፡፡

የቀዶ ጥገና፡- ኪንታሮቱን በመለስተኛ ቀዶ ጥገና ማስወገድ ወይም ኪንታሮቱን መቛጠር ሊሆን ይችላል፡፡

ሌሎች አነስተኛ የህክምና ዘዴዎች
በዉጪኛዉ የኪንታሮት አይነት ላይ የደም መርጋት ካለዎ የህክምና ባለሙያዎ የሚከተሉትን ቀላል መንገዶችን ሊተገብሩ ይችላሉ
ረበር ባንድ ላይጌሽን
ስኬሎሮቴራፒ
ኮአጉሌሽን ቴራፒ መጠቀም ይቻላል፡፡

የኑሮ ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና
• ሊቀቡ የሚችሉ መድሀኒቶችን መጠቀም፡- ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ የኪንታሮት ክሬሞችን ወይም በፊንጥጣ ሊገቡ የሚችሉ መድሃኒቶችን መጠቀም
• ለብ ባለ ዉሃ ዉስጥ መዘፍዘፍ፡- በቀን ሶስት ጊዜ ለብ ባለ ዉሃ ዉስጥ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ መዘፍዘፍ
• የፊንጥጣ ንፅህናን መጠበቅ፡- በፍንጥጣ አካባቢ ያለዉን ቆዳዎትን በየቀኑ ለብ ባለ ዉሃ በመታጠብ ንፅህናዉን መጠበቅ፤ሳሙና ችግሩን ስለሚያባብሰዉ ባይጠቀሙ ይመረጣል፡፡ ከታጠቡ በኃላ ቀስ ብለሁ ማደራረቅ
• ከተፀዳዱ በኃላ ደረቅ ሶፍት ያለመጠቀም፡- ከተፀዳዱ በኃላ ሽታና አልኮሆልነት የሌለዉ የረጠበ ሶፍት መጠቀም፡፡
• በፊንጥጣዎ አካባቢ ዕብጠት ካለዎ በረዶ ወይም ቀዝቃዛ የሆነ ነገር እብጠቱ ላይ ህመሙን ለማስታገስ መያዝ
• የህመም ማስታገሻ መዉሰድ፡- ህመምዎን ለማስታገስ እንደ አሴታሚኖፌን፣አስፒሪንና አይቡፕሮፌን ያሉ የህመም ማስታገሻዎችን መዉሰድ

ብዙዉን ጊዜ በእነዚህ ህክምናዎች በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ የኪንታሮት ህመምዎ ይቀንስልዎታል፡፡ በሳምንት ጊዜ ዉስጥ ህመምዎ ካልተሻሻለ፣ ከፍተኛ ህመም ወይም መድማት ካለዎ የህክምና ባለሙያዎን ፈጥነዉ ያማክሩ፡፡


Health: የእርጅና መድሃኒቶችን ያውቋቸዋል? ካላወቋቸው እነሆ እንንገራችሁ!

$
0
0

ከኢሳያስ ከበደ | ለዘ-ሐበሻ ጤና አምድ

ውድ አንባብያን እንደምን ከረማችሁ? ዛሬ ይህ እፁብ ድንቅ የሆነውን አካላችንን የልጅ መልክ እንዲኖረው የሚያደርግ አንድ ምስጢር ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡

አንድ ጥያቄ ላስቀድም፡፡ ይሄ የእኛ አካል ከምንድን ነው የተሰራው ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?  እንግዲህ ‹‹የእርጅና መድሃኒትን›› ማወቅ ከፈለጋችሁ ከዚህ በታች በማብራራው ጉዳይ ላይ ትዕግስት እንዲኖራችሁ ከወዲሁ እጠይቃለሁ፡፡ በተቻለኝ መጠን ነገሮችን ሳላወሳስብ አንድ መሰረታዊ የሆነን የሳይንስ ግንዛቤን ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡

foods

የሰው ልጅ አካል የተሰራው በዋነኝነት ከፕሮቲን ነው፡፡ ፕሮቲን ደግሞ የተገነባው ቢያንስ ከአምስት መሰረታዊ ንጥረ ነገሮች ነው፡፡ ይኸውም ካርቦን (C)፣ ሃይድሮጅን (H)፣ ኦክሲጂን (O)፣ ናይትሮጂን (N) እና ሰልፈር (S) ናቸው፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች ደግሞ በአየር፣ በውሃ፣ በአፈር፣ በእፀዋትና፣ በእንስሳት ውስጥ በተለያየ መጠን ይገኛሉ፡፡ ሕይወት እንዴት እንደተሳሰረ ተመለከታችሁ? ይሄ ማለት ወደ ተፈጥሮ ስር መሰረት ስሪት ስንመለስ ህይወት ያለውም ሕይወት የሌለውም አንድ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው እና መሰል ንጥረ ነገሮች (የካርቦን፣ ኦክስጂን፣ ሃይድሮጂን ወዘተ…) በቀላል ቋንቋ አተም እንላቸዋለን፡፡ አተሞች የተሰሩት ደግሞ ከሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ኤሌክትሮን ይባላል፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች እርስ በእርስ እየተሳሳቡና እየተጣመዱ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ይፈጥራሉ፡፡ ለምሳሌ ፕሮቲን፣ ስብ፣ ውሃ፣ አልኮል፣ ነዳጅ ወዘተ…፡፡

በአተሞች የላይኛው ምህዋራቸው ላይ የሚሽከረከሩት ኤሌክትሮኖች በባህሪያቸው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ ቁጥራቸው 8 ከሆነ የተረጋጉ (Stable) ይሆናሉ፡፡ ሰባትና ከዚያ በታች ሲሆኑ ደግሞ ያልተረጋጉ (Unstable) ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ያልተረጋጉ አተሞች ሁልጊዜ የህይወት ትግላቸው ለመረጋጋት የሚያስችላቸውን ተጨማሪ ኤሌክትሮን መፈለግ ነው፡፡ ይሄንን ተጨማሪ ኤሌክትሮን አንድ በመበደር ወይም በመጋራት አለዚያ አለመረጋጋቱን የፈጠረውን ትርፍ ኤሌክትሮን በማበደር ከሌሎች አተሞች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለመረጋጋት ይሞክራሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የህይወት ቅምር ሰንሰለት ሒደቱን ይቀጥላል፡፡ ይሄ ግንዛቤ ቀጥሎ ለማስረዳው ጉዳይ መሰረት ነው፡፡

የአካላችን ግንባታ የሚጀምረው ከሴሎች ነው (ሴሎች የተሰሩት ከላይ ከጠቀስናቸው ንጥረ ነገሮች መሆኑን አስታውሱ)፡፡ ልክ ቤት ሲሰራ ከብሎኬት ወይም ከጡብ እንደሆነ ሁሉ ማለት ነው፡፡ (ጡብና ብሎኬቱ የተሰሩት ደግሞ ከተለያዩ ግብዓቶች ነው)፡፡ ሴሎች በዓይን የማይታዩ ህዋሶች ናቸው፡፡ እነርሱ ተገጣጥመው ግን ቲሹ (Tissue) ይሰራሉ፡፡ ቲሹን እንደ የቤቱ የአንድ ጎን ግድግዳ እንመልከተው፡፡ ገና ቤት አልሆነም፡፡ ቲሹዎች ተገጣጥመው ደግሞ የአካላችንን የተለያዩ ክፍሎችን ይሰራሉ፡፡ ለምሳሌ፣ ዓይን፣ አፍንጫ፣ ሣንባ፣ ጉበት፣ ልብ ወዘተ…፡፡ እነዚህ ክፍሎች ደግሞ በተለያዩ ስርዓቶች (Systems) ተያይዘው የሰውን አካል ሙሉውን ይሰራሉ ማለት ነው፡፡

ይሄ አካል እንግዲህ በብዙ ትሪሊዮኖች ከሚቆጠሩ ሴሎች ነው የተገነባው፡፡ እነዚህ ሴሎች እያንዳንዳቸው ለራሳቸው የሚሆን ኃይል (Energy) ማመንጨት ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆነው ከምግብ የሚገኘውን የኃይል ምንጭ የሆነውን ግሉኮስ እንደማገዶ ሰባብሮ ወደ ኤቲፒ (ATP) የሚባል የኃይል ቅምር ወይም በቀላል አማርኛ የባትሪ ድንጋይ በመቀየር ነው፡፡ ይሄ ሂደት እያንዳንዷን ሴል በህይወት እንድትቆይ ያደርጋል፡፡

ሴሎች ከላይ የተብራራውን እጅግ በጣም አስፈላጊ ስራ ሲሰሩ በጎንዮሽ በጣም አጥፊ የሆኑ ኬሚካሎች ይፈጠራሉ፡፡ ስማቸውም ፍሪ ራዲካልስ (Free Radicals) ይባላል፡፡ ፍሪ ራዲካሎች በተፈጥሮ የሚኖሩያልተረጋጉ የኦክሲጅን አተሞች ናቸው፡፡ ይህ አለመረጋጋታቸው ደግሞ ሁልጊዜ የጎደላቸውን ኤሌክትሮን ለማሟላትና ለመረጋጋት ሲሉ አንድ እጅግ አደገኛ የሆነ ስራ ይሰራሉ፡፡ ይህም ራሳቸውን እየወረወሩ ተረጋግተው ስራቸውን ከሚሰሩት ሴሎቻችን ጋር እያጋጩ ኤሌክትሮን ለመስረቅ ትግል ይጀምራሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሳቢያ ይሄንን ውርጅብኝ የሚቀበሉ ሴሎቻችን ላይ ጉዳት ይደርሳል፡፡ ጉዳቱ ሴሎች ዳግመኛ በትክክል እንዳይሰሩ ከማድረግ በተጨማሪ በትክክል እንዳይራቡ የዘር ስሌትን እስከ መጉዳት (Genetic Matrial Damage) ሁሉ ሊያደርስ ይችላል፡፡

ይሄ የፍሪ ራዲካሎች ጦርነት እወጃ ሴሎቻችንን በጎዳ ቁጥር የእኛም ቆዳና አካል እያረጀ ይሄዳል፡፡ ማርጀት ብቻ ሳይሆን የፍሪ ራዲካሎች ጥቃት ከዚህም የከፋና ቁጥራቸው በርካታ ለሆኑ የጤና ችግሮች አካላችንን ያጋልጣል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የፍሪ ራዲካሎች ቁጥር በአካላችን ውስጥ መብዛትና የካንሰር በሽታ መፈጠር በከፍተኛ ደረጃ ተዛማጅነት አላቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለሌሎች በሽታዎች ማለትም ለልብ በሽታ፣ ለደም ስሮች መቆርፈድ፣ የደም መርጋት፣ ኢንፍላሜሽኖች (ለካንሰር መንሰራራት መንስኤ ነው)፣ ለቆዳ ጉዳት ወዘተ… መንስኤ ይሆናል፡፡

ከላይ እንደተገለፀው እንግዲህ ይነስም ይብዛም ይሄ በተፈጥሮ ፍሪ ራዲካሎችን እንደ የጎንዮሽ ውጤት የማምረቱ ሂደት በሁላችንም አካል ውስጥ አለ፡፡ ጥቁር ይሁን ነጭ፣ ቀይ ይሁን ቢጫ የተባለ የሰው ዘር ውስጥ ሁሉ የሚገኝ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ይሄን የፍሪ ራዲካሎችን ምርት የሚያባብሱ ነገሮች አሉ፡፡ እነርሱም ሲጃራ ማጤስ፣ መጠጥ መጠጣት፣ የአየር ብክለት (በተለያዩ ኬሚካሎች)፣ የተጠበሱ ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦች፣ በጣም ጣፋጭ ምግቦች፣ አርቴፊሻል ማጣፈጫዎች፣ እና ቀለሞች ወዘተ… ያሉባቸው ምግቦች እና የመሳሰሉት እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት አካላችንን የሚጎዱ ነገሮች ወደ ሰውነታችን ሲገቡ ሰውነት እነርሱ የያዙትን መርዝ (Toxin) ለማስወገድ በሚታገልበት ጊዜ በርካታ ፍሪ ራዲካሎች ይመረታሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የሚፈጠሩት ፍሪ ራዲካሎች ደግሞ ቁጥራቸው እጅግ በርካታ ከመሆኑ በተጨማሪ ጉዳታቸውም በተፈጥሮ ከሚመረቱት ፍሪ ራዲካሎች የከፋ ነው፡፡ ለዚህ ነው የአልኮል ጠጪዎች፣ ሲጃራ አጫሾች፣ የጫትና የሺሻ ወዘተ… ሱሰኞች ከእኩዮቻቸው ቶሎ የፊት ቆዳቸው ሲያረጅና አካላቸው ሲላሽቅ የምናየው፡፡ የልጅ መልክ የነበራቸው ሰዎች በእነዚህ ሱሶች ሲጠመዱ ወዲያውኑ በተለይ የፊት ቆዳቸው በዓይናቸው ዙሪያ ያለው ስስ ቆዳ የመጥቆርና የመሸብሸብ ምልክት ያሳያል፡፡ ይህ እንግዲህ ከውስጥ የሚፈጠረውን ጉዳት የማይጨምር ነው፡፡

እንግዲህ ወገኖቼ እዚህ ላይ ቆም ተብሎ ሊታሰብ ይገባል፡፡ በሰውነታችን ውስጥ በተፈጥሮ የሚፈጠሩት ፍሪ ራዲካሎች ሳያንሱ ከውጭ እያመጣን በምንሞጅራቸው መርዞች አማካኝነት ለምን ለተጨማሪ ጉዳት ራሳችንን እናጋልጣለን? ስለዚህ ቢያንስ የፍሪ ራዲካሎችን ምርት ሙሉ ለሙሉ ማስቆም ባይቻል እንኳ በከፍተኛ መጠን ግን መቀነስ እንችላለን፡፡ በተፈጥሮ የሚፈጠሩትን ከስር ከስር ማስወገድ ራሱ በቂ የቤት ስራ ነው፡፡

ፍሪ ራዲካሎች ከሰውነታችን እንዴት እናስወግድ?

‹‹ሳይደግስ አይጣላም›› እንዲሉ ለፍሪ ራዲካሎች የሚሆኑ አስገራሚ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ፍሪ ራዲካሎች ሴሎቻችንን እንዳይጎዱ እንደ ጋሻ እየተከላከሉ እና እንዲረጋጉ ደግሞ የሚፈልጉትን ኤሌክትሮኖች የሚለግሱ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ነፃ አውጪዎች ደግሞ ምንድን ናቸው? አትሉም፡፡ እነዚህ ነፃ አውጪዎች ስማቸው ‹ሚ‹አንታይ ኦክሲዳት›› ይባላል፡፡ የኬሚካል ስሞች እንደበዛባችሁ ይገባኛል፡፡ ነገር ግን ይሄንን ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ወደ አማርኛ ለመተርጎም ብንሞክር ሌላ የአማርኛ ፍቺ የሚጠይቅ የአማርኛ ቃል እንዳይሆንብን እሰጋለሁ፡፡ ስለዚህ ልክ የውጭ ሀገር የእግርኳስ ተጨዋቾችን ስም እንደምንሸመድደው እነዚህንም በቃላችን እንያዛቸው፡፡ ደጋግመን አንብበንም እናጥናቸው፡፡ ይሄ ጉዳይ የእያንዳንዳችን አካል ጉዳይ ነውና፡፡

አንታይ ኦክሲዳንቶች ከላይ እንደገለፅኩት በተፈጥረአቸው ትርፍ ኤሌክትሮን ለጋሾች ናቸው፡፡ ትርፍ ኤሌክትሮኖችን ለእነዚያ ኤሌክትሮን ተርበው ሴሎቻችንን ለሚወግሩት ፍሪ ራዲካሎች በመስጠት ያረጋጓቸዋል፡፡

ታዲያ አንታይ ኦክሲዳንቶችን ከየት ነው የምናገኛቸው? የሚል ጥያቄ ካነሳን በአንድ በኩል በመጠኑ ሰውነታችን ራሱ የሚያመርታቸው ሲሆን በሌላ በኩል ግን በበቂ መጠን በምግባችን አማካኝነት ለሰውነታችን መቅረብ አለበት፡፡

አንታይ ኦክሲዳንቶች እስከ ዛሬ በተደጋጋሚ እንደተገለፀው በብዛት የሚገኙት በአትክልትና ፍራፍሬ ውስጥ ሲሆን በተጨማሪ ከተለያዩ እርጥብና ደረቅ ቅመሞችና እንደ የወይራ ዘይት አይነት ጤናማ ቅባቶች ውስጥም ይገኛሉ፡፡

የሚገርማችሁ አንታይ ኦክሲዳንቶች ያለባቸውን ምግቦች ለይቶ መሸመት እጅግ በጣም ቀላል ከመሆኑ የተነሳ ምንም ያልተማረ ሰው እንኳን እየለቀመ ሊያወጣቸው ይችላል፡፡ ይኸውም ቀለማቸውን በማየት ነው፡፡

አንታይ ኦክሲዳንት ያለባቸው ምግቦች በአብዛኛው በቀለም ኮዳቸው ይመደባሉ፡፡ እነርሱም ቀያዮቹ፣ ቢጫና ብርቱካናማዎቹ፣ አረንጓዴዎቹ፣ ወይን ጠጅና ሰማያዎቹ፣ ነጭና ቡናማዎቹ ወዘተ… በመባል ነው፡፡

ቀያዮቹ

ቀያዮቹ አትክልትና ፍራፍሬዎች በውስጣቸው ላይኮፔን (Lycopen) የሚባል አንታይ ኦክሲዳንት የያዙ ሲሆን ለቀለማቸው ቀይ መሆን ምክንያትም ነው፡፡ ቀያዮቹን ለመጥቀስ ያህል ቲማቲም፣ ሐብሐብ፣ እንጀራ፣ የሮማን ፍሬ፣ ቀይ አፕል፣ ራድሽ (የቀይ ስር ዘሮች ሆነው ትንንሽ ናቸው)፣ ፕሪም፣ የፈረንጅ ቀዩ ቃሪያ፣ ቀይ ቦለቄ ወዘተ…፡፡

ቢጫና ብርቱካናማዎቹ

እነዚህ ደግሞ በውስጣቸው ቤታ ካሮቲንና አስኮርቢክ አሲድን (Beta Carotene and Ascotic Acid) የመሳሰሉት የአንታይ ኦክሲዳንት አይነቶችን የያዙ ሲሆን በተለምዶ ቫይታሚን ኤ እና ቫይታሚን ሲ በምሳሌነት ይነሳሉ፡፡ ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ብርቱካን፣ አናናስ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ካሮት፣ ዱባ፣ ቢጫውና ብርቱካናማው የፈረጅን ቃሪያ ወዘተ… ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ወይን ጠጅና ሰማያዊዎቹ

እነዚህኞቹ ደግሞ አንቶሳይኒን (Anthocyanin) እና ፍላቫኖይድ (Flavanoids) የሚባሉትን የአንታይ ኦክሲዳንት ዓይነት የያዙ ሲሆን እንደ ብሎቤሪ፣ ብላክቤሪ፣ ወይን ጠጅ ካሮት፣ ወይን ጠጅ አበባ፣ ወይን ጠጅ ጎመን፣ ወይን ጠጅ ድንች ያሉ እኛ ሀገር የማይገኙ ይሄንን አይነት አንታይ ኦክሲዳንቶች በብዛት የያዙ ፍራፍሬ እና አትክልት ናቸው፡፡ እኛ ሀገር ከሚገኙት መካከል ብርንጃል፣ ወይን ጠጅ ጥቅል ጎመን፣ ወይን ጠጅ የፈረጅን ቃሪያ፣ ወይን ጠጅ ወይን፣ ቀይ ስር፣ ወይን ጠጅ ቀይ ሽንኩርት (በተለምዶ ቀይ ሽንኩርት የሚባለው) ይጠቀሳሉ፡፡

አረንጓዴዎቹ

አረንጓዴዎቹ ደግሞ በዋናነት ሎቲን እና ዚያክሳንቲን (Lutein and Zeaxanthin) የተባሉትን የአንታይ ኦክሲዳንት አይነቶችን የያዙ ሲሆን ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ብሮክሊ፣ ስፒናች፣ አስፓርገስ፣ ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ጎመን፣ ቃሪያ፣ ፎሶሊያ፣ አረንጓዴ የፈረንጅ ቃሪያ፣ አረንጓዴ አፕል፣ የድንብላል ቅጠል፣ የስጎ ቅጠል፣ የጥብስ ቅጠል፣ ኮሰረት፣ ጦስኝ፣ በሶብላ፣ ወዘተ… ይጠቀሳሉ፡፡

ነጫጮቹና ቡናማዎቹ

እነዚህኞቹ ደግሞ አሊሲን (Allicin) እና ኪውርሲቲን (Quercetin) የተባሉትን አንታይ ኦክሲዳንቶች ይይዛሉ፡፡ እነዚህ አንታይ ኦክሲዳንት ነጭ ሽንኩርት፣ አበባ ጎመን፣ እንጉዳይ፣ ነጭ ቦለቄ፣ ነጭ ራዲሽ (ነጭ ካሮት የሚመስል)፣ የተፈጥሮ ካካዎ፣ ተልባ፣ አጃ ወዘተ… ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ በዚህ መልኩ ከተረዳነው በቀላሉ ሸምተን በገበታችን ላይ እንዲገኙ ማድረግ እንችላለን፡፡ እዚህ ላይ ላስገነዝብ የምፈልገው ከላይ የቀረበው አይነት አከፋፈል እንዲህ በቀላሉ አንታይ ኦክሲዳንቶቹን ለመረዳት እና ለመለየት እንዲያስችል ሆኖ የተዘጋጀና የአንታይ ኦክሲዳንቱ አይነት በጣም ጎልቶ በብዛት በሚገኘው ተመድቦ እንጂ በአንድ ቡድን ውስጥ ሌላው አይነት አንታይ ኦክሲዳንት ፈፅሞ አይገኝም ማለት አይደለም፡፡ ያው እንደምታውቁት ተፈጥሮ በቸርነት የተገነባች ነች፡፡ ተፈጥሮ ላይ አንድ ሲደመር አንድ ሁለት ብቻ ነው የሚባል ነገር የለም፡፡ ነገር ግን እንዳያችሁት እንደዚህ በቀለም ከፋፍለን ስናየው ብዙ ስራ ያቃልልልናል፡፡ በቀላሉ ያግባባናልም፡፡

ማስታወሻ

አንታይ ኦክሲዳንቶችን በተጨማሪ ምግብነት (Food Supplements) ተዘጋጅተው ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኢ ወዘተ… በመባል የሚቀረቡበት ሁኔታ አለ፡፡ ነገር ግን አንድን አይነት ንጥረ ነገር ለብቻው ነጥሎ አውጥቶ መጠቀምን የስነ ምግብ ሳይንቲስቶች አይመክሩም፡፡ የተሻለ የሚሆነው እነዚህን አንታይ ኦክሲዳንቶችን ከላይ ከተዘረዘሩት የተፈጥሮ ምግቦች ብናገኛቸው ነው፡፡ ለዚህም የሚያቀርቡት ምክንያት፣ አንታይ ኦክሲዳንቶች ለፍሪ ራዲካሎች ኤሌክትሮን ከለገሱ በኋላ ራሳቸውን እንዲያረጋጉ የሚያደርጉ ሌሎች አንታይ ኦክሲዳንቶች በምግቡ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ይህም የኤሌክትሮን እጦት የሚፈጥረውን ሠንሠለታዊ ሂደቶችን (Chain Reactions) እንዳይኖር ይረዳሉ፡፡ በአርቴፊሻል መንገድ አንድ አይነት አንታይ ኦክሲዳንትን ነጥለን ብንወስድ ግን ይሄን አይነት ድጋፍ አናገኘም፡፡

በመጨረሻም ‹‹በቂ አንታይ ኦክሲዳንት ያለበትን ምግብ እየበላሁ እንደሆነ በምን አውቃለሁ?›› ብሎ ለሚጠይቅ፣ የማዕዳችሁን ቀለም ተመልከቱ እላለሁ፡፡ በተለይ በተለይ ምግባችን በእሳት ያልተጎዳ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በየዕለቱ የምንመገበው ከሆነ ጥሩ የአንታይ ኦክሲዳንት ማዕድ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው፡፡

ስለዚህ ምግባችንን በእነዚህ ደማቅ ቀለሞች በታጀቡ ምግቦች በማስዋብ ወጣት እንደመሰልን እንድናረጅ እየመከርኩ ለዛሬ በዚሁ ልሰናበት፡፡

 

 

 

Health: የፍቅር ስጦታ የሆነውን ጽጌሬዳ አበባ ለምግብነት አስበው ያውቃሉ?

$
0
0

ኢሳያስ ከበደ | ለዘ-ሐበሻ ጤና

አበቦችን የምናውቃቸው በሽታቸው (በመዓዛቸው) ፣ በውበታቸውና በተለይ ደግሞ ለምንወደውና ለምናፈቅረው ሰው በምናቀርበው ገጸ በረከት ብቻ ሊሆን ይችላል፡፤ በአንዳንድ ሀገሮች የሚገኙ በርካታ ሕዝቦች ግን በብዙ መቶ ዓመታት ለምግብነት የሚያገለግሉ አበቦችን በመብላት ሲደሰቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በታች ለምግብነት ከቀረቡ አበቦች መካከል የተወሰኑትን ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

foods

ጽጌሬዳ አበባ

በሳይንሳዊ መጠሪያው / ጂነስ ሮዛ/ በመባል የሚታወቀው ይህ የጽጌሬዳ አበባ በመላው ዓለም በሰፊው የሚታወቅና በጣም የሚወደድ አበባ መሆኑ ሁላችንንም የሚያስማማ ነው፡፡ ከተፈጥሯዊው ጽጌሬዳ አበባ በተጨማሪ በሰው ሰራሽ ዘዴ የተዳቀሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡

የጽጌረዳ አበባ ጣዕም በአፈሩ ዓይነት፣ በአየሩ ሁኔታና በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች የተነሳ ሊለዋወጥ ስለሚችል ጽጌሬዳም ሆነ ሌላ አበባ ለምግብነት ከመጠቀማችን በፊት አበባውን መቅመሱ የተሻለ እንደሆነ የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ የአበባው የስረኛ ክፍል የመምረር ባህሪ ስላለው ይህንን የአበባ ክፍል / መራራ ክፍል/ ቆርጦ በማውጣት ወይንም ሙሉውን አበባ ለምግብነት ካዘጋጀን ውጪያዊውን ክፍል ብቻ እንድንመገብ ይመከራል፡፡

የጽጌረዳ አበባ በሰላጣ፣ ጣዕሙ ለስለስ ባለ አይብ ወይም የተፈጨ ኦቾሎኒ ባሉ የምግብ ዓይነቶች ውስጥ በመጨመር ጣዕሙን መቅመስ ይቻላል፡፡ እንዲሁም በምንወደው የስጎ አይነት ውስጥ የተፈጨ ቀይ ጽጌሬዳ በመጨመር ይበልጥ እንዲጣፍጥና መልኩ እንዲያምር ማድረግ ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ፓስታ ላይ ጽጌሬዳውን በጠስ በጠስ በማድረግ ጣል አድርጎ መመገብ ይቻላል፡፡ ጽጌሬዳ አበባ የአይስክሬምንና የምንወደውን የአልኮል መጠጥ ጣዕም ይበልጥ ለማጣፈጥም ሊያገለግል ይችላል፡፡

የዱባ አበባ

ከ16ኛው መቶ ዘመን ጀምሮ በአሜሪካ ለምግብነት ሲያገለግል የኖረው የዱባ አበባ ስሙ / ኩኩርቢታ ፒፓ/ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የአሜሪካ ሕንዶች ሴቴዎቹ አበቦች / ከጀርባቸው ትንሽ አበባ የሚያበቅሉት/ እንዲራቡ በሚል ወንዴዎቹን አበቦች / ረዥምና ቀጭን አንጓ ያላቸው/ ብቻ ይመገቡ የነበረ ይመስላል፡፡

እነዚህን አበቦች ከማብሰላችን በፊት በዙሪያው የሚገኙትን እሾሀማ ቅጠሎች ማስወገድ እንደሚገባ የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው አሜሪካውያን ይገልጻሉ፡፡ ሴቴውን የአበባ ክፍል ካስፈለገን ልንጥለው እንደምንችልም ይመክራሉ፡፡ ለስለስ ያለ ጣዕም ያለው የዱባ አበባ ከወይራ ዘይትና ከበቆሎው እሸት ጋር ተደባልቆ እንዲሁም ዱባ ራሱ ተደርጎበት በዋና ምግቦችና በሾርባ ውስጥ ተጨምሮ ሲሰራ በጣም ይጣፍጣል፡፡ የዱባው አበባ ጣዕሙ ትንሽ ጠንከር የሚል ከሆነ ደግሞ ከቀይ ሽንኩርት፣ ከነጭ ሽንኩርት፣ ከቅጠላ ቅጠል እና ከምንፈልገው ቅመም ጋር አድርገን በዘይት ወይም በሌላ ቅባት በትንሹ ጠበስ ጠበስ ልናደርገው እንችላለን፡፡ እንዲሁም አይብ፣ ቀይ ሽንኩርትና ቅጠላ ቅጠል በአበባው ውስጥ እንጠቀጥቅና አፉን እንደፍነዋለን፡፡ ከዚያም ነጩን የእንቁላል ክፍል ለብቻው በደንብ ከመታን በኋላ አስኳሉን እንቀላቅልና የተጠቀጠቀውን የዱባ አበባ እንነክርበታለን፡፡ በመጨረሻም የተፈጨ ዳቦ ውስጥ ከትተን እናወጣና በደንብ ጠብሰን እንመገበዋለን፡፡

ለመጠጥና ለከረሜላ የሚያገለግሉ

መጠጥ ውስጥ የሚጨመሩ ጣፋጭ አበቦችና፤ የአበባ ከረሜላ የሚሰራባቸው አበቦች መኖራቸውንም ያገኘነው መረጃ አስነብቦናል፡፡

የበረዶ መስሪያ ዕቃ ውስጥ መጠኑ አነስተኛ የሆነ አንድ ሙሉ አበባ ወይም ቅጠሏን በጥሰን ውኃ እንሞላበታለን፤ ከዚያም እንደተለመደው በረዶ እስኪሆን ድረስ እናቀዘቅዘዋለን፡፡ እነዚህን የበረዶ አንኳሮች በምንወደው መጠጥ ውስጥ ጨምረን መጠጣት እንችላለን፡፡

ሌላው ነጩን የእንቁላል ክፍል መትተን የደረቀውን ንጹህ አበባ በደቃቅ ብሩሽ በስሱ እንቀባው የአበባውን ቅጠሎች ሙሉ ለሙሉ መቀባታችንን እናረጋግጥ፤ ከዚያም ተጠንቅቀን ደቃቅ ስኳር በወንፊት እንነስንስበት ፤ አበባው ላይ ያለው ስኳር ከበዛ እናራግፈው ሊደርቅ በሚችልበት ቦታ ላይ ለረጅም ሰዓት እናቆየው ሲል የነገረን ደግሞ ኩክስ ቲሶርስ ነው፡፡

ጥንቃቄ ማድረግ

አንዳንድ አበቦች መርዝነት ስላላቸው የሚበሉትን በጥንቃቄ ለይተን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከተጠራጠርን አንብላቸው፡፡

ጸረ ተባይ መድኃኒት ወይም ማንኛውም ኬሚካል የተጨመረባቸውን አበቦች ፈጽሞ አንመገብ፡፡ / ብዙውን ጊዜ ከአበባ ሻጮች፣ ከአትክልት ቦታዎችና ከአንዳንድ የችግኝ መሸጫ ሱቆች የሚገዙ አበቦች እነዚህ ኬሚካሎች ይደረጉባቸዋል/ ምንም ኬሚካል ሳይደረግባቸው በተፈጥሮ የበቀሉና ከመንገዶች ራቅ ብለው የሚገኙ አበቦችን ብቻ እንመገብ፡፡

አስምና ከአትክልቶች ጋር የተያያዘ አለርጂ ያለበት ሰው አበባ መመገብ የለበትም፡፡ እንደፍራፍሬዎችና ቅጠላቅጠሎች ሁሉ በተለይ ጥሬያቸውን የሚበሉ አበቦች በሚገባ መታጠብ አለባቸው፡፡

የሚበሉት አበቦች እጅግ በጣም በርካታ ቢሆኑም በኛ ሀገር በብዛት የሚገኙት ሁለቱ በመሆናቸው የነሱን ብቻ ለማቅረብ ተገደናል፡፡ ይሁን እንጂ ሌሎችንም አበቦች የመመገብ ፍላጎቱ ያለን ሰዎች ከስነ ምግብ ባለሙያዎች ምክር ቢጠይቁ ይመከራል፡፡

ወሲብ ሰውነታችን በበሽታ በቀላሉ እንዳይጠቃ እንደሚያደርግ አንድ ጥናት አመለከተ •   በልብ በሽታ የመሞት አጋጣሚን ይቀንሳል •  የደም ዝውውርን ያፋጥናል

$
0
0

ሥነ ወሲብ ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ እና መሰረታዊ ከምንላቸው ምግብ፣ ልብስና፣ መጠለያ ቀጥሎ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይነገራል፡፡ ከጥንት ዘመን ባቢሎናዊያን፣ ግሪካውያን ሮማውያንና ከዛ ቀጥሎ በተነሱ መንግስታት ጭምር የስነ ወሲብ ችግርን ለመፍታት ከባህላዊ ሕክምና ጀምሮ የተለያዩ ወይኖችን በማስጠመቅና በማስቀመም ለችግራቸው መፍትሔ ለማምጣት ብዙ ደክመዋል፡፡ ምስራቃውያኑ ደግሞ አንዳንድ የባህር ምግቦችን ለወሲብ ማነቃቂያነት ሲጠቀሙበት ኖረዋል፡፡ እስካሁንም ይህንን መንገድ የሚጠቀሙ አገራትና ሕዝቦች በቁጥር በርካታ ናቸው፡፡
sex

በኛ ሀገር በገጠር የአገሪቱ አካባቢ የሚገኙ እናቶች ባይማሩም የራሳቸውን መላ ፈልገው እስከዛሬ ድረስ ለወሲብ ማነቃቂያነት (ማበረታቻነት) የተለያዩ ዘዴዎች ይጠቀማሉ፡፡ ከዚህም መካከል ባሏ ከእርሻ ስራው ደክሞት ሲመጣ ድፍን ምስር በብረትምጣድ ትቀቅልና በላዩ ላይ ጨው በትና ታወርደዋለች፡፡ ለእግሩ ውሃ አሙቃ ከተለቃለቀ በኋላ ያንን የድፍን ምስር ንፍሮ እየበላ ጠላውን በላዩ ላይ ያወራርዳል፡፡ ከተወሰነ ቆይታ በኃላ የድሮው ባህላችን የስንዴ፣ የገብስ( ከተገኘ የጤፍ) እንጀራ ሶስት አጥፋ በትሪ አድርጋ እቤት ካፈራው ወጥ ጋር ታቀርባለች፡፡ ከራት በኋላ የአበሻ አረቄ አቅርባ ‹‹በሉ ጠጡ›› ትላለች፡፤ ከዚህ በኋላ ባልና ሚስት ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን ፍቅር በቋንቋቸው ያወድሷታል፡፡

ይሁን እንጂ ዓለም በሳይንሱ ዘርፍ እያደገች ስትመጣ ደግሞ አመጋገባችንን በካሎሪና በመቶኛ በመቀመር የስነ ወሲብ መፍትሔ የሚባለውን የአመጋገብ ስርዓት አስቀመጡ፡፡ አንድ ሰው ከትዳር አጋሩ ጋር ጥሩ የወሲብ ጊዜ ለማሳለፍ ከፈለገ የጓሮ አትክልቶችን 10%፣ ፍራፍሬና ጥራጥሬ 10%፣ ጮማ 5% እንዲሁም ሀይል ሰጪ ምግቦች 75% መመገብ እንዳለበት ሲመክሩ ይደመጣል፡፡ ለመሆኑ ወሲብ ይሄን ያህል ተፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሳይንሱስ የወሲብን ጥቅም እንዴት ይገልፀዋል?

ወሲብና ጥቅሙ

ሚዛናዊ የሆነ ወሲብ የሚፈፅሙ ሰዎች ሰውነታቸው ጀርም ለመከላከል የሚኖረው ሃይል እንደሚጨምር የፔኒስሊቫኒያ ዩኒቨርስቲ ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡ ከጀርም በተጨማሪ ቫይረስና ባክቴሪያ የመሳሰሉ በሽታዎችን የመከላከል አቅማችንን በእጅጉ እንደሚያበረታው ይናገራሉ፡፡

በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ በተደረገው ጥናት መሰረት በሳምንት አንዴና ሁለቴ ወሲብ የሚፈፅሙ ሰዎች ከማይፈፅሙት ሰዎች የተሻለ በሽታን የመከላከል አቅም እንደሚኖራቸው ታውቋል፡፡ ነገር ግን ደስተኞችና ዘላቂነት ያለው ህይወት ለመምራት፣ ተገቢ የሆነ የአመጋገብ ስርዓት፣ በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ ከአነቃቂ መድኃኒቶች መታቀብና የትዳር እቅድ ከሌላችሁ ኮንዶም መጠቀም ተገቢ ነው ሲል ይኸው ጥናት አክሎ ይገልፃል፡፡

በወሲብ ጊዜ የደም ዝውውር የሚፋጠን ከመሆኑም የተነሳ ሰውነታችን ለማነቃቃት፣ ብሎም ድብርትን በመግፈፍ ለሰውነታችን ጤና ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ ሌላው ሴቶች በወር አበባ ወቅት የሚገጥሟቸውን ከፍተኛ የሕመም ስሜት በማስታገስ ደረጃም ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ በዓለማችን ላይ 30 ከመቶ የሚሆኑ ሴቶች በዚህ ወቅት ከፍተኛ የሕመም ስሜት እንደሚከሰትባቸው የሚታወቅ ሲሆን ካገቡ በኋላ ግን መፍትሔ እንደሚያገኙ ይነገራል፡፡

በቅርቡ በተደረገ ጥናት ደግሞ ወሲብ የደም ግፊትን በመቀነስ ረገድ ትልቅ መድኃኒት መሆኑን የገለፁት የአማይ ዌልነስ ሲኢኦ ዶክተር ጆሴፍ ጄ ፒንዞኔ፣ በዚህ ላይ ጥልቅ ምርምር ማድረጋቸውን ፅፈዋል፡፡ እኚሁ ዶክተር እንደሚሉት ወሲብ ከአካላዊ እንቅስቃሴ ተለይቶ መታየት የለበትም ይላሉ፡፡ ምክንያት ብለው ያቀረቡት ደግሞ በወሲብ ጊዜ በደቂቃ አምስት ካሎሪ መጠቀማችን ሲሆን ይህ ደግሞ ለጡንቻዎቻችን እንቅስቃሴና ለልብ ምታችን የራሱ ድርሻ ስላለው ነው፡፡

ወሲብ የኤስትሮጂንና ቴስቶትሮን መጠን ተመጣጣኝ (Balance) እንዲሆን ሲረዳ በልብ በሽታ የመሞት አጋጣሚንም ይቀንሰዋል፡፡ እንዲሁም ሴቶች በወሲባዊ መነቃቃት ወቅት የእግር ሕመም፣ ራስ ምታትና ጭንቀታቸውን በእጅጉ እንደሚቀንስላቸው ከጥናቱ መረዳት ተችሏል፡፡

የእንቅልፍ ችግር ያለባቸው ሰዎች፤ በተለይ ደግሞ በውጥረት የተነሳ ለእንቅልፍ ማጣት ችግር የሚጋለጡ ሴቶች በወሲብ ጊዜ አእምሯቸው ራሱን እንደሚያድስና በቂ እንቅልፍ ለማግኘት ምክንያት እንደሚሆንም ይነገራል፡፡

ጥያቄ ከቀረበላቸው 26ሺ ባለትዳር ሴቶች መካከል 90 በመቶ የሚሆኑት ሲመልሱ ‹‹ ወሲብ ከፈፀሙ በኋላ በስራቸውም ሆነ በእለት ውሎአቸው ደስተኛ ሆነው እንደሚያሳልፉ›› ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ብዙ ባለሙያዎች እንደሚገልፁት የወሲብ ችግር ምንጩ ከምግብ እጥረት ወይም ማህበራዊ ቀውስ ብቻ ሳይሆን ዋናው ምክንያት የሚሆነው  የስነ ልቦና ችግር ስለሆነ ባለሙያዎችን ማማከር ተገቢ ይሆናል ባይ ናቸው፡፡ አሊያ ግን ስነ ወሲብ ችግር ምናልባትም ለቤት መፍረስ መንስኤ ሊሆን ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ፡፡

Health: ደም በመስጠት የሚካሄድ ሕክምና

$
0
0

ደም በመስጠት የሚካሄደው ሕክምና ጉዳት አያስከትልም ማለት አይደለም፡፡ ከባድ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከነዚህ መካከል፣ ቫይረሶችን፣ባክቴሪያ ወይም ጥገኛ ነፍሳትን ወደ ሌላው ሰው የማስተላለፍ አደጋ አለ፡፡ በተጨማሪም የኩላሊትንና የሳንባን አሠራር የሚያዛባ አለርጂ ሊያስከትል ይችላል፡፡ በኒሞኒያ፣በኢንፌክሽን፣በልብ ድካምና በአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ የመጠቃትን አጋጣሚ ስለሚጨምር አንዳንድ ጊዜ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ በተለይ በአገራችን ብዙ ሰዎች ደም ፈሷቸው ሲሞቱ ይስተዋላል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ለማለት ይቻላል ለመዳን የሚችሉ ናቸው፡፡

Blood 2

የደም ባህርይ እና የሚያመጣው ተጽዕኖ

ደም እንደ ኦክስጅን፣አልሚ ምግቦችና በሽታ ተከላካዮች ያሉ ጥሩ ነገሮችን ወደ ሰውነት ሕዋሳት ያደርሳል፡፡ እንዲሁም ቆሻሻን ከሕዋሳት ውስጥ ያስወግዳል፣ከእነዚህም መካከል መርዛማ ካርቦን ዳይኦክሳይድ፣የተጎዱ እንዲሁም የሞቱ ሕዋሳትና ሌሎች ቆሻሻዎች ይገኙባቸዋል፡፡ደም ቆሻሻን በማስወገድ ረገድ የሚጫወተው ሚና፣ከሰውነት ከወጣ በኋላ መነካቱ አደገኛ ሊሆን የሚችልበትን ምክንያት ለመገንዘብ ይረዳል፡፡ እንዲሁም ለሕመምተኛ ደም ከመሰጠቱ በፊት በውስጡ የሚገኘው ቆሻሻ በሙሉ ተለይቶ ተወግዷል ብሎ ዋስትና መስጠት የሚችል ሰው የለም፡፡

ደም በሰውነታችን ውስጥ 100,000 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን በዚህ ጊዜ ደምን የሚያጣሩትንና በትክክል መሥራታቸው በደም ላይ የተመካውን ዋነኞቹን የሰውነት ክፍሎቻችንን ማለትም ልብን፣ኩላሊትን፣ጉበትንና ሳምባዎችን ጨምሮ በእያንዳንዱ የአካል ክፍል ውስጥ ያልፋል ለማለት ይቻላል፡፡

ደም መወሰድ ያለበት መቼ ነው?

ከባድ የመቁሰል አደጋ ሲያጋጥም ካልሆነ በስተቀር ለሕመምተኞች ደም መስጠት በደም ምትክ የሚሰጡ  አማራጭ የሕክምና ዘዴዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ደም ሥሮችን መተኮስ፣ ደም እንዳይፈስ ለማገድ አንዳንድ የሰውነት ክፍሎችን ኬሚካል ባለው ለየት ያለ ፋሻ መሸፈንና የደምን መጠን የሚጨምሩ መድኃኒቶችን መስጠት ይገኙበታል፡፡

ደም መስጠት

ደም ለሕይወት በጣም አስፈላጊ የሆኑ ተግባሮችን እንደሚያከናውን ምንም አያጠያይቅም፡፡ ደም ለፈሰሳቸው ሕመምተኞች ደም መስጠት በሕክምናው ማኀበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ብዙ ዶክተሮች ደምን እጅግ ዋጋማ ያደረገው በዚህ መንገድ ለሕክምና መዋሉ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ሆኖም በሕክምናው ዓለም ነገሮች እየተለዋወጡ ነው፡፡ ቀስ በቀስ አስገራሚ ለውጦች እየተካሄዱ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ በርካታ ዶክተሮችና የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች እንደበፊቱ ደም ለመስጠት አይቸኩሉም፡፡

ሆኖም ሙሉ ደምና የደም ክፍሎች የተገኙት ከሰው ደም በመሆኑ እንደ ቫይረስ ያሉ በሽታ አስተላላፊ ሕዋሳትን ሊይዙ ይችላሉ፡፡ ደም ለጋሾችን በጥንቃቄ መምረጥም ሆነ የላብራቶሪ ምርመራዎች ማድረግ አደጋውን አያስወግዱትም፡፡

በደም አያያዝ ረገድ የሚሠሩት ስህተቶችና የተወሰደው ደም ከሰውነት በሽታ መከላከያ ጋር ሊጋጭ መቻሉ ናቸው፡፡ የሌላን ሰው ደም የሚወስዱ ሰዎች፣የሌላ ሰው አካል የተተካላቸው ግለሰቦች ለሚያጋጥማቸው ዓይነት አደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡ የሰው በሽታን የመቋቋም ተፈጥሯዊ ኃይል ባዕዱን አካል ላይቀበል ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደም መውሰድ በሽታ የመቋቋም ተፈጥሯዊ አቅምን ሊያሳጣ ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ሕመምተኛው ከቀዶ ሕክምና በኋላ ለበሽታ እንዲዳረግና ቀደም ሲል በሰውነቱ ውስጥ ቢኖሩም ጉዳት የማያስከትሉበት በነበሩ ቫይረሶች እንዲጠቃ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ቁጥራቸውእያደገ የመጣው እንዲህ ያለ እውቀት ያላቸው የጤና አጠባበቅ ሠራተኞች፣ ለሕመምተኞች ደም በመስጠት የሚደረግ ሕክምናን በተመለከተ ከፍተኛ ጥንቃቄና ማስተዋል የተሞላበት ግምገማ እያደረጉ ነው፡፡

ለሕመምተኞች ደም በመስጠት የሚከናወን ሕክምና በርካታ አደጋዎች ቢኖሩትም፣ በተለይ ደግሞ ሌሎች አማራጮች እያሉ አሁንም በስፋት ጥቅም ላይ የሚውልበት ምክንያት

አንዱ በርካታ ሐኪሞች የሕክምና ዘዴዎችን ለመለወጥ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ወይም ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ያለደም የሚደረጉ አማራጭ ሕክምናዎች መኖራቸውን ባለማወቃቸው ነው፡፡ ሐኪሞች ደም ለመስጠት የሚወስኑት ቀደም ሲል ባገኙት ትምህርት፣ ከሌሎች ሐኪሞች በወረሱት እውቀትና በምርመራ ውጤት ላይ ተመሥርተው ነው፡፡ በተጨማሪም የቀዶ ሕክምና ዶክተሩ ችሎታ በሕክምናው ወቅት በሚፈሰው የደም መጠን ላይ የሚያመጣው ለውጥ አለ፡፡ በሕክምና ወቅት የሚፈሰው ደም ቀዶ ሕክምናውን እንደሚያከናውነው ባለሙያ በእጅጉ ይለያያል፣በመሆኑም በቀዶ ሕክምና ወቅት የደም መፍሰስን ማስቆም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች በተመለከተ ለቀዶ ሐኪሞች በቂ ማሠልጠኛ የመስጠቱ አስፈላጊነት እየጨመረ ሄዷል፡፡ ሌሎች ደግሞ ደም ከመውሰድ ውጪ ያሉት አማራጭ ዘዴዎች ዋጋቸው በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ፣ ሆኖም ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሁኔታው ከዚህ ተቃራኒ ነው፡፡

ከሙሉው ደም ውስጥ ከ38-48 በመቶ የሚሆኑት ቀይ የደም ሕዋሳት ናቸው፡፡ እነዚህ ሕዋሳት ሕብረሕዋስ ውስጥ ኦክስጅንን ያስገባሉ ካርቦን ዳይኦክሳይድን ደግሞ ያስወጣሉ፡፡ በዚህ መንገድ ሕብረ ሕዋሱ በሕይወት እንዲቀጥል ያደርጋሉ፡፡

ለጋሾች የሚሰጡት ይህ ሙሉውን ደም ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ግን ኘላዝም ብቻ ይለግሳሉ፡፡ በአንዳንድ አገሮች ሙሉው ደም ለታካሚዎች ቢሰጥም ደሙ ከመመርመሩና ለሕመምተኞች ደም በመስጠት ለማከናወን ሕክምና ከመዋሉ በፊት በዋና ዋና ክፍሎች መከፋፈልም በጣም የተለመደ ነው፡፡

በቀላሉ ለብስጭት የሚዳረጉ እና ቂመኛ የሆኑ ወንዶች /ኤትሪያል ፊብሪሌሽን/ ለተባለ የልብ ሕመም ሊጋለጡ ይችላሉ ተባለ

$
0
0
A guy too angry with green shirts

ቁጣ የልብ ሕመምን ያስከትላል ተባለ

‹‹ በቀላሉ ለብስጭት የሚዳረጉ እና ቂመኛ የሆኑ ወንዶች /ኤትሪያል ፊብሪሌሽን/ ለተባለ የልብ ሕመም ስለሚጋለጡ የልብ ምታቸው የተዛባ ይሆናል ሲል የኒውዮርኩ ዴይሊ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ሲናደዱ አንደበታቸውን መቆጣጠር የሚሳናቸው፣ ቁጡ ወይም ትዕግስት የለሽ የሆኑ ብስጩ ወንዶች ለተዛባ የልብ ምት ችግር የመጋለጥ አጋጣሚ 30 በመቶ ሊጨምር እንደሚችል ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

የጥናቱ ቡድን ዳይሬክተር የሆኑት ኢሌን ኤከር ሲናገሩ፡- ‹‹ የቁጣን ስሜት ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ አውጥቶ መግለጽ በጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ለመከላከል ይረዳል ተብሎ ይታሰብ ነበር፡፡..በዚህ ጥናት ላይ እንደታየው ግን ቁጡ የሆኑ ወንዶች ለኤትሪያል ፊብሬሌሽን ብቻ ሳይሆን ሞት ለሚያስከትሉ ሌሎች ችግሮችም የመጋለጥ አጋጣሚያቸው ከፍተኛ እንደሆነ በተጨባጭ ተረጋግጧል፡፡››

የድምጽ ብክለት የነርቭ መቃወስ ያስከትላል

የጫጫታ መብዛት ወይም የድምጽ ብክለት የነርቭ መቃወስ፣ የደም ግፊት፣ የማዳመጥ ችሎታ እክል፣ የእንቅልፍ ማጣትንና የግልፍተኝነትን ባህሪይ ሊያስከትል ይችላል በማለት ኤቢሲ የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

የጫጫታ መብዛት በከተሞች የሚኖሩ ሰዎችን የሕይወት ጣዕም እየቀነሰባቸው ነው ያለው ኤቢሲ ጋዜጣ ፣ የዓለም ጤና ድርጅትን ዋቢ በማድረግ በጤናቸውም ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ዘግቧል፡፡ የስፔን የሕገ መንግስት ፍርድ ቤት የከተማ ነዋሪዎች ጸጥታ ተረብሿል ተብሎ በተከሰሰ የሕዝብ መዝናኛ ድርጅት ላይ ባስተላለፈው ብይን የድምጽ ብክለት በጤንነት ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት እውቅና ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከመጠን ያለፈ ጫጫታ‹‹ አንድ ግለሰብ ያለውን የስነ ምግባር ደንብና አካላዊ ጤንነቱን የመጠበቅ መብቱ፣ የራሱንና የቤተሰቡን ሰላም እንዲሁም የመኖሪያ ቤቱን ያለመደፈር መብት ይጥሳል›› ብሏል፡፡ በፍርድ ቤቱ ብይን መሰረት ከባድ ጫጫታ ‹‹ የማዳመጥ ችሎታ እክል ፣ የእንቅልፍ ማጣት፣ የነርቭ መቃወስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊትና የግልፍተኝነት ባህሪ›› ሊያስከትል ይችላል ብሏል፡፡

የሌላን ሰው ደም የሚወስዱ ሰዎች የሌላ ሰው አካል የተተካላቸው ግለሰቦች ለሚያጋጥማቸው ዓይነት አደጋ የተጋለጡ ናቸው

ቫይረሶችን፣ባክቴሪያ ወይም ጥገኛ ነፍሳትን ወደ ሌላው ሰው የማስተላለፍ አደጋ አለው፡፡ በተጨማሪም የኩላሊትንና የሳንባን አሠራር የሚያዛባ አለርጂ ሊያስከትል ይችላል፡፡ በኒሞኒያ፣በኢንፌክሽን፣በልብ ድካምና በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ አጋጣሚ ስለሚጨምር አደጋ አለው፡፡

 

Viewing all 384 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>