Quantcast
Channel: ጤና – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Health: አለርጂን በተመለከተ ብዙዎቻችሁ ላቀረባችሁልን ጥያቄዎች የዶክተሩ ምላሽ

$
0
0

እንዲህ አይነት ምግብ ስመገብ ሰውነቴ ይቆጣል፣ እንዲህ አይነት ልብስ ወይም ደግ እንዲህ አይነት ቁሳቁ ስጠቀም አልያም አሞኝ የወሰድሁት መድሃኒት ሰውነቴ ያሳብጠዋል፣ ያሳክከኛል ወዘተ… የሚሉ ጥያቄዎች የብዙዎች አንባቢዎቻችን ናቸው፡፡ 

የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣውጤና መረጃ እንደሚያመለክተው ከሶስት እስከ አራት ሚሊየን የሚደርስ ሕዝብ ለተለያዩ ጉዳዮች አለርጂክ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በየዓመቱ ድንገት ራሳቸውን የሚስቱና ለሞት የሚዳረጉ ሰዎ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ ነው የሚገልፀው፡፡ 

በአለርጂ የጤና ችግር ምንነት፤ መንስኤና መፍትሄ ዙሪያ እንደተለመደው ዶ/ሩ ሙያዊ ማብራሪያ እንደሚከተለው ሰጥተዋል፡፡ 

ask your doctor zehabesha

ጥያቄ፡- አለርጂ ራሱን የቻለ በሽታ ነው ወይስ የሌሎች በሽታዎች ምልክት ነው?

ዶ/ር፡- አለርጂ ራሱን የቻለ መንስኤ ያለው የጤና ችግር ነው፡፡ 

ጥያቄ፡- ምን አይነት በሽታ ነው?

ዶ/ር፡- በህዋስም ሆነ በንጥረ ነገር መልክ ወደ ሰውነታችን በሚገቡ ነገሮች የሰውነታችን የመከላከያ ኃይል ከመደበኛው (ከሚጠበቀው) በላይ ምላሽ ሲሰጥ የሚፈጠር ክስተት ነው፡፡ በየትኛውም መንገድ ይሁን ወደ ሰውነታችን የሚገቡ ባዕድ ነገሮችን ለመከላከል ወይም ለማጥፋት የሚያስችሉ ንጥረ ነገሮች (anti body) ማንጨት የሰውነታችን በሽታን የመከላከል ስርዓት ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ ይህ ስርዓት ብዙውን ጊዜ የሚጠበቅበትን ተግባር የሚያከናውን ቢሆንም፣ አንዳንድ ጊዜ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች በሚፈጥሩት ተፅኖ ሳቢ፣ ጎጂዎችንና ጠቃሚ ሴሎችን በጅምላ በማጥፋት ከመጠን በላይ የሆነ እርምጃ ይወስዳል፡፡ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት አንዳንድ ጊዜ የራሳችንን አካል ክፍሎች ለምሳሌ ኩላሊትን፣ ልብን፣ መገጣሚያንና የአካል ንቅለ ተከላ ሲደረግ እንደ ባዕድ በመቁተር ያጠቃል፡፡ በዚህ ጊዜ ከሚፈጠሩ ችግሮች አንዱና ዋነኛው አለርጂ ነው፡፡  

ጥያቄ፡- ለአለርጂ አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

ዶ/ር፡- ማንኛውም ሰው በየትኛውም ጊዜና ሰዓት በአለርጂ በሚፈጠሩ የጤና ችግሮች የመጋለጥ ዕድል አለው፡፡ ለዚህ ችግር የሚያጋልጡ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለዚህ ውይይት ዋና ዋና የሚባሉትን ለማየት እንሞክራለን፡፡ የተለያዩ የምግብ አይነቶች ለአለርጂ መከሰት ምክንያት ይሆናሉ፡፡ በዓለም ላይ አለርጂን በማምጣት የሚታወቁ ወደ 8 የሚሆኑ የምግብ አይነቶች አሉ፡፡ እነዚህም ወተትና የወተት ተዋፅኦዎች፣ ዓሳና ዓሳ ነክ ምግቦች፣ እንቁላል፣ ከተለያዩ የኦቾሎጂ አይነቶች የሚዘጋጁ ምግቦች፣ አኩሪ አተርና ምግብን ለማጣፈጥ ወይም ለረጅም ጊዜ ለማቆየት ተብለው የሚጨምሩ ንጥረ ነገሮች እንዲሁም በመድሃኒት ውስጥ የሚጨመሩ ኬሚካሎችና በፋብሪካ የታሸጉ ምግቦች ለአለርጂ የማጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ለአንድ አይነት መድሃኒት አላርጂ ነው ማለት ባይቻልም፣ ለተለያዩ የህመም አይነቶች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለአለርጂ መከሰት ምክንያት ይሆናሉ፡፡

በኬሚካል ማምረቻዎች የሚሰሩ፣ ለአረም ማጥፊያ ኬሚካሎች ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አቧራ፣ የዕፅዋት ብናኝ፣ ቀዝቃዛ የአየር ፀባይና ከቤት ውስጥ እንስሳት ጋር የዕለት ተዕለት ግንኙነት የሚያደርጉ ሰዎች ለአለርጂ ተጋላጭ የመሆን ዕድል አላቸው፡፡

ነገር ግን ሁሉም ሰው ለአንድ አይነት ጉዳይ በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ አለርጂ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለአንዱ አለርጂ የሆነ ጉዳይ ለሌላው ላይሆን የሚችልበት ሁኔታ ሰፊ በመሆኑ ነው፡፡

ጥያቄ፡- አለርጂክ በብዛት የሚከሰትባቸው የአካል ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?

ዶ/ር፡- አለርጂ በአብዛኛው የሚከሰተው ቆዳ ጋር በአለ ንክኪ ቆዳ ላይ ይከሰታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓይን፣ በአፍንጫ፣ በአፍ፣ በመተንፈሻ አካላትና በአንጀት አካባቢ ይከሰታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓይን፣ በአፍንጫ፣ በአፍ፣ በመተንፈሻ አካላትና በአንጀት አካባቢ ይከሰታል፡፡ ከሌሎች ሰዎች በተለያየ ምክንያት በሚወሰድ ደም አለርጂ ሊከሰት ይችላል፡፡

 

ጥያቄ፡- አለርጂ ሲከሰት ከሚታዩ ምልክቶች ዋና ዋና የሚሉትን ቢገልፁልኝ?

ዶ/ር፡- አለርጂ ሲከት የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን፣ አለርጂው እንደሚከሰቱበት ቦታ የሚታዩ ምልክቶችም የተለያዩ ናቸው፡፡  

ዓይን አካባቢ ሲከሰት

ማሳከክ፣ መቅላት፣ ማበጥ፣ ህመም፣ ማበጥ፣ ቶሎ ቶሎ እንባ መፍሰስና ብርሃን ማየት መፍራት ይከሰታል፡፡

አፍንጫ እና የመተንፈሻ አካላት አካባቢ ሲከሰት፡- ቀጭን ውሃ መሳይ ንፍጥ፣ ማስነጠስ፣ የአፍንጫ መደፈን፣ ማሳከክ፣ ማሳል፣ የመተንፈሻ አካላት እብጠትና ውሃ መቋጠር፣ ፈሳሽ መብዛት፣ የአየር መታፈን፣ ማሳል፣ ስር ስር የሚል ድምፅ ሊከሰት ይችላል፡፡

ከምንመገበውና ከምንጠጣው ምግብ ጋር አለርጂ ሲከሰት፡- አፍና ከንፈር ማበጥ፣ ምግብ ለመዋጥ መቸገር፣ ጉረሮ አካባቢ ህመምን ጨምሮ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥና የሆድ አካባቢ ህመም ይከሰታል፡፡

ከንክኪ ጋር በተያያዘ ቆዳ ላይ ሲከሰት፣ ማሳከክ፣ መቅላት፣ ሽፍታ እና ማበጥ ናቸው፡፡ አለርጂ ሲከሰት የሚያሳያቸው ምልክቶች ቀለል ያሉ ቢመስሉም ራስን ከመሳት እስከ ሞት ድረስ ሊያደርስ የሚችል በሽታ እንደሆነ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ በአንድ ይሁን በሌላ ምክንያት የሚፈጠር አላርጅ፣ ተገቢውን ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚድን ቢሆንም ተመልሶ የመምጣት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ለምንድን ነው አለርጂ እየተመላለሰ የሚመጣው?

ዶ/ር፡- ቀደም ሲል ለአለርጂ መከሰት ምክንያቶችን ገልፀናል፡፡ ስለሆነም ከአለርጂ አማጭ ምክንያቶች ራስን በተገቢ ሁኔታ ጥንቃቄ ማድረግ ካልተቻለ የቱንም አይነት ህክምና ቢደረግ ተመልሶ መከሰቱ አይቀርም፡፡

ጥያቄ፡- የዚህ በሽታ ስርጭት በዓለምም ሆነ በሀገራችን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

ዶ/ር፡- የአለርጂ ጤና ችግር በሀገራችንም ሆነ በዓለም ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ነው ጥናቶች የሚያሳዩት፡፡ በዓለም ከ25 ሰዎች 1 ሰው ለተለያዩ ጉዳዮች አለርጂ ነው፡፡ ችግሩ ከፆታ አንፃር ሲታይ ሁለቱንም የሚያጠቃ ነው፡፡ ይሄ ነው ተብሎ የሚገለፅ ልዩነት የለም፡፡ ነገር ግን ከዕድሜ አንፃር ግን በህፃናት ላይ በስፋት ይታያል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ከህፃናት የታሸጉ ምግቦችን፣ ከዳይፐሮች፣ ከሚለብሷቸው ልብሶች፣ ከሚጠቀሙባቸው ሳሙናዎችና ቅባቶች ጋር የተያያዘ ነው፡፡  

ጥያቄ፡- አለርጂ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ምርመራዎችን ማየት ቢቻል?

ዶ/ር፡- የመጀመሪያው ምርመራ ህመምተኛው ስለበሽታው የሚሰጠው ታሪክ ነው፡፡ ምን አይነት ጉዳዮችን ሲጠቀም ችግሩ እንደተከሰተ ህመምተኛው ከሚናገረው ነገር መረዳት ይቻላል፡፡ ከበሽታው ጋር በሚደረግ ውይይት የተገኘውን  መረጃ መሰረት አድርጎ የተለያዩ የላቦራቶሪ ምርመራዎች ይደረጋሉ ከዚህ በተጨማሪ ናሙና በመውሰድ መመርመርና አለርጂ መኖር አለመኖሩን በትክክል ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ 

ጥያቄ፡- ህክምናውስ?

ዶ/ር፡- ከሁሉም የሚቀለው መፍትሄ እያንዳንዱ ግለሰብ ከሚጠጣቸውና ከሚመገባቸው ነገሮች፣ ከሚጠቀምባቸው ቁሳቁሶችና ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተብለው የሚወሰዱ መድሃኒቶችን በተቻለ አቅም በአግባቡ ለይቶ ማወቅ፡፡ ካወቅን በኋላ አለመጠቀምና ሁልጊዜም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አለርጂን ሙሉ በሙሉ አክሞ ለማዳን የሚያስችሉ የተለያዩ መድሃኒቶች አሉ፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች በሀገራችንም ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ያሉ ናቸው፡፡

ጥያቄ፡- በወቅቱ ያልታከመ አለርጂ የሚያስከትለው ጉዳት ምንድነው?

ዶ/ር፡- ብዙ ሰው አለርጂን እንደ ቀላል በሽታ ነው የሚመለከተው፡፡ ይሄ ደግሞ ትክክል አይደለም፡፡ ምክንያቱም በአግባቡ ትኩረት ካልተሰጠው አደገኛ በሽታ በመሆኑ ነው፡፡ ቀለል ካለው ሰውነትን ከማሳከክና ከማሳበጥ ጀምሮ ራስን ለመሳትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡

ጥያቄ፡- አስቀድሞ መከላከል የሚቻለው እንዴት ነው?

ዶ/ር፡- ከአለርጂ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ጤና ነክ ችሮችን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል፡፡ የአለርጂ መከሰቻ መንስኤ ከዕለት ተዕለት ኑሯችን ማለትም ከምግባችን፣ ከመጠጣችን፣ ከልብሶቻችንና ከምንኖርበት አካባቢያዊ ሁኔታዎች ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም የሰውነት እንቅስቃሴ አዘውትሮ በማድረግ፣ የግልና የአካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ፣ ከየትኛውም ዓይነት የቤት እንስሳት ጋር የሚደረግ  ንክኪን በማቋረጥ እንዲሁም ከአቧራና ከእፅዋት ብናኝ ራስን በመጠበቅ አለርጂን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በነበረው ታሪክ ከሚጠቀሙባቸው ምግቦች መካከል ለአለርጂ መከሰት ምክንያት የሆኑ ምግቦችን በጥንቃቄ መለየት ያስፈልጋል፡፡ በትክክል ከተለዩ በኋላ በቤትም ሆነ በሆቴል ቤቶች እነዚህን ምግቦች አለመጠቀም ነው፡፡

The post Health: አለርጂን በተመለከተ ብዙዎቻችሁ ላቀረባችሁልን ጥያቄዎች የዶክተሩ ምላሽ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>