Quantcast
Channel: ጤና – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

የትርፍ አንጀት ሕመም (APPENDICITIS)

$
0
0

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የትርፍ አንጀት ሕመም የምንለው የህመም ዓይነት የሚከሰተው ከትልቁ አንጀት ቀጣይ በሆነው እና የ3 ½ inch ርዝመት ባለው የአንጀት ክፍል ነው፡፡
እስካሁን ድረስ የትርፍ አንጀት ጥቅም በእርግጠኝነት ያልታወቀ ሲሆን ያለ ትርፍ አንጀት ጤናማ ኑሮንም መምራት እንደሚቻል የሚታወቅ ነው፡፡
የትርፍ አንጀት ሕመም በአፋጣኝ ሕክምና ማግኘት ያለበት ሲሆን ሕክምና ካልተደረገለት ግን በሰውነት ውስጥ ይፈነዳና ኢንፌክሽን አምጪ ተዋስያንን በሆድ ዕቃ ውስጥ የከፋ ኢንፌክሽን እንዲፈጥሩ ያደርጋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ መግል የያዘ ኢንፌክሽን ከሌላው የሰውንት ክፍል ራሱን ለይቶ ስለሚቆይ በጣም አጣዳፊ ባይሆንም እንኳን በእርግጠኝነት ለመለየት ግን ቀዶ ጥገና አስፈላጊ ስለሆነ ሁሉም የትርፍ አንጀት ሕመሞች የቀዶ ጥገና ሕመምና ያስፈልጋቸዋል፡፡
✔ የትርፍ አንጀት ሕመም በምን ይከሰታል?
የትርፍ አንጀት ሕመም የሚመጣው በትርፍ አንጀትና በትልቁ አንጀት መካከል የሚገኘው አንገት ሲዘጋ ነው፡፡ ይህ በሠገራ፣በቁስ አካል ወይንም በካንሰር አልያም በኢንፌክሽን ምክንያት ሊዘጋ ይችላል፡፡
✔ የትርፍ አንጀት ሕመም ምልክቶች
• ከእምብርት አካባቢ ጀምሮ ወደ ታችኛው የቀኝ የሆድ ክፍል የሚወርድ የህመም ስሜት
• የምግብ ፍላጎት ማጣት
• ማቅለሽለሽና ማስመለስ ከሆድ ሕመሙ በመቀጠል ይከሰታል
• ትኩሳት
• አየር ለማስወጣት መቸገር
• ለመንቀሳቀስ መቸገር
ከላይ የተጠቀሱትን ዓይነት የህመም ስሜት ከተሰማዎ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ተገቢ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በአፋጣኝ ሕመሙ ታውቆ ሕክምና ሊደረግ ስለሚገባው ነው፡፡

appendicitis-600x330
ምንም ዓይነት ምግብ ወይንም መጠጥ ወይንም ሕመም ለማስታገስ የሚወሰዱ የቤት ውስጥ መድኃኒቶች እንዳይወሰዱ ይመከራል፡፡ ይህም ያበጠው ትርፍ አንጀት እንዳይፈነዳ ያደርጋል፡፡
✔ የትርፍ አንጀት ሕመም ምርመራዎች
በምልክቶች ብቻ የትርፍ አንጀት ሕመምን በእርግጠኝነት ለማወቅ ስለሚያስቸግር ሌሎች በመሳሪያ የታገዙ ምርመራዎች ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
• የሆድ አልትራሰውንድ
• የደም እና የሽንት ምርመራዎች የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
✔ የትርፍ አንጀት ሕክምና ምንድን ነው?
• በቀዶ ጥገና የትርፍ አንጀቱን ቆርጦ ማውጣት ይህም በህክምናዉ (Appendectomy) የምንለዉ ዋነኛው ሕክምና ሲሆን መግል የያዘ ትርፍ አንጅት መጀመሪያ መግሉን በማስወገድ አልያም ፀረባክቴሪያ መድኃኒቶችን በመጠቀም የቀዶ ጥገና ጊዜው የሚራዘምበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡
✔ ቀዶ ጥገናው ከተደረገ በ12 ሰዓት ውስጥ እቅስቃሴ መጀመር የሚቻል ሲሆን፣
• የማይቆም ማስመለስ
• ከፍተኛ የሆድ ሕመም
• ራስ ማዞር
• ደም የቀላቀለ ማስመለስና ሽንት ከጋጠምዎ
• በስፌቱ ላይ ሕመም እና መቅላት ካመጣ
• ትኩሳት እና መግል ከቁስሉ የወጣ ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ሐኪምዎ በመሄድ እንዲያማክሩ ይመከራል፡፡
የትርፍ አንጀት እንዳይመጣ ለመከላከል የማይቻል ቢሆንም፣ ጥናቶች እንደሚሳዩት ከሆነ ግን በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን (ፍራፍሬዎችና አትክልት) የሚመገቡ ሰዎች ላይ የመከሰት ዕድሉ እንደሚቀንስ ነው፡፡
ጤና ይስጥልኝ

The post የትርፍ አንጀት ሕመም (APPENDICITIS) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>