Quantcast
Channel: ጤና – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

ቲማቲምን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

$
0
0

በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)
• ቲማቲምን መመገብ ለቆዳ ጥራት ጠቃሚ ነው፡፡ ቲማቲም በውስጡ ያዘው ንጥረ ነገር ለቆዳ ተስማሚ የሆነ ሲሆን ቲማቲምን ልጦ የልጣጩን ውስጠኛ ክፍል በፊትዎ ላይ በመለጠፍ ለ10 ደቂቃ በማቆየት መታጠብ ንፁህና የሚያበራ ፊት እንዲኖርዎ ያደርጋል፡፡
• ቲማቲም ለተለያዩ የካንሰር ዓይነቶችን ይከላከላል የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ሊኮፒን የተባለ ንጥረ ነገር በፕሮስቴት ካንሰር፣የጨጓራ እና የአንጀት ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው፡፡

fresh-tomatoes-with-visible-drops-of-water-t-monticello-600x330
• ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን ያደርጋል
ቲማቲም በውስጡ ካልሲየም እና ቫይታሚን ኬን ያዘ ሲሆን ሁለቱም ንጥረ ነገሮች አጥንትን ጠንካራ እንዲሆን ያስችላሉ፡፡
• ቲማቲም ለልባችን ጠቀሜታም አለው
ቲማቲም በቫይታሚን ቢ እና በፖታሺየም የበለፀገ ሲሆን ኮሌስትሮልን እና የደም ግፊትን የመቀነስ አቅምም አለው፡፡ ቲማቲምን በዕለት ተዕለት የምግብ ስርአትዎ ውስጥ ማስገባት ከድንገተኛ የልብ ሕመም እና ኮሌስትሮል እራስዎን ይከላከላሉ፡፡
• ለፀጉርዎ ጠቀሜታ አለው
በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ፀጉርዎን ጠንካራና አንፀባራቂ እንዲሆን ያደርጋል
• ቲማቲም ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ ዕድልዎን ይቀንሳል
• ለዓይንዎ ጥራት
ቫይታሚን ኤን ያዘውን ቲማቲም መመገብ ለዓይንዎ ጥራት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Trending Articles