Quantcast
Channel: ጤና – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Health: 11ዱ የጀርባ ህመም ዋና ዋና ምክንያቶችና 8ቱ ምርጥ የቤት ውስጥ ህክምናዎች

$
0
0

 

back pain

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ ነው:: ደግማችሁ ማተም ለምትፈልጉ የዘ-ሐበሻን ስም በምንጭነት መጥቀሳችሁን አትርሱ::

80 በመቶ የስርጭት አድማስ ያለው የጀርባ ህመም ከበሽታዎች ሁሉ ወደ ሐኪም የሚያመላልስ አስገራሚ ህመም ነው፡፡ አዎን ጥርስዎን ሊነክሱ፣ ፊትዎን ቅጭም ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴም ስራዎን በሰላም ለማከናወን ፈተና መሆኑ አይቀርም፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ህመም ምን አይነት ችግር እንዳስከተለው ላይረዱ ይችላሉ፡፡ የጀርባ ህመም መንስኤው የተለያየ ነው፡፡ ከጀርባ አካባቢ ካሉ የሰውነት ክፍሎች ሊነሳ አልያም ከሰውነት ውስጥ ካሉ አካላት ሊመነጭ ይችላል፡፡ ቀላል የጀርባ ውጥረት አልያም የውስጥ ሰውነት ክፍል ካንሰር ሊሆን ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች፡፡ የአጥንት ችግር፣ የነርቭ ህመም፣ የጡንቻ፣ የጅማት ከኩላሊትና ከማህፀን ግድግዳ፣ እንዲሁም ከሌላ ቦታ የተሰራጨ ካንሰር አሊያም ደግሞ የአጥንት ኢንፌክሽን፡፡

በሁሉም ሰው ላይ ማለት በሚቻል መልኩ በህይወት ዘመን ውስጥ የወገብ ህመም ያጋጥማል የቢሊዮኖች ህመም በመባልም ይታወቃል፡፡ በተለይ የአጥንት ክብደትና ጥንካሬ በዕድሜ ተፅዕኖ መዳከም ሲጀምር ወገብ ለአደጋ ይበልጥ ተጋላጭ እየሆነ ይመጣል፡፡ ለብዙዎች ከአደጋ በፍጥነት አገግሞ የጤነኛ ጀርባ ባለቤት መሆንም እንዲሁ ቀላል የሚባል ሂደት አይሆንም፡፡

እንዲሁም አንዳንድ ያልተለመዱ የጀርባ ችግሮች እንደ ካንሰር ካሉ ጠንከር ካሉ በሽታዎች መነሻነት ይመጣሉ፡፡ ለወራት የሚዘልቁ የጀርባ ህመሞችም የህክምና ባለሙያዎች የተለየ ድጋፍ የሚጠይቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

 

11 ዋና ዋና የጀርባ ህመም ምክንያቶች

  1. ከአቅም በላይ ወይም በተሳሳተ መንገድ ዕቃ ማንሳት
  2. ድንገተኛ አደጋ፤ መውደቅ፣ በስፖርት አማካኝነት የሚመጣ ችግር
  3. የአጥንት መሳሳት
  4. ከልክ ያለፈ ውፍረት በተለይ ደግሞ በመሀከለኛው የሰውነት ክፍል ላይ /ሆድ አካባቢ/ ከፍተኛ ውፍረት መኖር
  5. በየዕለቱ የሚገጥም ጭንቀትና ድብርት
  6. በተሳሳተ መንገድ መተኛት/በተለይ በሆድ በኩል መገኘት/
  7. በተሳሳተ መንገድ መቀመጥና ከተቀመጥንበት መነሳት
  8. ለረዥም ሰዓት መቀመጥ በተለይ ቁጥጥ ማለት እና መቀመጫን የሚቆረቁር ነገር ላይ መቆየት
  9. ከበድ ያለ የእጅ ቦርሳና የጀርባ ቦርሳን መሸከም
  10. ከወገብ ታጥፎ ለረዥም ጊዜ መቆየት
  11. በእርግዝና ወቅት ጡንቻን እና ጅማትን የማሳሰብ እንቅስቃሴ ማድረግ ናቸው፡፡

አይዘናጉ ጀርባዎ ላይ ያልተለመደ ህመም የተሰማዎ ከሆነ የጀመሩትን ስራ ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ወይም ሌሎች ተግባራትን የማቆም እርምጃ ወዲያው ነው መውለድ ያለብዎት፡፡

Back-Pain2በወገብ ላይ የሚገጥም ህመም ለ48 ወይም ለ72 ሰዓታት የሚዘልቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙዎቹ የጀርባ ችግሮች ደግሞ የተወሰኑ ሳምንታትን ይፈልጉ ይሆናል፡፡ የጀርባ ጤና ላይ መሻሻል ከታየ በኋላም ስቃዩ አልፎ አልፎም ቢሆን ሊቀጥል ይችላል፡፡

8 ለጀርባ ህመም የሚወሰዱ የቤት ውስጥ ህክምናዎች

የጀርባ ህመምን የሚያመጡ እና የሚያባብሱ እንቅስቃሴዎችን በማስወገድ እንዲሁም ከታች የተዘረዘሩትን የመፍትሄ አማራጮች በየዕለቱ አልያም ባስቀመጡት ፕሮግራም መሰረት የሚተገበሩ ከሆነ መዳን ከእርሶ ብዙ የራቀ አይሆንም፡፡

በተለይ ትንንሽ የወገብ ወለምታዎችና ህመሞች ላይ ጠንከር ያለ ክትትል በማድረግ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ መዳን ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከበድ ካሉት ብዙዎቹ የጀርባ ችግሮች ሙሉ ለሙሉ ለመፈወስ ወይም ለማገገም ከአራት እስከ ስድስት ሳምንት ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ 12 ሳምንት እንደሚወስዱ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

  1. በረዶ፡ በዋናነት ስቃይን ለመቀነስ የሚመከር ነው፡፡ በበረዶ የታጨቀ ከረጢት ወይም ቦርሳ እንዲሁም በጣም የቀዘቀዙ አትክልቶችን ካዘጋጀን በኋላ የታመሙ የሰውነት ክፍላችን /ጀርባችን/ ላይ ቢያንስ ለ15 ደቂቃ መያዝ፡፡ በሶስት እና አራት ሰዓታት ውስጥም ይህንን ተግባር መደጋገም ታዲያ በረዶውን በቆዳችን ላይ አለማሳረፋችንን እርግጠና መሆን አለብን፡፡
  2. ማረፍ ነገር ግን የተወሰነ መንቀሳቀስ፡ ረዥም የእረፍት ጊዜ ብናገኝ ከገጠመን የወገብ ችግር በፍጥነት ለማገገም ሰፊ ዕድል ይኖረናል፡፡ ነገር ግን ለአንድ እና ለሁለት ቀናት እረፍት ማድረግ የማገገሚያ ሂደቱን ሊያዘገየው ይችላል፡፡

ስለዚህ ጡንቻን ለማጠንከር በሚዳን ሁኔታ ከእረፍቱ ጎንለጎን የተወሰነ እንቅስቃሴ ማድረግ በእጅጉ ይረዳል፡፡

በተረፈ አደጋ ሊያስከትሉ ከሚችሉ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ፡፡ በተለይ ደግሞ ዕቃ ከማንሳት፣ ከማስቀመጥ በተደጋጋሚ ከመተጣጠፍ እና ከመጠምዘዝ በዚህ ጊዜ መራቅ ግድ ይሆናል፡፡

  1. ሙቀትን መተግበር፡ ህመሙ ከተከሰተ ከ48 ሰዓት በኋላ ወይም የህመም ስቃዩ ከራቀ በኋላ የታመመውን የሰውነት ክፍል /ጀርባ/ እና ጡንቻዎችን ለማፍታታትና የቀድሞ ጥንካሬአቸውን ለመመለስ ሙቅ ውሃን በሻወር መልክ፣ በከረጢትና ቦርሳ በማድረግ መታጠብና መያዝ ይመከራል፡፡

ታዲያ ከልክ በላይ በሞቀ ውሃ ቆዳን መጉዳት እንዳይመጣ መጠንቀቅ እንዳይረሳ፡፡

በእርግጥ ከሙቅ ውሃ ይልቅ ቀዝቃዛ ውሃ የማገገም ሂደቱን እንደሚያፋጥነው የታመነ ሲሆን ሁለቱንም በጋራ መጠቀሙ ደግሞ የተሻለ የሚባለው መንገድ ነው፡፡

  1. መዘረጋጋት

የታሰበበት ለመዘረጋጋት እንቅስቃሴ ወገብን በቤት ውስጥ ለማስታመም የሚመከረው አንዱ መፍትሄ ነው፡፡ በመዘረጋጋት ሂደት ግን መጣደፍና መንጠርን የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች የጀርባ ችግር ላለባቸው አካላት በፍፁም አይመከሩም፡፡ ከዚህ ባለፈ በቀን ውስጥ ለ10 እና 15 ደቂቃዎች በፍፁም ህመም የማያስከትል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፈውስን ሊያመጣ ይችላል፡፡

  1. ማሳጅ /ለተመረጠ የጀርባ ችግር/

በተለይ የወገብ ችግሩ የመጣው ጡንቻዎች ስራና ውጥረት ስለበዛባቸው ከሆነ ማሳጅ መፍታታትን በመፍጠር ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል፡፡

  1. ደረጃ ያለው መፍታታት፡ይሄ የመፍታታት ቴክኒክ በርካታ የሰውነታችንን ጡንቻዎች በማፍታት ነው የሚተገበረው፡፡
  2. ዮጋ፡ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ዮጋ የወገብ ህመምን የማዳን ከፍተኛ አቅም አለው፡፡ ሂደቱ በርካታ ወራትን ሊወስድ ቢችልም ችግሩን በዘላቂነት በማጥፋት ግን የተዋጣለት አማራጭ ነው፡፡
  3. መቆም፡መቀመጥና ማንሳት በብልሃት፡- ስንቆም ወገባችንን አጥፈን ሳይሆን ቀጥ ብለን ይሁን፡፡ ስንቆም በፍፁም ትከሻችንን አስቀድመን ሊሆን አይገባም፡፡ ስንቀመጥም የታችኛው የጀርባችን ክፍል በቅድሚያ ወንበር እንዲነካ በማድረግ ይሁን፡፡ የምንቀመጥበት ወንበርም ቢሆን የታችኛውን የወገብ ክፍል የሚደግፍ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡

ዕቃን በማንሳት ሂደትም ዋናውን የሸክም ስራ እግሮቻችን እንዲፈፅሙት እናድርግ ወገብ በፍፁም መታጠፍ የለበትም፡፡

ወደ ሐኪም መሄድ የሚጠይቅ የጀርባ ህመም ደግሞ ይህን ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ህመሙ ወደ እግርዎ ጭምር ከተሰራጨ፣ የጡንቻ መዛል፣ መደንዘዝና እንደመርፌ ጠቅጠቅ የሚያደርግ ህመም አብሮት ካለ፡፡ የጀርባ ህመሙ ከተለወጠ የሰገራ አወጣጥ ለምሳሌ ድርቀት ጋር አልያ የተለየ የሽንት ምልክቶች ካሉ፡፡ እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የክብደት መቀነስና የሰውነት ፍላጎት መቀነስ፣ የክብደት መቀነስና የሰውነት ሙቀት መጨመር አብሮት ካለ፡፡ የአጥንት መሳሳት የረጅም ጊዜ ችግር ካለብዎ፡፡ ህመሙ እየከፋ ከሄደና ከላይ ባሉት ቀላል እርምጃዎች ሊሻልዎ ካልቻለ ወደ ሐኪም በመሄድ ቀጣይ ምርመራ ያድርጉ፡፡

መልካም ጤንነት፡፡

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>