ከብዙ ዓመታት በፊት የመጀመሪያ ዲግሪዬን ስማር ለካውንስሊንግ ልምምድ ወጥቼ ጊዜ ያጋጠመኝን ጉዳይ በአጭሩ ላካፍላችሁ፡፡
የተመደብኩበት ትምህርት ቤት ካውንስለር ስላልነበረው፣ ዳይሬክተሯን ነበር ያነጋገርኳት፡፡ ‹‹በትምህርቷ ጎበዝ የነበረች ተማሪ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት እጅጉን የሰነፈች ሲሆን አምና ደግሞ ወደቀች፣ ፍቅር ይዞኛል ትላለች›. ብላ ሁኔታውን ካወራችኝ በኋላ ልጅቱን አገናኘችኝ፡፡ ልጅቱ የ17 ዓት ወጣት ነበረች፡፡ ከብዙ መለማመድ በኋላ ሁኔታውን በዝርዝር አጫወተችኝ፡፡ ከክፍለ ሀገር መጥታ አዲስ አበባ ከአክስቷ ጋር የምትማር ልጅ ነች፡፡ በአጋጣሚ የአክስቷን ጓደኛ ባል ወደደችው፡፡ ሰውዬው ትልቅ ፎቅ፣ ውድ መኪና ያለው ሀብታምና የአራት ልጆች አባት ነው፡፡ የሰውዬው ምስል በተደጋጋሚ ይመጣባታል፡፡ መኪና ባየች ቁጥር የሰውዬው ሐሳ ይመጣባታል፡፡ ወንድ አስተማሪ ሲያስተምር የሚታያት ሰውዬው ነው፡፡ ትምህርት ቤትም ሆነ ቤቷ ስትሆን የሰውዬው ምስል ይታያታል፡፡ በሁኔታውም ትጨነቃለች፡፡ ሲጨንቃት ደግሞ የህዝብ ስልክ ባለበት ቦታ ትሄድና ትደውልለታለች፡፡ ሰውዬው በደወለች ቁጥር ይስድባታል፡፡ እሷ ግን ስለደወለች ብቻ ትንሽ ቀለል ይላታል፡፡ ሰውዬው እያስቸገረችው እንደሆነ ለአክስቷ በመናገሩ አክስትየዋ ከቤት አስጣቻት፡፡
ወደ ክፍለ ሀገር ለመሄድ ባለመፈለጓ፣ ከቤተሰቦቿ በሚላክላት 120.00 ብር የአዲስ አበባን ኑሮ ተያያዘችው፡፡ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ግማሹን በስልክ ታጠፋዋለች፡፡ ቀሪው ገንዘብ ስለሚያንሳት፣ ልብሶቿንና ጫማዎቿን ሸጣ የቀራት የተቀዳደዱ ልብሶችና አንድ ነጠላ ጫማ ብቻ ነው፡፡ እሷ ግን ይህ ግድ አይሰጣትም፡፡ ምን አይነት ፍቅር ነው የያዛት ብዬ አሰብኩ፡፡ብዙ አነበብኩ፡፡ በስተመጨረሻ ደረስኩበት፡፡ ይኸው ዛሬ ደግሞ፣ የልጅቱን አደገኛ ተግባራትን ለተመተንተን ፈቀድኩና እንዲህ ጻፍኩት፡፡
‹‹ፍቅር ፍቅር አሉት ስሙን አሳንሰው፣ ከድንጋይ ይበልጣል ለተሸከመው ሰው››
የሚል የዘፈን ግጥም እየሰማን ለኖርን ሰዎች፣ ፍቅር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገንዘብ ቀላል አይደለም፡፡ የግጥሙን ሁለተኛ ስንኝ ስንቃኝ ደግሞ ከድንጋይ የሚበልጥ ነገር እንደሆነ በቀላሉ እንገነዘባለን፡፡ ይህን ስንኝ በጥልቀት ስንቃኘው ምን አይነት ድንጋይ? ትንሽ ወይንስ ትልቅ ድንጋይ? ድንጋዩ ትንሽና በኪሳችን ይዘነው የምንዞር ከሆነ እኮ ፍቅር ቀላል ነው፡፡ በተቃራኒው ድንጋዩ በጣም ትልቅ ከሆነ ደግሞ ፍቅር ልንሸከመው የማንችል ነገር ነው ማለት ነው፡፡
በመሰረቱ ፍቅርን ከባድም ሆነ ቀላል የሚያደርጉ ነገራት አሉ፡፡ ከእነዘህም ውስጥ አንዱ በፍቅር ውስጥ ያሉ ሶስት ምሰሶዎች መዋቅሮች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መዋቅሮች ውስጥ አንደኛው፣ ቅርብ ግንኙነት (intimacy) የሚባለው ሲሆን ይህም በዋናነት የስሜታዊነት ባህሪያትን የሚይዝ ሆኖ መቀራረብ፣ የጋለ ስሜት፣ የመገናኘት እና የመቀራረብ ስሜቶችን የሚያጠቃልል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ጥልቅ ስሜት (Passion) ሲሆን ይህም የተነሳሽነት ሁኔታዎችን የሚይዝ ሆኖ የመሳብ፣ የወሲብ እና ወዘተ ስሜቶችን የሚያካትት ነው፡፡ ሶስተኛው የመስዋዕትነት (Commitment) ሲሆን በአብዛኛው፣ ከአስተሳሰብ ጋር የሚያያዝና ሰዎችን ለመውደድ የምናደርገውን የአጭር ጊዜ ውሳኔ (Short-term decision) እና ፍቅራችንን ለማስቀጠል የምናደርገውን የረዥም ጊዜ ውሳኔ (long-term decision) የሚይዝ ነው፡፡
በመሆኑም ሰዎች በቀላሉ መቀራረብ ከቻሉ፣ የሁለቱም ስሜት ከተቀራረበና አንዱ ለአንዱ መስዋዕት መሆን ከቻሉ፣ ፍቅራቸው ቀላልና ጥሩ የህይወት ቅመም ይሆናል፡፡ በተቃራኒው መቀራረብ የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ከሆኑ፣ ስሜታዊነት በአንደኛው ግለሰብ በቻ ካለ፣ አንዱ ብቻውን መስዋዕት የሚከፍል ከሆነ፣ በሁለቱም ግለሰቦች ዘንድ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ካልሆኑ ወዘተ… ፍቅር የተባለው ነገር የተጓደለ ብሎም ለመሸከም ከሚከብድ ድንጋይ ጋር የሚነፃፀርና ከባድ ይሆናል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አንዳንዶቹ ፍቅር ውስጥ ያሉ እየመሰላቸው ነገር ግን የፍቅር ሱስ ብዬ የምጠራው አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነው፣ ራሳቸውም ሆነ አፈቀርኩት/ኳት ከሚሉት ግለሰብ ላይ ጉት ሲያደርሱ እናስታውሳለን፡፡ በቀላል አገላለፅ በፍቅር ሱስ ተጠምደው በፍቅር ስም አደገኛ ተግባራትን ይፈጽማሉ፡፡
1. የፍቅር ሱስ (Obsessive love)
የፍቅር ሱስን ለማብራራት ከመሞከሬ በፊት አንድ የአዕምሮ ህመምን ላብራራ፡፡ ይህም በእንግሊዝኛው ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲዝኦርደር (Obsessive-compulsive disorder) በአማርኛ ደግሞ ‹‹በሐሳብ የመወጠርና የግዳጅ ተግባር ህመም›› ብዬ የተረጎምኩት፡፡ የስነ ልቦና እና የሳይካትሪስት ባለሙያዎች በዋናነት የሚቆሙበት የDSM ማኑዋል እንደሚያብራራው፣ ይህ ህመም ከጭንቀት ችግሮች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን፣ ህመሙ ላለበት ሰውን ለመለየት የሚያስችሉ 5 መሰረታዊ መስፈርቶች አሉት፡፡
– በሌሎች ሐሳቦች መሀል ጣልቃ የሚገባ ወይም ከፍተኛ ጭንቀት የሚፈጥር ሐሳብ ወይም ምስል በተደጋጋሚ መከሰት (obsession)
– ተደጋጋሚ የሀሳብ ምልልሱን ለማጥፋት ወይም ለመቀነስ በተደጋጋሚ የሚከወን ተግባር መኖር፤
– የጭንቀት መጠኑ ደግሞ የዕለት ተዕለት ተግባራችንን እስከማዛባት ሲደርስ፤
– ተደጋጋሚ ሐሳቡ እና ተግባሩ በአንድ ቀን ውስጥ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት የሚታይ ከሆነ፤
– ተደጋጋሚ ሐሳቡ ወይም ድርጊቱ መከሰት ከጀመረ ግለሰቡ እያሰበ ያለው ሐሳብ ወይም እየከወነ ያለው ተግባር፣ በቂ ምክንያት የሌለው ወይም የተሳሳተ ነው ብሎ የሚያምን ከሆነ (ይህን መስፈርት ለማያሟሉ ግለሰቦች ደግሞ ደካማ እይታ ያላቸው መሆናቸው ይፈተሽና እንደ መስፈርት ይወሰዳል)
በአጭሩ በዚህ ችግር የተያዙ ሰዎች፣ የሆነ ሐሳብ ወይም ምስል በየሐሳቦቻቸው መሀል እየመጣ ጭንቀት ይፈጥርባቸዋል፡፡ ከጭንቀት ለመገላገል ደግሞ የሆነን ተግባር በተደጋጋሚ ይከውናል፡፡ በምሳሌ ለማስረዳት ያህል እንደ ካውንስሊንግ የምሰጠው ግለሰብ በተደጋጋሚ ቤቴን አልቆለፍኩትም የሚል ሐሳብ ይመጣበታል፡፡ ጭንቅ ሲለውም የቤቱን ቁልፍ በተደጋጋሚ በመሄድ ያረጋግጣል፡፡
እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ዝም ብለው የሚከሰቱ ሁኔታዎች ሳይሆኑ በተለያዩ አነሳሽ ነገሮች (triggers) የሚከሰቱ ናቸው፡፡ አነሳሽ የሚባሉት በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ሐሳቦችን የሚፈጥሩ ክስተቶች ወይም ፍንጮቹ ናቸው፡፡ ለምሳሌ እላይ የጠቀስኩት ግለሰብ፣ ቤቴን አልቆለፍኩም የሚል ሐሳብ የሚያስታውሰው የቤቱን ቁልፍ ማየት እና ስለ ጓደኛው ወሬ መነሳት ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት አንድ ጓደኛው ቤቱን ሳይቆልፍ አድሮ ሌቦች ገብተው እንደ ዘረፉት ካወራው ወዲህ፣ ቁልፍ ባየ ቁጥርና ሰዎች ስለጓደኛው የሆነ ወሬ ባወሩ ቁጥር ወይም ስለጓደኛው ባሰበ ቁጥር ቤቴን አልቆለፍኩም የሚለው ሐሳብ ይመጣበታል፡፡ ሌላ ስራ እየሰራም ሆነ ሌላ ሐሳብ እያሰበ፣ ይህ ሐሳብ ከተከሰተበት ወዲያውኑ ወደ በሩ በማምራት ቁልፉን ያረጋግጣል፡፡
በአጠቃላይም በዚህ ህመም የተያዙ ግለሰቦች በተለያዩ ሀገራት አነሳሽነት ወደ ህመሙ የገቡ ናቸው፡፡ አነሳሽ የሚባሉት ነገሮች አንዱ ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ አንድ ግለሰብ የተፈቀረው ግለሰብ ሁኔታ ወይም ምስል በሌሎች ሐሳቦች መሀል እየመጣ ድቅን ይልበታል፡፡ ይህ ሁኔታም ጭንቀትን ይፈጥርበታል፡፡ ጭንቀቱ ደግሞ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ማስታጎል ይጀምራል፡፡ ይህንን ጭንቀት ለማስወገድ ወይም ለመቀነስ የተለያዩ ተግባራትን በተደጋጋሚ ይከውናል፡፡ በምሳሌ ለማስረዳት፣ በመግቢያዬ የጠቀስኳት ወጣት የወደደችው ሰውዬ ምስል በተደጋጋሚ ይከሰትበታል፡፡ ጭንቀትመወ ጥር ያደርጋታል፤ ይህ ጭንቀቷም ትምህርቷን እንዳትማር ያደርጋታል፡፡ ከዚህ ጭንቀት ለመውጣትም በተደጋጋሚ ስልክ ትደውላለች፡፡
ይህ ማለት ይህቺ ወጣት፣ በሐሳብ የመመሰጥና የአስገዳጅ ተግባር ህመም ይዟታል ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይም ይህቺው ወጣትና በዙሪያዋ ያሉ ሰዎች፣ ልጅቱ ከሰውዬው ጋር ፍቅር እንደያዛት ያምናሉ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ የፍቅር ሱስ (obsessive love) የሚባለው፡፡ በእንደዚህ አይነት ሱስ ያሉ ግለሰቦች ያፈቀሩት ሰው ምስል ወይም ሁኔታ በተደጋጋሚ በሐሳቦቻቸው መሀል ድቅን ይልባቸዋል፡፡ በዚህ ሐሳብም ይመሰጣሉ፤ ጭንቀት ይፈጥርባቸዋል፤ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውም ይስተጓጎላል፡፡ እናም ጭንቀቱን ለማስወገድ ተደጋጋሚ ተግባራት ይፈጽማሉ ወይም ሐሳቡ የሆነ ተግባር እንዲፈጽሙ ያስገድዳቸዋል፡፡
ችግሩ የሚመጣው የሚከውኑት ተግባር ምንነት ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሚያፈቅሩት ሰው ሃሳብ/ምስል በተደጋጋሚ ሲመጣባቸው፣ ተፈቃሪው/ተፈቃሪዋ ያለበት/ያለችበት አካባቢ በመሄድ የመመልከት ተግባር ያከናውናሉ፡፡ በመግቢያዬ የጠቀስኳት ወጣት ደግሞ፣ የሰውዬው ሐሳብ ሲመጣባት ስልክ የመደወል ተግባርን በተደጋጋሚ ታከናውናለች፡፡ እዚህ ላይ ነው እንግዲህ በፍቅር ስም የሚከወኑ ህገወጥ ተግባራት የሚመጡት፡፡ ያፈቀሯት ሴት ምስል በተደጋጋሚ ሲከሰትብዎት፣ የሚፈጠረውን ጭንቀት ለማስወገድ ተፈቃሪዋን ማስገደድ፣ መማታት፣ አሲድ መድፋትና መግደልን የመሳሰሉ ተግባራት የሚፈጸመው፡፡ ሴቶችም ማስፈራራት፣ በተለያዩ ነገራት የመጠምዘዝ ተግባር መከወን፣ ማስመታት፣ ዐዋቂ ቤት ሄዶ የመስተፋቅር መድሃኒት በመፈለግ ማጥቃት፣ መግደል፣ ማስገደልን የመሳሰሉ ተግባራት የሚፈጽሙት፡፡
2. ተግባራቱ ፍቅርን ይገልፃሉ ወይ?
ፍቅር ምሉዕ የሚባለው ወይም እውነተኛ ፍቅር የሚባለው፣ ሶስቱንም የፍቅር ምሰሶዎች/መዋቅሮች አጣምሮ ሲይዝ ነው፡፡ በዚህ መነፅር የመወጣጠር ፍቅርን ስንቃኘው፣ የተወሰኑት ስሜታዊነትንና መስዋዕትነት የሚይዙ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ስሜታዊነትን ብቻ የሚይዙ ናቸው፡፡ ጠቅለል አድርገን ሁሉም የመወጣጠር ስሜታዊነት የሚታይባቸውና ምንም አይት የመቀራረብ መዋቅር የሌላቸው ናቸው፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ የመወጣጠረ ፍቅር ውስጥ ያሉ ሰዎች የተሟላ ፍቅር ውስጥ አይደሉም የሚል ድምዳሜ መድረስ ይቻላል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ በመወጣጠር ፍቅር ውስጥ የሚካሄደው ተግባር መቀራረብን በስሜታዊነት ለማምጣት የሚደረግ ስራ ነው፡፡ በመሰረቱ መቀራረብ ስሜታዊነትን ይፈጥራ እንጂ ስሜታዊነት መቀራረብን መፍጠር እንደማይችል የስነ ልቦና ባለሙያዎች በጥናቶቻቸው አረጋግጠዋል፡፡ እኛም በገሃዱ ዓለም እንመለከተዋለን፡፡ አንድን ሰው በማጨናነቅ እንዲቀርበን አድርገን እኛን የመቅረብ ስሜት እንዲሰማው፣ እኛን የመውደድ ስሜትና ራሱን ለእኛ መስዋዕት እንዲያደርግ ማድረግ አይቻለንም፡፡
በሶስተኛ ደረጃ ማየት ያለብን ሁኔታ፣ ተደጋጋሚ ሐሳብ (ምስል ሲከሰትብን፣ ጭንቀትን ይፈጥራል፣ ጭንቀቱን ለማስወገድ የተለያዩ ተግባራት ይከውናሉ፡፡ ይህ ክስተት ደግሞ ቀደም ብለን የጠቀስናቸው ተግባራት የሚሰሩት ጭንቀትን ለመቀነስ/ለማስወገድ እንጂ ለፍቅር የሚደረጉ ተግባራት አይደሉም፡፡
በመሆኑም ከእነዚህ ሁኔታዎች በመነሳት፣ የመወጣጠር ፍቅር በያዛቸው የተለያዩ ተግባራትን የሚከወኑ ግለሰቦች የአዕምሮ ጤና ችግር እንጂ እውነተኛ ፍቅር የሚገልፁ አይደሉም፡፡
3. መለያየት
በፍቅር ስም የሚፈፀም አንደኛ ተግባር ደግሞ በፍቅር ኖው የተለያዩ ሰዎች የሚፈጽሟቸው ተግባራት ናቸው፡፡
ጥንዶች በፍቅር ሲኖሩ ተቀራርበዋል፡፡ በስሜት ተፈላልገዋል፣ አንዱ ለአንዱ መስዋዕት ሆነዋል፡፡ እነዚህ ጥንዶች በተለያዩ ምክንያቶች ተለያዩ፡፡ በዚህ ጊዜም መቀራረባቸው፣ ስሜታዊነታቸውና መስዋዕትነታቸው የመክፈል ሁኔታቸው ይቀንሳል/ይጠፋል፡፡ ታዲያማ እዚህ ላይ ችግሮች የሚፈጠሩት፣ አንዳንዶች የተለያቸውን ሰው ወደ ማጥቃት ሁኔታ ወይም ስሜት ይጓዛሉ፡፡ የቀድሞ ፍቅረኛውን ሆቴል ወስዶ በጩቤ ወጋግቶ የገደለ ወጣት ታሪክ ሰምተናል፡፡ ለአነሳሁት ሐሳብም ከበቂ በላይ ምሳሌ ይሆናል፡፡
የዚህ አይነት ሁኔታዎችን ጠለቅ ብለን ብንመለከት ደግሞ የአስተሳሰብ ክፍተትን እንመለከታለን፡፡ ሁለት ግለሰቦች አንድን ሁኔታ በተለያየ መንገድ ይገነዘቡታል፡፡ በምድብ ከፍለን ስንመለከት ደግሞ አንዳንዶቹ ሁኔታውን በአሉታዊነቱ ሲያስቡት ሌሎቹ ደግሞ ሁኔታውን በአሉታዊነት ያስቡታል፡፡
ጥንዶች በፍቅር ለመዝለቅ፣ የመቀራረብ የመፈላለግና የመስዋዕትነት ሁኔታው አብሮ መዝለቅ አለበት፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ መዝለቅ ካልቻለ በመጀመሪያ የተዛባውን ምሰሶ ለማስተካከል መሞከር ወሳኝ ነው፡፡ ሙከራው ካልተሳካ ደግሞ በመነጋገርና በመስማማት መለያየት ይቻላል፡፡ በአዎንታዊ አስተሳሰብ የሚያስቡ ሰዎች ጎዶሎ ፍቅር ይዞ ከመቀጠል፣ ተለያይቶ ሙሉ ፍቅርን ማምጣት እንደሚቻል ሲያስቡ፣ አሉታዊ አስተሳሰብ ያላቸው ደግሞ ሲጀመር የተወላገደ ጎደሎ ፍቅሩን ለማስተካከል አይሞክሩም፡፡ ሲቀጥሉም መለያየትን ልክ እንደ አብሮ መኖር ሁሉ አንድ አማራጭ አድርገው አያስቡም፡፡ በአንድ አብነት ለማስረዳት ልሞክር፡፡
ሁለት ግለሰቦች በፍቅር አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች፣ በሁለቱ መካከል የነበረው ፍቅር እየቀዘቀዘ መጣ፡፡ እንዲያውም አንዴ ወንዱ ለጥቂት ሴቷ በቢላዋ ልትወጋው ስትንደረደር በሰራተኛዋ ዋይታ ለጥቂት ተረፈ፡፡ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ተደጋጋሚ ጥረቶች አደረጉ፡፡ በስተመጨረሻም በመተማመን ለመለያየት ወሰኑ፡፡ ለእኔ በገረመኝ ሁኔታ ሴቷ ከእንደዚህ አይነት ፍቅር መለያየት ጥሩ ነው የሚል አስተሳሰብ ብትይዝ፣ ወንድየው በተቀራኒው ከእሷ መለየት መሞት ማለት ነው የሚል አስተሳሰብ በመያዝ ራሱን ለማጥፋት እስከማሰብ ደረሰ፡፡
ከመለያየት ጋር የተያዘ ሌላው ተግባር ደግሞ፣ እኔ የፈለኩት ካልሆነ የሚል ሁኔታና የፈለጉት ሳይሆን ሲቀር ወደ ጎጂ ተግባራት የማምራት ሁኔታ ነው፡፡ በፍቅር ውስጥ አንዱ ምሰሶ መስዋዕትነት ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በተቻለ መጠን ያፈቀርነውን ግለሰብ ፍላጎት ለማርካት መጣር ነው፡፡ ይህንን የማናደርግ ከሆነ ደግሞ ያፈቀርነው ራሳችንን እንጂ ሌላ ሰው ለማለት ይከብዳል፡፡ ምሳሌ ልስጥ፣ ሁለት ፍቅረኞች ተለያዩ፡፡ ከቆይታ በኋላ ወንዱ ሌላ ፍቅረኛ ያዘ፡፡ ከተለያዩ በግምት ከዓመት በኋላ ከአንድ ወንድ ጋር ስትሄድ አያት፡፡ በዚህ ጊዜ ወንዱ አፍቃሪ፣ ጓደኞቹን በመሰብሰብ ሌላ ወንድ ጋር ላይሽ አልፈልግም በሚል ፈሊጥ የቀድሞ ፍቅረኛውንና አብሯት የሚሄደውን ልጅ መቀጥቀጥ ጀመሩ፡፡ ተደባዳቢው አፍቃሪ፣ ሌላ ፍቅረኛ መያዙና የቀድሞ ፍቅረኛው ጋ እየሄደ ያለው ልጅ ምን እንደሆነ አለማረጋገጡን ልብ ይሏል፡፡
በመለያየት ዙሪያ አንድ ሌላ ጉዳይ ልጨምር፡፡ የዚህ ጉዳይ መነሻ ችግር ጥንዶች በፍቅር አብረው በነበሩበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የራሳቸውን ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ በመገደብ የፍቅረኞቻቸውን ፍላጎት ብቻ ለማርካት ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ በፍቅረኞቸው ላይ ጥገኛ ያደርጋሉ፡፡ እንዲዘሀ አይነት ሰዎች ደግሞ መለያየት ሲመጣ ራሳቸውን ችለው ለመቆም ሲቸገሩ እናያለን፡፡
ይህን ሁኔታ በበኩሉ ፍቅረኞቸው ላይም ሆነ ራሳቸው ላይ አደገኛ ነገራትን እንዲፈጽሙ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ በመሰረቱ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እንደሚያብራሩት፣ የበሰሉ ፍቅረኞች (Mature lovers) ብዙ ጊዜያቸውን ከፍቅረኞቻቸው ጋር የሚያሳልፉ ሲሆን እንደ ግለሰብ ደግሞ የራሳቸው ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡
ይህ ደግሞ ለራሳቸው አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን ለመከወን የሚያስችላቸው ከመሆኑም በላይ ራስን ችሎ የማስተዳደር ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ በተቃራኒው በፍቅር ስም ራሳቸውን ለፍቅረኞቸው ሙሉ ለሙሉ አሳልፈው የሚሰጡ ፍቅረኞች ይህ ስሜት የላቸውም፤ ስለሆነም መለያየት ሲመጣ ለችግር ይጋለጣሉ፡፡ በፍቅረኛዋ ጠያቂነት ከቤተሰቦቿና ከጓደኞቿ ራሷን አግልላ የኖረች ሴት፣ ባሏ ሌላ ሴት አፍቅሮ ከቤት ሲያስወጣት ወደ ሆቴል በማምራት፣ ሴተኛ አዳሪ የሆነች ሴት ታሪክ ጋዜጣ ላይ አንብቤያለሁ፤ ላነሳሁት ሐሳብም ምርጥ ምሳሌ ነው፡፡
4. ፍቺ
ቀደም ብዬ በመለያየት ዙሪያ ያነሳኋቸው ጉዳዮ በትዳር/በጋብቻ ተሳስረው የነበሩና የተለያዩ/የተፋቱ ጥንዶች ጉዳዮች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ፍቺ ከፍቅረኞች መለያየት የሚለዩት ሁለት አበይት ሁኔታዎች ስላሉት፣ በትኩረት ለማየት ያስችለን ዘንድ ራሱን እንዲችል አድርጌ እቃኘዋለሁ፡፡
አንደኛው ሁኔታ ሰዎች/ጥንዶች በሚጋቡበት ሰዓት የሁለት ቤተሰቦች ጥምረት ተፈጥሯል፡፡ ሕግና ደንብ ሲጥሱ የሚጠብቃቸው ቅጣት ራሳቸውን ዝግጁ ስለሚያደርግ፣ በውስጣቸው ጥላቻን ሲያሳድሩ አይስተዋሉም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስነ ምግባራቸውን ለማበረታታት ወላጆች የተለያዩ ስጦታዎችን ያበረክቱላቸዋል፡፡ ሚዛናዊ አስተዳደግን በሚጠቀም ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ልጅ በአብዛኛው፡፡
– ደስተኛ እና ስኬታማ ይሆናሉ፡፡
– ከፍተኛ የሆነ የውሳኔ ብቃት ሲታይባቸው፤ በውሳኔ ጊዜም የተለያዩ አማራጮችን መመልከትና ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችንም ቀድመው ለመገመት ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡
– በሕይወታቸው ላይ ኃላፊነትን የሚወስዱ ግለሰቦች ይሆናሉ፡፡
– ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ይታይባቸዋል፡፡
– ራሳቸውን መግጽ ይችላሉ፡፡
– የሰውን ሐሳብ የመቀበል ችግር አይኖርባቸውም፡፡
– በአጠቃላይ ለህይወት በጎ የሆነ እይታ ያዳብራሉ፡፡
– በቀላሉ ራሳቸውን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር ማለማመድ ይችላሉ፡፡
5. ነፃ አስተዳደግ
ይህን የአስተዳደግ ዘዴ የሚጠቀሙ ቤተሰቦች፣ ምንም አይነት ህግ እና ደንብ ለቤታቸው አያወጡም፡፡ ለልጆቻቸው ያስፈልጋሉ ያሉትን ቁሳቁስ በራሳቸው ተነሳሽትም ሆነ በልጆቹ ጠያቂነት ከማሟላት ወደኋላ አይሉም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ‹‹ልጆች ልጆ›› ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ ጥፋታቸውም ከልጅነታቸው ጋር የተያያዘ እንጂ በወደፊት ህይወታቸው ላይ ሊያመጣ የሚችለውን የባህሪ ብልሹነት አይቀበሉትም፡፡ ሁሉንም ነገር ሲያድጉ ይተውታል ብለውም ያስባሉ፡፡ ከልጆቸው ጋር ሊወያዩ የሚችሉት ምናልባት እቤት ውስጥ ከባድ የሚባል ችግር ሲፈጠር ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ቢሆን የተፈጠረውን ችግር ወይም ልጁ የሚያንፀባርቀውን መልካም ያልሆነ ባህሪ ለማስተካከል ብዙም ጥረት አያደርጉም፡፡ ከልጆቻቸው ጋር የሚኖራቸውም ግንኙነት የወላጅ እና የልጅ ሳይሆን የጓደኛ አይነት ነው፡፡
ነፃ አስተዳደግን በሚጠቀም ቤተሰብ ውስጥ የሚያድግ ልጅ የሚያንፀባርቃቸው ባህሪዎች በአብዛኛው፡፡
– ከልክ ያለፈ በራስ መተማመን ይስተዋልባቸዋል፡፡
– በሚፈልጉት ጊዜ ማንኛውንም ነገር እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡
– ሕግና ደንብን ያለማክበር ችግር ይታይባቸዋል፡፡
ወላጆቻቸው ሁሉንም ነገር እየሰጡ ስላሳደጓቸው፤ በትምህርት ህይወታቸውም ሆነ ስራ ላይ፤ ይሄ ነው የሚባል ጥረት ስለማያሳዩ እኔ ብቻ የተሻልኩ ነኝ ብለው ስለሚያስቡ ስኬት ሲርቃቸው ይስተዋላል፡፡ ዝቅተኛ የሆነ የድብርት መጠን ይስተዋልባቸዋል፡፡
6. ቸልተኛ
እነዚህ አይነት ቤተሰቦች በአብዛኛው፣ የልጆቻቸውን መሰረታዊ ፍላጎት እንኳን በአግባቡ የማያሟሉ ናቸው፡፡ የእነሱ እምነት ልጅ በዕድሉ ያድጋል የሚል ሲሆን በራሳቸው ተፍጨርጭረው ህይወታቸውን እንዲለውጡ ይጠብቃሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ልጆች በስራና በሌላው ህይወታቸው በጣም የተዋጡ ወይም ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የሱስ ተጠቂዎች፣ የአዕምሮ በሽተኞች ወይም ደግሞ በልጅነት ዘመናቸው ከቤተሰባቸው ወይም ከማህበረሰቡ መልካም እንክብካ ያልተደረገላቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥናቶቹ ያመለክታሉ፡፡ እንደ ጥናቱ ምናልባት ልጆቹ የተፈጠሩት ሁለቱም ወላጆች፣ ልጅ ወልደው ለማሳደግ ዝግጁ ሳይሆኑ ወይም በአንደኛው ወገን ግፊትና ፍላጎትም ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል፡፡
እንደዘህ አይነት ባህሪ በሚንፀባረቅበት ቤተሰብ ያደጉ ልጆች በአብዛኛው
– ለመኖር አስፈላጊ የሆነ የህይወት ልምድና ክህሎት ማጣት ይስተዋልባቸዋል፡፡
– በሱስ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
– የወላጆቸውን በቂ ፍቅርና አትኩሮት ሳያገኙ ያደጉ ስለሆነ፣ ካደጉ በኋላም የሰውን አትኩሮት የመሳብ ይስተዋልባቸዋል፡፡
– ዕድሜያቸው ለተቃራ ፆታ ፍቅር ሲደርስም፣ ተፈላጊነታቸውን ለማረጋገጥ ከቀረቧቸው ሰዎች ጋር ሁሉ በቀላሉ በፍቅር የመውደቅ አባዜ ይስተዋልባቸዋል፡፡
– በአብዛኛው ወንጀል በመፈፀም የሚታወቁ ግለሰቦች ከዚህ አይነት ቤተሰብ እንደመጡ ይኸው ጥናት ያመለክታል፡፡
7.ምን ይደረግ?
ከላይ በመግቢያችን የጠቀስናት ተመራማሪ በጥናቷ ያሰፈረችው፣ ልጆችን በማሳደግ አስፈላጊ የሆነው ነጥብ ኃላፊነትን መወጣትና ከልጆች መጠበቅ የሚል ሲሆን፣ ከዚህ እሴት አኳያ እያንዳንዱን የአስተዳደግ ዘዴ እናያለን፡፡ ፈላጭ ቆጭ የልጅ አስተዳደግ ዘዴ (demanding not responsive) ተብሎ የሚፈረጅ ሲሆን፣ እንዲከበርለት የሚፈልጋቸውን የቤተሰብ እሴቶች ከመዘርዘር ውጪ ልጁ ከቤተሰቡ የሚፈልጋቸውን ቅድመ ሁኔታ ስለማያሟላ፣ ተመራጭ ያልሆነ የልጅ አስተዳደግ መሆኑን ትገልፃለች፡፡
ነፃ የሆነ የቤተሰብ አስተዳደግን ስንመለከት ደግሞ (Responsive but not demanding) (ሚዛናዊ) የሚባለው የአስተዳደግ አይነት ‹‹Both responsive and demanding›› በመሆኑ፣ እጅግ ተመራጭና ለልጁ ሁለንተናዊ ዕድገት አዎንታዊ የሆነ ተፅዕኖ የሚያሳድር፣ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ወላጆች ቢከተሉት መልካም ውጤት እንደሚያመጣ ይታመናል፡፡ እንግዲህ የዛሬው ህፃን፣ የነገው አባወራና ሀገር ተረካቢ ነውና በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፣ ልጆቻችንን በማሳደግ ሂደት ውስጥ ለምናከናውናቸው ተግባሮች ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ልጆች የምንፈልገውን ነገር እንዲያደርጉ ከመናገር ይልቅ፣ ምሳሌ ሆኖ መገኘቱ ከሁሉም በላይ ተመራጭ ስለሆነ፣ የመልካም ባህሪ ባለቤትነት ፈርቀዳጅ በመሆን የመልካም ቤተሰብ ባለቤት መሆን ይቻላል እላለሁ፡፡