Quantcast
Channel: ጤና – Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Health: የመገጣጠሚያ አካላት የህመም ስሜቶችና መፍትሄዎቻቸው

$
0
0

 

ከዶ/ር ቁምላቸው አባተ (ሜ/ ዶክተር)

ከመቶ በላይ የሚሆኑ የመገጣጠሚያ ህመሞች አሉ፡፡ የመገጣጠሚያ ህመም ሲባል በጥቅሉ በሰውነት የሚገኙ ትናንሽም ይሁኑ ትላልቅ መገጣጠሚያዎችን ያማከለ በዋነኝነት እብጠትና የመጠዝጠዝ ስሜት የሚያስከትል ህመም ሲሆን መጠኑ፣ ዓይነቱን ተከትሎ የሚከሰተው ችግር ይለያይ እንጂ ልጅ አዋቂ ሳይል በማንኛውም እድሜ ክልል ፆታና ዘርን ሳይለይ ይከሰታል፡፡ በመሰረቱ የመገጣጠሚያ ህመም ሲባል የግድ መነሻው መገጣጠሚያ ነው ማለት አይደለም፡፡ ማንኛውም በሽታ የመገጣጠሚያ ህመም አያስከትልም ባይባልም አብዛኛውን ጊዜ የአጥንት፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመሞች መገለጫ ሊባል ግን ይችላል፡፡ ቀላል ወይም ከባድ የጤና ችግር የሚያስከትሉ የመገጣጠሚያ ህመሞች ባጀማመራቸው ተመሳሳይ ምልክቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡

bone

ለመገጣጠሚያ ህመሞች የሚደረግ ምርመራ አፋጣኝ ምላሽ ማግኘት የሚገባቸውን፤ በጊዜ ሂደት ሊፈቱ ከሚችሉት ለመለየት ያስችላል፡፡ የመገጣጠሚያ ህመም መነሻ ምንድን? የሚለውን ለመመለስ ሙሉ የጤና ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም፡፡ ለባለሙያ በሚነገረው የምልክት ይዘት፣ ሂደት፣ ተከታታይ ስሜቶች ወዘተርፈ የህመሙን ክብደት መገመት ይቻላል፡፡ ቀጥሎ ሊከወን የሚገባውንም የአካል ምርመራ እንዲሁም ትኩረት የሚሹ የላቦራቶሪና ተያያዥ ምርመራዎች ለመምረጥ አቅጣጫ መተለሚያ ነው፡፡ አንድ ታማሚ ሊገልፃቸው የሚገቡ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትት ይገባል፡፡ የመገጣጠሚያ አካላት አካባቢ ያሉ ማናቸውም የህመም ስሜቶችን (ለምሳሌ መጠዝጠዝ)፣ የታመሙ መገጣጠሚያዎች ቁጥር፣ የህመሙ አስከፊነት፣ድግግሞሽ፣ ቆይታ እንድሁም ጠቅላላ ይዘት (አልፎም መዘርዘር የሚገባቸው እውነታዎች ቢኖሩትም) መገለፅ ይገባዋል፡፡ የእብጠቱም እንዲሁ ሂደቱ፣ ቆይታው፣ የእብጠቱ ሙቀት፣ እብጠቱን የሸፈነው ቆዳ መልክ ለውጥና የመሳሰሉትም በተመሳሳይ መገለፅ ይኖርባቸዋል፡፡

• ህመም፣ እብጠት በዚህም የተነሳ መገጣጠሚያን ማጠፍ መዘርጋት አለመቻል፡ ፡ እብጠትን እንጂ የህመምን ልክ በወጉ ለመግለፅ ሊከብድ ይችላል፡፡ የሆነው ሆኖ አስቀድሜ ከጠቀስኳቸው ምልክቶች ባሻገር የታመመው መገጣጠሚያ፣ የህመሙ ክስተት ፍጥነት እንዲሁም አጠቃላይ ህመሙን የሚያባብሱ ወይም የሚያሻሽሉ ነገሮች መገለፅ ይገባቸዋል፡፡

• የህመሙን የክፋት ልክ በወጉ መግለፅ ከባድ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡

ህፃናት (በተለይ በለጋ ዕድሜ ያሉት ህመማቸውን በወጉ መግለፅ ስለማይችሉ) የበለጠ ሊያስቸግር ይችላል፡ ፡ ለማንኛውም የመገጣጠሚያ ህመሙ ምንም ዓይነት ስራ ለማከናወን የማይቻልበትን ሁኔታ ካስከተለ አሳሳቢ እንደሆነ መረዳቱ ፈጣን ምላሽም እንደሚያሻው አያጠራጥርም፡፡ ለእንዲህ ዓይነት መገጣጠሚያዎች እብጠት፣ ቃንዣ፣ ማጠፍ፣ መዘርጋት አለመቻል መነሻዎች አጥንት ወይም መገጣጠሚያ በባክቴሪያ ወይም በካንሰር ህመም ተይዞ መሆኑን ጠቋሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ መስራት አለመቻል፣ የታመመውን የአካል ክፍል ጨርሶውኑ አለማንቀሳቀስ፣ እንቅልፍን ማጣጣም አለመቻል ወዘተ የህመሙን ክብደት ማሳያዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ • የታመሙትን መገጣጠሚያዎች ማወቅ (የትኛውን መገጣጠሚያ ነው የሚያመኝ? ምን ያህል መገጣጠሚያዎችን?….ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት፣ በቀጣይነት መወሰድ የሚገባቸውን ምርመራዎች እንዲሁም ሊሰጥ የሚገባውን ህክምና ፈር ማስያዣ ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አንድ መገጣጠሚያ ሲታመም ፈጣን ምላሽ ሊያሻው እንደሚችል መገመት መልካም ነው፡፡ • የህመሙ ተከታታይነት፣ አልፎ አልፎ መከሰት፤ አለበለዚያም ካንድ መገጣጠሚያ ወደ ሌላ መዛወሩ መነሻ ምክንያቱን ጠቋሚ በመሆኑ አፋጣኝ ህክምና ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ለምሳሌ ፋታ የማይሰጥ፤ ተከታታይ ህመም ባንፃሩ አሳሳቢ መነሻዎች አሉት፡፡ ህመሙ የሚባባስበት ሰዓትም እንዲሁ የህመሙን አስከፊነት መገመቻ ነው፡፡

አንዳንድ የመገጣጠሚያ ህመሞች ጧት ሰላም ሆነው ቀኑ እየገፋ ሲሄድ የሚባባሱ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በተቃራኒው ቀን ምንም ሳይሉ ሌሊት አያስተኙም፡፡ ህመሙ የተስተዋለበት ፍጥነትም በተመሳሳይ ሁኔታ ለህመሙ መሰጠት የሚገባውን ትኩረት ያመላክታል፡፡ የሚያባብሱ ሁኔታዎች በእርግጥ በአካል ላይ የሚደርሱ አደጋዎች የመገጣጠሚያ ህመሞች ብቸኛ መነሻ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በሌላ የሰውነት ክፍል ላይ የተስተዋሉ ቁስለቶች፣ ህመሞች ወዘተ፤ ከህመሙ በፊት የነበረው ያጠቃላይ የሰውነት እንቅስቃሴ ይሄን ለመገመት ያስችላል፡፡ በዘር የሚተላለፉ የመገጣጠሚያ ህመም መነሻዎችም እንዳሉ ማስታወሱ የግድ ነው፡፡ በእህት፣ ወንድም ብቻ ሳይሆን በብዙ ዘመዶችም የሚስተዋል ሊሆን ይችላል፡፡ አጠቃላይ የአካል ክፍሎችን መመርመር ለምሳሌ ትኩሳት፣ ቁስለት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የሆድ ቁርጠት፣ እንዲሁም የዓይን ህመም መኖር አለመኖሩን መርምሮ ማወቅ መሰረታዊ ነው፡፡ መገጣጠሚያዎች ሊያብጡ፣ሊቀሉ፣ ሲነኩ የህመም ስሜት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ የመገጣጠሚያ አካላቱ ከትንሽ ጀምሮ አስከ መካከለኛ ከዚያም ሲብስ ባጠቃላይ አካላትን ማንቀሳቀስ ሊያቅት ይችላል፡፡ የመገጣጠሚያ እብጠት ወይም ህመም መነሻ የሆኑ ብዙ የሰውነት ክፍል ህመሞች ስላሉ አነዚህን የአካል ክፍሎች ያማከለ ምርመራ ማድረግ ይገባል፡፡ (ለምሳሌ የሳንባ፣ የልብ፣ የአንጀት ወዘተ) በባለሙያ በሚታዘዙ ምርመራዎች በመገጣጠሚያዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት መጠን ወይም ዓይነት ማወቅ ይቻላል፡፡ የራጅ ምርመራ እንዲሁም የተለያዩ የደም ምርመራዎች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ ከመገጣጠሚያ እባጮችም ፈሳሽ ተቀድቶ የላቦራቶሪ ምርመራ ይደረጋል፡፡

 

ህክምና እንግዲህ ታማሚው በሚናገረው፣ በአካላዊም ይሁን በሌላ ምርመራ በሚገኘው ውጤት መሰረት የተለያዩ ህክምናዎች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ በመሰረቱ ለመገጣጠሚያ ህመም የሚደረግ ህክምና ዓላማዎች ህመም(ቃንዣ) ለመቀነስ፣ የተጎዳውን መገጣጠሚያ ስራ ለማሻሻል እንዲሁም የመገጣጠሚያ ህመም የጎንዮሽ ጉዳትን ለመቀነስ ነው፡፡ በአብዛኛው (ለማስታወስ ያህል ከመቶ ያላነሱ ምክንያቶች ስላሉት) መነሻ ምክንያቱን ማዳን ይከብዳል፡፡ ያኗኗር ዘይቤን ማሻሻል /መለወጥ/ እርስዎ መገጣጠሚያዎትን ካመመዎት ከህክምና ባለሙያ ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት አጥንት እና መገጣጠሚያ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማስታገስ ብዙ መፍትሄዎችን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ለማጠፍ ለመዘርጋት ያስቸገረ መገጣጠሚያን፣የህመም እና የድካም ስሜቱን ለማስታገስ የጡንቻን እና የአጥንትን ጥንካሬ ለማሻሻል እንቅስቃሴ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ ሊደረግ የሚገባው የእንቅስቃሴ ዓይነት እንደ ተጎዳው አካል ይለያያል፡ ፡ ለማጠፍ ለመዘርጋት፣ለጥንካሬ ወዘተ፡፡

ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ እንደ ህመሙ አይነት ሊመከሩ የሚችሉበት አጋጣሚም ይኖራል፡፡ በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ የተጎዳውን መገጣጠሚያ አንድ ቦታ ላይ ለረዥም ጊዜ አለማቆየት ፣ በእንቅስቃሴም ይሁን በሌላ አጋጣሚ የተጎዳው መገጣጠሚያ ላይ ጫና አለማሳረፍ እና የመሳሰሉት ለህመሙ በጊዜ መሻር የራሳቸውን አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ ለፈውስ ወይም ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት የተለያዩ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ፡፡ አንድ ጊዜ የታዘዙ መድሃኒቶችን በራስ ተነሳሽነት እየገዙ ከታቀደለት ጊዜ በላይ መጠቀም መጥፎ ነው፡፡ እንደሚታወቀውም ያለ ባለሙያ ትዕዛዝ የሚወሰዱ ብዙ የዕውነትም ጥሩ መድሃኒቶች ቢኖሩም ሊያስከትሏቸው የሚችሏቸው ብዙ ችግሮች ስላሉ ከመውሰድዎ በፊት ባለሙያ ያማክሩ፡፡ ለማንኛውም መድሃኒትዎትን ባለሙያ ባዘዘው ልክ ላዘዘው የጊዜ ርዝማኔ ያህል ብቻ ይውሰዱ፡፡ ሌሎች የሚወስዷቸው መድሃኒቶችም ካሉ ለሚከታተለዎት ባለሙያ ያሳውቁ፡፡ ለአንዳንድ የመገጣጠሚያ ህመሞች ሌሎች የህክምና አማራጮች ካልተሳኩ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልግበት አጋጣሚም አለ ፡፡ በመገጣጠሚያዎች ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለመቀነስ ሳይዘገዩ ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡ ፡ ስለሆነም ከሚከተሉት የህመም ስሜቶች አንዱን ካስተዋሉ ባለሙያ ከማማከር አይቦዝኑ፡-

• የመገጣጠሚያ ህመምዎ ከ3 ቀናት በላይ ከቆየብዎት

• ሊገልፁት የማይችሉት ህመም ካለብዎት

• መገጣጠሚያዎትን ማንቀሳቀስ ካልቻሉ

• የታመመው መገጣጠሚያ ቆዳ ከቀላ፣ ከሞቀ

• ትኩሳት ካለብዎት እንዲሁም ክብደት ከቀነሱ ወዘተርፈ ባለሙያ ያማክሩ፡፡ በቸር እንሰንብት!!!

 

Source: Enku Magazine


Viewing all articles
Browse latest Browse all 384

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>