ብልቴ በደህና ቀን ሆዴ ውስጥ ትገባና ትጠፋለች፡፡ በዚህ የተነሳ በሚስቴ አጠገብ መቆም እያፈርኩ ነው፡፡ ሌላ ችግር የለብኝም፡፡ ሳውና ባዝ ስጠቀም የአንዳንድ ወንዶችን ብልት ስመለከት ደግሞ መጠኑ ረዘም ያለ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ በሚስቴም ሆነ በወንዶች መሀልም በድንገት እንኳን ስጋለጥ እፈራለሁ፡፡ እባካችሁ ህክምና ካለው አንድ በሉኝ፡፡
ዘላለም
ውድ ዘላለም ጥያቄህ የብዙ አንባቢዎቻችን እንደሚሆን እንረዳለን፡፡ በመሆኑም ምላሽህን እንደሚከተለው አስተናግደንልሀል፡፡
ለመሆኑ የብልት መጠን ወንዶች እንደሚጨነቁበት፣ ሴቶችስ ተመሳሳይ የሆነ አመለካከት ይኖራቸው ይሆን? ወይስ ሴቶች ከወንዶች የፍትወት አካል ይልቅ የሚያስጨንቃቸው ፍቅር ብቻ ይሆን? አነስተኛ የወንዶች የብልት መጠንስ፣ በሩካቤ አፈፃፀምና በመውለድ ብቃት ላይ የሚያስከትለው ተፅዕኖስ ይኖር ይሆን፣ ጥናቱ በእነዚህ ዙሪያ ምን ይላል?
አጭር ቁመት ያለውም ብልቱ አጭር ነው ካለ መናገርም አይቻልም፡፡ እንዳውም የአጭሩ ሰው ብልት ከቀውላላው ሰውዬ ሊበልጥ ይችላል፡፡ ታዋቂው የስነ ወሲብ ሐኪም ዶ/ር ሩት በዚህ ጉዳይ ላይ የምትለው አላት፡፡ ብዙዎች ወንዶች ከሌላው ያነሰ የብልት መጠን አለን ብለው ስለሚጨነቁና በራሳቸው ስለማይተማመኑ ወደ ድክመተ ወሲብ ያመራሉ፡፡ ምክንያቱም ጭንቀቱ ራሱ ስኬታማ ግንኙነት እንዳያደርጉ ስለሚያደርጋቸው ነው፡፡ በመሆኑም ትላለች ዶ/ር ሩት የወንዶች ብልት የሚያንሰው ጭንቅላታቸው ውስጥ ነው፡፡
በተለያዩ ሰዎች ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፣ ሴቶች ለወንዶች የብልት መጠን ትኩረት እንደሚሰጡ ይታወቃል፡፡ ለወንዶች ልጆች የሴቶች መልክና ቅርጽ ስሜት ቀስቃሽ የመሆኑን ያህል ለሴቶች ደግሞ የወንዱ የብልት መጠን ትኩረት እንደሚሰጡ ይታወቃል፡፡ ለወንዶች ልጆች የሴቶች መልክና ቅርፅ ስሜት ቀስቃሽ የመሆኑን ያህል ለሴቶች ደግሞ የወንዱ የብልት መጠን ተነፃፃሪ እንደሆነ ነው የሚታወቀው፡፡ በእርግጥ የብልት መጠን በተለይ በውፍረት ደረጃ ገዘፍ ማለቱ፣ ብዙዎቹን የሴቷ ፍትወት አካል ውስጥ የሚገኙ የነርቭ ጫፎችን የመዳሰስ አቅም ስለሚኖው ለሴቷም ስሜት ለጭነቱ አያጠያይቅም፡፡ በተለያዩ ወሲባዊ ችግሮች ወደ ህክምና ከሚሄዱ ሴቶች ውስጥ 67 በመቶ የሚሆኑት፣ በወንዶቻቸው የብልት መጠን አይረኩም፡፡ በእርግጥ ለወንዱ ስሜት አንቃቂነት የሴቷ የብልት ቀዳዳ መጠን መጥበቡ ነው ተፈላጊ የሚያደርገው፡፡ ይሄም በወንዱ ብልት ላይ ያሉትን የነርቭ ጫፎች በመፋተግ ስሜትን ስለሚያነቃቃ ነው፡፡
ለመሆኑ የወንዶች የብልት መጠን በአማካይ ምን ያህል ይሆናል? በአብዛኛው 90 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች ብልታቸው በተነሳሳ ጊዜ፣ በጋራ የሚጋሩት የብልት መጠን እርዝማኔ ከ5-7 ኢንች ወይም በአማካይ 6.16 ኢንች የሚርስ ሲሆን ይሄም ከ12.7-17.8 ሴ.ሜ ወይም በአማካይ 13.65 ሴንቲ ሜትር ይደርሳል፡፡
የብልት መጠን ማሳያ ቻርት/ሙሉ በሙሉ ከተወጠረ በኋላ/
መጠን ቁመት
ትንሽ <6 ኢንች
አማካይ 6-7 ኢንች
ትልቅ 7-8 ኢንች
ግዙፍ > 8 ኢንች
የብልት ርዝማኔን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
በቅድሚያ መለካቱ የሚመጣው በራስ ካለመተማመን ግፊት ነው፡፡ በጥናት እንደሚታወቀውም 98 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች፣ ትክክለኛ ወይም በጤናማ የመጠን ልኬት ውስጥ እንደሚያርፉ ነው፡፡ እንግዲህ የግድ ይህንን ማወቅ አለብኝ የሚል ወንድ ካለ፣ እንደሚከተለው አድርጎ መለካት ማንም የማይነፍገው መብቱ ነው፡፡
1. ማስመሪያ በመያዝ ብልት በስሜት ተነቃቅቶ ሙሉ በሙሉ እስኪወጠር ጠብቅ፡፡
2. ማስመሪያውን ከብልት መነሻ እስከ ጫፍ ድረስ በትክክል አጋድመው፡፡ ይህን ስታደርግ ግን ማስመሪያውን የኢንች ክፍል ወደ ሰውነትህ ሳትጫነው መሆን አለበት፡፡
የተለያዩ የብልት ማነስ ችግር ያለባቸው ወንዶች፣ ብልታቸውን ለማስረዘም ታዲያ ፍላጎት ማሳደራቸው አልቀረም፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ያሰቡት ያልተሳካላቸው ግለሰቦች ለከፍተኛ የስነ ልቦናዊ ችግር ተጋልጠዋል፡፡ ከእነዚህ ዘዴዎች መካከል ውስይ እምደው፣ የተወሰኑት ዘዴዎች ከ2-3 ኢንች ድረስ የብልት መጠን ቁመትን የመጨመር ኃይል ሁሉ ያላቸው ናቸው፡፡ ከመቶ በላይ ያሉ ልዩ ልዩ ዘዴዎች ይገኛሉ፡፡ ያም ሆኖ ውጤታማ የተባሉት ዘዴዎ ጥቂት ብቻ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ዘዴዎች አሰራሩን የሚያዘወትሩም፣ ኮርፖራ ካቫርኖዛ በተባለው የብልት ጡንቻ ላይ ነው፡፡ ኮርፖራ ካቫርኖዛ የብልት ውስጥ ጡንቻ ሲሆን፣ በውስጡም ጥቃቅን የደም ስሮችን የያዘ በወሲብ ወቅትም በደም በመሞላት የሚለጠጥ ክፍል ነው፡፡
ስለ ወንዶች ብልት ሴቶች ምን ይላሉ?
ወንዶች የሚያስጨንቃቸውን ያህል ሴቶች ለወንዶች የብልት መጠን ትኩረት ይሰጣሉ ወይ በሚለው ላይ ያጠነጥናል፡፡ እንደሚታወቀው ወንዶችን በብልት መጠናቸው የሚጨነቁት፣ በአመዛኙ ሴቶች ለመጠን ግዝፈት የተለየ ምርጫ ይኖራቸዋል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ስለሚጨነቁም ምንም እንኳን ተገቢ መጠን ቢኖራቸውም በቂ አይደለም ብለው ይረብሻሉ፡፡ ብዙዎቹ በዚሁ ዙሪያ የሚቸገሩ ወንዶች ችግሩ ራሳቸው በፈጠሩት ጭንቀት ሳቢያ የሚመጣ ነው፡፡ ሌላው የችግሩ መነሻ ደግሞ ወንዶች ብልታቸውን እርስ በርስ በማወዳደር ልማዳቸው ነው፡፡ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም፡፡ የእያንዳንዱ ወንድ ቁመትና ክብደት ተመሳሳይ እንደማይሆን ሁሉ የብልት መጠናቸውም እኩል ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ዋናው ጭብጥም መሆን ያለበት የብልት ልኬታቸው መጠን በተገቢው መስፈርት ውስጥ ይገኛል ወይ? ብሎ ማወቁ ላይ ነው፡፡
እንደሚታወቀው የወንዱ የብልት መጠን ከፍተኛ መሆን፣ በግንኙነት የበላይነትን እንደሚያስጨብጥ በአፈ ታሪክ ደረጃ ቢነገርም፣ እውነታው ግን በሴቶች ዘንድ ብዙ የሚታመንበት አለመሆኑ አስተሳሰቡን አስቂኝ ያደርገዋል፡፡ ‹‹ለምን?›› የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስም፣ የሚከተሉትን መረጃዎች ማየቱ በቂ ነው፡፡
1. እንደሚታወቀው የሴት ልጅ ፍትወት አካል፣ በአፈጣጠሩ ከተለጣጭ ጡንቻዎች የተሰራ እንደመሆኑ መጠን በውስጡ የህፃን ልጅን ያክል ግዙፍ አካል ማሳለፍ የሚችል ነው፡፡ እንዲሁም ሞዴስን ያህል የደም መምጠጫ በውስጥ አፍኖ የመያዝም አቅም ያለው ነው፡፡ በአጠቃላይም ማንኛውንም በውስጡ የሚገባ አካል የመቀበልና የማፈን ባህሪ አለው፡፡ ከዚህ አንፃር ታዲያ የወንዶች ብልት ወፍራምም ይሁን ቀጭን የሚያመጣው ለውጥ እምብዛም ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱንም አይት መጠኖች ለማስተናገድ ከተለጣጭነት ባህሪው የተነሳ በተመሳሳይ ደረጃ የማፈን ብቃት ስላለው ነው፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ብዙውን ጊዜ ሁለቱም ፆታዎች የበለጠ ክብደት የሚሰጡት ለስሜት ነው፡፡ ማለትም የሴቷን ስሜት ከመኮርኮርና ከማርካት አንፃር፣ ረዘም ያለው የወንዱ የፍትወት አካል የተሻለ እንደሚሆን ያምናሉ፡፡ ይህም ምክንያት የሴቷ ውስጠናው የፍትወት አካል የበለጠ ተነቃቂ እንደሆነ በማሰባቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ 70 በመቶ ከፍተኛ የተነቃቂነት ባህሪ ያለው የሴቷ የፍትወት አካል ከውጫዊ አካል ቀረብ ያለው የብልት ውስጣዊ ክፍል ነው፡፡ ማለትም 10 ሣንቲ ሜትር ያህል ገባ ብሎ የሚገኘው ነው፡፡ ይህን አካባቢ ደግሞ አማካይ ርዝማኔ ያለው አብዛኛው የወንዶች ፍትወት አካል በቀላሉ ሊደርስበት የሚችል እንደመሆኑ መጠን መርዘሙ የግድ አይደለም፡፡
በሶስተኛ ደረጃ ከአራት ሴቶች ውስጥ ሶስቱ፣ በተራክቦ ወቅት አብሮ የክሊቶሪስ /ቂንጥር/ መነቃቃት እንዲኖር ካልተደረገ በቀላሉ መርካት የሚችሉ አለመሆናቸው በጥናት የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ዋናው ቁም ነገር በዚህ መልኩ የሚደረግ የግንኙነት አፈፃፀም ችሎታ እንጂ የወንዱ ብልት ስለወፈረና ስለረዘመ አይደለም፡፡
በእርግጥ ርዝማኔው ከ20 ሣ.ሜ በላይ አካባቢ የሚሆን መጠን ያለው ወንድ፣ የሴቷን የማህፀን ጫፍ ጋር የመፈጋፈግ ዕድሉ ላቅ ስለሚል፣ በሴቷ ላይ ህመምና ስቃይን ሊፈጥርባት ይችላል፡፡በአጠቃላይ ምንም እንኳን አብላጫ የርዝማኔና የውፍረት መጠን ያለው የወንድ ፍትወት አካል፣ ከአናሳዎቹ ጋር ሲነፃፀር በተወሰነ መልኩ የተሻለ ቢሆንም በግርድፉ ሲታይ ግን እውነታው በአፈፃፀም ብቃት መለያየት ላይ የሚመሰረት ይሆናል፡፡ እርግጥ ነው ሴትን ልጅ ለማስረገዝ ወንዱ የዘር ፈሳሹን የማህፀን በር/ጫፍ አካባቢ ማድረስ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ አንፃር የበለጠ ውጤታማው አብላጫ እርዝማኔ ያለው ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ረዘም ያለው የማስረገዝ ዕድልን ያሰፋል ለማለት እንጂ አነስተኛ መጠን ያላቸው አያስረግዙም ለማለት አይደለም፡፡
በብልት መጠን ዙሪያ ወንዶች ያላቸው ስነ ልቦና እንደተጠናው ከሆነ 50 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች የፍትወት አካላቸው መጠን ቢምርላቸው የሚመኙ ናቸው፡፡ ይሄው ተመሳሳይ ጥናት በሴቶች ላይ ያሳየው አስገራሚ ውጤት፣ 85 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች በወንድ ፍቅረኞቻቸው የብልት መጠን በጣም የረኩና የተለየ አሉታዊ መልክ እንደሌላቸው ነበር የተደረሰበት፡፡ 9 በመቶ የሚሆኑት በቂ ነው ብለው የተቀበሉ ሲሆን፣ 6 በመቶ የሚሆኑት ብቻ በፍቅረኞቻቸው የብልት መጠን ቅራኔ እንዳለባቸው የገለፁት በመሆኑም ይህ በ50 ሺ ሴቶችና ወንዶች ላይ የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ፣ የወንዶች የብልት መጠን የሚያስጨንቃቸው ወንዶችን እንጂ ብዙዎች ሴቶች ላይ የሌለ አስተሳሰብ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ለብልት ማነስ መፍትሄው ምን ይሆን?
እንደሚታወቀው ህክምና የሚያስፈልገው፣ በውል የታወቀና ባይስተካከል ችግር ለሚያስከትል እንከን ነው፡፡ በመሆኑም የዘርፉ ባለሙያዎች አነስተኛ የብልት መጠን ላላቸው ወንዶች የተለያዩ የመፍትሄ አማራጮችን መጠቀም እንደሚቻል ይመክራሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
1. የሆርሞን ህክምና፡- ይህ ቴስቴስትሮን የተባለውንና የወንዳወንድነት ባህሪ የሚያላብሰውን ሆርሞን በመርፌ መልክ በመስጠት የሚደረግ ህክምና ሲሀን፣ ብዙውን ጊዜ በህፃንነት ሲሰጥ ውጤታማነቱ የጎላ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በጎልማሳነት ዕድሜ ላይ መውሰዱ አናሳ ውጤታማነት ያለው ነው፡፡
2. መድሃኒቶች፡- እነዚህ በሚዋጥና በቅባት መልክ ተዘጋጅተው የመውሰዱ የህክክና ዘዴዎች ሲሆኑ የሚዘጋጁትም ከአንዳንድ ዕፅዋት ነው፡፡ በእነዚህ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንዳስረገጡት ከሆነ፣ መድሃኒቶቹ ውስጥ አንዳንድ ጎጂ አካል ነገሮች ተገኝቶባቸዋል፡፡ ለምሳሌም ሻጋ /ፈንገስን/፣ ኢ ኮላይ የተሰኘ ባክቴሪያ፣ እንዲሁም ፀረ አረም ኬሚካሎችነ ሊድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ባለሙያዎቹ እንዳመለከቱትም ምናልባት መድሃኒቶቹ ከተሰሩባቸው ዕፅዋቶች አካባቢ የሚጋለጡ እንስሳት አይነ ምድር ብክለት የተነሳ ሳይሆን እንደማይቀር ይጠረጥራሉ፡፡ በመድሃኒቶቹ ውጤታማነት ላይም ቀጥተኛ የሆነ ብቃት አልያም ምናልባትም ውጤት ቢያመጡ፣ ተጠቃሚዎቹ ችግሬን ይቀርፉልኛል ብለው በማመናቸው የመጣ ስነ ልቦናዊ የህይወት ለውጥ እንደሚሆን ነው፡፡ ይህም በራስ የመተማመንን ባህሪ ያዳብርላቸዋል ብለዋል፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች በክኒን ወይም በቅባት መልክ የሚዘጋጁ ሲሆን በኢንተርኔት በኩል ለሽያጭ የሚቀርቡ ናቸው፡፡
3. ፓምፕ፡- ይህ በብልት ላይ የሚገጠም አነስተኛ መሳሪያ ሲሆን ትንሽ በእጅ የሚሰራ መዝውር ያለው ነው፡፡ ዋናው አላማውም በብልት ውስጥ በዛ ያለ ደም እንዲገባ በማድረግ የብለትን ውጥረት በመጨመር መጠኑን መጨመር ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው በብልት ላይ የሚገጠመው መሳሪያ ‹‹ኔጌቲቭ ፕሬዠር›› በመፍጠር የመሳብ ኃይል የሚኖረው ሲሆን፣ በዚህ የመሳብ ኃይሉም ደምን ከደም ስሮች ወደ ብልት ውስጥ በደንብ እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ልክ ነዳጅን በቱቦ በኩል በእ ስቦ እንደማስተላለፍ ይቆጠራል፡፡ የመዘውሩም ጥቅም ኔጌቲቭ ፕሬዠሩን ለመፍጠር ነው፡፡
ይሁን እንጂ የመሳብ ኃይሉ ከበዛ ወደ ብልት የሚገባው የደም መጠን በጣም ስለሚጨምር፣ የብልት ውስጣዊ ለስላሳ አካላት ላይ ጉዳት ሊያስከትልበት ስለሚችል የግፊት አጨማመሩ በፋብሪካው ትዕዛዝ መሰረት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ፓምፕ አንዳንዶች ራስን በራስ ለማርካት ዘዴም ይጠቀሙበታ፡፡ በዚህ በኩል ለየት ያለ ዕውቅና ያተረፈው ዶናሊድ ቶምሰን የተባለው ዳኛ ሲሆን፣ በፍርድ ሂደት ወቅት ማሽኑን በመጠቀም ማስተርቤሽን ሲፈፅም ስለተደረሰበት የአራት ዓመት እስር እንደተፈረደበት በታሪክ ይዘከራል፡፡ በተለይ በስሜት የመነቃቃት እና የመወጠር ችግር ላለበት ብልት የተዋጣለት ዘዴነው፡፡ እንዲሁም ቶሎ የመርካት ችግር ላለባቸው ወንዶችም በሰፊው ጠቀሜታን የሚሰጥነው፡፡ መሳሪያው ለረጅም ጊዜ ብልት እንደተወጠረ እንዲቆይ የማድረግ ብቃትም ያለው ነው፡፡ መሳሪያው በልዩ ስሙ ‹‹ቫኪውም ፓምፕ›› በመባል የሚታወቅ ነው፡፡
4. ተወጣሪ ተቀባሪዎች፡-እነዚህን የሕክምና አማራጮች ‹‹Inflatable Implants›› በመባል የሚጠሩ ሲሆን፣ በብልት ውስጥ የሚቀበሩና ከፍተኛ የተለጣጭነት ባህሪያቸው ቀጫጭን ቱቦዎች ናቸው፡፡ አላማውም ብልት በስሜት በሚነሳሳበት ወቅት ደም እንደ ልብ ወደ እነዚህ ቱቦዎች በቀላሉ በመግባትና እነሱን በመለጠጥ፣ የብልትን የውጥረት መጠን መጨመር ነው፡፡ እንዳስፈላጊነቱ የቱቦዎቹ መጠን መጨመር ነው፡፡ እንዳስፈላጊነቱ የቱቦዎች መጠን ተለቅ ተለቅ ማድረግ የሚቻል ሲሀን፣ ለረጅም ጊዜም ብልትን እንደተወጠረ የማቆየት ኃይል አላቸው፡፡ ቱቦዎቹ በብልት ውስጥ የሚቀበሩት በቀዶ ጥገና ሲሆን መጥፎው ነገር የተቀበሩትን ቱቦዎች መልሶ ማውጣት የማይቻል መሆኑ ሲሆን ባይወጡ ግን ጉዳት አያስከትሉም፡፡
5. የማሰብ ዘዴ፡- ይህ ዘዴ ዋና አላማው በብልት ውስጥ የሚገባውን የደም መጠን በመጨመር፣ የብልትን ውጥረት በሂደት የመጨመር ዘዴ ሲሆን የሚደረገውም በእጅ ጣቶች ነው፡፡ በከፊል የተነሳሳ ብልትን በአውራ ጣትና በሌባ ጣት ጠበቅ አድርጎ በመያዝ ወደ ላይ የመግፋት ሁኔታ ሲሆን አላማውም ደምን ወደ ብልት የማስገባት ሂደት ነው፡፡ ዘዴው የብልትን ውስጣዊ የደም አቀባበል አቅም በመጨመር በቋሚነት መጠኑን መጨመር ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ በሞቀ ውሃ የተነከረን ጨርቅ ከጣቶቹ ስር (ከብልቱ ላይ) አብሮ በመጠቀም መከወን የበለጠ ውጤት እንዳላውም ይታወቃል፡፡
6. ክላምፒንግ፡- ይህ ደግሞ በአንድ የተወጠረ ብልት ስር ጠበቅ ባለ ቀለበት ወይም የጫማ ማሰሪያ ማሰርና ከዚያም ረዘም ያለ ማስተርቤሽን ማድረግን የሚያካትት ነው፡፡ ብልቱን የሚያስሩት ቀለበት ወይም ክር አላማው ወደ ብልት የገባው ደም ወደ ኋላ እንዳይመለስና ብልት በደንብ እንደተወጠረ እንዲቆይ የሚያደርግ ሲሆ፣ብልትን በሚገባ ማሸት ዘለቄታዊ የደም የመቀበል አቅምንና መጠኑን እንዲጨምር ለማድረግም ነው፡፡
7. በቅድሚያ አትጨነቅ፡- የብልት መጠን መርዘምን፣ ከታላቅ የፍቅር ስኬት ጋር አጣምረህ ለማየት የምትሞክር ከሆነ ሲበዛ የዋህ ነህና፣ ይህ ባህሪህ በተለይ ለፅድቅ ብቻ እጅግ ይጠቅምሃል፡፡ ረጅም ብልት ስላለህ ታላቅ አፍቃሪ ትሆናለህ ወይም ደግሞ የወንዶች የበላይ ነህ ማለት አይደለም፡፡ ተፈቃሪነት ብዙ ነገሮች በውስጡ የያዘ ቃል ነውና፡፡ በዚያ ላይ ሴቶች በግንኙነት ትልቅ ግምት ሊሰጡት ቢችሉ የሚሰጡት አፈፃፀምህን እንጂ ያለህን ብልት መጠን ማጠርና መርዘም አለመሆኑን ልብህ ልብ ይበል፡፡ ቁመትህም ቢሆን!
8. አወዳድር /አትወዳደርም/፡- በቅድሚያ ትንሽ ነው ወይም ትልቅ የሚለው ሐሳብ በጭንቅላትህ አይምጣ፡፡ ምክንያቱም ስለማያስፈልግ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በቁመትና በክብደት እንዲሁም በሌላው አካሉ ከሌላው እንደሚለይ ሁሉ፣ በብልት መጠንም እንዲሁ ልዩነት መኖሩን ተፈጥሯዊ መሆኑን፣ እንዲሁምበፊልምና ኢንተርኔት ፓርኖግራፊ ላይ የምታየውን የወንዶች ብልት ከአንተ ጋር አታነፃፅር፡፡ እነዚህ ወንዶች ከስንት አንድ የተገኙና በብልት ርዝማነሀያቸው ብቻ ፊልሙ እንዲሳተፉ የተደረጉ ናቸውና አብዛኛውን ወንድ አይወክሉም፡፡ በተጨማሪም በካሜራ አንግላዊ አተያይ ውስጥ ትንሹም ቢሆን ገዝፎ እንዲያድግ ማድረግ ስለሚቻል አትጭበርበር፡፡
9. አትገረም! የብልት መጠን እንደ አቋቋምህ፣ አቀማመጥህ፣ እንደ ብልትህ የስሜት መነቃቃት ደረጃ፣ እንደ አየሩ ሙቀትና ቅዝቃዜ በየጊዜው ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ሙቀትና ቀዝቃዛ ሻወር ስትወድ እንኳ በቅፅበት ውስጥልዩነቱን ስለምታየው ባነሰብህ ወቅት አትበርግግ፡፡
10. በመቀነስ ጨምር፡- የብልትህን መጠን በአንድ ኢንች ለማስረዘም ወደ ከፍተኛ ህክምና ውስጥ ከመግባትህ በፊት አንድ ቀላል ዘዴን ተግበር፡፡ የሰውነትህን ክብደት መቀነስ (ወፍራም ከሆንክ ማለት ነው) ይህ አካሄድ ብልት ያረፈበትን የቆዳ ስር ቅባትም ስለሚቀንስ ቁመቱን ማስረዘም ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ 16 ኪሎ ግራም ክብደት ከነበረህ ላይ ብትቀንስ በብልትህ ላይ የአንድ ኢንች ርዝማኔ (2.54 ሣ.ሜ) መጨመር ያስችልሃል፡፡
11. ክብደት ማንጠልጠል፡- ይህ አይነቱ ዘዴ ደግሞ የኮርፖራ ካቫርኖሳ ጡንቻን ከመለጠጥ አንፃር ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ብልት በቆመበት ወቅት መጠነኛ የሆነና ሊቋቋመው የሚችለውን ክብደት ወደ ታች እንዲያንጠለጥል ማድረግ ነው፡፡ ይህ በየቀኑ ለሁለት ወይም ለሶስት ጊዜ የሚከወን ዘዴ ሲሆን፣ ክብደቱ ብልቱን እንዳይጎዳው መጠንቀቅን ይጠይቃል፡፡
12. የቀዶ ጥገና ዘዴ፡- ብልትን በቀዶ ጥገና ከወትሮ መጠኑ እንዲጨምር ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህ ዘዴ የሚታወቀው ደግሞ በዋጋው ውድነት ሲሆን፣ አንድን ብልት በቀዶ ጥገና ቴክኒክ ለማስረዘም በትንሹ የ6000 ዶላር ወጪን ይጠይቃል፡፡ ከቀዶ ትገናው በኋላም ብልት ወደነበረበት እንዳይመለስ ወደ 15 ፓውንድ የሚመዝን ክብደት ወደ ታች እንዲታሰርበት ይሆናል፡፡ ይህም እንኳን ቢሆን አንዳንዶቹ እንደ ስንፈተ ወሲብ መሰል ተያያዥ ችግሮች መጋለጣቸው አይቀርም፡፡